Tuesday, July 3, 2012

‹‹ብዙ ሃይማት አንዲት ሀገር›› ኢቲቪ የለቀቀው ውዥንብር


  •  982 ነጻ አስተያየት ወደ ኢቲቪ ከደወሉት አስተያየት ሰጪዎች ውስጥ 90 በመቶ ባዩት ነገር የተናደዱ እና የነበሳጩ ሆነው ነገኝተዋል
  • እውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መጤ ነችን?
(አንድ አድርገን ሰኔ 27 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ክብር ባህል እምነትና ስርዓት መንግስትና ቋንቋ ያቋቋመች የማትናወጥ ከመሆኗ ጋር ከሔኖክ ፤ ከኖህ ፤ ከመልከ ጼዴቅ ከነብያትና ከሀዋርያት ተላለፈውን ትምህርት ስርዓት ፤ እምነት ከትውልድ ወደ ትውልድ ስታስተላልፍ የኖረች በማስተላለፍ ላይ ያለች ፎኖተ ህይወት መሆኗ የተረጋጠ ነው፡፡  ቅዱሳን አበውን ፤ ኃያላን ነገስታትን ፤ ልዑላን መሳፍንትን ፤ ክቡራን መኳንንትን ፤ ዐይናሞች ሊቃውንትን በስጋ በነፍስ ወልዳ ያሳደገች የሌላ የማትፈልግ የራሷ የማትለቅ ዕጥፍ እናት ፤ ስንዱ እመቤት ናት፡፡


ከሳምታት በፊት አንድ አማርኛ ፊልም አምባሳደር ሲኒማ አዳራሽ ለመመልከት ችዬ ነበር ፤ ፊልሙ ከስክሪፕት ጽሁፉ ጀምሮ ይህ ነው የሚባል የታሪክ ፍሰት የሌለው ፤  ለሰሪውም ሆነ ለተመልካቹ  ትምህርት የማይሰጥ ፊልም ነበር ፤ በስተመጨረሻ ፊልሙ ተጠናቅቆ ከሲኒማ አዳራሹ ስወጣ የፊልሙን አርእስት ሙሉ በሙሉ መርሳቴ እጅጉን ራሴን አስገርሞኛል ፤ ሰኞ ማታ ኢቲቪ ላይ የተመለከትኩት ወቅታዊ ፊልም አምባሳደር ያየሁትን ፊልም እንዳስታውስ አስገድዶኛል ፤ ወቅታዊ ዘገባው ሲጀምር የክርስትያኖች መገለጫ የሆነውን መስቀልን ፤ የሙስሊሞች መገለጫ የሆነወን ጨረቃና ኮከብን ፤ የአይሁዶች መገለጫ የሆነውን ባለ ስድስት ኮከብ ምስሎችን አንድ ላይ አድርጎ የያዘ ነው፡፡ በመሰረቱ አዚህ ሀገር ውስጥ የአይሁድ እምነት ተከታዮች ሊኖሩ ይችላሉ ነገር የካቶሊክ እምነት ተከታዮችን ያህል እንኳ 0.7 በመቶ ቁጥር የላቸውም ፤ የአምልኮ ቦታቸው የት እንደሆነም ሰምቼም ይሁን አይቼ አላውቅም ፤ ታዲያ ለምን ይህን ምስል መጠቀም ፈለጉ ? ፤
የቀረበው ዘገባ በተቻላቸው መጠን ከእስልምና እና ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የእምነት አስተማሪዎችን ማካተት ችለዋል ፤ የታሪክ ምሁራንና መሰል ባለሙያዎችንም ማካተት ችሏል ፤ የቀረበው ፕሮግራም የተሰጠው አርዕስ እና የሄደበት አካሄድ ብዥታን ፈጥሮብናል  ፕሮግራሙ 2፡35 ቢጀመርም እስከ ፕሮግራሙ ፍጻሜ ድረስ ማስተላለፍ የተፈለገው ሃሳብ ከአሁን አሁን ይገባናል እያልን ብንሰማውም ዋና ነጥቡን ማግኝት ተስኖናል ፤

በአሁኑ ሰዓት ግን መንግስት የተፈጠረውን ያለመረጋጋት ለማቀዝቀዝ ሲል የታሪክን መፋለስ የሚያመጣ ጭብጡን በተገቢው መንገድ ልተገነዘብነውን ዶክመንተሪ ፊልም በኢቲቪ አስተላልፎልናል ፤ ተጀምሮ እስከሚልቅ ድረስ ማስተላለፍ የፈለገውን ሃሳብ በቅጡ መረዳት አቶናል ፤ በአንድ በኩል የታሪክ ምሁር ተብዬ በቅጡ ባለመረዳት በግርድፉ በመተርጎም “እንዴት ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት ልትባል ትችላች?” ብለው ሲተረጉሙ ለእሳቸው ሃሳብ መልስ በሚሆን መልኩ ዲ/ን ብርሀኑ አድማስ የክርስቲያን ደሴት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሲተረጉምና ሲያስረዳ እንመለከታለን ፤ ለምን ይህን ነገር ማንሳት ተፈለገ? ፤ በሌላ በኩል ይች ሀገር ላይ ያሉ አማንያን ክርስትያኑም ሆኑ ሙስሊም ማህበረሰቦች ለሀገሪቱ መጤ መሆናቸውን አስረድተው ሲያበቁ ዲ/ን አባይነህ ካሴ በዚህ ጉዳይ እንደማይስማማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰትያ መጤ ልትባል የማትችል መሆኗን ከመልከ ጼዴቅ ጀምሮ ያለውን ታሪኳን ሲያስረዳ ተመልክተናል ፤ በዚች አጋጣሚ ዲ/ን ብርሃኑ አድማስን እና ዲ/ን አባይነህ ካሴን የመሰሉ መምህሮችን ለቤተክርስቲያን የሰጠን አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ 

እኛን ግራ የገባን ነገር ፕሮግራሙ የተዘጋጀበት አላማ ምንድነው ? ፤ የክርስትያኑን ታሪክ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ለማጋጨት ? ወይንስ ነገሮችን በዘመናዊ አይን በመመልከት የሰዎችን እይታ ለህዝቡ ማቅረብ ? ምንም ዘመናዊ ብንሆን መኪና ባልተፈጠረበት ዘመን አይሮፕላን እንደተፈጠረ ማቅረብ መቻል ተገቢ አይደለም ፤ የዶክመንተሪ ፊልሙን ፍሬ ነገሩን እናገኛለን ብለን  ከአንድ ሰዓት በላይ ተቀምጠን ፊልሙን ብንመለከትም በስተመጨረሻ ብንጨምቀው ጠብ የሚል ነገር በማጣታችን አዝነናል ፤ ድንገት እኛ ያየንበት እይታ የጠበቅነው ነገር እና በአሁኑ ሰዓት ያለው ሁኔታ አብሮ ሊሄድልን ባለመቻሉ ከእኛ ችግር ነው በማለት ሰዎች ይህን ፊልም ከተረዱት ብለን ሶስት አራት ቦታ ስልካችንን አንስተን  ብንደውልም ከሁሉም ያገኝነው መልስ ቢኖር የተዘጋጀበት አላማ ማስተላለፍ የፈለገው መልእክት በቅጡ እንዳልገባቸው አስገንዝበውናል ፤ እና መንግስት ምንን ለማስተላለፍ ነው ይህን ነገር ዶክመንተሪ ፊልም ያዘጋጀው ? ፤ 

በአንድ በኩል የሙስሊሙን እይታ ሲገልጽ በሌላ በኩል ደግሞ የክርስትያኑን እይታ ያስቀምጣል ፤ ማንም የፈለገው እምነት የመከተልና ያለመከተል መብት የተሰጠው በንጉሱ ጊዜ ሆኖ ሳለ አሁን ግን መንግስት ያሳየን ፊልም ህዝቦች የማመን መብታቸው የተከበረላቸው ኢህአዴግ ስልጣኑን እንደተረከበ ሆኖ ሲናገሩ ተመልክተናል ፤ በንጉሱ ዘመነ መንግስት ሙስሊሞች ስራ ለመቀጠር ሃይማኖታችሁን ቀይሩ እንደሚባሉም ለመጀመሪያ ጊዜ ሰምተናል ፤ “አስሬ ከመታጠብ አንድ ጊዜ መጠመቅ” የሚል ለተናጋሪውም ሆነ ለሰሚው ጸያፍ የሆነ ነገር ጆሯችን አስተናግዷል ፤ ይህ ከአንዳድ ሰዎች የሰማነው ታሪክ ስለሆነ ለማመመን ትንሽ የምንቸገር ይመስለናል ፤ በንጉሱ ዘመን የነበሩ አንድ አባት የኖሩባቸውን መንግስትታት ኃይለስላሴን ፤ ደርግን ፤ አሁን ያሉበትን ሁኔታ ለህሊናቸው ብለው አነጻጽረው ቢያቀርቡልን የተናገሩትን ለማመን አንቸገርም ነበር ፤ የትኛውም መንግስት ሙሉ ጻድቅ ፤ የትኛውም መንግስት ሙሉ እርኩስ ሊሆን አይችልም ፤ ኢህአዴግ ከደርግ እና ከኃይለስላሴ የሚሻልባቸው ነገሮች እንዳሉ ሆነው ሳለ የሚብስባቸው እና የሚዘቅጥባቸው ነገሮች እንዳሉም መዘንጋት የለብንም ፤ ስናመሰግንም ሆነ ስንነቅፍ መጠንቀቅ አለብን ፤ 

ይች ሀገር ሙስሊም አማኞችን በእንግድነት የተቀበለችው ከ1500 ዓመት በፊት መሆኑ ይታወቃል ፤ አሁን ደግሞ ይህን እውነት እኛም እንሁን እነርሱ ለዚች ሀገር መጻኢ(መጤዎች) ነን ወደ ማለት ተቀይሯል ፤ ይህን ያሉት ግን ሙስሊም ወንድሞቻችን አይደሉም ፤ ይህን ሃሳብ በጥያቄ መልክ ያቀረበው የኢቲቪ ጋዜጠኛ ነው ፤ ታሪክ በቃለ መጠይቅ ይለወጥ የሚመስላቸው ሰዎች ታሪክን ለማደብዘዝ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ፤ አይደለም ያለፈው ታሪክ ይቅርና አሁን እነርሱ እየሰሩት የሚገኙት ስራ በታሪክ መልክ እንደሚቀመጥ የሚያውቁም አይመስሉም ፤ 

