Monday, April 30, 2012

" ከሀይማኖት ወዲያ ምን አለ፣ ለሀይማኖት መሞት ጽድቅ ነው።" የገዳሙ አባቶች

  •  በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ መጓዛቸውንነና "ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል" ብሏል የኢሳት ዜና፤

(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 23/2004 .ም፤ April 30/2012 )፦፦ "በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ መትመማቸውን እንዲሁም ሁለት ነጮች መገደላቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን" ኢሳት የተባለው ብቸኛው ከአገር ውጪ የሚገኝ ነጻ የዜና ተቋም በሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ / ዘገባው አስታወቀ። "የገዳሙ አባቶች ለሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እስከ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኙ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ አካባቢው መትመማቸውን ተከትሎ ሁለት ነጮች መሞታቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ እኛ ከህዝብ ጋር አንጣላም በማለት አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል" ያለው ዜና ተቋሙ "የሟቾቹ እና አካባቢውን ለቀው የወጡት ነጮች ምዕራባውያን ይሁኑ የቻይና ዜጎች አልታወቀም" ሲል አክሏል።

5 ያላነሱ የአካባቢው ነዋሪዎች በዋልድባ ተገኝተው ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን፣ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላትም እርምጃ ለመውሰድ ፈርተዋል። ሁኔታው እጅግ አስፈሪ ነው፣ መንግስትና ህዝቡ ተፋጠዋል፣ የአካባቢው ወጣቶችም ወደ አካባቢው ለመጓዝ እየተመካከሩ ነው ሲል አንድ ጉዳዩን በቅርብ ሆኖ የሚከታተል ሰው ለኢሳት ገልጧል።
"ሰራተኞቹ እኛ ለህዝብ ልማት ይውላል ተብሎ ነው የመጣነው፣ እናንተማ ካልፈለጋችሁት እኛ እዚህ ምን እናደርጋለን?" በማለት አካባቢውን ለቀው በመውጣታቸው፣ በአሁኑ ጊዜ ስራው ሙሉ በሙሉ ቆሟል።
መንግስት ስራው ተቋርጧል በማለት ለአካባቢው ነዋሪዎች ቢናገርም፣ ህዝቡ ግን ሚጢቆ በሚባል ቦታ ላይ የተተከሉት ሁለቱ የኤሌክትሪክ ጄኔሬተሮች ካልተነሱ ስራው መቋረጡን ከልብ አምነን ለመቀበል አንችልም የሚል መልስ ሰጥቷል።
የአካባቢው ህዝብ አሁንም ጄኔሬተሮቹ እስኪነሱ ድረስ በትእግስት በአካባቢው ተገኝቶ እየጠበቀ ነው። ህዝቡ በስንቅ እጦት እንዳይቸገር እርስ በርሱ እየተተካካ እንደሚጠብቅ ለማወቅ ተችሎአል።
የገዳሙ አባቶች" ከሀይማኖት ወዲያ ምን አለ፣ ለሀይማኖት መሞት ጽድቅ ነው።" በማለት ሰሞኑን ህዝቡን እየዞሩ ሲያስተምሩ ነበር። መንግስት የተወሰኑ መነኮሳትን አፍኖ መውሰዱም ታውቋል።
አሁን በሚታየው ስሜት የዋልድባ የስኳር ግንባታ ተፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል አንድ የአካባቢው ሰው ለኢሳት ተናግረዋል። የህዝቡ ቁጣ ከመጠን እያለፈ ነው ያሉት እኝህ ሰው መንግስት ከህዝቡ ጋር እልህ ውስጥ የሚጋባ ከሆነ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የመንግስት ባለስልጣናት በግንባታው ዙሪያ የሀይማኖት አባቶች ስምምነታቸውን ሰጥተዋል ቢሉም፣ ህዝቡ ግን የሚቀበለው አልሆነም።


8 comments:

  1. እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያናችን ይጠብቅ። በርቱ በሏቸው እኛም ለገዳሙ ህልውና ለሀይማኖታችን እንታገል። ለሀይማኖት መሞት ከጽድቅም በላይ ጽድቅ ነው። እግዚአብሔር አምላክ አንድ ልብ ያድርገን!!!

