Sunday, October 30, 2011

ቅ/ሲኖዶስ አባ ሰረቀ ላይ ከሥልጣን ማውረዱ የፓትርያርኩ ሐውልት ላይ እንደተወሰነው ውሳኔ እንዳይሆን ሥጋት አለ


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 20/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 31/2011PDF)፦ አወዛጋቢው የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃን ወል ሳሙኤል ቅዳሜ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ቅ/ሲኖዶስ እንደወሰነባቸው ከታወቀ ጀምሮ ምዕመናን ደስታቸውን በተለያየ መንገድ በመግለጽ ላይ ሲሆኑ ቅ/ሲኖዶስ ከረዥም እልፍ አስጨራሽ ስብሰባ በኋላ እዚህ መደምደሚያ ላይ በመድረሱ ምሥጋናቸውን እየቀረቡ ነው። 


የቅዱስ ሲኖዶሱን ያለፉ ውሳኔዎች አፈጻጸም በጥልቀት የሚመለከቱ አንዳንድ ደጀ ሰላማውያን ደግሞ “ይህ ደስታችን ዘላቂ የሚሆነው የቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔ እንዳለፈው ዓመት የፓትርያርኩ ሐውልት ውሳኔ የወረቀት ላይ ነብር፣ ተግባር ላይ የማይውል፣ አለመሆኑን ስናረጋግጥ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። አንድ የፌስቡክ ተጠቃሚ በበኩላቸው ሌላ አወዛጋቢ ደግሞ አስቀምጠውእስኪያስጨንቁን በዚህ ዜና እንደሰትንእኔምለው የቤተክርስቲያን አገልግሎት ሐሰትንናእኩዮችን በመቃወም ተጠምዶ ሌሎች ተግባራት እንዳይከወኑ ሲዘገይ አይታያችሁም።” ሲሉ ጠይቀዋል።


 ከሥልጣናቸው መነሣትችም ብቻ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ በሚከሰሱበት ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ውጪ ነው  የሚባለውን እምነታቸውን የሚመረምር አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የሚገኙበት ኮሚቴም ተሰይሟል። የኮሚቴው አባላትም ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ  ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ እና ብፁዕ አቡነ ያሬድ መሆናቸውን፣ እንዲሁም አባ ሰረቀ ከሓላፊነታቸው እንዳይነሡ በጥብዓት ሲከራከሩላቸው የቆዩት ቅዱስ ፓትርያርኩ ይዘውት የነበረውን አቋም እንዲቀይሩ ወጣቱ በቅርቡ ያሳየውን ተቃውሞ የተረዳው መንግሥት ተጽዕኖ ሳያደርግ አልቀረም መባሉን መዘገባችን ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment