Monday, October 31, 2011

“የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት” በሦስቱ አህጉረ ስብከት ሥር እንዲሆን አልያም እንዲዘጋ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ



 (ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 20/2004 ዓ.ም)፦
  • የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን በሰሜን አሜሪካ ያሏትን ሦስት አህጉረ ስብከት “ከመንበረ ፓትርያኩ ጋራ ለማገናኘት” በሚል ተጠሪነቱ ለመንበረ ፓትርያኩ የውጭ ጉዳይ መምሪያ ሆኖ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና የተቋቋመው “የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት” አገልግሎቱና ጥቅሙ በሚገባ ተመርምሮ በሦስቱ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ሥር እንደ አንድ የመረጃ ክፍል ሆኖ እንዲዋቀር፣ ይህ ካልሆነ ግን እንዲዘጋ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡

የመድፈር ሙከራ በቤተክርስትያን

ቶሮንቶ ካናዳ በሚገኝው የኢትዮጵያውያኑ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ውስጥ አንዲት ሴት ላይ የአስገድዶ መድፈር ሙከራ መቃጣቱን ከስፍራው የተሰራጨው ዜና ያስረዳል፡፡ በደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ውስጥ የበጎ ፍቃድ አገልጋይ የሆነው የ32 ዓመቱ አሸናፊ ካህሳይ በአንዲት ሴት አስገድዶ መድፈር ክስ ቀርቦበት የቶሮንቶ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ አሸናፊ ካህሳይ በኮሌጅ ፓርክ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ በዋስትና የተለቀቀ ሲሆን ፖሊስ ግን በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ መስጠት የሚችል ማንኛውም ሰው እንዲተባበረው ጠይቋል፡፡

ቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ዛሬም ይቀጥላል፤ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ በቋሚነት በሚመደብ ሊቀ ጳጳስ ይመራል

“እስከ መቼ ነው እርስዎ ሕግ እየጣሱ የሚቀጥሉት? የሚጠቅሱት ሕገ ቤተ ክርስቲያን ለእርስዎ አይሠራም ወይ? መጣራት የሚገባው ጉዳይ እንዳለ ሲኖዶሱ ካመነበት መጣራት በሚገባቸው በርካታ ጉዳዮች ላይ ልንነጋገር ይገባል 
 ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል  ለፓትርያርኩ 
  • ሊቀ ጳጳሱ ተደራቢ ሥራ ሳይኖራቸው የማደራጃ መምሪያው መዋቅራዊ አሠራር በሰው ኀይል እና በፋይናንሳዊ አቅሙ ለማጠናከር የሚያስችል መመሪያ የማስቀረጽ፤ በ1986 ዓ.ም የወጣውየማደራጃ መምሪያው ውስጠ ደንብ እና በ1994 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ ተሻሽሎ የጸደቀው የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ ከሚሻሻለው ቃለ ዐዋዲ፣ ሌሎች ሕጎች እና ከጊዜው ጋራ በማጣጣምእንዲሻሻል በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተላለፈውን ውሳኔ የማስፈጸም፤ በዚህም ሕፃናትን፣ ወጣቶችንና ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ አስተባብሮ የመምራትሓላፊነት ይጠብቃቸዋል።
  • አባ ሰረቀ ከዋና ሓላፊነታቸው ተነስተው ሃይማኖታዊ ሕጸጻቸው እንዲመረመር የተላለፈው ውሳኔ የቤተ ክህነቱን ቢሮክራሲ (የሊቃውንት ጉባኤ መምሪያን ጭምር)ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ደጋፊዎች ለማጽዳት በቀጣይነት በመካሄድ ላይ ለሚገኘው ተጋድሎ አብነታዊ ርምጃ ተደርጎ ተወስዷል፤

Sunday, October 30, 2011

ወቅታዊ ቃለምልልስ

  • ይህ ቡድን አርማጌዶን ቁጥር 1 ከወጣ በኋላ መደናገጥ ተፈጠረበት ፤ ይህ መደናገጥ ቡድኑ ተሰብስቦ አንድ ቦታ እንዲቆም አድርጎታል ቀጣዩ ነገር ምንድነው በማለት አብያተ ክርስትያናቱ ሁሉ በራቸውን ዘጉ ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ህጋዊ ሰውነት ለማላበስ ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ መጠጋት ነበረባቸው ፡፡ እናም ወደ ሐውልት ስራ ሄዱ…. ብቻ ሁኔታው ውስብስብ ሆነ
  • ችግሩ ካላቆመ አርማጌዶን ይቀጥላል



መልካም ምንባብ  READ IN PDF click her
Click Read more by image format

ቅ/ሲኖዶስ አባ ሰረቀ ላይ ከሥልጣን ማውረዱ የፓትርያርኩ ሐውልት ላይ እንደተወሰነው ውሳኔ እንዳይሆን ሥጋት አለ


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 20/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 31/2011PDF)፦ አወዛጋቢው የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃን ወል ሳሙኤል ቅዳሜ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ቅ/ሲኖዶስ እንደወሰነባቸው ከታወቀ ጀምሮ ምዕመናን ደስታቸውን በተለያየ መንገድ በመግለጽ ላይ ሲሆኑ ቅ/ሲኖዶስ ከረዥም እልፍ አስጨራሽ ስብሰባ በኋላ እዚህ መደምደሚያ ላይ በመድረሱ ምሥጋናቸውን እየቀረቡ ነው። 

ትልቁ መርዛማ እሾህ ተነቀለ

Adios Abba Sereke!!!!!!!!!!!!!!
ቅ/ሲኖዶስ አባ ሰረቀን ከሥልጣናቸው አወረደ
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 18/2004 ዓ.ም፤ )፦ አወዛጋቢው የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃን ወደል ሳሙኤል ዛሬ ቅዳሜ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ቅ/ሲኖዶስ ወሰነባቸው። ከሥልጣናቸው መነሣትችም ብቻ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ በሚከሰሱበት ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ውጪ ነው  የሚባለውን እምነታቸውን የሚመረምር አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የሚገኙበት ኮሚቴም ተሰይሟል። የኮሚቴው አባላትም ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ  ናትናኤል፣
ብፁዕ አቡነሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ እና ብፁዕ አቡነ ያሬድ ናቸው።

Saturday, October 29, 2011

Before One Month.......

   መነኩሴው በተክሊል ጋብቻ መፈፀማቸው
  • ምንኩስናው ቢፈርስ እንኳን በተክሊል ማግባት አይቻልም.. - ቤተክርስቲያን
  • ከሳምንት በፊት ቆቤን ለቸገረው ሰጥቻለሁ.. - ሙሽራው
  • ምንኩስናውን አፍርሻለሁ ስላለኝ ጋብቻውን ተቀብያለሁ.. - ሙሽሪት
  • ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቁት ..መነኩሴ.. የምንኩስና ሥርዓቱን ጠብቀው ምንኩስናቸውን ሳያፈርሱ በሙሽሪቷ የትውልድ አገር በሀዲያ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ቤተ መቅደስ በይፋ በተክሊል ሥርዓተ ጋብቻ መፈፀማቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

ቤተክርስቲያን የጋብቻ እና የምንኩስና ሥርዓት እንዳላት የሚናገሩት የጉራጌ ከንባታና ሐዲያ ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ ቀለምጢዎስ፤ አንድ መነኩሴ ሥርዓቱን ፈሞ ምንኩስናውን ሲወስድ ከዓለማዊ ነገር ተገልሎ ቆቡን እንደሚስት አግብቶ መኖር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ቆቡን ሳያወልቅ ወይም ምንኩስናውን ሳያፈርስ ምንም ዓይነት ዓለማዊ ሥርዓት መፈፀም እንደማይችልም አስገንዝበዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ለ4ኛ ተከታታይ ቀን በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ እና ማ/ቅዱሳን መካከል ባሉት ችግሮች ዙሪያ እየተወያየ ነው


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 18/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 29/2011/ PDF)፦

  • ምልአተ ጉባኤው የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት በተሰጠው መመሪያ መሠረት ባለመቅረቡ አልተቀበለውም፤ ኮሚቴው የአባ ሰረቀን በማስረጃ ያልተደገፉ 20 ክሶች በማጉላት የማኅበሩን 10 ተጨባጭ አቤቱታዎች በማኮሰስ አቅርቧል
  • የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ማ/መምሪያው ቋሚ ሊቀ ጳጳስ እንዲመደብለት፣ አባ ሰረቀ ከዋና ሓላፊነታቸው እንዲነሡ፣ የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ አባ ሰረቀ ካቀረቧቸው ክሶች አንጻር የማ/መምሪያውን ሥልጣን በሚያጠናክር አኳኋን እንዲሻሻል በመፍትሔ ሐሳብ አቅርቧል
  • ምልአተ ጉባኤው “አጣሪ ኮሚቴው በሁለቱም በኩል የቀረቡ ማስረጃዎችን ይዞ የማጣራቱን ውጤት እንዲያቀርብልን እንጂ‹እገሌ እንዲህ አለ፤ እገሌ ደግሞ እንዲህ አለ› የሚል ሪፖርት እንዲያቀርብ አልጠበቅንም” በማለት ሪፖርቱን ተችቷል፤ የሪፖርቱን ተቀባይነት ማጣት በመመልከት ጉዳዩ በቋሚ ሲኖዶስ ታይቶ ውሳኔ እንዲሰጠው ፓትርያርኩ ያቀረቡትን ሐሳብ በመቃወምም የማ/መምሪያውን ሦስት ተወካዮች እና የማኅበረ ቅዱሳንን ሁለት ተወካዮች በመጥራት ጉዳያቸውን እንዲያስረዱ አድርጓል

Friday, October 28, 2011

አፅም የማይበሰብስበት


(አንድ አድርገን ጥቅምት 17/2004ዓ.ም) የሰው ልጅ ቅሪተ አካል  ዓመታት ሳይፈርስና አፈር ሆኖ ሳይደቅ ሞቶም  የአጥንቱ ቅሪት ሙሉ አፅሙም የማይፈርስበት ስፍራ አለ ቢባሉ ምን ይላሉ? በምናብ ተከተሉን.....
ወደ አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን የቦታው መጠሪያ መልከ ፀዴቅ ገዳም ይባላል፡፡ በሚዳ ወረሞ ወረዳ ከመራኛ ከተማ አቅራቢያተዳፋት ከተከበበ ልዩ ስፍራ የመሸገ ነው አዲ አበባ 230 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ገዳሙ ያረፈበት መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ እጅግ የሚማርክ ነው ፀጥታው ዙሪያው የተወረወሩት ቁልቁለቶች የየራሳቸው መልክ ያስደንቃል፡፡ ጉልበት የሚያንደረድረው የገዳሙ መውረጃ ደረጃ ከግማሽ በላይ በጥሩ ሁኔታ የተገነባ ነው፡፡

ለሰባኪዎቻችን

To continue Click Read more

Thursday, October 27, 2011

ተሀድሶን የተቃወሙት ወጣቶች ከእስር ተፈቱ

‹‹ተቻችሎ እና ተከባብሮየኖረውን ሕዝብ ወደ ብጥብጥ በመምራት›› እና “ሰው በመደብደብ” የሚሉ ሁለት የወንጀል ክሦች የቀረቡባቸው “የአዲስ አበባ የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶች ማኅበር” ስምንት አባላት ጥቅምት 12 ቀን 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ከስምንቱ መካከል ስድስቱ እያንዳንዳቸው በብር 600 ዋስ እንዲወጡ ሲወሰንላቸው፣ የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ ለጥቅምት 16 ቀን 2004 ዓ.ም እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር - 

ዛሬ ጥቅምት 17 /2004 ዓ.ም የወጣ ፍትህ ጋዜጣ ጠቅላላ ከታሰሩት 10 ወጣቶች ውስጥ ስምንቱን ትላንት ከ5 ቀን የእስር ቆይታ በኋላ በዋስ መፈታታቸውን እና ሁለቱ እስረኞች ዛሬ እንደሚፈቱ አስነብቧል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ፖሊስ አስተባባሪ ነው ያለውን ወጣት እየፈለገው መሆኑን ጨምሮ ገልጧል

የመናፍቃንን መዝሙር መስማት..........

