Thursday, April 5, 2012

ጌታቸው ዶኒ የቤተክርስትያን ቦታ ለመሸጥ እያስማማ ነው


(አንድ አድርገን መጋቢት 27 2004 ዓ.ም) ፡- አቶ ጌታቸው ዶኒ በደብረዘይት በባቦጋያ መድሀኒአለም ያለውን የቦታ ጉዳይ በሚመለከት በደብረዘይት ከተማ ከከተም 6 ቀናቶች ተቆጥረዋል ፤ በደብረ ዘይት 7E የሚባል ሆቴል ካረፈ ቀናቶች ተቆጥረዋል ፤ እሱ እንደሚለው የቦታው መሸጥ ይግባኝ እንደሌለው እና የቤተክርስትያኒቱ የበላይ አካል ሲኖዶስ የወሰነበት ጉዳይ ስለሆነ ህዝቡን በአውደ ምህረት ላይ አትልፉ አትድከሙ ቦታው ለቤተክርስትያኒቱ ሳይሆን ለባለሀብቱ ይገባዋል የሚል ደብዳቤ ከጠቅላይ ቤተክህነት አምጥቼዋለሁ ያለውን ማስፈራሪያ የተሞላበት ደብዳቤ  እሁድ 23/07/2004  ከቅዳሴ በኋላ ለህዝቡ ሊያነብብ ችሏል ፤ የደብዳቤው ሀሳብ ‹‹ዉሳኔዉ ይግባኝ የለዉም ፣ ከሲኖዶስ በላይ ማንም የለም አባቶች አይሳሳቱም፣ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የግል ፍላጎታቸዉን ለማሟላት ነዉ ፣ ዝም ብሎ መቀበል ነው  ምንም አስተያየት አልቀበልም ፤ ለቤተክርስትያኒቱ ካሳ ባለሀብቱ እንደሚከፍሉም አሳስቧል›› የሚል ፍሬ ሀሳብ አለው ፡፡››  እኛ የምናውቀው ቤተክህነቱ ስለ ቤተክርስትያኒቱ ቦታ ተከራክሮ ያስመልሳል ብለን ነበር ፤ አሁን ግን እየሆነ ያለው ቦታዋን የመሸጥና በኪራይ ሰብሳቢነት የተጠመዱ ሰዎች ለፍላጎታቸውን መሟያ መሬቷን እንደ ገቢ ማስገኛ እየተጠቀሙባት ይገኛሉ ፤ 


ይህን እጃቸው ባለበት ሰዎች የተሸረበ ጽሁፍ በሚያነብበት ጊዜም ይዞ የመጣው ደብዳቤ የቤተክርስትያኒቱን ቦታ ሽጡ ፤ ካሳ ይሰጣችኋል የሚል መልዕክት ስላለው በጊዜው የነበረው ህዝበ ክርስትያን ሊቀበለው እንደማይችል እና በፍርድ ቤት ቦታውን የማስመለስ ስራ አጥብቀው እንደሚሰሩ አስገንዝበዋል ፡፡ በጊዜውም ቤተክርስትኒቷን በፌደራል ፖሊስ አስከብቦ ነበር ፤ ፖሊሶቹም አንደከዚ ቀደማችሁ ዱላ ሳይሆን መሳሪያ ይዛችሁ ውጡ የሚባልም ትዕዛዝም  ደርሷቸዋል ፤ ደብረ ዘይት ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ከ OPDO(የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፖለቲካ ቢሮ) ሲመላለስ ለመመልከት ችለናል ፤ እዚያም ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ጉዳዩን ጫፍ ለማድረስ ያለ እረፍት ቀን ከሌት ያለ እንቅልፍ እየሰራ ይገኛል ፤ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ቤተክርስትያኒቷ የመደበቻቸው አካላት ተከራክረው ጉዳዩን ዳር እንዲያደርሱት ፤ የመጠየቅ መብት እንዳላቸው መብታቸውም እንደሆነ ያረጋገጠ ሲሆን ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ ግን ቦታውን ለባለሀብት ለመሸጥ ሽንጡን ገትሮ ሲከራከር ሰንብቷል ፡፡ አሁንም በደብረዘይት የቦታውን መሸጥ ለማረጋገጥ እና ቦታው የባቦጋያ ማስፋፊያ ሪዞርት መሆኑን ለማስረገጥ ለዚህ እኩይ ምግባሩ በደብረዘይት የመንግስት ቢሮ ውስጥ ይገኛል ፡፡ የዚህ ሙሉ የተቀረጸ ቪዲዮ  በሚቀጥሉት ቀናት ብሎጋችን ላይ ፖስት ለማድረግ እሞክራለን ፡፡