በጣም የገረመን ነገር በነገስታት ጊዜ ሙስሊም ማህበረሰቦች በጣም እንደተጨቆኑ አድርጎ ፕሮግራሙ ላይ በመመልከታችን ነው ፤ እኛ ግን እንላለን አሁንም ይች ሀገር የክርስትያኖች ብቻ ማለት አይደለችም ፤ የክርስትያን ደሴት ማለት ሌላው አይኖርባትም ማለትም አይደለም ፤ ለዚህ ጥያቄ ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ በቂ  መልስ የሰጠ ይመስለናል ፤ ባይሆን የዛሬ 50 ዓመት የተፈጠረን ታሪክ ተውትና አሁን የጠየቃችሁትን ጥያቄ ዳር ብታደርሱት መልካም ነው  ፤ በ1923 ዓ.ም ከ80 ዓመት በፊት የተጻፈውን ህገመንግስት መሰረት አድርጎ ለዚያ ነገር ተጠያቂ በሌለበት ሁኔታ ላይ የሌላው የፖለቲካ ግብአት በመሆን  ተጨቁነን ነበር ብሎ መቅረብ መፍትሄ የለው ፤ የዛሬ ጥያቄያችሁ ሳይመለስ  ከ50 ዓመት በኋላ እንደማትደግሙት አሁን ላይ እርግጠኞች ሁኑ ፤ ከተጨቆናችሁም የጨቆናችሁ በጊዜው የነበረው መንግስት እንጂ አሁን ያለችው ቤተክርስትያን አይደለችም ፤ ያለፈውን እንዳለፈ ቆጥራችሁ አሁንስ በዚህ አገዛዝ የእምነት ነጻነታችንን አግኝተናልን? በማለት ራሳችሁን ጠይቁ ፤ 

እኛ ግን በቅርቡ መጽሀፍ ስናገላብጥ ያገኝነው ነገር እናንተ ከምታወሩት ተገላቢጦሽ ሆኖ እግኝተነዋል ፤ ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብሎ ለመቃኝት በወቅቱ የተጻፉ ጽሁፎችን ማገላበጥ ተገቢ ነው ፤ ከእነዚህ በላይም እማኝ ሊሆን የሚችል ነገር አናገኝም ፤ በጊዜው ስላልነበርን በወቅቱ የተጻፉትን ጽሁፎች ማመን ግድ ይለናል ፤ ከ50 ዓመት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ቁርአን ከአረብኛ ወደ አማርኛ የማስተርጎም ስራ ሲሰራ ትልቁን ሚና የተጫወቱት ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ነበሩ ፤ ከየመስጅዱ ያሉትን በእምቱ ላይ የጠለቀ እውቀት ያላቸውን ሰዎች በመሰብሰብ ቁርአኑን ወደ አማርኛ እንዲቀየር ባደረጉት አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋና ከእምነቱ መሪዎች በቁርአን የመጀመሪያ ገጽ ላይ ሰፍሮ በመመልከታችን በጣም ተገርመናል ፤ ይህን ነገር እኛ ተመልክተናል ፤ ይህን ጥያቄ የሚያነሱት ሙስሊም ወንድሞቻችን ግን የሚያውቁት አይመስለንም ፤ ኃይለስላሴ በጊዜው ይህን በመስራታቸው ምን ያህል የሃይማኖች እኩልነት እንደገባቸው የሚሳይ ህያው ማስረጃ ነው ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በወቅቱ ያለውን ሃይማኖታዊ ፤ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ሁኔታዎችን በመመልት “ሃይማኖት የግል ነው ሀገር የጋራ ነው” ያሉ መሪ ቢኖሩ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ነበሩ ፤ አሁን ግን በጊዜው የተፈጠረው ነገር ወደ ኋላ በማለት ሙስሊሞች ሌላ አለም ውስጥ ገብተው ሌላ ነገር እንዲያስቡ መንግስት እያደረጋቸው ይገኛል ፤ እኛ ሳንናገር አንዳንድ ክርስትያኖች “አንዲት ሀገር አንዲት እምነት” ይላሉ በማለት ስማችንን በአደባባይ ያጠፋል ፤ 

አይደለም ከ50 ዓመት በፊት አሁንም አይኑን ያፈጠጠ ችግር በእምነት ተቋማቶቹ መካከል ተጋርጦባቸው እናያለን ፤ ነገር ግን ይህን ችግር መፍታት ያለባቸው በአሁኑ ወቅት ያሉ የሃይማኖት አባቶች መሆናቸው ማወቅ አለብን፤ አሁን ያልተፈታን ችግር ለትውልድ በማቆየት ተወቃሽ የሚያደርግ ስራ መሰራት የለበትም ፤ መንግስት ከማስማማት ይልቅ ሲጣሉ ማስታረቅ ደስ የሚለው ይመስለናል ፤ ክርስትያን ማህበረሰብ ሙስሊሙን መቶ በመቶ አክራሪ ነው የሚል እይታ የለውም ፤ ከስንዴ መካከል እንክርዳድ እንደማይጠፋው ሁሉ የእምነቱን አስተምህሮ ከሚከተሉ  ሙስሊም አማኞች መካከልም የአክራሪነት መንፈስ የተጠናወተው ሰዎች አይታጡም የሚል እምነት አለን ፡፡   
  
በቅዱስ መጽሀፍ ስለ ቅድስናዋ እግዚአብሔር ደጋግሞ የመሰከረላት አገራችን ኢትዮጵያም ቅድስት ክብርት ሐገር ናት ፡፡ ሰይጣን በእባብ አድሮ አዳምንና ሔዋንን እንደተዋጋቸው ሁሉ በልዩ ልዩ ሥጋውያንና መንፈሳውያን የውጭ ጠላቶች አድሮ ኢትዮጵያን ሲዋጋ ኖሯል፡፡  ዛሬም በመዋጋት ላይ ነው ፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ትጥቋን አጥብቃ ከቆመች ሳታርፍ ፤ ከዘረጋች ሳታጥፍ በኖረችበት ዘመን ሁሉ ኢትዮጵያ ሳትደፈር ኖራለች፡፡ በ10ኛው መቶ ዓመት የጉዲት ወረራ ፤ የ16ኛው መቶ ዓመት የግራኝ ወረራ ፤ ከ17ኛው -20ኛው መቶ ዓመት ተደጋግሞ የደረሰው የካቶሊክ ፤ የፕሮቴስታንት ፤ የቱርክና የግብጽ እስላማዊ ወረራ(አክራሪዎች) ተደጋግሞ የከሸፈው ባልተበረዘውና ባልተከለሰው የኢትዮጵያ  ቤተክርስትያን  የእምነት ኃይል ነው፡፡ ይህ ሊታወቅ የሚገባው እውነት ነው ፤ ይችን ቤተክርስትያን ከኢትዮጵያ ጋር እንዴትም መለየት አይቻልም ፤  የአምስት ዓመት የፋሽስት ወረራም ጉዳት ማድረሱ የታወቀ ቢሆንም ከስሩ የተነቀለው ፤ ቁጥቋጦው የተመለመለ ፤ እንደ አንበጣ በዝቶ የመጣው የፋሽስት ሰራዊትም የውሀ ሽታ ሆኖ የቀረው በኢትዮጵያ ቤተክርስትያን የእምነት ኃይልና በልጆቿ ደም ነው፡፡ በጊዜው የቁም ፍትሃት በማድረግ ህዝቡ ለሃገሩ ዘብ ሆኖ እንዲቆም ያደረገችው ይች ቤተክርስቲያን ናት ፤ 

ዛሬ ሁሉ ባለ ሀገር ነኝ በማለት ለአገሪቱ ባለ ውለታ መስሎ ይታይ እንጂ ለ3000 ዓመታት ለኢትዮጵያ ቆማ የኖረች የሰላም ፋና የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ብቻ ናት፡፡ ታሪክን መለስ ብለን ስንመለከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሌላ ሃይማኖት(ካቶሊክ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ፤ ነገስታት ሙስሊም የሆኑበት ጊዜ በታሪክ ስላልተጻፈ) ፤ ከኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ሌላ የሃይማት ክፍል ለመሻት ፤ ለመጠጋት ነገስታቱ ወይም ህዝቡ በሞከሩ ጊዜ ሁሉ የእግዚአብሔር ቁጣና ቅጣት አለ፡፡ ሲመለሱ ይመለሳል ፡፡ ይህም ዝንባሌ ከስጋዊ ወገን እንጂ ከኢትዮጵያ ቤተክርስትያን አበው በኩል የታየበት ጊዜ የለም፡፡

የነብያት ፤ የሐዋርያት እምነት ከተሰበከበት ጊዜ ጀምሮ በሐዋርያት ዘመንም ሆነ በተከታታዩ ዘመን በውጭ የታየውና የተነገረው የመናፍቃን ትምህርትና ግብር በኢትዮጵያ የታየበት ጊዜ የለም፡፡ ይልቁንም በ444 ዓመተ ምህረት በኬሌቄዶን በተደረገው ጉባኤ ምክንያት በውግዘት መለያየት ከተደረገ ወዲህ ኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ከሮምና ከቁስጥንጥንያ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳታደርግ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ኖራለች፡፡ 

በዚህ ዘመን ሁሉ የአበው ስርዓት ሳይፈርስ ፤ ህጉም ውግዘቱም ሳይጣስ ተጠብቆ ኖሯል ፡፡ ልዩ ልዩ የሃይማት ተከታዮች የመንግስት መልዕክተኞች እየሆኑ ጠብ እየቀሰቀሱ ፤ ጦርነት እያስነሱ ቢፈታተኗትም የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን አበው ግን በመስቀልና በሰንደቅ አላማቸው ስር ሆነው ደማቸውን ሲያፈሱ ኖሩ እንጂ የመላላት ግንባር አላሳዩም፡፡ ከዚህም የተነሳ በ1928 ዓ.ም የዘመተው የፋሺስት ሰራዊት ኢትዮጵያን ሲዋጋ ስንቅና ትጥቁን አዘጋጅታ ባርካ ያዘመተችው የልዮን መንበር ስትሆን በዚህም ጦርነት ሁለቱ ታላላቅ አባቶች አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ሚካኤል ሰማዕትነትን ሲቀበሉ ፤ በደብረ ሊባኖስ ፤ በዝቋላ ፤ በዲማ ፤በዋሸራና በሌሎች አብያተ ክርስትያን ብዙ ካህናትና ምዕመናን መስዋዕት ሆነዋል ፡፡ 

አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን ከኢትዮጵያ ጋር ለመለያየት በማሰብ መጤዎች ናችሁ የሚል ነገር እየሰማን እንገኛለን ፤ ታሪክን አለማወቅ ከሆነ ወደ ኋላ ዞር ብሎ ታሪክን ማንበብ ተገቢ ነው ፤ ታሪክን አለማወቅ ከሆነም ከሚያውቁት መጠየቅ መልካም ነው ፤ እናንተ ግራ ተጋብታችሁ ህዝቡን ግራ አታጋቡት ፤ ያልተደረገን ነገር እንደተደረገ በማድረግ አታቅርቡልን ፤ አሁን በክርስትያኑም ሆነ በሙስሊሙ መካከል ችግር እንዳለ እናውቃለን ችግሩን የሚሰሙ መፍትሄ የሚያመጡ አባቶችን በማጣት እንጂ የተፈጠረው ችግር የማይፈታ ሆኖ አይደለም ፤ ብዙ ቦታዎች ላይ የክርስትያኑን ቤተክርስትያን አብረው እንደሰሩ ሁላ ክርስትያኑም መስኪዳቸውን የሰራበት አጋጣሚዎች ነበሩ ፤ 

