Tuesday, July 24, 2012

“ሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ፓርቲ” ለመመስረት ጥያቄ መቅረቡ ተሰማ


  •   መንግስት በጥያቄው ደንግጧ
  •    “ ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለው ፡፡” የኢትዮጵያ ህገ መንገስት አንቀጽ 31

(አንድ አድርገን ሐምሌ 18 2004 ዓ.ም)፡- የሀገሬ ሰው “የባሰ አለና ሀገርህን አትልቀቅ” ይላል ፤  በአሁኑ ሰዓት  እንዲህማ አይታሰብብ የምንለው ጉዳይ እንደ ትልቅ ጉዳይ ብቅ ብሏል ፤ ይህ ጥያቄ ውስጠ ወይራ ነው ፤ መንግስት የሚደሰኩርለትን ዲሞክራሲን መሰረት አድርጎ የውስጥን አላማ ለማሳካት የተነሳ ጥያቄ ፤ ካለመጠይቅ ደጃዝማችነት ይቀራል በማለት የተነሳ ወቅታዊ ጥያቄ ፤ ሙስሊሙን ነጻ አወጣለው በማለት የሙስሊምን የበላይነት ለማረጋገጥ ሲባል የዘመናት ጥያቄዎቻውን ለመመለስ ያመቻቸው ዘንድ የጠየቁት ጥያቄ ፤ ……


የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ተሰናባቹ የአሜሪካ የአዲስ አበባ አምባሳደር በጊዜው  ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ስለሚደረገው ሰርጎ ገብ ውሀቢዝም እንቅስቃሴ ከዊኪሊክስ የተገኝ መረጃ ለዓለም ወጥቶ ነበር ፤ ይህን መረጃ ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ከመላኩ በፊት የኢህአዴግ መንግስት ጠንቅቆ እንደሚያውቀው በጊዜው በሚወጡ ማስረጃዎች ለማወቅ ተችሏል ፤ የአሜሪካ ኢምባሲ ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ወደፊት ወሀቢያ የእግር እሳት እንደሚሆንባት ጨምሮም ገልጾ ነበር ፤  የዛሬ ሁለት ዓመት በደሴ ፤ በአርሲ ፤ በሀረር ፤ በምስራቅ ሀረርጌ እና በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ወሀቢያን የሚያራምዱ ሰዎች የራሳቸው በሚሏቸው ሰዎች አማካኝነት ረብጣ የነዳጅ ብር እየከፈሏቸው አመለካከታቸውንና አይዲዎሎጂያቸውን ወደ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የማውረድ ስራ ሲሰሩ እንደነበር ይታወቃል ፤ከዊኪሊክስ የወጣ መረጃን ለማንበብ ይህን ይጫኑ Wahabism in Ethiopia as "CULTURAL IMPERIALISM") 

ይህ አካሄድ መጨረሻው ኢስላማዊ መንግስት እስከ ማቋቋም ይደርሳል ፤ እኛ ይህን ለማለት የደፈርነው በጊዜው ከወጡ ሁለት መረጃዎች በመነሳት እንጂ መንግስት በኢቲቪ የሚደሰኩረውን ነገር መሰረት አድርገን አይደለም ፤ በመሰረቱ ኢቲቪ ላይ በአሁኑ ወቅት እያየን ያለነው ሁሉም እውነት አይደለም ሁሉም ደግሞ ውሸት አይደለም ፤ የፖለቲካ አካሄድ እንዳለ ሆነ በርካታ እውነታዎችም አብረውት እንዳሉት ለማየት ችለናል ፤ መንግስት ይህ ስር የሰደደ ለሀገርም ይሁን ለህዝብ የማይጠቅምን ፤ ሀገርን አደጋ ላይ የሚጥልን አመለካከት በጊዜው እንደ ተራ ነገር በመመልከት በ2003 ዓ.ም የካቲት ወር የሚመለከታቸውን የእስልምና የእምነቱን አባቶች በመጥራት በሀገሪቱ የሚካሄደውን ነገር እንደደረሰበት እና እጃቸውን እዚህ ላይ የሰደዱ ሰዎች እጃቸውን ከዚህ አመለካከት ላይ እንዲያነሱ ያለበለዚያ ግን ህጉ በሚፈቅደው መጠን እርምጃ እንደሚወስድ አበክሮ መናገሩ ይታወቃል ፤   ነገር ግን መንግስት የተናገረውን ወደ ተግባር ሲለውጠው መመልከት አልቻልንም ፤ ይህ አመለካከት ሲጀምር ግብር በሚከፈልበት ቦታ ላይ ሙስሊም ማህበረሰብ እንዳይሰግድ ያዛል ፤ ኢትዮጵያ የአረብ ሀገራት አባል እንድትሆን ጠንክሮ ይሰራል ፤ ሙስሊም ነጋዴ ግብር መክፈል ያለበት ለእስልምና መንግስት እንጂ ለማንም እንዳልሆነ አበክሮ ያሰብካል ፤ ሀገሪቱ በሸሪአ ህግ  እንድትተዳደር ይደነግጋል ፤ ወሃቢያን ለማስፋፋት ፍቃደኛ ለሆነ ሰው ለአንድ ተራ ምዕመንም በወር ከ10 ሺህ ብር በላይ በካሽ እንደሚከፍለው መረጃዎች ያመለክታሉ ፤

መጀመሪያ የታሰበውና የተነሱበትን አላማ ማሳካት ያስችላቸው ዘንድ በአገሪቱ ላይ ሙስሊሞችን የሚወክል ፤ ሙስሊሞችን ነጻ ለማውጣት የሚታትር የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም ፍቃድ መጠየቃቸው በአሁኑ ወቅት ተሰምቷል ፤ ይህ ጥያቄ መቅረብ ማንንም ሳይሆን የመንግስት ባለስልጣናትን ክፉኛ አስደንግጧቸዋል ፤ ሰዎቹ ይህን ጥያቄ ሊያነሱ የፈለጉበት ነጥብ ምንድነው ?  ጥያቄው መነሳቱ ሳይሆን ትልቁ ጥያቄ ሊሆን የሚችለው አሁን የያዙት አመለካከት ምን ያህል ረዥም ርቀት ለመጓዝ ቆርጠው መነሳታቸው ጭምር ነው ፤ ይህ የፖለቲካ ፓርቲ መተዳደሪያ ደንቡ ምን ሊሆን ይችላል ?  አባላቶቻቸው እነማን ናቸው ? ምን አይነት አላማ ለማሳካት ነው በፖለቲካ ፓርቲነት መቋቋም ያስፈለጋቸው ? ይህ ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ ነው ፡፡ ይህ ወሬ የተሰማው በአሁኑ ሰዓት ሀገሪቱ ያለችበትን የሃይማኖት ችግር እንዴት እዚህ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ፤ ከእምነት ተቋማት ምን አይነት ጥያቄዎች ለመንግስት አካላት እንዳቀረቡ ፤ ጥያቄዎች ከህገመንግስቱ አኳያ እንዴት እንደሚታዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሚወያዩበት ወቅት የተነሳ ሃሳብ ነው ፤

