Thursday, October 20, 2011

ተኩላዎቹ የአመፅ ጥሪ አካሔዱ


በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት ከሆኑት ወዳጆቼ ያገኘሁት መረጃ ቀንደኞቹ የተሐድሶ አቀንቃኞች በጋሻው አሰግድ እና ግብርአበሮቹ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መጀመሩን አስመልክቶ በሚደረገው የብጹአን አባቶች የጸሎት ስነስርዐት ላይ አመፅ ሊወጡ ነው፡፡ የኮሌጁ መደበኛ ተማሪዎች የደንብ ልብስ የሆነውን ጥቁር ቀሚስ በመልበስ እንደሚደረግም ሲገለጽ የአመፅ ሰልፉን አሰግድ እያስተባበረና “ለሚመስሏችሁ አገልጋዮች ብቻ ተናገሩ” በማለት ለአንዳንድ አገልጋዮች መናገሩም ተሰምቷል፡፡ ነገ 10፡00 ፊደል ካፌ እንገናኝ የሚለው ጥሪ የካፌው ባለቤት የሆነውን አቶ ኤፍሬም ኤርሚያስ በአዲስ አበባ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ምዕመናን ዓይን በጥርጣሬ እንዲታይ አድርጎታል፡፡ ጥቅምት 12 ቀን 2004 ዓ.ም. ቀን 10፡00 የተጠራው ስብሰባ እውን ከሆነ ካፌው አካባቢ አጓጉል ነገር እንደሚፈጠር ወጣቶቹ እየዛቱ ሲሆን በተያያዘ ዜና የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ህብረት በተመሳሳይ ሁኔታ የተሐድሶን እንቅስቃሴ አስመልቶ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲያሳልፍ በሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠይቁ ይጠበቃል፡፡ የነበጋሻው፣ አሰግድ እና ግብረ አበሮቹ በአመፅ ሰልፉ የሚያነሱት ሐሳብ መናፍቅ እየተባልን አናስተምርም፣ ስማችን ጠፍቷል ቅዱስ ሲኖዶስ ስማችንን ያድስልን የሚል እንደሆነም ታውቋል፡፡ ቤተክርስቲያንን የማደስ ስውር ተልዕኮአቸው ያልተሳካላቸው በጋሻው እና አሰግድ ስማቸውን ለማደስ መነሳታቸው ምን ያህል በተሐድሶ ሱሰኞች መሆናቸውን የሚያሳይ መሆኑን አንዳንድ ጥሪው የደረሳቸው የኮሌጁ ደቀመዛሙርት ገልጸዋል፡፡

Posted on  by ገብር ኄር
በማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com)

1 comment: