Tuesday, October 18, 2011

አውደምህረትን በገንዘብ


  • እነ በጋሻው ከመንግስት መስሪያ ቤት የፍቃድ ደብዳቤ ገዙ 
  • በጋሻው አንድ ነገር እንንገርህ በሚሊንየም አዳራሽ ለተጎዱ አብያተክርስቲያናት ብለህ እንደሰበሰብከው ግድቡ ጠያቂ የሌለው አይምሰልህ መንግስት አፍንጫህን ይዞ እንደሚቀበልህ አትዘንጋው” 
  • የስትራቴጂ ለውጥ በማድረግ ‹‹ታላቁ የህዳሴ ግድብ›› ብለው ብቅ ብለዋል
  • ‹‹ወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያወጣ ጀመር፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ›› የማርቆስ ወንጌል 11፤15 


እነበጋሻው ደሳለኝ ህገወጥ ሰባኪ ተብለው ከማህበረሰቡ እየደረሰባቸው ያለውን ተቃዎሞ ስላልቻሉት እንዲሁም የምስራቅ ሀረርጌ ሀገረ ስብከት ህገወጥ ሰባኪያንን አስመልከቶ ያስተላለፈውን መመሪያ ማለፍ ስላቃታቸው የባቢሌ ወረዳ ቤተ ከህነትን ወደጎን በመተው ማህበረ እስጢፋኖስ ቁጠር 2 የተባለው የተሃድሶ ክንፍ ከነበጋሻው ጋር በመነጋገር ጉባኤ አዘጋጅተዋል:፡


ጉባኤውንም የወረዳው ቤተክህነት እንደማይቀበለው ለሀገረ ስብከቱ አሳወቀ ሀገረ ስብከቱም ለኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር ጽ/ቤት በደብዳቤ አሳወቀ፡፡ የዞኑ ጊዜአዊ ኃላፊ አቶ አሰግድ ግን በጋሻውና ግብር አበሮቹ ጳጳሱም ስራስኪያጁም ተነስተዋል ካሁን በኋላ የሚመጡት የኛ ሰዎች ናቸው፡፡በማለት የነገሩትን ፈጠራ በማመን፤ የተቀመጠበትን የህዝብ አደራ ወደ ጎን በመተውና ሥልጣኑን እንደይሁዳ በገንዘብ በመሸጥ፤

ግርማ ደረሴ በተባለ ግለሰብ ደላላነት ከዲ/ን በጋሻውና ከጥንት ጀምሮ የተሐድሶ ነገረ ፈጅ ሆኖ ከሚያገለግለው ከአቶ ሽፈታው እጅ 10፣000 (አስር ሺ ብር) ተቀብሎ ሕጉ በማይፈቅድለትና በማያገባው አካሔድ ለባቢሌ ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን ጉባኤው እንዲካሔድ ተፈቅዶል የሚል ደብዳቤ አበረረ፡፡ ልብ አድርጉ እንግዲህ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖትና መንግስት ተለያይተዋል የሚል ሕገ መንግስት ባለበት አገር አንድ የዞን መስተዳድር ጽ/ቤት ከሜዳ ተነስቶ ጉባዔ ፈቃጅና መምህር መዳቢ ሆኖ ሲያርፍ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በጋሻው ዳሳለኝ አቡነ ጳውሎስን አስደውላለሁ እያለም ሲሯሯጥ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ግን ይህ ዜና በማቲዎስ አጥምዛ እስከ ተጠናከረበት ድረስ እንኳንስ ቅዱስነታቸው ማንም እንዳልደወለ ታውቋል፡፡ የምስራቅ ሀረርጌ ሀገረ ስብከትም የዞኑን ሓላፊ ለኦሮሚያ ክልል በሥራችን ጣልቃ ገባብን ብሎ እንደሚያመለክት ታውቋል፡፡ ግብረ በላዎቹ በጋሻው ፣ ትዝታው፣ ተረፈ ፣ምርትነሽ ፣በብዙ ሺ ብሮች ተገዝተው እንዳልመጡ አሁን ደግሞ ጉባኤ መግዛት ጀምረዋል፡፡ የሚገርመው ግን ምንም ቢያረጉ የህዝቡ ተቃዎሞ መጨመሩ ነው፡፡ ባለፈው ግሸን ላይ እንኳን የገጠር ገበሬው ሳይቀር አርማጌዶን የሚለው ሲዲ እየገዛና መዋጮ እየሰበሰበ ሲከፍላቸው በነበረው ገንዘብ እያዘነና እየተቆጨ ነበር ሲሄድ የነበረው ፡፡ አሁን ደግሞ ሲፈልጉ ለመንግስት እቅድ አሳቢ በመምሰል ለህዳሴ ግድብ የሚል የመዝረፊያ እቅድ እንደቀየሱ ነው የሚሰማው፡፡ በገዳማት አጭበረበሩ ህዝቡ ነቃባቸው አሁን ደግሞ ሌላ ዘየዱ፤ የህዳሴው ግድብ የሚል ለምድ ለብሰው ብቅ አሉ፡፡ 