በአሁኑ ሰዓት ተሀድሶያውያንን ለመጠራረግና ከቤተክርስቲያን ውስጥ ለማስወጣት ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል ፤ በዚህ አጋጣሚ ብዙዎች ለምን እንዲወጡ ትገፏችዋላችሁ? ለምን ተምረው አይመለሱም ይላሉ?  ሰዎቹ የእውቀት ችግር የለባቸውም ፤ “አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም” ነው ብሂሉ ፤ ይህ የውስጥ ችግር ሲሆን ይህን የመሰለ የውጭ ችግርን ለመከላከል ምን እየሰራን እንገኛለን ? እኛ እንደሚታየን ይህም የወደፊት ቤተክርስቲያን አደጋ ነው ፤ ዛሬ ዘሩን ለመዝራት ሲሞክሩ ብንመለከት ነገ ፍሬ አፍርቶ የምናጭድበት ጊዜ እንደማይመጣ እርግጠኞች ሆነን መናገር አንችልም ፤ አይኖቻችንን ረዥም ርቀት እንዲያዩ እንፍቀድላቸው ፤

ይህን የመሰለ ፓርቲ ስያሜ የምናገኝው በግብጽ ፤ በሊቢያ ፤ በቱኒዚያ ባህሪን በሶሪያ እና መሰል የአረብ ሀገራት ነው ፤ በግብጽ 90 በመቶ የሚሆነው የእስልምና ተከታይ ሲሆን ቀሪው 10 በመቶ ደግሞ የክርስትና ተከታይ መሆኑ ይታወቃል ፤ ባህሬን ውስጥ ካላት 1.2 ሚሊየን ህዝብ ውስጥ 98 በመቶ የሚሆነው የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ የተለያዩ እምነቶችን ይከተላሉ ፤ በተመሳሳይ ኳታር 1.7 ሚሊየን ከሚሆነው ህዝቧ አብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታይ ነው ፤ በሶሪያ 89 በመቶ የሚሆነው ሙስሊም ሲሆን 11 በመቶ ግድም የሮማን ካቶሊክና ክርስትያኖች እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ ፤ ይህን ነገር ያነሳነው ያለምክንያት አይደለም ፤ እነዚህ ሀገራት ላይ ሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም ጥያቄ ቢነሳ ተገቢ ነው ብለን መቀበል እንችል ይሆናል ፤ መጀመሪያውኑ ህገ መንግስታቸው የሸሪያን ህግ መሰረት አድርገው ስለመሰረቱት የፓርቲውን ምስረታ ለመፍቀድ ብዙም አዳጋች አይሆንባቸውም የሚል ግምት አለን ፤ እንደ ኢትዮጵያ ባለች ከ45 በመቶ በላይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትያኖች፤ 33 በመቶ ሙስሊም አማኞች ፤ 18 በመቶ አካባቢ ፕሮቴስታንቶች በሚኖሩበት ሃገር ላይ ይህን ጥያቄ ማቅረብ ማለት ምን ማለት ነው ?

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በአንቀጽ 11 “የመንግስትና የሃይማኖት መለያየት” በሚል በንኡስ አንቀጽ 1 ላይ “መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው” ይላል ፤ በንኡስ አንቀጽ 2 ላይ “መንግስታዊ ሃይማኖት አይኖርም” በማለት ያክላል ፤ በስተመጨረሻም በንኡስ አንቀጽ 3 ላይ “ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ፤ ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም” በማለት በግልጽ ያስቀምጣል ፡፡ ይህን አንቀጽ እንደ አንቀጽ ከመቀመጡ በተጨማሪ መንግስት የእምነት ተቋማት እና ተከታዮቻቸው በዚህ አንቀጽ ላይ መብታቸው ምን ድረስ ነው ? ግዴታቸውስ ? የሚለውን ጉዳይ በአግባቡ የማስተማር እና የመተርጎም ስራ የሰራ አይመስለንም ፤ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 27 ንኡስ አንቀጽ 2 ላይ “ የሃይማት ተከታዮች ሃይማታቸውን ለማስፋፋትና ለማደራጀት የሚያስችሏቸውን የሃይማት የትምህርትና የአስተዳደር ተቋማትን ማቋቋም ይችላሉ” በማት ያስቀምጣል ፤ ይህ አንቀጽ እንደሚነግረን “የሃይማት የትምህርትና የአስተዳደር” ተቋማትን እንጂ የፖለቲካ ተቋም አይልም ፤  ህገ መንገስቱ አንቀጽ 31  ላይ “ ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለው ፡፡ ሆኖም አግባብ ያለውን ህግ በመጣስ ወይም ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በህገወጥ መንገድ ለማፍረስ ተመሰረቱ ወይም የተጠቀሱትን ተግባራት የሚያራምዱ ድርጅቶች የተከለከሉ ይሆናሉ” በማለት ያስቀምጣል ፤ እዚህ አንቀጽ ላይ “ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለው ” ማለት ሁሉንም ስለሚያካትት ለምን ሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ፓርቲን ለመመስረት ጥያቄ አቀረቡ ማለት   አይቻልም ፤ ለምን ቢባል ህገመንግስቱ ለማንኛውም አላማ በማህበር የመደራጀት መብትን ስለሚፈቅድ ፤ ሙሉ ህገ መንግስቱን ቢያነቡት አንድም ቦታ ሃይማኖትን መሰረት አድርጎ ስለሚቋቋም የፖለቲካ ፓርቲ የሚለው ነጥብ የለውም ፤ ይህ ለጥያቄያቸው ክፍተት የሰጣቸው ይመስለናል ፤ የህጎች ሁሉ የበላይ ደግሞ ህገመንግስቱ ነው፡፡ 