ሰውየው በአሁኑ ሰዓት በደብረ ዘይት ከደህንነት ሰዎች ጋር እየተንቀሳቀሰ ነው ፤ መቼስ ከመንግስት ደህንነት ሰዎች ጋር ስለ ጤናና ቤተሰብ ያወራሉ ብለን አናስብም ፤ ዛሬ መድሀኒዓለም ንግስ ቢሆንም ቦታው ላይ አልታየም ፤ ንግሱ ለሱ ምኑ ነው ?  የእሱ ሀሳብ ብሩ ላይ ነው ፤ ቀን ከደህንነቶች ጋር ማታ ደግሞ ሪዞርት ውስጥ ለመዝናናት ፤ ከዚያ ወደ ያዘው ሆቴል ሆኗል ስራው ፤ ታዲያ ይህ ሰው ነው ቤተክህነቱ ወክሎት መፍትሄ ለማምጣት ሰው ተብሎ የሚላከው ? ባለፈው አቶ ተስፋዬን ዋልድባ ልከው አይቶ እንዳላየ ሁኔታን ሲክድ ምንም እንዳልተፈጠረ ሲያብራራ ሲመለከቱት ሰውየው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው የላኩት ? ወይስ ቤተክህነቷ ? ያስብላል ፤ የዚህ ደግሞ ይባስ ብሎ በጠራራ ፀሀይ እየዶለተልን ይገኛል


በዋልድባ ገዳም አካባቢ የሚገኙትን 18 አብያተክርስያናት ስናፈርስ በአንድ  ቤተክርስን 1 ሚሊየን ብር ካሳ እንከፍላለን የሚል የመንግስት ሀሳብ ስንገረም ፤በአሜሪካ ስለ ዋልድባ ገዳም ክርስትያኖች ግድ ብሏቸው ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ እዛ ያሉ አባት ህገወጥና ፖለቲከኞች ናቸው ማለታቸው ሲደንቀን ፤ አቶ ጌታቸው ደግሞ በላያችን ላይ ቤተክርስትያኒቱን ለመሸጥ ራሱን በፌደራል ፖሊስ በማስጠበቅ በድፍረት ለምዕመኑ መልእክት ማስተላለፋቸው አግራሞትን ፈጥሮብናል  ፤ ይህ ሰው ሶስት ሺህ በማይሞላ የወር ደመወዝ 2 ሚሊየን ብር ሚገመት የራሱን ቤት አሰርቶ የደሴ ቅዱስ ገብርኤል ምርቃት ላይ መገኝት ያልፈለጉትን አቡነ ጳውሎስን የምርቃት ስርአቱ ላይ እንደጋበዛቸው እና እሳቸውም ከሊቀ መልአኩ ከቅዱስ ግብርኤል ቤተክርስትን ምርቃት ይልቅ የእሱ ቤት በልጦባቸው በእለቱ እንደተገኙ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው ፡፡  ታዲያ ይህ ብር እኮ ከየትም መጥቶ ሳይሆን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ የቤተክርስትያኒቱ ብር ተመዝብሮ መሆኑን ለማወቅ ነጋሪ የሚያሻን አይመስለንም ፤ ይህ ሰው በቃሊቲ የምትገኝውን ጉስቋም ማርያም ቤተክርስትያን ለሊት 8፡00 ሰአትመኪና በማዘዝ ምዕመኑ ያመጣውን ቆርቆሮ ሊያወጣ ሲል እጅ ከፍንጅ መኪናው ከጫነው ቆርቆሮ ጋር መያዙን ጉዳዩም ፖሊስ ዘንድ ድረሶ ውሳኔ ያልተሰጠበትንም ጉዳይ መሆኑን እናውቃለን ፡፡ ሌላው ሌላው ስራው ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን ፤

የአካባቢው ምዕመን ጥያቄ ቦታው የቤተክርስትያኒቱ ነው ፤ በባለስልጣናት እና እኛን መስለው በውስጣችን በተቀመጡ ሰዎች አማካኝነት ግን ለባለሀብቱ ለሪዞርት ማስፋፊያ ተሰቷቸዋል ፤ ይህ ህገወጥነት ስለሆነ የቤተክርስትየኒቱ ከ10ሺህ ካሬ በላይ የሚሆን ቦታ ይመለስላት ነው ፡፡

ቤተክርስትያናችን ፈተናዋ ቢበዛም እንዲህ አይነት የተቀነባበረ ድፍረት የተሞላበት ስራ ከቤተክህነቱ ይሰራል ብለን ገምተን አናውቅም ፤ እኛው ተባብረን ቤተክርስትያናችን ካልጠበቅን ማንም ሊጠብቅልን አይችልም ፤ ፈተናችን ቢበዛም ሸክማችን ቢከብድም ትላንትናም ዛሬም ይሁን ነገ በቤተክርስየን ላይ የሚደረግን ህገ ወጥነትን እየተቃወምን እንኖራለን ፤ መረጃ ሰዎች ዘንድ እንዲደርስ የመፍትሄ አካልም እንዲሆኑ እንሰራለን ፤  

4 comments:

  1. betam yasazenal yemechereshaw gize yedersen yemeselgnale mech liblawo now egzabeher firduen yestachew

    ReplyDelete
  2. And Adrgen

    May GOD Bless u all

    ReplyDelete
  3. እነዚህ የዚህ ዘመን ሰዎች እኛን ምእመናንን በቤተክርስቲናችን ጉዳይ እንዲህ የሚያስጨንቁን ለምንድን ነው? ድንጋይ ወርውረን በጥይት ሊፈጁን ከሆነ እኛ አናደርገውም ለምን ቢባል እሳት ከሰማይ አውርዶ የሰናክሬምን ሠራዊት የፈጀ አምላክ አለንና ሁሉን ለሱ አደራ ስለሰጠን ነው እሱም አያሳፍረንም:: እንደ ሰናክሬም ሰራዊት ስሳት ከሰማይ አውርዶ እንዲፈጃቸው ባንሻም የልባቸውን ድንዳኔ አይቶ አልመለስ ማለታቸውን ሲያውቅ አንገታቸውን የሚሰብርበት ቀን አለውና ዝምታው ስላላስተዋለ አይደለም:: ለዚህም አንገታቸውን አደንድነው ፓትርያርካችንን አንቀው ገድለው አብያተክርስቲናትን ለ17 ዓመታት ሲዘጉ የነበሩ የደርግ ዘመን ሰዎች ትምህርት ሊሆኑን በተገባ ነበር:: ግን ምን ያደርጋል ከፍከፍ ለ ሁሉ ዝቅ የሚል ስለማይመስለው ታሪክ በሀገራችን ሲደጋገም ይታያል ቤተክርስቲያን ግን ሁሉንም አሳልፋ እየኞረች ነው፡፡
    መንፈሳውያን አባቶቻችን ያልናቸውና ያከበርናቸው ቤታችንን አሳልፈው ከሸጡብን ፍትህን ይበይኑልን ዘንድ ፈጣሪ የሾማቸው ባለስልጣኖቻችን በግፍ ከፈረዱብን ዐይኖቻችን ወደ ሰማይ አቅንተን ከማልቀስና የማያዳላው አምላክ የሚሰጠንን ፍርድ ከመጠበቅ በቀር ምን እንላለን፡፡ መጽሐፉስ “እስመ አቡየ ወእምየ ገደፉን ወእግዚአብሄር ተወክፈኒ/ እናት አባቴ ትተውኛልና እግዚአብሔር ሆይ ተቀበለኝ” አይደል የሚለው በመዝሙር 26:: ጌታችንም በማይታበል ቃሉ “የጥፋት ርኩሰት በቅድስናው ስፍራ ቆሞ ስታዩ በደጅ እንደቀረበ አንባቢ ያስተውል” እንዳለው የምናየው ሁሉ ከመጻህፍት ቃል የወጣ ስላልሆነ እንደ ተዓምር ልናየው አይገባም ልናስተውል እንጂ፡፡
    አምላክ ሆይ ሀገራችንንና ቤተክርሲቲያናችንን በምህረት ዐይኖችህ ተመልከትልን አሜን!!!

    ReplyDelete
  4. አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ እባክህን ያቤተክርስትያናችንን ፈተናዋን አቅልልን ውጊያው ከማን ጋር ይሁን ባለ ሐብቱ ቤተክርስቲያንን እርጂ መስሎ ያርሱን ሐብት ያሚያካብትበትን መንገድ የሚፈልግ ሆኗልና ማን ይታመናል አስመሳይ ክርስቲያን በዛ የሰጠዉን አምላኩን እንደገና ሊሰርቅ ተነሳ እግዚአብሔር አምላካችን ከተሰወር ከ ድፍርት ሐጥያት ያዉጣን አቤቱ አምላካችን ሆይ እባክ የግፍ ብር ያሰከራችዉ እንደነ ጌታቸው ዶኒ ላሉት ባለሐብቶች ተዉ ተመለሱ በላችዉ ካልሆነም የግፍ ብር አስክሯችሗልና እናንተም እንደ ይሁዳ ሞታችሁ ስቅላት ይሁን ዋ!!! አምላክ ታግሶ ሲፍርድም የዚያኑ ያህል ነዉ!!!

    ReplyDelete