- ለሳተላይት ሥርጭቱ ከ12ሚ. ብር በላይ ዓመታዊ በጀት ጸድቋል
(አዲስ አድማስ ጥቅምት 20 2008 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ፣ ምእመና ድምፅዋን የምታሰማበትና መረጃ የምትሰጥበት የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት እንድትጀምር ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡
ከጥቅምት 12 ጀምሮ የዓመቱን የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በማካሔድ ላይ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የቴሌቪዥን አገልግሎቱን ለማስጀመር ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ በጀት ከትላንት በስቲያ ማጽደቁ ታውቋል፡፡