ስህተቶች የሚፈጠሩት አንድም ባለማወቅ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ የተቀመጠውን ነገር በአግባቡ ከመተርጎም ጋር በተያያዘ ችግር ወይም ህጉን ክፍተት በመጠቀም የሚደረግ የህግ ትርጓሜ  ሊሆን ይችላል ፤ ምንም ይሁን ምን ይህን ጥያቄ እንደ ተለያዩ የአረብ ሃገራት በሀገራችንም ፓርቲውን ለማቋቋም የሚፈልጉ ሰዎች ተነስተዋል ፤ በመሰረቱ ይህ አደጋው መጀመሪያ ለማን እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው ፤ ጥያቄውን የተቀበለው አካል በመጀመሪያ ያስብበት ፤ እኛ ግን ሁለተኛ ተጎጂም መሆን ስለሌለብን የሚመለከቱንን ነገሮችን ብቻ አጽንኦት ሰጥተን ብንከታተላቸው መልካም ነው የሚል ሃሳብ አለን ፡፡ እኛ የሆነውንና የተደረገውን ለእናንተ ለአንባቢያን አድርሰናል ፤ ይህን ጥያቄ  እርስዎ እንዴት ይመለከቱታል ? ሃሳብዎትን ያካፍሉን……
በሀይማኖት፣ በብሔር፣ በዘር ፣ በቋንቋ ተጠራርቶ የሚመሰረት የፖለቲካ ፓርቲ ለሀገራችን አንዳች የሚያመጣው ሰላም አይኖርም፡

 “ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም” …..

ቸር ሰንብቱ


42 comments:

  1. ገና ከመጀመሪያው ሲነሱ እኔ ገምቼ ነበር። 100% ተቀባይነት የሌለው ጥያቄ

    ReplyDelete
  2. why now? Would it harm if you waited until the dust settle? The government is looking for any reason to divide the Muslim protest and this could use this for its advantage.

    ReplyDelete
  3. ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ መንግስት ነው!! ምክንያቱም መለያየታቸው እና መከፋፈላቸው ለጊው የሚጠቅመው መስሎት ነው: ይህ ደግሞ ከሀገር ይልቅ ለራስ ፖለቲካ ቆይታ ማሰብ ነው:ፖለቲካ የሚኖረው መጀመሪያ ሀገር ስትኖር ነው:

    ReplyDelete
  4. መንግስት ይህ ስር የሰደደ ለሀገርም ይሁን ለህዝብ የማይጠቅምን ፤ ሀገርን አደጋ ላይ የሚጥልን አመለካከት በጊዜው እንደ ተራ ነገር በመመልከት በ2003 ዓ.ም የካቲት ወር የሚመለከታቸውን የእስልምና የእምነቱን አባቶች በመጥራት በሀገሪቱ የሚካሄደውን ነገር እንደደረሰበት እና እጃቸውን እዚህ ላይ የሰደዱ ሰዎች እጃቸውን ከዚህ አመለካከት ላይ እንዲያነሱ ያለበለዚያ ግን ህጉ በሚፈቅደው መጠን እርምጃ እንደሚወስድ አበክሮ መናገሩ ይታወቃል ፤ ነገር ግን መንግስት የተናገረውን ወደ ተግባር ሲለውጠው መመልከት አልቻልንም ፤ ይህ አመለካከት ሲጀምር ግብር በሚከፈልበት ቦታ ላይ ሙስሊም ማህበረሰብ እንዳይሰግድ ያዛል ፤ ኢትዮጵያ የአረብ ሀገራት አባል እንድትሆን ጠንክሮ ይሰራል ፤ ሙስሊም ነጋዴ ግብር መክፈል ያለበት ለእስልምና መንግስት እንጂ ለማንም እንዳልሆነ አበክሮ ያሰብካል ፤ ሀገሪቱ በሸሪአ ህግ እንድትተዳደር ይደነግጋል ፤ ወሃቢያን ለማስፋፋት ፍቃደኛ ለሆነ ሰው ለአንድ ተራ ምዕመንም በወር ከ10 ሺህ ብር በላይ በካሽ እንደሚከፍለው መረጃዎች ያመለክታሉ ፤

    ምን አይነት አካሔድ ነው እየሄዱ ያሉት? እነዚህ ሰዎች ለሃይማኖታቸው እንዴት እንደሚሆኑ እንዴት እንደሚሰሩ ደግሞም ኮኔክሽናቸው ከአረብ ጋር ሆነው ተቀናጅተው ለመስራት ሲነሱ ሳስብ ይገርመኛል:: እነዚህ ሰዎች እኮ የተሳሳተ መንገድ ቢሆኑም የሚዙት ጉዞ: ላመኑበት ነገር እስከሞት ድረስ መጓዛቸውም የሚያስደንቅ ነገር ነው:: መንግስት አለመቀበሉ መልካም ነው ቢሆንም እኛ ግን እውነተኛዋንና ርትዕት የሆነች ሃይማኖትን ይዘን አብረን ለመስራት አልቻልንም:: ከሃይማኖት ይልቅ ሆድ ገዛን:: ገዳማት ሲቃጠሉ: ገዳማት እንደ እርሻ ሲታረሱ: አብያተ ክርስቲያናት ሲፈርሱ: ንዋያተ ቅዱሳት ሲዘረፉ ይህ ሁሉ እየሆነ በፎቶ ብቻ ሳይሆን በቪዲዮም የተደገፈ ምስል እያየን አጃችን አጣጥፈን ዝም አልን መሪዎቻችንም ዝም አሉ ጭራሽ መንግስት ሃይማኖትን አልነካም እያሉ ይከራከሩ ጀመር:: እስኪ ልቦና ይስጠን አምላካችን እኛም ለሃይማኖታችን በአንድነት እንነሳ ሃይማኖታችንን እናስከብር:: ለወደፊቱ እነዚህ ሰዎች የጠየቁት ጥያቄ ቢፈቀድላቸው እኮ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን ለማጥፋት እንደሚነሱ አትጠራጠሩ::
    እንንቃ በህብረት እንስራ ሃይማኖታችንን አናስከብር:: ለዚህም የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን አሜን::

    ReplyDelete
  5. dddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddddd

    ReplyDelete
  6. It is expected. Nothing new. We know that the recent movement of Muslims is part of this request. Sorry to say that congratulations for those of you who support behind the recent movement of Muslims in Ethiopia. Especially, the so called Orthodox father in the other Synod in USA, opposition parties, and the ESAT television. You all together activating the recent Muslim movement in the name of fighting against EPRDF government. You are not in a position to differentiate your church and politics. Do worry when we die in the coming conflict, you will wish in our blood..... For The current ruling government EPRDF, this is the fruit of your weakness which cause the recent movement to their target.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Willy?do u believe in what u said?

