- አቡነ ቴዎፍሎስ በ1968 ዓ.ም ለአባ ገ/መድህን (የአሁኑ አቡነ ጳውሎስ) እንዲ ብለው ነበር …. አባ ገብረመድን (የአሁኑ አቡነ ጳውሎስ) በነገሮች በጣም ሲቸኩሉ ፤ ለመሾም በጣም ሲጣደፉ፤ ለጵጵስና እንዲያጯቸው እና በጊዜው የነበረው ሲኖዶስ እንዲያፀድቅላቸው ከልክ ያለፈ ምኞታቸውን የተመለከቱት አቡነ ቴዎፍሎስ ‹‹ ልጄ ቀስ በል ጵጵስናውን ትደርስበታለህ ኋላ ግን ሸክሙን አትችለውም›› ብለዋቸው ነበር፡፡
.............ኢትዮጵያውያን አብዮትን የምናወቀው በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ሳይሆን በውስጡ አልፈን በቃጠሎው ተገርፈን ወላፈኑን ቀምሰን ነው፡፡ በዛን ወቅት የነበረው የሶሻሊስት ርዕዮት አለም አብዮታዊነትን እንደ ታላቅ ነገር ሲሰብክ የነበረ በመሆኑ ብዙ ወጣቶች አብዮተኛ ተብለው ሀገሪቱንም አብዮታዊት ኢትዮጵያ አስብለዋታል፡፡ በዚህች ተአምረኛ ሃገር አብዮታውያን ወንድሞቻችን ጸረ አብዮተኛ የተባሉ ወንድሞችቻቸውንና እህቶቻቸውን ቅርጥፍ አድርገው በልተዋል፡፡ በዚያ ክፍለ ዘመን አብዮት ልጆቿን ትበላለች በሚል ፈሊጥ ብዙዎች ወጣቶች ጸረ-አብዮት፤ ጸረ ህዝብ ተብለው አይሆኑ ሆነዋል..ጊዜው ጥቁር ጠባሳውን ጥሎ ያለፈው ሁሉም ላይ በመሆኑ የጊዜው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን 2ኛ ፓትርያልክ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ላይ የደረሰው በደል ግን ለየት ያደርገዋል....
በዚያ ወቅት ደርግ ጳጳስ እንዲይሾሙ ትእዛዝ አውጥቶ ነበር።አቡነ ቴዎፍሎስ የደርግን ትእዛዝ ሽረው ሦስት ጳጳሳትን ሾሙ።ደርግም ትእዛዜን አልሰማህም ብሎ ፓትሪያርኩንና ሦስቱን ተሿሚ ጳጳሳት እስር ቤት ጨመራቸው።በወቅቱ የተሾሙት ጳጳሳት አቡነ ባስልዮስ፤አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ጳውሎስ ነበሩ።ከጊዜ በኋላ ሦስቱ ጳጳሳት ከእስር ሲፈቱ ፓትሪያሪኩ ብቻ በዚያው ቀርተዋል።
ጥቂት ከመፅሐፉ የተወሰደ......
በእስር ቤት ደረሰባቸውን ፀዋትወ መከራ በዓይን ያዩ በታላቁ ቤተመንግስት አብረዋቸው ታስረው የቆዩ ፤ በአፄ ኃ/ስላሴ ዘመን በስልጣን ላይ የነበሩ ታላላቅ ሰዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ የአይን ምስክሮች መካከል እስካሁን ድረስ በህይወተ ስጋ ካሉት ከአቶ አብርሐም ወርቅነህ እና ከጀኔራል መኮንን ደነቀ በተገኝው የቃል መረጃ መሰረት ቅዱስነታቸው መጀመሪያ የታሰሩት ለብቻቸው በኢዮቤልዩ ቤተመንግስት ነበር፡፡ በዚህ ቦታ ጥቂት ቀናት ከቆዩ በኋላ ........