መንግስት ስራው ሊሆን የሚገባው በአማኞቹ መካከል ክፍተት ለመፍጠር የእምነቱ አስተምህሮ ሳይገባቸው አብያተክርስትያናት ላይ ክብሪት የሚለኮሱትን ሰዎች በማደን ፍርድ ፊት ቢያቀርባቸው ያለው ነገር የተፈጠረው ነገር በረገበ ነበር ፤ ይህን ማድረግ ሲገባው ይህን ያደረጉት ሰዎች የኢህአዴግ አባላት ፤ ሰርገው የገቡ ኢማሞች ፤ ከውጭ በብር የሚረዱ ሰዎች እንደሆኑ ደርሶባቸው ሳለ ችግሩን ለህዝቡ ገልጾ ውጤቱን ግን መግለጽ ሲሳነው ተመልክተናል ፤ አሁንም መፍትሄ ሊመጣ የሚችለው መንግስት ከእምነት ተቋማት ላይ እጁን ሙሉ በሙሉ በማንሳት የጠባቂነት ስራውን ብቻ ይስራ ፤ ለእኩይ አላማ የቆሙትን ሰዎች አጋልጦ ፍርድ ቤት  በማቅረብ ትክክለኛ ቅጣታቸውን ሲያገኙ ለማህበረሰቡ ያሳይ ፤ ሙስሊሙም ሆነ ክርስትያኑ የውስጥ ችግሩን በራሱ አካላት እንዲፈታ ያድርግ ፤ በሁለቱም ወገን ተከሰቱ የተባሉ ችግሮች ህዝብ ፊት በማቅረብ ማህበረሰቡን በማወያየት የመፍትሄ አቅጣጫዎቹን ህዝቡ ራሱ እንዲያመላክት ያድርግ ፤ ያለፉትን መልካም ተሞክሮዎች በመውሰድ የማዳበር ስራ የሃይማኖት አባቶች እንዲሰሩ መንገዱን ያመቻች ፤ ከዘመናት በፊት የተደረጉ የእምነት ነጻነት ገፈፋዎችን ነገ እዳይፈጠሩ የማድረግ ስራ ይስራ ፤ እንደ እስልምና ታሪክ አጥኝው ለዚች ሀገር ኃላፊነት ያለበት በዓለም ላይ ያለው 1.6 ቢሊየን ሙስሊም ማህበረሰብ ሳይሆን እዚው ሀገር ውስጥ የምንገኝ 33 ሚሊየን ኦርቶዶክሳውያን እና 26 ሚሊየን ሙስሊም ማህበረሰብ መሆኑን አንዘንጋ ፤ የውጭ ጣልቃ ግብነትን እስከ አሁን ለሶሪያ ቀውስ ያመጣላት ነገር አለመኖሩን እንመልከት ፤ ሀገሪቱን የሰላም ማድረግ የምንችለው እኛው ነን ፤  ታሪካችን አክብሩልን እኛም ታሪካችሁን እናከብርላችኋለን ፤ ከክርስትስ ልደት በፊት የኦሪት መስዋትን ስታቀርብ የነበረች ቤተክርስትያን መጤ ብሎ ከመናገር እና ከማሰብ ውጪ ምንም የሚያበሳጭ ነገር የለም ፤ ሙስሊሞችን መጤ ናቸው ብለን ያልሆነ ስም አልሰጠናቸውም ፤ ነብዩ መሃመድ ወደ ኢትዮጵያ በላካቸው ጊዜ ለእንግዳ የሚሰጠውን ክብር ሰጥታ የተቀበለች ሃገር ናት ኢትዮጵያ ፤ መንግስት አውቆ ቢያጠፋ ተባባሪው ከመሆን እጃችሁን ሰብስቡ ፤ የሰለሞን ንግስናም ዘመኑ ሲደርስ ተቋጭቷል ፤ ነገ ይህ መንግስት እንዳመጣጡ ይሄዳል ፤ ህዝቦች ግን አብረው ይኖራሉ ፤ አማኞችም ወደፊት ይዘልቃሉ ፤ ዛሬ በሌላው አለም የምናየውም የአንዱ ላንዱ ጥላቻ ለልጆቻችን ለልጆቻችሁ አስቀምጠን ማለፍ የለብንም ፤  ከመንግስት ጎን በመሆን የመንግስት ሁለተኛ ልሳን ሆኖ መናገር ተገቢ አይደለም ፤ 