      Delete
    2. የስደተኛ "ሲኖዶስ" አባቶች እና ኢሳት ቲቪ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው የሚለው ሁሌም አይሰራም። ኢህዲግን መቃወም ምን ማለት እንደሆነ ይግባችሁ። የሀገር ህልውና እና አንድ ፓርቲ በጣም የተራራቁ ናቸው። ወያኔ ከዚህ በፊት ከፋፍሎ ሰላማዊ ተቃውሞ ለማዳከም እንዳይጠቀምበት በብልሃት ብንይዘው ጥሩ ይመስለኛል።

      Delete
    3. You said z right. This is the main point.

      Delete
  7. በሀይማኖት፣ በብሔር፣ በዘር ፣ በቋንቋ ተጠራርቶ የሚመሰረት የፖለቲካ ፓርቲ ለሀገራችን አንዳች የሚያመጣው ሰላም አይኖርም፡

    ReplyDelete
  8. Egziabhere Yestachu Andadrgen

    It is a very good information and document.
    Now it is a time to act. Never ever trust muslims we all know they are run by devil.
    ምን አይነት አካሔድ ነው እየሄዱ ያሉት? እነዚህ ሰዎች ለሃይማኖታቸው እንዴት እንደሚሆኑ እንዴት እንደሚሰሩ ደግሞም ኮኔክሽናቸው ከአረብ ጋር ሆነው ተቀናጅተው ለመስራት ሲነሱ ሳስብ ይገርመኛል:: እነዚህ ሰዎች እኮ የተሳሳተ መንገድ ቢሆኑም የሚዙት ጉዞ: ላመኑበት ነገር እስከሞት ድረስ መጓዛቸውም የሚያስደንቅ ነገር ነው:: መንግስት አለመቀበሉ መልካም ነው ቢሆንም እኛ ግን እውነተኛዋንና ርትዕት የሆነች ሃይማኖትን ይዘን አብረን ለመስራት አልቻልንም:: ከሃይማኖት ይልቅ ሆድ ገዛን:: ገዳማት ሲቃጠሉ: ገዳማት እንደ እርሻ ሲታረሱ: አብያተ ክርስቲያናት ሲፈርሱ: ንዋያተ ቅዱሳት ሲዘረፉ ይህ ሁሉ እየሆነ በፎቶ ብቻ ሳይሆን በቪዲዮም የተደገፈ ምስል እያየን አጃችን አጣጥፈን ዝም አልን መሪዎቻችንም ዝም አሉ ጭራሽ መንግስት ሃይማኖትን አልነካም እያሉ ይከራከሩ ጀመር:: እስኪ ልቦና ይስጠን አምላካችን እኛም ለሃይማኖታችን በአንድነት እንነሳ ሃይማኖታችንን እናስከብር:: ለወደፊቱ እነዚህ ሰዎች የጠየቁት ጥያቄ ቢፈቀድላቸው እኮ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን ለማጥፋት እንደሚነሱ አትጠራጠሩ::
    እንንቃ በህብረት እንስራ ሃይማኖታችንን አናስከብር:: ለዚህም የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን አሜን::

    ReplyDelete
  9. What we learn from this activity? When they got power no dout they starts to attack EOTC

    ReplyDelete
  10. የድረገፁ መጠርያ 'አንድ አድርገን'ይላል፡፡ በስሩ ያየክዋቸው ሃሳቦች ግን አንድ የሚያደርጉ አይደሉም፡፡ ሕገ መንግስታችን የሁላችንም "ብዙህነታችንን ግምት ውስጥ ያስገባ" መብትና ግዴታ በግልፅ ያስቀመጠና ዴሞክራሲያዊ ነው፡፡ይሁንና በህዝበ ሙስሊሙም ሆነ ክርስትያኑ ውስጥ ከሃይማኖታዊ አመለካከት ውጭ ፖለቲካዊ ወይንም ግላዊ ፍላጎቶች በሚያራምዱ የውስጥና የውጭ ሃይላት የሚታወኩበት ሁኔታ ይታያል፡፡ ይህም ድረ ገፅ የቡድኖች አመለካከት የሚያራምድ እንጂ ኢትዮጵያን በብዙህነት የሚያስተናግድ አንድነት የሚሰብክ አይደለም፡፡ አንድነትን ለማምጣት በሃይማኖቶች ውስጥ በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መካከል በተቻለ መጠን መቀራረብን የሚፈጥሩ ሃሳቦችን ለማመንጨት ከጠባብነትና የግል ፍላጎትን ከመጫን መቆጠብ ይኖርብናል፡፡ መቻቻልን በማዳበር ሃገርንና ህዝብን ከሚጎዳ ተግባር ስንቆጠብ አንድ እንሆናለን፡፡ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. Yeraey metsihet giligbach new?

      Delete
  11. Ahun New Gudu Anadand Papasat America-Canada -Auropa Kemusilimu Gon Komew Selamaw Selefi siyadergu -Alah Weakiber Silu Tayitewal Ethiopia Lay Yetaredut Abatoch -Yetekatselew Church Teresana Bezih Guday D Efirem Eshet Yetsafutn Book Mayet yitsekmal Ethiopia Yalu Musilimoch Alamachew MIn Endehone Mawk Yichalal Le Girag Mehamed Mesikid lemesirat -Esilamaw Bank Bet Lemekifet- Eisilamaw Mihuran yemiyasitemrubet school lemekifet yetenesu nachew Ahun Abiren Eninesa Malet MIn Malet Neber ?
    Andadirgen Melkam zegeba new Deje Selam -Ahat Tewhedo Yetebalut Sile Sew Mezegebachewin titew Lehayimanotachin bikomu Abba Selam -Awde Mihiret- Deje Birhan yetebalu yemenafikan biloogoch Lehagerna Mahibere Kidusann Kemasaded Tekotsibew Melkam neger mastelalef bichilu Melkam neger neber
    Andadirgen Addis Neger -tsekam neger yemagegegew Kezih newna bertu Ahun New Gizew

