- በአባ ጳውሎስ 20ኛ ዓመት በዓለ ሲመት 5 ሚሊዮን ለማትረፍ ታቅዶል፡፡
- የአዲስ አበባ እና ጠንካራ ሀገረ ስብከቶች ጠቀም ያለ ገንዘብ ይጠበቅባቸዋል ከተሳክ አውሮፕላን ከተገዛ አባ ጳውሎስ በአፍሪካ የመጀመሪያው ይሆናሉ የጳጳሳት ሹመት ኮሚቴ ተቋቁሟል
- በ18ኛ ሲመት ዓመት ላይ ሰርፕራይዝ ለማድረግ ሀውልት ብለው ጣኦት አቆሙላቸው
- በ20ኛው ሲመት ላይ አውሮፕላን ለመግዛት እቅድ ይዘዋል
- በ22ኛው ሲመት ላይ ቅዱስ ብለው ፅላት ሊያስቀርፁላቸው ይችላሉ
- በ24ኛው ሲመት ላይ……….?????????
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ 5ኛው ፓትርያርክ ሲሆኑ በ2004 ዓ.ም. ዘመነ ፕትርክናቸው 20 ዓመት ይሆነዋል በመሆኑም 20ኛው የበዓለ ሲመት በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር እና ከተሰበሰበው ገንዘብ ላይ 5000000 (አምሰት ሚሊዮን) ብር ለነወ/ሮ እጅጋየሁ ለግላቸው ለማትረፍ ገንዘቡን ለመሰብሰብ ምክንያቱ የአውሮፕላን ግዢው እንዲሆን ከየአጥቢያው እና አቅም ካላቸው ሀገረ ስብከቶች ገንዘብ በማሰባሰብ በዓሉን ልዩ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ በሚሰበሰበውም ገንዘብ ለፓትርያሪኩ ልዩ አውሮፕላን ለመግዛትም ታቅዷል፡፡