ዲያቆን ህብረት የሺጥላ 
(ከሕይወተ ወራዙት መፅሀፍ ላይ የተወሰደ)

  • ዘፈን መስማት ኃጢአት ነው የመናፍቃንን «መዝሙር›› መስማት ግን ዓመፅና ክህደት ነው፡፡ ኃጢአት የምግባር ሕፀፅ ሲሆን ዓመፅ ደግሞ የሃይማኖት ሕፀፅ ነው፡፡ የቱ የሚከፋ ይመስልሃል?  
  •  «የመናፍቃንን መጽሐፍ ከመመልከት ተከልከል››ማር ይስሐቅ  :: 
  • «ዑቅ ከመኢትቅረብ ኀቤሃ - ወደ እርሷ ከመቅረብና ገልጾ ከማየት እንኳን ተጠንቀቅ›› ይላል፡፡ ምክንያቱንም ሲያስረዳ መንፈሰ ጽርፈት / የስድብ መንፈስ/ እንዳያድርብህ ነው ይላል፡፡  በእርግጥ ይህ ቃል የተነገረው የመናፍቃንን መጽሐፍ ስለማንበብ ነው፡፡ ማር ይሥሐቅ ከላይ እንዳስጠነቀቀን የመናፍቃንን መጽሐፍ ማንበብ ክፉ ነገር ነው፡፡ መጽሐፋቸውን ከማንበብ በላይ በዘፈን ዜማ የወዛ «መዝሙራቸውን መስማት›› እጅግ አይከፋምን? ስለዚህ እንደ መጽሐፋቸው ሁሉ «መዝሙራቸውንም›› መስማት ይከለክለናል፡፡
  • እነርሱ «የምስጋና መዝሙር›› ቢሏቸውም አስተውሎ ለሰማቸው ፉከራና ሽለላዎች ናቸው፡፡
  • የመዝሙሮቻቸው የጌታችንና የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን ሲያነሡ ልክ ባልጀራቸውን እንደሚጠሩ ያህል በድፍረት መሆኑ ደግሞ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ታዲያ አንተ መዝሙራቸውን እየሰማህ ከእነርሱ ጋር «ኢየሱስ ጓዴ›› ለማለት ልብህ ይከጅላልን? 
‹‹ይህ ነው ምስጋናቸው›› ይመልከቱት


ዘፈን መስማትና ዘፋኝነት ለመናፍቃን መዝሙር ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የመናፍቃን መዝሙር ከሚያስጨፍር ዘፈን አይለይምና፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ለመናፍቃን መዝሙር የቀረበ አመለካከት እንዲኖራቸው ያደረገው በውስጣቸው ያለው የዘፈን እርሾ ነው፡፡ ብዙ ዘፋኞች ወደ መናፍቅነት እንዲሄዱና በዚያም «ዘማሪ›› እስከመባል መድረሳቸው በዚህ ውጤት ነው፡፡

ይድረስ በዝምታ ውስጥ ላለው ሊቃውንት ጉባኤ


Click Read more........

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ 17 አጀንዳዎችን በማጽደቅ መወያየቱን ቀጥሏል


  • በቤተ ክርስቲያን ሥርዐተ እምነት ላይ ያለውን ችግር በቀረበው ማስረጃ ላይ ተመሥርቶ መወያየት፣ የተጀመረው የዕርቀ ሰላም ንግግር ፍጻሜ የሚገኝበት ሁኔታ፣ በቃለ ዐዋዲው መሻሻል የሚገባቸውን ክፍሎች መወሰንብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በሞተ ሥጋ ሲለዩ [ሀብት፣ ንብረታቸው] ምን መሆን እንዳለበት፣ ስለ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ በአጣሪ ኮሚቴው ተጠንቶ በቀረበው ጽሑፍ ላይ መወያየት የሚሉት ከአጀንዳዎቹ ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው
  • የተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እና የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻል የአጀንዳ ሐሳቦች ተቀባይነት አላገኙም
  • ዛሬ ከቀትር በፊት ስለ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ በአጣሪ ኮሚቴው ተጠንቶ በቀረበው ጽሑፍ ላይ ውይይቱንአካሂዷል

Tuesday, October 25, 2011

ማኅበረ ቅዱሳንን ከምሁራንና ከካህናት ጋር ለማጋጨት እየተሞከረ ነው


  •  ማኅበሩ ምላሽ አለመስጠቱ ብዙዎችን አበሳጭቷል፤ 
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 14/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 25/2011)፦ ተፋፍሞ በቀጠለው የፀረ ፕቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ መሪ ነው የሚሉትን ማ/ቅዱሳንን በመቃወም ላይ የሚገኙት የተሐድሶ-መናፍቃን አሁን በያዙት አዲስ ስልት ማኅበሩ ከታዋቂ ምሁራን እና ካህናተ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለማጋጨት እየሞከሩ ነው።  


በዚህ አዲስ የማጋጨት ተግባር “ማኅበረ ቅዱሳን ተሐድሶ-መናፍቃን ናቸው ብሏችኋል” ከተባሉት መካከል ታዋቂዎች ምሁራን ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እና ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ሲገኙበት ከእነርሱም በተጨማሪ ካህሣይ ገብረ እግዚአብሔር፣ ግርማ ኤልያስ (ከዚህዓለም በሞት የተለዩ)፣ ሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ኀይሌ፣   ሊቀ ማእምራን / አማረ ካሣዬ፣ ሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ እና ዲ/ን በእደ ማርያም እጅጉ ይገኙበታል።

ማኅበሩ ግን በፈንታው እየተካሄደበት ላለው ዘመቻ ምንም ዓይነት መልስ ባለመስጠቱ ቆይቶ ተጎጂ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

ከቅዳሜው ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶን የሚቃወም ትዕይንት ጋራ በተያያዘ ፖሊስ ተጨማሪ ወጣቶችን እየያዘ ነው



  • ፓትርያርኩ፣ ተሐድሶዎቹን ደግፈው ለቆሙትና በፖሊስ ለታሰሩት ወጣቶችለቀለብ እንዲሆናቸው በሚል፣ ዛሬ 10 ሺህ ብር ልከዋል እየተባለ ነው 
  • ለሌሎቹ ወጣቶች ግን ስላደረጉት ነገር ምንም አልተሰማም፤
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 14/2004 ዓ.ም)፦  “ተቻችሎ እና ተከባብሮየኖረውን ሕዝብ ወደ ብጥብጥ በመምራት እና ሰው በመደብደብ የሚሉ ሁለት የወንጀልክሦች የቀረቡባቸው “የአዲስ አበባ የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶች ማኅበር” ስምንት አባላትትላንት ጥቅምት 12 ቀን 2004 .ም ጠዋት  በአዲስ አበባ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ /ቤትአራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ከስምንቱ መካከል ስድስቱ እያንዳንዳቸው በብር 600 ዋስ እንዲወጡ ሲወሰንላቸው፣ የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ ለጥቅምት 16 ቀን 2004 ዓ.ም እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር - ዋነኛ አስተባባሪዎች ናቸው በሚል፡፡

የማይሰማ የለ




በአሁኑ ሰዓት ይህ ከላይ የምታዩትን መልዕክት በአዲስ አበባ በሺህ የሚቆጠር 2 ገፅ ብዛት ያለው ፅሁፍ በማህበረ ስላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ የተፃፈ በየሰዉ እጅ ላይ ይገኛል ፡
ከመልእክቱ ላይ የተወሰደ
‹‹በምድር ላይ ያለን የሰው ልጆች ሁሉ ነገርን ሊያደላድል የቅድስት ምድር ኢትዮጵያን ክብር ሊገልፅ ትንሳኤዋን ሊያረጋግጥ ከብሔረ ህያዋን የመጣው የኃያል ባለስልጣን ቃልና ትዕዛዝ ሰምተን በማስተዋል ወደ እውነት በመምጣት በንስሀ በመታደስ እራሳችንን ልናተርፍ ይገባናል፡፡ ›››  ይላል 

ማህበረ ስላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ የሚባሉት ቅድስት ስላሴ ጀርባ መሰብሰቢያ ያላቸው ፤ ብዙ ሰው ተከታይ ያለው ማህበር እንደሆነ ሰውን እያወዛገቡት እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡


ሙሉውን ያንብቡ  Click Read more

ተሐድሶን” የተቃወሙት ወጣቶች በእስር ላይ ናቸው


  • ወጣቶቹ “ሕዝብን ወደ ብጥብጥ የመምራት” እና “ሰውን የመደብደብ” ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል፤
  • ወጣቶቹ እርስ በርስ የማይተዋወቁ እና ከተለያየ አካባቢ የመጡ “የአዲስ አበባ ጥምቀት ተመላሽ ወጣት ማኅበር” አባላት ናቸው፤ ማኅበሩ ወጣቶቹ መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲፈቱ ጠይቋል፤
  • የሕገ ወጡ ቡድን አባላት (በጋሻው ደሳለኝ፣ በሪሁን ወንደወሰን፣ ትዝታው ሳሙኤል. . .) እና ለወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ቀራቢ የሆኑ ባለሥልጣናት ወጣቶቹ የዋስትና መብታቸውን ተነፍገው በእስር እንዲሰነብቱ እየተሯሯጡ ነው፤

በተለያዩ ዘዴዎች ቤተ ክርስቲያንን ለመውረር ከውስጥና ከውጭ እየተከናወነ ባለው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተወያይቶ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ታሪካዊ ሚናውን እንዲጫወት” ለመጠየቅ ቅዳሜ ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመሰብሰብ ድምፃቸውን ካሰሙት ከ1000 የማያንሱ ወጣቶች መካከል ተይዘው በእስር ላይ የሚገኙት ስምንት ወጣቶች ጥቅምት 13 ቀን 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፡፡

አነጋጋሪው እና አደናጋሪው የመጋቢ ሐዲስነት ጉዳይ…


  • መጋቢ ሐዲስ ለመባል ምን ያስፈልጋል ? 
  • ቤተክርስትያን ለምን አይነት መምህራን መጋቢ ሐዲስ የሚል የመአረግ ስም ትሰጣለች ?
  • መጋቢ ሐዲስ የሚል መአረግ ለተሰጠው አገልጋይ ከእሱ ምን ይጠበቃል ? 
የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8
18 ሲሞንም በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጥ ባየ ጊዜ፥ ገንዘብ አመጣላቸውና።
19 እጄን የምጭንበት ሁሉ መንፈስ ቅዱስን ይቀበል ዘንድ ለእኔ ደግሞ ይህን ሥልጣን ስጡኝ አለ።
2ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለውየእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ
21  ልብህ በእግዚአብሔር ፊት የቀና አይደለምና ከዚህ ነገር ዕድል ወይም ፈንታ የለህም።
22 እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንሰሐ ግባ፥ ምናልባትም የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደ ሆነ ወደ እግዚአብሔር ለምን፤ 
23 በመራራ መርዝና በዓመፅ እስራት እንዳለህ አይሃለሁና።
                                                                                                  የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 ፤18-23

አሁንም ባለንበት ዘመን እግዚአብሔር የሚገለገልበትን ነገር በገንዘብ ለማግኝት የሚጥሩ ፤ በገንዘብ ኃይል ቅስናውን፤ ድቁናውን፤ መጋቢ ሐዲስ ፤  ከፍተኛ ሐላፊነትን ፤ የደብር አስተዳዳሪነት ፤ሌሎች የቤተክርስትያናችንን የአገልጋይ ስሞችን  ማእረጉን ያገኙ ሰዎች አሉ ፡፡ የዛሬ ዓመት በዚህ ሰዓት ብዙ መነኮሳት ጵጵስናን ለመሾም ከ300,000-500,000 የኢትዮጵያ ብር በጉቦ መልክ ፤ በእጅ መንሻ መልክ ማቅረባቸው የዛሬ ዓመት ትውስታችን ነው፡፡ለእነዚህ ሰዎች የእኛ መልእክት ከላይ የሐዋርያት ላይ ‹‹የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ››  ካለው የጴጥሮስ መልዕክት የሚለይ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣ መጥታ ከምታነዳቸው በንስሃ ህይወታቸውን ይመለከቱ ዘንድ  የዘወትር መልዕክታችን ነው፡፡


READ IN PDF click here


Click Read more to continue 

እንኳን አደረሳችሁ



(by Wubishet Tekle )ጥቅምት 14 ቤተክርስቲያን የ 3 ታላላቅ አባቶችን መታሰቢያ ታከብራለች፤አንዱ አቡነ አረጋዊ ናቸው ደብረ ዳሞ ላይ በፍጹም ተጋድሎ ኖረው ለኢትዮጵያ ብርሃን ሆነው በ 99 ዓመት ከ 3 ቀናቸው ተሰወሩ፤የአቡነ አረጋዊ እናት ንግስት እድና ንግስናዋን ትታ ልጇን ተከትላ መጥታ ደብረ ዳሞ ተራራው ስር በ89 ዓመቷ አርፋለች፤ 



ሁለተኛው ጻድቅ መናኙ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ነው እርሱም የንጉስ ልጅ ነው፤ከጫጉላ ቤት ጠፍቶ መነነ፤ አባቱ ወታደሮችን ላከበት፤ ገብረ ክርስቶስ ሌት ተቀን ተጉዞ የእመቤታችንን ደብር አገኘ ተንበርክኮም እመቤቴ ወታደሮች እንዳይዙኝ መልኬን ቀይሪሊኝ አላት የውስጥ ሰውነቱ ተገለበጠ በቁስልም የተመታ ሆነ ደጀ ሰላሙ ላይ ምጽዋት ከሚለምኑ ድሆች ጋር ተቀመጠ ወታደሮቹ ደረሱበት አላወቁትም ምጽዋት ሰጥተውት ያልፋሉ፤ በዚያች በቤተክርስቲያን 15 ዓመት በተጋድሎ ኖረ ከዚያም ወደ አገሩ ተመልሶ በአባቱ ደጅ 15 ዓመት ወድቆ ለመነ፤ አባቱ ለአሸከሮቹ እንዲህ አለ ይህንን ደሃ ምጽዋት ስጡት ልጄ ምናልባት ልክ እንደዚህ ደሃ በሰው አገር እየተንከራተተ ይሆናልና አላቸው፤ የአባቱ አሸከሮች ግን የእጅ እጣቢ፤ሽንት ይደፉበት ነበር በላዩ ላይ አጥንት እየወረወሩ ውሾች እንዲጣሉበት ያደርጉ ነበር፤ በእንዲህ ያለ ተጋድሎ 15 ዓመት ኖረ፤የእረፍቱ ቀን ሲደርስ የንጉሱ የቴዎድዮስ ልጅ መሆኑን የደረሰበትን ሁሉ መከራ ጽፎ ይሞታል፤ሊቀብሩት ሲሰበሰቡ ይህችን ጽሁፍ ያገኛሉ፤ አባትና እናቱ መሪር ለቀሶ አለቀሱ አገሩ በሙሉ አለቀሰለት ከበድኑ ገራሚ ገራሚ ተአምራት ተገለጹ ድውያን ሁሉ ተፈወሱ፤በታላቅ ክብርም ቀበሩት፤ ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን፤ 



ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን የኢትዮጰያዊቷ ንግስት ህንደኬ በጀሮንዷ የሆነውን ጀንደረባውን ያጠመቀው ታሪኩ በሐዋርያት ስራ ምዕራፍ 8፤27 ላይ ተገልጾ የሚገኘው ሐዋርያው ፊሊጰስ ያረፈበት ቀን ነው፤ይህ ሐዋርያ ከ 72ቱ አርድእት አንዱ ነው። የአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን። 



ስለ ደብረ ዳሞ ገዳም ታሪክ ከአኮቴት ቴሌቪዥን መርሀ ግብር ላይ የተወሰደ

Monday, October 24, 2011

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጀመረ

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በአጀንዳ ረቂቅ ላይ ሲወያይ ዋለ 
  • በኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እና በዕርቀ ሰላም ጉዳይ አጀንዳ ላይ ልዩነቶች አሉ፤ 
  • የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እና ማኅበረ ቅዱሳን ከማ/መምሪያው ጋራ ስላለው ግንኙነት የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት በአጀንዳው ረቂቅ ውስጥ ተካተዋል፤ 
  • ያረፉ ብፁዓን አበው ሀብት እና ንብረት ወራሾች ነን” በሚሉ ሐሰተኞች ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እየተቸገረ መሆኑ ተገለጸ፤
  • በኤጲስ ቆጶሳት ሹመት የካህናት እና የምእመናን ተሳትፎ ይጨመርበት፤ በጳጳሳት ሀብት እና ንብረት ውርስ ጉዳይ የቀድሞው ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይመለስ” (የዜና ቤተ ክርስቲያን ርእሰ አንቀጽ)፤
  • ዛሬ ገንዘብም ጭምር የሚዘረፍባትና የሚነጠቅባት እንጅ ቅኔ ብቻ የሚዘረፍባትና የሚነጠቅባት የትናንቷ ደሃ ቤተ ክርስቲያን የለችም” (ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ)፤

ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል



(By Cherinet Yigrem )የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ በእስራኤል(በኢትዮጵያ) እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥ እረኞችንም እንዲህ በላቸው። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል(የኢትዮጵያ) እረኞች ወዮላቸው! እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን? ጮማውን ትበላላችሁ ጠጕሩንም ትለብሳላችሁ፥ የወፈሩትን ታርዳላችሁ፤ በጎቹን ግን አታሰማሩም። የደከመውን አላጸናችሁትም የታመመውንም አላከማችሁትም የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም የባዘነውንም አልመለሳችሁትም የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው። እረኛንም በማጣት ተበተኑ፥ ለምድርም አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ፥ ተበተኑ በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በጎቼም በምድር ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል፤ የሚሻም የሚፈልግም አልነበረም ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ: ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እኔ ሕያው ነኝና እረኛ ስለሌለ እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎቼን ስላላሰማሩ፥ በጎቼ ንጥቂያ ሆነዋልና፥ በጎቼም ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና

Sunday, October 23, 2011

30ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ 4ኛ ቀን ሪፖርታዥ


30ኛው አጠቃላይ ጉባኤ ባለ33 ነጥብ የውሳኔ ነጥቦች እና የጋራ አቋም የያዘ መግለጫ አውጥቷል፤ ከእኒህም መካከል፡-
  • የአብነት ት/ቤቶች ትምህርት ከዘመናዊው ትምህርት እና ሥርዓት ጋራ ተቀናጅቶ ሊሰጥ በሚችልበት ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ሥርዓተ ትምህርት በትምህርት እና ማሠልጠኛ መምሪያ ማዕከልነት እንዲዘጋጅ፤
  • ቃለ ዐዋዲው በአንዳንድ አካባቢ “የመንግሥት ዕውቅና የለውም” የሚል ጥያቄ እያስነሣ መሆኑ ለጉባኤው ስለተገለጸ በሥራ ላይ ያለው ቃለ ዐዋዲ በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሻሻልና ለመንግሥት ቀርቦ ዕውቅና እንዲያገኝ እንዲደረግ ጉባኤው በአትኩሮት ያሳስባል፡፡
  • በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ተመሳሳይነት እና እኩልነት የሚታይበት አገልግሎትን በትክክል ለመፈጸም፣ የካህናትን ወደ አዲስ አበባ መምጣት ለማስቀረት የበጀት ማዕከላዊነት ቢኖር እንደሚበጅ በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተገለጸውን ጉባኤው በአትኩሮት ተገንዝቦታል፡፡ በመሆኑም በአፈጻጸም ጥልቅ ጥናት ተደርጎ ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዲቀርብና ተግባራዊ እንዲሆን ጉባኤው አምኖበታል፡፡