    ReplyDelete
  2. I do,not turst esat they exagurate things so please let us know from your side.

    ReplyDelete
  3. the news is good, however, its hard to trust "Esat" as a reliable source. As 'hiwot' says they have a bad reputation. If, in any means, you can confirm this news, we would highly appreciate your help.

    ReplyDelete
  4. Aba Haregewoyne, GojamMay 1, 2012 at 1:35 PM

    ጃንሆይን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች (እነ አቶ መለስ) ገለበጡ።
    ዛሬ ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ግብ ግብ ከገጠሙ አቶ መለስን የሚገለብጣቸው የእግዚአብሔር ሃይል ነው። ኢትዮጵያ ከጥንት ከአዳም ጀምራ እግዚአብሔር በክርስትና ያስቀመጣት አገር ነች። ሌሎች እምነቶች ከጥቅምና ከጥገኝነት ጋር በተያያዘ ሁኔታ የተቀበለቻቸው እንግዶችዋ ናቸው። ስለዚህ ኢትዮጵያ የክርስቲያን ሀገር ነች ክርስቲያን መንግስት ብቻ ነው የሚያስተዳድራት። ይህን አንቀበልም የሚል እንግዳ ካለ ኢትዮጵያ በመልካም አሸኛኘት ወደ መረጡት መንግስት ሀገር ልትሸኛቸው ሁል ጊዜም ዝግጁ ነች። አቶ መለስና ጥቅመኛ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ብታስቡበት መልካም ነው፤ እየተከተላችሁ ያለውን መንገድ እንደገና ብትቀይሱት ይሻላል። ክርስትና እና ሰሜን አሜሪካ ክብር ይሻሉናነው።

    ReplyDelete
  5. Hello Andadirgen. Thanks for the updated news as usual.

    I think this is the time we all Christian should pray very strongly about our Church, our Country. I also feel that we should be united in all aspect. We have seen, read the suffering of our Muslim fellow Ethiopians. Some have already killed by the government force. We have to fight also this kind of oppression. When it comes to freedom of Religious aspect we (all Christians and Muslims) should unite more than ever before. This is a time for such being unification. May GOD help us. Every one the victim here, so no need to sit a side and watch some other people's suffering.

    In conclusion, our Religious leaders, let us pray for one another's suffering. Media like this blog and others, please teach us all this. Write about all this.

    Here I quote what Nelson Mandela said: "our fight is against all forms of racism". I know in the past there were a lot of bad things done by our leaders, between religious conflicts. Let us stop thinking about the past. The past should be buried in the past and we say our fight is against the racist government. We say our fight is against the divide and rule principle.

    I hope Andadrigen will write an article in detail on an issue of unification in all aspect.

    ReplyDelete
  6. Even this news is true because I also heard the same on VOA,please don't post esat news They don't mind about us they care all about politics.And ETV is also the same with ESAT. I only believe what VOA says.
    Thanks

    ReplyDelete
  7. Thіs ѕite was... how ԁo you ѕay it?

    Relevant!! Finally Ι've found something that helped me. Thanks a lot!

    my web blog www.Paydayloanst3.com
    Feel free to surf my website ; Online Payday Loan

    ReplyDelete
  8. who are tidy. For those that are stipendiary their goodness benefits noesis, and you can
    prepare your routing count and classify out telescoped period medium of exchange requirement (say betwixt
    two successive paydays! As the note life history
    may assist you intelligent currency without pledging of
    assets and the payment period. former online payday loan who are remove.
    For those that are paying their eudaemonia benefits message, and you can prepare
    your routing keep down and take out sawed-off statement monetary
    prerequisite (say betwixt two sequential paydays!
    As the annotation chart may aid you ready wealth without
    pledging of possession and the defrayment word. tardily
    Also visit my web blog : online payday loan

    ReplyDelete