በስተመጨረሻ የደረሰን ዘገባ እንደሚያስረዳው ይህ ህዝብ ላይ ውዥንብርን የፈጠረን ፊልም ከተመለከቱት 90 በመቶ የሚሆኑት  በጣም የተናደዱ ስሜታቸውን መቆጣጠር ያቃታቸውን ሰዎች 982 ላይ በመደወል ቀኑን ሙሉ ኢቲቪ ላይ የስድብ ውርጅብኝ ሲያወርዱ እንደዋሉ ከቦታው የደረሰን ታማኝ ምንጭ ገልጾልናል  ፤ በቅርብ ጊዜ የህዝቡ አስተያየት በማለት ጥሩ ጥሩውን መርጠው ብቻ ለማቅረብ ደፋ ቀና እያሉም መሆኑን ተነግሮናል ፤ በተጨማሪ በክፍለ ከተማ እና በቀበሌ ደረጃ ህዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ የፌደራል ጉዳዮች መስሪያ ቤት እና የአቶ በረከት ስምኦን ቢሮ አብረው እየሰሩ መሆኑንም ጭምር ለማወቅ ችለናል፡፡
ቸር ሰንብቱ

19 comments:

  1. what is to be said let to be said but the governoment pls do not lie us for more than 20 years. Did not learn still, we are sorry u are not our leader b/c lier

    ReplyDelete
  2. በስተመጨረሻ የደረሰን ዘገባ እንደሚያስረዳው ይህ ህዝብ ላይ ውዥንብርን የፈጠረን ፊልም ከተመለከቱት 90 በመቶ የሚሆኑት በጣም የተናደዱ ስሜታቸውን መቆጣጠር ያቃታቸውን ሰዎች 982 ላይ በመደወል ቀኑን ሙሉ ኢቲቪ ላይ የስድብ ውርጅብኝ ሲያወርዱ እንደዋሉ ከቦታው የደረሰን ታማኝ ምንጭ ገልጾልናል

    ReplyDelete
  3. መንግስት እንዴት አስተዋይ ሰዉ አጣ
    ለጊዜያዊ ጥቅም ሲባል የማይጠፋ እሳት በአገሪቱ ላይ እየለኮሰ ነዉ
    ከ1984 ጀምሮ ህዝቡን በዘርና በኃይማኖት ለማጋጨት እየተሞከረ ነዉ ያለዉ ይህ ደግሞ ለማንም አይጠቅምም ሁላችንንም ወደ ጥፋት ነዉ ይዞ የሚሄደዉ
    ስለዚህ መንግስት ቆም ብሎ ማሰብ አለበት አገር ለማስተዳደር ሆደ ሰፊነት ያስፈልጋል ከህዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች በእልህ ሳይሆን በአባታዊ መልክ መፍትሄ መሻት አለበት
    ለምሳሌ የዋልድባን ጉዳይ ህዝቡን በማዳመጥ የተሻለ መፍትሄ ማግኘት ሲችል በእልህ እንደያዘዉ ለማንም ግልጽ ነዉ
    መንፈሳዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩና ለመነኮሳቱ አክብሮት ቢያሳይ ምንኛ የሰዎችን ልብ ማግኘት በቻለ ነበር

    እባካችሁ ልባችሁን አታጠጥሩት መንግስትም ሊሳሳት እንደሚችል አስቡ
    ዛሬ ላይ ህዝቡ የሚያስበዉ ከሃያ አመት በፊት እንደነበረዉ አይደለም በዲስኩር ብቻ አያምንም በደንብ አብጠርጥሮ ማን እንደሆናችሁ ያዉቃል ጥሩ ከሰራችሁና ፍላጎቱን ካከበራችሁ አብሮ ይቆማል አለበለዚያ ግን የግፍ ጽዋችሁ ሲሞላ እንደ አመጣጣችሁ አዉርዶ ነዉ የሚጥላቸሁ አገር በተንኮል አይመራም ለማንኛዉም እግዚአበሔር ልቦና ይስጣቸሁ!

    ReplyDelete
  4. Mkochi Zare gena EIWUNET tafachihu!! Betekirisitiyanachin Fitum Mete Ayidelechim!! Yihenini Yemilu Wegeenochi Arifewu Yiqemetu!! Eijachewun Keeiminetachini layi Yanisu!!

    ReplyDelete
  5. አንድ አድርገን፦ከጽሁፋችሁ እንደምረዳው ከሆነ እንደ አጀማመራችሁ አላለቀልኝም።ስትጀምሩ መንግስት ውዥንብር አመጣ ነበር እንድምታው።መጨረሻ ላይ ግን ሙስሊሞችን ወቀሳ ጀመራችሁ፡፤መንግስትም እኮ የሚፈልገው ነገር ይህ ነው።በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉ ምሁሮቻችን እያንዳንዳቸው ለ 3 ሰአት ነበር የ ኢቲቪ ጋዘጠኛ ያነጋገራቸው ከዚያ ውስጥ 3 ደቂቃ የማትሞላ አንድን ቃል ለሁለት በመክፈል እና በመሰንጠቅ የተሰራን አሉባልታ ዶክመንታሪ ፊል ብለን እንደ መረጃ ልንጠቅሰው አንችልም።በ እውነት እህ ብለን ብናዳምጠው የቡና ላይ ወሬ ከዚህ ፊልም ተብየው ፍሬከርስኪ ይሻላል።ሙስሊሞች ምንጊዜም ቢሆን ለክርስቲያኖች ጠላት አይደሉም።የሙስሊሞች ታሪካዊ ጠላት አይሁዶች ናቸው።አይሁዶች ደግሞ የ እናንተም ታሪካዊ ጠላት ናቸው እየሱስን በ30 ብር ሸጡ ትሉ የለ?ኢስላም የሚያስተምረን ክርስቲያኖች ለሙስሊሞች ቅርብ እንደሆኑ ነው።በግድ ስለሙ ተብሎ የምንሰማው ሁሉ የመንግስት ልብወለድ እንጅ በሙስሊሞች የተሰራ አይደለም።ሙስሊሞች መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ ስለገባ እና የ አህባሽ አፈንጋጭ እምነት ተዋንያንን ከሊባኖስ ለምን አመጣ የሚል ክስ ለማድበስበስ ከአንድ መንግስት የማይጠበቅ አሳፋሪ የሽፍታ ስራ እና አሉባልታ ሲፈጽም ይታያል።ከዚህ አልፎም ተርፎም ሙስሊሞች ለሃገር አንድነት እና ደህንነት አደጋ ናቸው ብሎ ህብረተሰቡ ላይ ውዥንብር መልቀቅ ጀምሮአል።ጥያቄዎቻችን ግልጽ እና የማያሻሙ ሆነው ሳለ ይህ እንዲሆ የተፈለገበት ዋናው ምክንያት በስመ ሙስሊም የመንግስት ቦዲ ጋርድ ካድሬ መጅሊስ አንፈልግም ስለተባለ ብቻ ነው።ይህ ደግሞ በ እናንተ እምነት ዘንድም ያለውን ሁኔታ ልቅም አድርገን እናውቃለን።በ እምነታችን ጣልቃ የተገባ በሁላችንም ላይ ነው።የጆርጅ ቡሽ እምነት ግን አልተነካም፡፤እንደውም የአማኞች ብዛት በቁጥር ከፍ እንዲል ተደርጎለታል።ወጣም ወረደም እኛ ሰላማዊ መሆናችንን ብቻ ተረዱልን፡፤ይህን ስንል የፍራቻ አይደለም ።የምንፈራው የሰማያት እና የምድርን ፈጣሪ አላህ ብቻ ነው።ሰዎች ግን ባልሆነ ነገር ተረድተውን የመንግስት ብሮፖጋንዳ ሰለባ እንዳይሆኑ ስለምንፈልግ እንጅ ነገ ሲነጋ መንግስት አፍሮ ለፍርድ ይቀርባል።ለ እኛ ሙስሊሞች ዋልድባም ይሁን ዝቋላ እንዲሁም የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት እና ሌሎችም ታሪካዊ እሴቶችን የባህላችን እና የታሪካችን አካል በመሆናቸው እንኮራለን።ግብጾች በፒራሚዳቸው የሚኮሩትን ያክል።እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በግድ ስለሙ ብሎ አንገት የሚቆርጥ አካል ካለ ወያኔ ብቻ ነው።ለምን የስልጣን እድሜውን ለማራዘም።የጅማ ጨፍጫፊዎች የሙስሊም ልብስ ለብሰው አሏዋክቦር እያሉ ሙስሊም አለመሆናቸውን ከቅላጼያቸው ተረድተናል ምክንያቱም ማንኛምውም ዉሸት ከጎኑ ትልቅ እውነት እንደማስረጃነት ይዞ ስለሚሄድ ነው።ስለዚህ የዚህ መንግስት በደል ይቆም ዘንድ እንተባበር።ዶክመንታሪ የተባለው አሉባልታ ፊልም መሳይ ነገር እኛ የመንግስትን ውሸት የምናይበት መስታወት ሊሆን ይግገባል እንጅ እርስ በ እርሳችን መተቻቸት የለብንም ባይ ነኝ።የገበያ ግርግ ለቀጣፊ በጀው እንዳይሆን........እየተስተዋለ ቢሆን ይመረጣል

    ReplyDelete
    Replies
    1. Very Good Opinion and very true.

      Delete
    2. i can appreciate your commnet b/c u said the truth.keep on bro/sis!

      Delete
    3. dear thank you for your deep writing...i really appreciate that. we Ethiopians are one whether Christian,Muslim or other local religion follower or even oromo or amhara.these strangers should not be allowed to divide us. we have to be able to say NO.enough is enough...any way i thank you all. this is your muslim ethiopian brother. ethiopia lezelalem tinur

      Delete
  6. 1.6 bilon yalute bealem yalu hulu Ethiopia muslim bale maderegachewe yeteyekalu newe yemilute yehe hasabe (2003 bazegagute exibtion laye sinagerute semichalewe ) Ethiopia laye LARGE MUSIUM lemegenbate ye ( HAGIYA SOFIA cHURCH) bemasetawese

    ReplyDelete
  7. God bless you for the splendid summary.

    ReplyDelete
  8. The number of Orthodox followers is 43 million not 33 million should be corrected.

    መንግስት ስራው ሊሆን የሚገባው በአማኞቹ መካከል ክፍተት ለመፍጠር የእምነቱ አስተምህሮ ሳይገባቸው አብያተክርስትያናት ላይ ክብሪት የሚለኮሱትን ሰዎች በማደን ፍርድ ፊት ቢያቀርባቸው ያለው ነገር የተፈጠረው ነገር በረገበ ነበር ፤ ይህን ማድረግ ሲገባው ይህን ያደረጉት ሰዎች የኢህአዴግ አባላት ፤ ሰርገው የገቡ ኢማሞች ፤ ከውጭ በብር የሚረዱ ሰዎች እንደሆኑ ደርሶባቸው ሳለ ችግሩን ለህዝቡ ገልጾ ውጤቱን ግን መግለጽ ሲሳነው ተመልክተናል ፤ አሁንም መፍትሄ ሊመጣ የሚችለው መንግስት ከእምነት ተቋማት ላይ እጁን ሙሉ በሙሉ በማንሳት የጠባቂነት ስራውን ብቻ ይስራ ፤ ለእኩይ አላማ የቆሙትን ሰዎች አጋልጦ ፍርድ ቤት በማቅረብ ትክክለኛ ቅጣታቸውን ሲያገኙ ለማህበረሰቡ ያሳይ ፤ ሙስሊሙም ሆነ ክርስትያኑ የውስጥ ችግሩን በራሱ አካላት እንዲፈታ ያድርግ

    ReplyDelete
  9. enante mechem ende aheyaum hula aytemacehum. ahun ye etv program min cheger alew? asebari selehonachu gena legena semachen yeteral belachu new aydel. maferiyawoche.

    ReplyDelete
  10. perogramu saytay yetekawemachute setay yetesal neger alachu teblo aytbekim. egziabhere yiker yebalchu. selecelemebacu yimeseegal hulun yemetetekrut.

    ReplyDelete
  11. We are fed up of propogandas against Ethiopian heritages incluuding Tewahdo. No one can deny the role of EOTC in Ethiopian history. Totally impossible to rewrite history retroactively.

    ReplyDelete
  12. እውነት ነው እኛ ኢትዮጵያዊያን የሙስሊምና የክስርስትና እምነት ተከታዮች እዚህ ላይ ብልጥ መሆን አለብን ምክንያቱም እንደ መንግስት አዝማሚያ ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን ለማፋጀት ነው ስለዚህ አስተውለን እንራመድ እርስ በርስ ተከባብረን እንደኖርን አሁንም ይህ ነገር እንዲቀጥል ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጐቱ ካለበለዛ ሐገራችን ድምጥማጧ ነው የሚጠፋው እንደሰለጠነ እናስብ ሁሉም የራሱን ኃይማኖት የመከተል መብት አለው ግን በሰው ኃይማኖት ውስጥ ግን ጥልቅ ማለት አይበጅም ሕዝቡ ደግሞ ይህንን ለዘመናት ጠብቆ፣ ተቻችሎ ኖራል አሁን ምን መጣ እና ነው ይህ መንግስት እንዲህ የሚያራግበው ተጠንቀቁ ሰዎች ሐገራችንን ከውድቀት እናድን ምናልባት የእኛን መጠንከር ማለትም የኢትዮጵያዊያንን መጠንከር የማይፈልጉ ኃይሎች የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘር እምቢ አልከፋፈልም ሲል ደግሞ በኃይማኖት ሊከፋፍሉት እና ይችን ሐገር ብትንትኗን ለማውጣት የቆመ ኃይል አንድ ኃይል ሳይኖር አይቀርም እናስተውል ጐበዝ፡፡ እምቢኝ እንበል የኃይማኖት ነገር ከባድ ነው እንደቀድሞዋችን እንኑር፡፡

    ReplyDelete
  13. የዚህን ጽሁፍ አቅራቢ በርግጥ አደንቃለሁ፡፡ጊዜ ወስዶ እንዲህ አይነት ጽሁፍ ማዘጋጀት ከባድ መሆኑን እረዳለሁ፡፡ ሆኖም ቅሬታ አዘል አስተያየቴን የምሰጠው ክርስትና አለም አቀፍ ሃይማኖት እንጂ ሀገራዊ አይደለም፡፡ ሆኖም በተለያዩ መልኩ እምነቱ የሚያስገድድ እስኪመስል ለዘውድ አገዛዙ ጠበቃ ሆኖ መቅረብ ስህተት ከመሆኑም በላይ አስፈላጊ አይደለም፡፡ እንደምሳሌም “ከ50 ዓመት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ቁርአን ከአረብኛ ወደ አማርኛ የማስተርጎም ስራ ሲሰራ ትልቁን ሚና የተጫወቱት ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ነበሩ ፤ ከየመስጅዱ ያሉትን በእምቱ ላይ የጠለቀ እውቀት ያላቸውን ሰዎች በመሰብሰብ ቁርአኑን ወደ አማርኛ እንዲቀየር ባደረጉት አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋና ከእምነቱ መሪዎች በቁርአን የመጀመሪያ ገጽ ላይ ሰፍሮ በመመልከታችን በጣም ተገርመናል” የሚለው ሀሳብ በእውነት ነው የምለው አስፈላጊ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም አጼው ያንን ያስፈፀሙት በግዳጅና የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ከተቀሩት የአለም ሙስሊሞች ለመነጠል አንድ የሚያረጋቸውን መገለጫዎች በሙሉ(መጠሪያ ስምን፤አለባበስን ወዘተን…ጨምሮ) ለማጥፋት የነበረው ዕቅዳቸው አካል ነበር፡፡ተርጓሚዎቹም የተከበሩ ሰዎች ቢሆኑም በወቅቱ በነበሩ አማኞች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸው እንደነበር ህያው ታሪክ ነው፡፡ ለአጼው ስርዓት በዚህ መልኩ መቆርቆር ትርፋማ አያድርግም፡፡የኢትዮጵያንም ህዝብ አብዮት ምክንያት አልባ አድርጎ የማቅረብ ያህል ጨካኝ ይሆናል፡፡ በተረፈ የፅሁፉን አጠቃላይ ስሜት ወድጀዋለሁ

    ReplyDelete
  14. "....ታሪካችን አክብሩልን እኛም ታሪካችሁን እናከብርላችኋለን...."

    "...ይህ መንግስት እንዳመጣጡ ይሄዳል ፤ ህዝቦች ግን አብረው ይኖራሉ ፤ አማኞችም ወደፊት ይዘልቃሉ..."

    ReplyDelete