አንዳንድ ምዕመናን በጉዳዩ አዝነውና ተበሳጭተው “በጋሻው አንድ ነገር እንንገርህ በሚሊንየም አዳራሽ ለተጎዱ አብያተክርስቲያናት ብለህ  እንደሰበሰብከው ግድቡ ጠያቂ የሌለው አይምሰልህ መንግስት አፍንጫህን ይዞ እንደሚቀበልህ አትዘንጋወ፡፡” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አንዳንድ ምንጮች እንደሚያሳዩት በጋሻው ማኅበረ እስጢፋኖስ የተባለ የተሃድሶ ማህበርን ይዞና የመንግስት መስሪያ ቤትን በገንዘብ ገዝቶ የቤተክርስቲያኑን አለቃ እስከማባረር ደርሷል ፡፡ እንደውም የደብሩ አገልጋይ ካህናት መንግስት ስለሌለ ታቦቱ ለመጠበቅ እንፈራላን ፤ የሀገረ ስብከቱን መመሪያ እናስከብራልን ግን ካቅማችን በላይ ስለሆነ ሀገረ ስብከቱ ይድረስልን፡፡ በማለት ተፈራርመው ለሀገረ ስብከቱ እንዳስገቡ ነው የሚነገረው፡፡ ሀገረ ስብከቱም የዞኑ ጽ/ቤት በገንዘብ ሸጠው እንጂ ህገወጥ ሰባኪዎችን እንዳያስታግስለት በህግ አምላክ የሚል ደብዳቤ ለዞኑ መስተዳደር ጽ/ቤት ጽፎ ነበር፡፡ እዚህ ላይ ገብርኄር ላማለት የሚፈልገው መንግስት እንደዚህ በትንንሽ ገንዘብ የህዝብን አዳራ የሚሸጡ ሰዎችን ማስወገድ አለበት፡፡ እነዚህን ይዞ ሀገርና የሀገር እድገት፣ የትራንስፎርሜሽን እቅድ ቢሉት መሳካት አይችልም፡፡ ጥቂት ስግብግቦች ህዝቡ ባለፈው ስርአት ጥሎት የመጣውን በገንዘብ ጉዳይዩን ማስፈፀም ሊያስታውሱት አይገባም እንላለን ፡፡

ቤተክህነቱም እነዚህ አካላት ወንጀል ለመስራት ወደየት እየሄዱ እንደሆነ በመራዳት ከመቸውም ጊዜ በላይ ይህንን ሀሳብ በማጠንጠን ከፋተኛ ድርሻ ያላቸው ላይ እርምጃ በመውሰድና በቤተክርስቲያን አሰራር ላይ ጣልቃ በመግባት ወንጀል የሚጽሙትን የመንግስት አካላት በመቃዎም ለበላይ አካል ማሳዎቅ ይገባል፡፡
      
ከዚህ ጋር ተያይዞ ነገ የሚጀመረው የሰበካ መ/ጠቅላላ ስብሰባና ጥቅምት 12 የሚጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስም ጉባኤ በጉዳዩ ላይ መወያየት ብቻ ሳይሆን እነዚህን ገንዘብ እየሰበሰቡ ኑፋቄ የሚዘሩትን በመለየት ትናት የወሰናቸውን በማጽናት ፣እንዲሁም መወገዝ ያለባቸውን ማውገዝ አለበት እንላለን፡፡

የመጨረሻው የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች የሰላምና ምክክር ጽ/ቤት አሁን እየሳራ ያለው ጅምር መልካምና የሚያስመሰግን በመሆኑ በነዚህ በየአካባቢው እየዞሩ በሚበጠብጡት ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ እንደሚቻልም ሊያረጋግጥን ይገባል እንላለን፡፡
Posted on  by ገብር ኄር       
በሸዊት ገብረ ኪዳን(shewitgbrkdn95@gmail.com


‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን››

           

No comments:

Post a Comment