“በቀልን ለተጠማ አባት ራሴን አሳልፌ አልሰጥም” - ብፁዕ አቡነ አብርሃም

  • ሊቃነ ጳጳሳቱ ፓትርያሪኩን በጣልቃ ገብነት ወቀሱ
  • ሁለት ሊቃነ ጳጳሳት በፓስፖርት እና በመኖሪያ ፈቃድ እድሳት እጦት እየተንገላቱ ነው
  • በ’ተሐድሶ’ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የተፈጠረው ውዝግብ ተባብሶ ቀጥሏል
  • የማያቋርጥ አቤቱታ መብዛት ጠቅላይ ቤተ ክህነታችን የመዋቅርና የሥራ ሂደት መሻሻል እንደሚያስፈልገው አመላካች ነው” - የጠ/ቤ/ክ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ጥናት
(አዲስ አድማስ ጥቅምት 11/2004)የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ ካሏት ሦስት አህጉረ ስብከት መካከል የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና የሰሜን ምዕራብ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፤ ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ያለቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና በሊቃነ ጳጳሳቱ ላይ የበላይ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት በዋሽንግተን ዲሲ እንዲቋቋም ያስተላለፉትን ትእዛዝ ተቃወሙ፡፡ አቡነ ፋኑኤል ያለቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድና ያለሀገረ ስብከቶቹ ዕውቅና በሚፈጥሩት ችግር ላይ ርምጃ ባለመውሰዳቸውም ፓትርያርኩን በጣልቃ ገብነት ወቅሰዋቸዋል፡፡

Friday, October 21, 2011

ተሐድሶን ከማውገዝ እኩል ትጥቅ ያላቸውን ማስፈታት ያስፈልጋል፤ የመውጣት ምልክቱ ጫጫታ ነውና

(by Wendemsesha Ayele Kesis ) መምህር ዘመድኩን በቀለ በቪሲዲው አርማጌዶን ቁጥር ሁለት ላይ እንደተነተነው ከዓመታት በፊት ደሴ ላይ የተብራራው የመውጣት ምልክት ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው።  «የቤተክርስቲያን አስተዳደር መሻሻል ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ» በሚል ርእስ የጻፍኩት ክታቤ ላይ በአፈጻጸም ደረጃ በ፫ኛና አራተኛ ደረጃ ያስቀመጥኳቸው ጉዳዮች በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በቅጥር ያሉና ትጥቅ ያላቸውን ሰዎች ይመለከታል። ዛሬ ተሐድሶን ለማውገዝ ከሰፊና ሁለገብ ድካም በኋላ ሊሳካ ይመስላል። ይሁን እንጂ በ፲፱፻፺ ዓም በውግዘትና በእርማት ከታለፉት ጀምሮ በየጊዜው ሥልጠና እየሰጡ የተራቡት እንዲሁም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚተባበሯቸው ክህነት ያላቸውና የሌላቸው የቤተክርስቲያን ተቀጣሪዎች ሕጋዊና ሕገወጥ ትጥቅ ይዘው የመገኘታቸውን ነገር ትኩረት የሰጠው መኖሩን እጠራጠራለሁ።

‹‹እግዚአብሔር አይዘበትበትም››

ከፎከስ ያገኝነውን እናካፍላችሁ
 ‹‹እግዚአብሔር አይዘበትበትም›› መምህር ተስፋዬ ሸዋዬ
To Read by Pdf Click here


To read by image format click Read more

30ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ 3ኛ ቀን ሪፖርታዥ

  • በቋንቋው ጠንቅቆ የሚያስተምር መምህር ባጣው በአዲሱ የቄለም ወለጋ ሀ/ስብከት በተሐድሶ መናፍቃን ከተወረሩት ሰባት ወረዳዎች በአንዱ ወረዳ በሚገኙ ሰባት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሴቶች ካህናቱን አንበርክከው ይጸልዩላቸዋል፤ ‹ቅዳሴ አያስፈልግም፤ ቅዱሳን አያማልዱም› የሚል ክሕደት በግልጽ እየተነገረ ነው”/የሀገረ ስብከቱ ሪፖርት/፤
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመንበረ ፓትርያርኩን 35% ድርሻ ብር 24 ሚልዮን ገቢ አደረገ“ኑሯችን ለምንሰብከው ምእመን ምሳሌ የሚሆን ነው ወይ?” ሲሉ የጠየቁት የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ “እጃችን መሰብሰብ አለበት” ሲሉም መክረዋል፤ ጉባኤው ለሥራ አስኪያጁ ንቡረ እድ አባ ገ/ማርያም ገ/ሥላሴ ከመቀመጫው ተነሥቶ ከፍ ያለ ጭብጨባ/standing ovation/ ችሯቸዋል
  • በከምባታ አላባ እና ጠንባሮ ሀ/ስብከት በአንድ ቀን እስከ 2228 ሰዎች ተጠምቀዋል፤ በዕለቱ የሀገር ሽማግሌዎች የሀ/ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስን ዝናም እንዲያዘንሙላቸው ጠይቀዋል፤ በተደረገውም እግዚኦታ ለ40 ደቂቃ ያህል ዝናም ዘንሟል፤
  • በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ ከ70 በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን 52ቱ ደቡብ አፍሪካውያን ካህናት የሚያስተዳድሯቸው ናቸው
  • ከሰሜን አሜሪካ ሦስት አህጉረ ስብከት የሁለቱ (የዋሽንግተን ዲሲ እና የካሊፎርኒያ) ሊቃነ ጳጳሳት በአቡነ ጳውሎስ ትእዛዝ “በዋሽንግተን ዲሲ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት” በሚል ከሊቃነ ጳጳሳቱ የበላይ የሆነ አካል መቋቋሙን በመቃወም እና በፓትርያርኩ ደርሶብናል በሚሉት በደል ዙሪያ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለፓትርያርኩ የጻፏቸው ደብዳቤዎች በጉባኤተኛውና በሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘንድ አነጋጋሪ ሆነዋል /መረጃዎቹ ደርሰውናል፣ ዝርዝሩን ወደፊት እናቀርባለን/፤

Thursday, October 20, 2011

የፓትርያርክ ጳውሎስ ቁማርና የቤተክርስቲያን ተስፋ

by Wendemsesha Ayele Kesis

ቁማር ከመዝናናት ሌላ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የሚጫወቱት ሕጋዊና ሕገወጥ ጫወታ መሆኑና ማንኛውንም ጫወታ በቁማርነትም ሆነ በመዝናኛነት ለይቶ የመጫወቱ ድርሻ የተጫዋቹ መሆኑ ግልጥ ነው፤ ካርታን ለመዝናኛነትም፣ ሲያስፈልግ ደግሞ በሕገወጡ ቁማርነትም መጫወት እንደሚቻል። ይህም መንፈሳዊውን ሥልጣን በያዘው ሰው ዘንድ መነገሩ እጅግ የሚያሳስብና የሚያሳዝን ነው። «አባት»ን ቁማርተኛ ብሎ ለሚናገረውም ሁለት ጊዜ ብቻ ሳይሆን አሥር ጊዜ አስቦ ዓላማንም ለይቶ የሚጸናውን ከያዙ ላያሳፍር ብሎም ሊጠቅም ይችላል። ተሳድቦና ዘልፎ ለመርካት ወይም ብስጭትን ለመወጣት ሊረዳ ቢችልም ከኅሊና ዕዳ ነፃ ለመሆን ግን እውነተኛ መረጃ ይፈልጋል፤ እንደነ በጋሻውም በአደባባይ ለመገላበጥ አይገደድም። እኛምይህን ታሳቢ አድርገን እንቀጥል።