    ReplyDelete
  12. ጉዳዩ አሳሳቢ ነው እኔ ግን ይህችን ጉዳይ ወያኔ አሁን ሙስሊም ወገኖቻችን ያነሱትን ጥያቄ ለማፈን እና የእኛን የክርስቲያኖችን ድጋፍ ለማግኘት በዚያውም እድሜውን ለማራዘም ያቀነባበራት ተንኮል መሆንዋ ይሰማኛል ወገኖቼ በሰከነ ልብ ሁሉን መርምሩ ወያኔ እኮ ሁሉ በእጁ ነውና ፎርጅድ ማመልከቻ ፎረጅድ መተዳደሪያ ደንብ ወዘተ አውጥቶ ህዝቡን ሙስሊሞች መጡብህ ብሎ ከፋፍሎ ለመግዛት አይተኛም እናም እባካችሁ ይህን ተንኮለኛ መንግስት እወቁበት ቁርጡን ማወቅ ከፈለጋችሁ ወያኔ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር ለማፈራረስ የኤርትራን አደራ እያስፈጸመ ነውና ከቻላችሁ እስላም ክርስቲያን ሳትሉ ሀገራችንን ለማዳን በአንድነት ጸልዩ

    ReplyDelete
    Replies
    1. Dear anonymous you don't deserve to comment on this blog. Although we take what andadirgen tells us wrong, we can check personally the interest of some extremists. What does it mean "Muslim Brotherhood Party"? can give insight here us is that these guys are not sleeping for peace but to disturb. Are they going to become the leader for all? No. So our brother/sister Anonymous take this for your info and look after what is going on to deter their movement.

      Delete
    2. "ዳዩ አሳሳቢ ነው እኔ ግን ይህችን ጉዳይ ወያኔ አሁን ሙስሊም ወገኖቻችን ያነሱትን ጥያቄ ለማፈን እና የእኛን የክርስቲያኖችን ድጋፍ ለማግኘት በዚያውም እድሜውን ለማራዘም ያቀነባበራት ተንኮል መሆንዋ ይሰማኛል ወገኖቼ በሰከነ ልብ ሁሉን መርምሩ " I agree 100%. Please take this advice into account.

      Delete
    3. ጉዳዩ አሳሳቢ ነው እኔ ግን ይህችን ጉዳይ ወያኔ አሁን ሙስሊም ወገኖቻችን ያነሱትን ጥያቄ ለማፈን እና የእኛን የክርስቲያኖችን ድጋፍ ለማግኘት በዚያውም እድሜውን ለማራዘም ያቀነባበራት ተንኮል መሆንዋ ይሰማኛል ወገኖቼ በሰከነ ልብ ሁሉን መርምሩ ወያኔ እኮ ሁሉ በእጁ ነውና ፎርጅድ ማመልከቻ ፎረጅድ መተዳደሪያ ደንብ ወዘተ አውጥቶ ህዝቡን ሙስሊሞች መጡብህ ብሎ ከፋፍሎ ለመግዛት አይተኛም GREAT!

      Delete
  13. I am an orthodox christian and I believe this is the fault of our government. The government has assigned corrupt individuals who do not have moral or spritual ground to lead devouted spritual members. The typical examples are the so called mejlis and the corrupt and morally decayed people like Aba paulos of orthodox. The fellowers wanted their leaders to be real sprituals and started movement. And the government gave these gangs cover. Then the fellowers then understood that the problems is not with their spritual leaders rather with the government who wants to control not only what people talk or discuss but also what they think. Therefore, the fellowers then started to challenge the government, Unless the governemnt lift up its hand from the religious institutions and respect the constitution, every body is waiting for opportunity. And we the orthodox christains must also fight for our right. How long shall we be led by a corrupt individual like aba paulos ? do not critizize the others while we are suffering from the same problem.

    ReplyDelete
  14. Woyyyy gudddddd.... degmo endih alu? Muslim brotherhood? Mechereshaw ken mekrebun temelketu.....

    ReplyDelete
  15. የሁሉም የሃይማኖት ድርጅቶች ፣ ተከታዮቻቸውን ከሚያስጨብጡት የሃይማኖት ትምህርት ባሻገር የሃይማኖት ልዩነቶችንም እየተነተኑ እንዲመለከቷቸው ፣ እንዲያጠኗቸው ፣ እንዲገዙላቸው ፣ እንዲጋደልሏቸው እየገፋፉአቸው ያሉ ይመስላል ፡፡ በእስልምናው በኩል ነገሩ ከረር ያለና ለኀብረተሰቡ አስጊ መሆኑን ለመመልከት በሚከተሉት ርዕሶች ያቀረቡዋቸውን መቀስቀሻ መመልከቱ መልካም ነው ፡፡ እነርሱም ተሳክቶላቸውና ቀንቷቸው መብታቸውን ቢያስከብሩ መልካም ነው ፤ ነገር ግን ሌላውም መብቱን ለማስከበር ተግቶ መንቀሳቀስ እንደሚነሳ ሊረዱና እንዲያውም ሊያግዙት ያስፈልጋል ፡፡ የመብት ጥያቄ የሁሉም ኀብረተሰባችን ጥያቄ እንጅ የአንድ ወገን ብቻ ስላልሆነ በተናጠል እንደምኞት መጋለብ አይቻልም ፡፡

    Islamist vision for ethiopia
    http://www.youtube.com/watch?v=v5wsqz7R4Vk

    Ethiopia: Muslim plan to takeover politically through jihad
    http://www.youtube.com/watch?v=nwyZH_s4vGE

    Ethiopia: The influence of wahabism
    http://www.youtube.com/watch?v=aVXEy4bVVgo

    ከተመለከትኩት በመነሳት ግምቶቼ
    - የእስላም አክራሪዎች /የሶማልያው አልሻባብን ተከትለው/ ሊዘምቱብን እየተዘጋጁ ነው
    - ጥቂት ግለሰቦች ከእስላም አገሮች እርዳታ ለማግኘትና ለመበልጸግ የሚፈጥሩት እንቅስቃሴ ነው
    - መንግሥት በሥልጣን ላይ ለመቆየት ሲል የፈጠራቸው ቡድኖች ወሬ ነው

    ReplyDelete
  16. There is a prophesy according Ethiopian Orthodox Church. The Muslim government will come but there stay as a government in Ethiopia depends on the strength of Christians(Orthodox Christians) prayers to God. It could be 3 days, or 3 years. But depends on the strength of our prayers to God. But before the Muslim government comes the existing government will disappear as a cloud disappears(I don't know I translated this one well)and after that there will be a blood shade in this country then after this time the so called Theodros, Orthodox christian leader come to this country and this years become golden times for Ethiopia.
    Source: I heard it while our grandmothers talking.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Yes this is true. But no one knows how long is 3 days according to God.Just pray.

