Thursday, October 4, 2012

“ድካም በፍሬ ሲታጀብ ለሚቀጥለዉ አገልግሎት ያተጋል”


በአቡነ እስጢፋኖስ እና በምዕመናኑ ብርቱ ድጋፍ ለጅማ ከተማ መጀመሪያ የሆነ  G + 5 ሁለገብ ህንጻ


በእርግጥ የእግዚአብሔር ቤት የሚሰራዉ ራሱ ባለቤቱ ፍቃድ ብቻ ነዉ። ያኔ ሀገረ ስብከቱ ይህንን ህንጻ ሲጀምር ቤተክርስቲያን መቃብር ቤት እንጂ ፎቅ መቼ ትሰራለች ያሉን የቅዱስ ላሊበላን ውቅር አብያተክርስቲያናት  ያላዩና ያልታደሉ አእምሮዎች በጊዜው ነበሩ ፤ በብጹዕ አባታችን አቡነ እስጢፋኖስ እና በምዕመናኑ ብርቱ ድጋፍ ለጅማ ከተማ መጀመሪያ የሆነው ባለ አምስት ፎቅ ግዙፍ (G + 5) ሁለገብ  ህንጻ ተጀምሮ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷ ፤ ይህ ስራ ሲጀመር እዚህ ደረጃ ይደርሳል ብሎ የገመተ ማንም የለም ፤ እንደ ሌሎች ተቋማት ህንጻዎች የህንፃ ዲዛይኑ ብቻ ቆሞ ይቀራል የሚሉ ብዙዎች ነበሩ  ፤ የሚሰራበትም ብር ብዙ ከመሆኑ አኳያ በጣም ባጭር ጊዜ አሁን ያለውን የደረሰበት ደረጃ ይደርሳል ማለትም አስቸጋሪ ነበር ፡፡

ምዕመናን መሪ አባት ካገኙ ገና ብዙ ስራ ይሰራሉ ፤ ከዓመታት በፊት በቦታው የተደረገው ነገር የደረሰው መከራ ሀገር ለቆ የሚያበር ነበር ፤ በአሁኑ ሰዓት በጅማ እየተሰራ ያለውን ሃይማኖታዊ ስራዎች ለተመለከተ ክርስትያን እንደ ሚስማር ሲመቱት ለመጠንከሩ ምስክር ይሆናል ፤ የጅማ ሀገረ ስብከት በልማት እንቅስቃሴዉ ለሌሎች ሀገረ ስብከት ብቻ ሳይሆን ለከተማዉም ተምሳሌነቱ የላቀ ስፍራ የሚሰጠዉ መሆኑን አሳይቷል ወደፊትም ያሳያል አሁንም የተሰራው እና ከዚህ በፊት በተከናወኑ  ተግባራት ወደ ኋላ ሳንል የተሻለ ልንሰራ ፤ በኖርንበት ዘመን ለመጪው ትውልድ አሻችንን ልንጥልለት ይገባናል ፤ በዚህ መደሰት ብቻ ሳይሆን ሌሎችን የቀሩንን አገልግሎት ልናስብ እና ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ እንደተናገረዉ የኃላችንን ትተን የፊታችንን ልንይዝ ይገባናል።

10 comments:

  1. This is such a great news!!! Egziabiher Yimesgen!!! Gena bizu eniseralen!!!

    ReplyDelete
  2. Wow thanks God, we know that you repay us.

    Habtamu z hawassa

    ReplyDelete
  3. Good news! All h/sibkets learn more from Jima h.sibket.

    ReplyDelete
  4. Good news! All h/sibkets learn more from Jima h.sibket.

    ReplyDelete
    Replies
    1. "Le Egziyabher yemisanew neger yelem" enquan yerasun bet yikirena yesew bet yemisera amlak gena bizu yiseral kegna yemitebekew bekin menesat new le abatachin edime ketena gar yistilin ye jimma mihimenan bertu EGZIYABHER kenante gar yihun.

      Delete
  5. Egziabher yisebah. Des yemil zena new.

    ReplyDelete
  6. ጉረኛ፤- እንኩአን ለዲንቢጥ ለዝሆንም አንደነግጥ- የፈለጋችሁትን ሥም ብትሰጡንና ብትፈራገጡ፣ ለሌላው ለማስጠላት ውሸቱን ሁሉ
    በክፉ ብትናገሩ፣ አምላካችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእያንዳንዳችንን ውስጥና ውጭ በድንብ ስለሚያውቅ ብዙ አትቸገሩ።
    ያመነውን አውቀናል የቆምንበትን አለት፤ ፅኑ ነው መሠረቱ የታመነ ነው ከጥንቱ። እሱ ያውቀናል ምን አስጨነቃችሁ። በሌላው
    የክርስትና ህይዎት ውስጥ ምን አገባችሁ። አንድ ሰው የፈለገውን የመሆን ነፃነት እኮ በእግዚአብሔር ዘንድም ተሰጥቶአል። ታዲያ
    እናንተ አንዴ ተሃድሶ ፣አንዴ ደግሞ መናፍቅ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ተቀንጥሶ፣ ተበጥሶ እያላችሁ ህዝበ ክርስቲያኑን ከእግዚአብሔር ቤት
    ለማሸሽና በሰዎች መካክል ክርስቲያናዊ ፍቅር እንዳይኖር ለማድረግ እንቅልፍ እስክ ማጣት ድረስ መጫር ምን ይሉታል ጌታችን
    እንኩአን እሳትና ውሀ ቀርቦልሃል፤ እጅህን ወደ ፈለግህበት ላክ አይደል ያለው ስለዚህ ሰዎች ያልበላቸውን ጀርባ በግድ ልከክላችሁ
    አትበሉ። እንኩአን ክርስቲያኖችን እስላሞችንም ቢሆን እንደእምነታቸው ማመን ይችላሉ እንጂ ፤ አንተ እንዲህ ነህ አንቺ እንዲያ ነሽ
    አንተ ልክ አይደለህም እኔ ልክ ነኝ በማለት ጉንጫችሁን ባታለፉ መልካም ነው። ምክር ለመስጠት ያህል ነው ። ካስተዋላችሁ እኛን
    ፍቅር የሚያሳጣን ፤ በማያገባን ነገር ውስጥ ስንገባ ነው። ማለትም በሰው የግል እምነትና ህይወት ወስጥ ስንገባ ነው። እስቲ ሌሎች
    አለሞችን ተመልከቱ በግል እምነትና በግል ህይወት ውስጥ ገብተው አይበጣበጡም። ለምን አናስተውልም የሰይጣንን ሥራ እኮ እየሰራንለት
    መሆኑን አንዘንጋ። በሌላ ጊዜ እስክንገናኝ ድረስ ደህና ሁን\ኝ።

    ReplyDelete
    Replies
    1. WEDAJE YETSAFIKIBET MIKINYAT ALGEBAGNIM.KERESU GAR MINIM YEMIGENANIBET NEGER YELEM EKO.BERGIT LEZIH TSIHUF NEW COMMENT YADEREGIKEW?YAM HONE YIH GIN MESADEB KEKIFU NEWNA KEKIRSTIYAN AYITEBEKIM.

      Delete
  7. Wondim asteway libona yistih 'woreh arambana kobo new'. This article is talking about investment. Do you oppose investment? Who are you? Are part of orthodox?

    ReplyDelete
  8. Wondim asteway libona yistih 'woreh arambana kobo new'. This article is talking about investment. Do you oppose investment? Who are you? Are part of orthodox?

    ReplyDelete