ከረጅሙ ታሪካቸው ባጭሩ

አባ ጳውሎስ አሁን በሕይወት ከሌሉ አንድ ዘመዴ ጋር የሃይስኩል ተማሪ ሆነው በቅድስት ሥላሴ ት/ቤት ሲማሩ የነበሩበትንና ከያኔው ግርማ /አሁን አቡነ ገሪማ/ ጋር ሆነው ሁለቱ ጓደኞቻቸው በጥቁር ራስነት እሳቸው ግን ያኔም በምንኩስና ሲኖሩ ድብቅነት ይታይባቸው ነበረ። ጵጵስና ከተሾሙ በኋላ ሳይቀር ቆባቸውንና ቀሚሳቸውን አውልቀው በሱሪና ኮት እንደተራ ሰው ከተማ የሚዞሩበት አጋጣሚም ነበረ፤ ምክንያቱን ራሳቸው ይወቁት። ከሃይስኩል በኋላ ባገኙት ዕድል የቲዎሎጂ ዲግሪ ይዘው ቅዳሴ ተምረው ጵጵስና ለመቀበል እንዴት እንደቻሉ መጠናት አለበት፤ ምክንያቱ ደግሞ ዕድሜያቸው ለጵጵስና ያልደረሰ፣ ቅስና እንኳ ለመቀበል የቤ/ክ/ ጥልቅ ሙያ በሚጠየቅበት ተጠይቆም ሲገኙ /በዘመኑ ሞልተዋል/ አልሾምም እያሉ በሚሸሹበት ዘመን በወጣትነታቸው ለኤጲስ ቆጶስነት መታጨታቸው፣ በከባዱ የፖለቲካ ውጥረት መሐል የፓትርያርኩን ልብ ከፍተው የገቡትና ለዛሬው ጥፋት መሪ ተዋናይ የሆኑበት ሁኔታ ቀድሞ የተጠና ይመስላል። ያኔ ግን ታላላቁ ብፁዐን አባቶች በዕውቀታቸውና በመንፈሳዊ ሞገሳቸው በሕዝቡ ዘንድ እጅግ የተከበሩ ነበሩ።ሌሎች አባቶች በመንግሥት ጭምር እየተፈሩና እየተፈለጉ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሚናቸውን እንዲጫወቱ በአስፈሪው ደርግ ሲጋበዙ ለተራበ ለምነው እርዳታ በማስመጣት፣ ቤተክርስቲያን የሄደውን ምእመን አስተባብረው ልማትንና ወንጌልን በሙሉ ኃይላቸው በማስፋፋት በገቢረ ተአምር ጭምር ሲመላለሱ ነው የሚታወቁት። አቡነ ጳውሎስና ሌሎች ሁለት ግን ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ጋር በፖለቲካ ጉዳይ ተከሰው ታሠሩ።



ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ እንዲገደሉ ሤራ ሲሸረብ እነርሱ ሰባት ዓመት ታሥረው ተፈቱ፤ አሜሪካም ሄደው በብዙ በሚያስወቅሳቸው ተግባር ተጠመዱ፤ ፓትርያርክ ከሆኑ በኋላ አሜሪካ ሲሄዱ የበሰበሰ ቲማቲምና የገማ እንቁላል የተወረወረባቸው ከዚሁ ቆይታቸው መታወቅ ጋር በተያያዘ ነበረ። ዛሬ እንደምሳሌ የሚያነሧቸውና የእርሳቸውን ሥራ እንደቀጠሉ የሚያስወሩት ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ ጠንካራ አቋም ይዘው ከንጽሕናና ቅድስና ጋር ርስቷን ላጣችው ቤተክርስቲያን መተዳደሪያ ዕቅድ ያወጡላት፣ ዛሬ እንደፈለጉ የሚዘርፉትን የሰበካ ጉባኤ አስተዳደርና ፐርሰንት አሰባሰብ ለመጀመሪያ ጊዜ ዐውጀው የተገበሩት፣ በየሀገረስብከቱም እየታደመባቸውና እየተዘለፉ ያደራጁት እርሳቸው ናቸው። አስተዳደራዊና ቀኖናዊ ነገሮችን በመቀላቀል ከመንግሥት ጋር ሲያጣሏቸው አድርባይ ባለመሆናቸውና ሀሳባቸውን ባለመለወጣቸው በሞቅታ ውሳኔ ፓትርያርኩ ሲገደሉ ብዙ ይሠራሉ ተብሎ ሲጠበቁ የነበሩትና ባለብሩህ አእምሮው ቴዎፍሎስ ንጽሕናቸውን ይዘው በክብር ዐረፉ። እዚህ ጋር ተሐድሶዎች እንደ ደቂቀ እስጢፋ ታሪክ ለሀሳባቸው ማስኬጃ ሊጠቀሙባቸው እንደሚፈልጉ ያስታውሷል። አቡነ ቴዎፍሎስም ሆኑ ደቂቀ እስጢፋ ያላቸው ሀሳብ ከዛሬዎቹ ፕሮቴስታንታዊዎቹ ተሐድሶዎች ጋር ምንም ተዘምዶ የላቸውም /ታሪካቸውን በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመሥርተን መናገር ያለብን ወቅት ላይ ሳንደርስ አንቀርም።/