      Delete
  17. ለምን ተጨባጭ መረጃ በሌለለው ተራ አሉባልታ እንነታረካለን። መች ነው የት ጥያቄው የቀረበው ለማን ነው ፀሐፊው ምንጩን ያሳውቀን ።ይህ ተራ የባልቴት ወሬ ነው።

    ReplyDelete
  18. ena melaw muslimu hezeb yerasu yehonewen mesqid be sereaatu meyazena balebet mehon yalechale berasu yehayemanot tekuam hayemnotun metegeber yalechale endet aregachu new yehaymanot mengest leyakuakomu new belachu setaweru yalseketetachu ewen yehe stehuf alamaw mendenew ?enante yehayemanot mengest leyakuakumo mengesten fekad teyeku yalachut egna hager new weyes lela aydelam polticawi teyake leyanesa kerto be seratu hayemanotun metgeber techerual ergetegna negn endezh aynet teyake ke muslim mahbereseb almensatu yestuhufu balebet yawekweal enante metawerut selaltefeterchew ethiopia new egna eyenornbat yalechew
    ethiopia gn yehen tera wera lemqebael betam yekebdenal

    ReplyDelete
  19. እኛ ሙስሊም ኢትዮፒያውያን ያነሳነው የመብት ጥያቄ እንጂ አንተ በእኛ ላይ እንደምትቀጥፈው አይደለም ለኢትዩፒያውያን ሙስሊም ወገኖችህ የምታስብ ከሆነ ለምን እውነቱን አትናገርም እኛ የጠየቅነው ሶስት መሰረታዊ ጥያቄ 1ኛ የሀይማኖት መሪዎቻችንን እራሳችን እንምረጥ 2ኛ መንግስት በግድ የአህባሽን አይዲዮሎጂ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ አይጫን 3ኛ አወሊያ የህዝበ ሙስሊሙ ብቸኛ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ሙስሊሙ በመረጣቸው ይተዳደር የሚል ነው ጥያቄያችን ግልፅ ነው ሰዎችን ለማደናገር አትሞክር በኢቲቪ ውሸት ስለተነገረ እውነት አይሆንም የጠየቅነው የመብት ጥያቄ እንጂ የፖለቲካ ጥያቄ አይደለም

    ReplyDelete
  20. ይህች ሃገር የሁላችንም ነች የሀገራችን እድገት ልማትና ሰላም የሚጠቅመው ሁላችንንም ነው፣ በዚህች ሃገር የምንገኝ ህዝቦች ሙስሊሙም ክርስቲያኑም ኦሮሞውም አማራውም ከምባታውም ሶማሌውም ጉራጌውም፣ አፋሩም ወላይታውም……ሁሉም መብቱ ተከብሮለት በሰላም በፍቅር በመደጋገፍ ይህችን ሃገር ማሳደግ ይጠበቅብናል የአንዱ የመብት ጥያቄ ሲያነሳ ሌላውም ሊያግዘውና በተባበረ እና አንድ በሆነ ክን...ድ አምባገንነተን መቃወም ይኖርብናል ከዚህ ውጭ ግን የሌለ ፈጠራ እና የፖለቲከኞች ጭፍን አይን ያወጣ ቅጥፈትን በማቅረብ ሰላም ወዳዱን የኢትዮጵያ ሙስሊም የመብት ጥያቄን ከአምባገነኖችና ከከፋፋዮች ጋር በመሆን ቅጥፈት ማብዛት ለማንም አይጠቅምም ግን ግን አንተና መሰሎችህ የፈለጋቹትን ብትቀጥፉ እኛ የመብት ጥያቄዎቻችን ከመጠየቅና በሰላማዊ መልኩ ከመታገል ወደ ኋላ አንልም በተጨማሪም የመብት ጥያቄዎቻችን የተረዱት በርካታ ክርስቲያን ወንድሞቻችና ወገኖቻችንም ከጎናችን እንደሆኑ 100 በ 100 እርግጠኞች ነን በተራ ቅጥፈትን በሬ ወለደ ውሸት አንድነታችንን ማንም አይበጣጥሰውም ጥያቄው ምናልባት ካልገባህ በወናነት የእምነት ተቋማችን መሪዎችን እኛው እንምረጥ ነው ተግባባን

    ReplyDelete
    Replies
    1. ነውጥ ለማንም አይበጅምና እንደ አባባልህ ያድርግልን ፡፡ ነገር ግን በንጹህ ሙስሊም ወገናችን ስም ፣ ሌላ ስውር ዓላማ ያላቸው ቡድኖች ውስጥ ውስጡን ሳይሆን በአደባባይ የሚለፍፉትን አዳምጥና ለራስህም ትንሽ ግንዛቤ ውሰድ ፡፡ ብንራብ ብንጠማም አገራችን ሰላም ሆና ፣ የሁሉም ኀብረተሰብ መብት ተከብሮ ፣ ተከባብረንና ተፈቃቅደን እንድንኖር ምኞታችን ነው ፡፡ ግን ይህን ለትምህርት የሚሆን ታሪካችንን ሊበርዙት የሚንቀሳቀሱ ወገኖች በመሃላችን ስላሉ ወንድሜ ነቃ ብለህ ተከታተል ፡፡ ከመብት ጥያቄ በስተ ጀርባ የሚባለውን እንድታዳምጥ የተለቀቀው መፈክራቸውና መቀስቀሻቸው ይኸው ቀርቧል ፡፡

      Islamist vision for ethiopia
      http://www.youtube.com/watch?v=v5wsqz7R4Vk

      Ethiopia: Muslim plan to takeover politically through jihad
      http://www.youtube.com/watch?v=nwyZH_s4vGE

      Ethiopia: The influence of wahabism
      http://www.youtube.com/watch?v=aVXEy4bVVgo

      Ethiopia: ABU HYDER radicalising muslims
      http://www.youtube.com/watch?v=joIcRLVxtYI&feature=relmfu

      Delete
  21. ለኢትዮጵያ ሙስሊም ወገኖቼ በሙሉ!!!

    በለቅሷችን በሰርጋችንና በማንኛውም ማህበራዊ የሕይወት ጉዞአችን ላይ ሳንለያይ በፍቅርና በሰላም በዚች ዘርፈ ብዙ ችግር በሚያላጋት አገራችን ውስጥ ለበራካታ ዘመናት አብረን ኖረናል:: ታዲያ ይህን ትዝታ እንደሚገባ የማያውቀውን ሙስሊም ወጣት በልተው በተረፋቸውና እንዲያውም ዓለምን ከዘይት በሚያገኙት ዶላር ጉልበት ሰይፍ መዘው አላህ ወ አክብር በማለት የአላህ ሳይሆን የእግዚአብሔር አምላክ የከበረ የእጅ ሥራ የሆነውን ሰውን ለሞት ለሚጋብዝ ለነፍሰ ገዳዩ ትምህርት አሳልፋችሁ መስጠታችሁና አገራችንን እንደ ሌላው የአረብ ምድር የደም መሬት ለማድረግ መነሳታችሁ ምን ይባላል????????

    ምናልባት በዚች ተቻችለን በኖርንባት ምድር የአረቡ ዓይነት የእርስ በርስ መተላለቅ አስነስተን ድብቅ የሃይማኖት ማስፋፋቱን እድል ለመጠቀም አስባችሁ ከሆነ የኢትዮጵያ ሁኔታ እንደ ግብጽና ሊቢያ አይደለምና አጥብቃችሁ ብታስቡበት ሁላችንም እጅግ እንጠቀማለን:: ይልቅስ የጋራ በሆነው ጉዳያችን ላይ መንግሥት እንደ መንግሥትነቱ ማስተካከል ያለበትን ፓለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስህተቶች ላይ ተገቢውን እርምት እንዲያደርግ አብረን ለመጠየቅ ብንነሳ ይሻላልና በዚህ አብረን እንድንበረታ ማሳሰብ እወዳለሁ::

    ከዚህ በተረፈ የክፉውን ሃሳብ አንስተውም ተብሎ በአምላካችን ቃል እንደተነገረን ይህ ዓለምን ሁሉ እስላም አድርጌ እገዛለሁ የሚል የሃሰተኛው ክርስቶስ መንፈስ በምድራችን ላይ ስር ሰዶ እልቂት እንዳይመጣ የሃይማኖት መሪዎች የአገር ሽማግሌዎች ምሑራን የመንግሥት ባላደራዎች ባለሃብቶች (ምነው የተከበሩ አላሙዲን ዝም አሉ??) መምህራን ተማሪዎች ወንዶችና ሴቶች በመመካከር ለሁላችንም የሚበጀውን የሰላም ኑሮ ለመኖር እንሞክር??? የእስላማይዜሽን ዓላማ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደዚህ በቀላሉ የሚታይና ቸል የሚባል ጉዳይ አይደለምና በሁሉም አቅጣጫ የተሰለፋችሁ ፓለቲከኞቻችንም አሳፋሪና ተራ የሆነ በሬ ወለደ ቅስቀሳችሁን በማቆም ለትክክለኛ ለውጥ ተናገሩ ታገሉ ትርፉ ትዝብት ነውና::

    እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሙስሊም ወገኖቻችን መብት ይከበር!
    የእስላማይዜሽን ቅዥት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ቅጥረኞች እስከ ታቀፉት ዶላር ይጠፋሉ!!!

    አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ሰውን ሁሉ(እስላሞችን ጭምር)የወደደ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ!!!
    አሜን አሜን::

    ሰላም ለኢትዮጵያውያን በሙሉ!!

    እህታችሁ

    ሰላም ነኝ

    ReplyDelete
  22. ምንድን ነዉ የዚህ ፅሁፍ ትርጉም ? እኛ ባሁን ሰአት የራሳችን ስንት ችግር እያለ ለንደዚ አይነት ቶፒክ ጊዜ መስጠት ( የራስዋ እያረረ ......) አይነት እንዳይሆን . በመጀመሪያ በኢትዮ. ውስጥ በብሔር፣ በዘር ፣ በቋንቋ ያልተከፋፈለ የፖለቲካ ፓርቲ አለ ዎይ ?
    እባካችሁ በማያገባን እየገባነ የተቀደሰችዋን ሀይማኖታችንን እና ቤተ-ክርስቲያናችንን አናሳጣት ....
    አንድ የማምንበትን ልናገርና ላብቃ .. "ሳለ መድሀኒአለም ማንም በምንም ቢደራጅ ሀይማኖታችን ያው ነች ክርስቲያን ኦርቶዶክስ "
    እግዚአቤሄር ኢትዮጲያን ይባርክ !!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. በጎጥም ሆነ በሃይማኖት መከፋፈሉ የሰው ሳይሆን የእንስሳ ባህርይ ነው ፡፡ ካልተቸገረ በስተቀር አህያ በቀንድ ከብቶች መሃል እየተጋፋ አይሄድም ፡፡ ሰው ግን እንስሳ ስላልሆነ ፣ አንዱ የሌላውን ዓላማና ፍላጎት ሳያደናቅፍና ሳያስተጓጉል በሥርዓት መጓዝ ስለሚሆንለት ፣ አንዱ ከሌላው ጋር ያለ ችግር አብሮ መጓዝ ይችላል ፡፡ ይህን በአገራችን ያልነበረ የመከፋፈል ብልሃት ለመጠቀም የሚሞክሩት ሰውን እንደ እንስሳ ለመቁጠር የሚዳዳቸው ብልጦች ብቻ ናቸው ፡፡ አሁን እየተጠቀሰ ያለው ግን እስልምናን በክርስትና ላይ ብቻ ሳይሆን ፣ ኢትዮጵያዊ እስልምናንም ሊውጠው የተዘጋጀ አዲስ የአክራሪነት እንቅስቃሴ ነው ፡፡ ስለዚህም ነው አሁን በየመስጂዱ ፣ በየከተማውና በየገጠሩ እኛን አይወክሉንም እያሉ የሚሰለፉባቸው ፤ እነዚህ የውጭ ቅጥረኞች ናቸው ፣ እስልምና ሰላምን ነው የሚሰብከው ፣ ወንድም ከወንድም ለማጋጨት የሚሯሯጡት በውጭ ኃይሎች የተገዙ ቅጥረኞች ናቸው በማለት የሚያወግዟቸው ፡፡ ስለሆነም ክርስቲያን ከክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ከእስላም ወንድሞችም ጋር አብሮ በመሰለፍ በእናት አገር ላይ የተጋረጠውን ሴራ ማምከን ግድ ይለናልና ጠቅልሎ ለፖለቲካና ለሌላ የባሰ ምክንያት መስጠቱ ብዙ አያዘልቀንም ፡፡ ሌላው ችግር እስከሚፈታ አገር በዚህኛው ሊፈታ ይችላል ፡፡ አልሻባብ በሱማሌ ያካሄደውን ርዕዮት የመሰለ ሩቅ ሳይሆን ጅማ አካባቢ እንደተጀመረ ያዩ ግለሰቦች መስክረዋልና ሱሪ ከሚያስወልቅ ውርደት የባሰ ስለማይኖር በጥሞና ተከታተለው ፡፡

      Delete
  23. ውድ አንድ አድርገኖች ያልተጻፈ በማንበብ ያልሆነ ነገር በብሎጋችሁ አታስነብቡን!!ውበቱን ይቀንሰዋል እና!ይህ የመንግስት ወሬ እንጅ ሌላ አይደለም
    በ እርትግጥ፡በፕሮቴስታንት ዌብ ሳይት ላይ አንብቤዋለሁ እድሜ ለዶክተር ሽፈራው ወደ ስልጣን ውርውር ብለዋል!ህዝብ ለ ህዝብ ለማጋጨት የተወራ እንጅ ሙስሊሙ መጅሊስ አይወክለኝም እንጅ ሌላ ሲል አልተሰማም!

    ReplyDelete
  24. it is amazing text and i expect the writer is member of the EPRDF cauz at tis time they are trying to insigate hateratism between the two religion and extend their life. please lets be honest have you seen a country led by a small group(even which doesn't have legal ground or even assembeled as rebelion before)? moreover Ethiopian muslims are far from the politics, and the military. so how could they aspire to lead the country at this time? the other thing is if you have seen after september 11 even in our country establishing muslim NGO is difficult so who are this people who want to establish political party. Definetly this is the last game for EPRDF if we are getting into it we will let them another 30 years to rule this country and moreover want to divert the ortodox followers from Waldeba affair. so be wise!

    ReplyDelete
  25. ethiopia west enkuan y muslim wondemamachoch party ayedelem majority muslim yalebet party maquaquam erasu yikebedal......ere ameroachenen eneteqemebet!

    ReplyDelete
  26. I have question please? There are government supported muslims in Ethiopia named Ahbash (Habash). To which group do they belong ? To wahabists or sufis? I will appreciate someone who give the right/true answer for this question. The answer for this question helps us to know the role of Ethiopian government behind the interest of these conflicting groups Wahabists and Sufis!

    ReplyDelete
  27. they belongs to Mr hagay elrich group of zionist.that is why he the first time gave leture in addis ababa univercity before i think 4 or five yeras ago.

    ReplyDelete
  28. ውድ አንድ አድርገኖች አምላክ አገልግሎታችሁን ይባርክ! ከዚህም በላይ በትጋት ሰርታችሁ ግንዛቤ ልታስጨብጡን ይገባል። ኢትዮጵያውያን ከእምነት ባሻገር ባህላችን ፍቅርና አንድነትን ስለሚሰብክ ሁሉን በፍቅር ማየታችን መልካም ነበር ግን የክርስቲያኑን የዋህነት በመመልከት በተለይም በአሁን ወቅት ሙስሊሞች ለኢትዮጵያ የሚያቅዱት ሃሳብ አሳፋሪም አስደንጋጭም ነው። በየፓልቶክ ሩማቸው ለሃገራችን ያላቸውን እቅድ ሰምተናል አውቀናል! ከዚህ በላይ ተኝተን ነገ ራሳችንን ለሰይፍ ግብር መስጠት የለብም፣ ከእኛ የሚጠበቀውን እየሰራን የእግዚአብሔርን እጅ በጽኑ ልንጠይቅ ይገባል።


    ውድ ፖለቲከኞች እባካችሁ ስለ ሃይማኖት ተዉና ስለቆማችሁለት አላማ ብቻ ስሩ! ዛሬ እንደ ገደል ማሚቶ ድምጽ አስተጋብታችሁ ሲሳካላቸው ደማችንን ለማስፈሰስ መከራችንን ለማብዛት አትትጉ...

    ReplyDelete
  29. እናንተ አንዳንድ ክርስቲያያኖች ሆይ
    ለምንድን ነው በመንግስት ፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ተሸውዳችሁ ሙስሊሞችን የስጋት ምንጭ እና ጨካኝ አድርጋችሁ የምትስሉ?
    ከአሁን በፊት የደረ ችግር አለ?ለምን ሚዛናዊ አትሆኑም!ሙስሊሞች ሌላ እቅድ አላቸው የምትሉ ከምን ተነስታችሁ ነው?ፓልቶክ መረጃ ሊሆን አይችልም።ማንም በ ሙስሊም ስም ሊናገር ይችላል!እንደ ህዝብ ግን እኛ የስጋት ምንጭ አይደለም ሆነንም አናውቅም!እና ምናለበት የሌለ ስጋት እና ጦርነት ባትቀሰቅሱ! ሚዛናዊነት የየትኛውም ሃይማኖት መመዘኛ ነው!! ለዚህም ነው ስለ ኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ለሙስሊሙ ቅርበት አላቸው ምክንያቱም አይኮሩም እና(ኩራት ማለት እውነትን አለመቀበል)ማለት ነው!!ስለዚህ እምነታችን ምንም ይሁን ምን ስለ እኛ እውነት ተናገሩ እንጅ የመንግስትን ፕሮፓጋንዳ እንዳለ ተቀብላችሁ አታስተናግዱ.

    ReplyDelete
    Replies
    1. ውድ ሙስሊም አስተያየት ሰጪ በእውነት ቅንነትህን ሳላመሰግን አላልፍም! እኛ አንዳንድ ክርስቲያኖች የመንግስት ፕሮፓጋንዳ ምን እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን፣ እኔ በራሴ የመንግስት ደጋፊም ተቃዋሚም አይደለሁም! የሙስሊሞችን እቅድ ለማወቅ ፓልቶክ ሩም ብቅ ማለት በቂ ነው እንዳልከው ሁሉም በእስልምና ስም ሊናገር ይችላል የነ ኡስታዝ ሳዲቅን ድምጽ መለየት ግን አያቅተንም! የማንኛውም እምነት ተከታይ የራሱን እምነት በነጻነት ማራመድ እንዳለበት ብናምንም ለነገ ቢላ ሳልንላችሁ ሲባል እየሰማን እልልል አበጃችሁ እንድንል እንደማትጠብቁ ተስፋ አደርጋለው! ሰላማውያን ሙስሊሞች ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትን ካመናችሁ በጓዳ የሚቀጠረውን ቀጠሮ ልትቃወሙ ይገባል

      እግዚአብሔር ሃገራችንን ይጠብቅልን!

      Delete
  30. Thanks for shaгіng your thoughts. I truly aρpreciate youг effоrts and ӏ аm ωaiting fοr
    your neхt ωrite ups thank you once again.


    Heге is my wеb рage
    - Online Payday oan
    Feel free to visit my weblog :: Payday Loans

    ReplyDelete