የዛሬው ፓትርያርክ ጳውሎስ በየትኛው ሥራቸው እንደተከተሏቸው ታሪክና ፈጣሪ ይግለጠው እንጂ ለእኔ ከሽፋን በቀር የተረዳሁት ነጥብ የለም። ባይሆን አሁን የሃይማኖት ድብቅ አጀንዳ ይዘው በሚታዩ የአስተዳደር ችግሮች ላይ ድምፃቸውን እያጮኹ «ቤተክርስቲያን ትታደስ» የሚሉትን ተሐድሶዎች ለመተባበር የማያዛልቅ መደገፊያ ሊሆኗቸው ይችላሉ። ቴዎፍሎስ ግን እንደተገለጡት ተሐድሶዎች /ለምሳሌ ጽጌ ስጦታው/ ኢየሱስ ክርስቶስን ይለምንልናል አማላጅ ነው፣ ቅዱሳንን ከእመቤታችን ጀምሮ እነ አቡነ ተክለሃይማኖት «ጣዖቶችና ሰይጣን» እያሉ አንድም ቀን ተናግረውም ሆነ ሲነገር ዝም ብለው አያውቁም ነበረ። ቆይቶ በዩኒቨርሳሊዝም አስተሳሰብ የተጠለፈውን የወጣቶች ማኅበር «ሃይማኖተ አበው» በወቅቱ ቤተክርስቲያንን ከማጠናከርና ዘመኑን ከመዋጀት አንጻር ተፈላጊ በመሆኑ ይደግፉት ነበረ፤ በእርሳቸው ዘመን ግን «የማያድን ሃይማኖት የለም፤ ሁሉም በማዳን አይበላለጡም እኩል ናቸው» ብሎ ከፕሮቴስታንቶች ጋር ያለውን የልዩነት ድንበር ይህ ማኅበር ሲያፈርስ አያውቁም፤ አልተገለጠም ነበረ። የሃይማኖተ አበው በዩኒቨርሳሊዝም አስተሳሰብ መጠለፍ የተገለጠው በባሕታዊው ፓትርያርክ ተክለሃይማኖት ዘመን ነው፤ ወዲያውም ተወግዟል። ፓትርያርክ ጳውሎስ እነጽጌ ስጦታው በግልጥ ኑፋቂያቸውን እያስፋፉ አባቶችን ሲዘልፉ ሊያወግዟቸው አላሰቡም፤ እንዲያውም እንዳይወገዙ ሽፋን በመስጠትና ሊቃውንቱን በማሳደድ ሥራ ተጠምደው እስከዛሬ ቆዩ።



ከአሜሪካ የተመለሱትና ለአንድ ዓመት ያህል በልዩ ልዩ ኃላፊነት የቆዩት አዲስ አበባ ነው። ከምንኩስናቸው ጊዜ ጀምሮ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስን በማንቆለጳጰስ ለጵጵስና ሲጎመጁ ሰነበቱ እንጂ አንድ ሀገረስብከት ወይም ደብር በክህነት ወይም በመምህርነት በወጉ ያገለገሉበት ጊዜ አልተጠቀሰም። የፓትርያርክ መርቆሬዎስ ስደት ሲሸረብ /እጃቸው ይኖርበት እንደሁ እንጃ፤/ ዋናው አጀንዳ ፖለቲካ በመሆኑ ለኢሕአዴግ ደግሞ በደርግ ተበዳይነትም ሆነ በትጥቅ ትግል የበላዩ ሕወኃት ወገንነት በመኩራራት ተገቢ ሰው ሆነው፤ ለዕውቀትም ሆነ ለመንፈሳዊነት እንደሚጠቅም ባልተገለጠው ፒኤችዲ ተከልለው /በእውነቱ እንደተማሩ የሚያሳይ ምሁራዊ ተግባር የላቸውምና እኔ መማራቸውን እጠራጠራለሁ/ «አማራጭ የሌለው አማራጭ» ሆነው ፓትርያርክነት ሐምሌ ፬ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓም ተሾሙ። ይህንም በወቅቱ የነበሩት ሊቃውንት ከሰብሳቢያቸው ሊ/ሊ/ አያሌው ታምሩ ጭምር ተቃወሙት፣ የግብፅ ሲኖዶስም አወገዘ። በዚያው ወቅት እንደወረራ የተከሠቱት ባሕታያንም ከፊሎቹ በኃይል ሌሎቹም በየጉባኤያቸው ተቃወሟቸው። በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ትልቁ ሽፋን «ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደእሳቸው ማን አጻፈ፣ የቤ/ክ/ ርስቶችና ቤቶችን ማን አስመለሰ» እያሉ በቅኔና በዜማ ማሰበክ ነው። ተደርጎ የማይታወቀው መሣሪያ ታጥቆ መቅደስ መግባት፣ ከመጠን በላይ በተረፈ ወጪና ዘመናዊነት መምነሽነሽ፣ ጳጳሳት በዐዋጅ ሀብት እንዲያፈሩና ለፈለጉት ሰው እንዲያወርሱ የተፈቀደው፣ የአዲስ አበባ አድባራት ለሌሎች አኅጉረስብከት መዳከምና ለጥቅም እሽቅድምድም አደባባይነት የተዳረጉት፣ የትም ያለው ካህንና መምህር ከጠቅላይ ቤተክህነት በጀት የሚያገኘው በእሳቸውና በረጅሙ ሥራአስኪያጅነት ሥልጣን ዘመናቸው አብሮ አደጉ አቡነ ገሪማ ዘመን ነው። ነገሩ መመርመርና መፈተን የጀመረው፣ ለዘላቂ መፍትሔነትም ቃለዐዋዲውም ሆነ ሕገቤተክርስቲያኑ የተከለሰው በ፲፱፻፺፩ ነበረ። ይህ ባይሆን ኑሮ፣ በፓትርያርክ ሥልጣን ያለው ገደብ ባይተነተን ኑሮ ደግሞ ከዚህ የባሰ ጥፋት ይመጣ ነበረ። /አሁንም ቃለዐዋዲው ብቻ ተስተካክሎ የሚፈጸም ላይሆን ስለሚችል ጥንቃቄ ሳይሻ አይቀርም/ በአጠቃላይ ካልታወቀባቸው አሠራሩን እየጣሱ፣ ተቃዋሚ ከገጠማቸው ደግሞ ሥልጣናቸውን አላግባብ እየተጠቀሙ ያሻቸውን ሲያደርጉ የቆዩት ፓትርያርክ ዛሬ እንዴት እናሸንፋቸውና ቤ/ክ/ ሰላም ታግኝ? ጥያቄያችን ነው።


ሊቀካህናት ሃና /«ሃ» ላልቶ ይነበብ/

«ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል። ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም፥ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ።» እንዳለው የሾማቸው እግዚአብሔር ፊታቸውን ጸፍቶ አፋቸውን ከፍቶ «ዓለሙ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ቢጠፋ ይሻላል» እንዲሉ አድርጓቸዋል። ይህ አባባል ከአዳም ጀምሮ ያለው ትውልድ ከሚጠፋ አንድ ክርስቶስ ሞት ተፈርዶበት ዓለሙን በሞቱ ቢያድን ይሻላል በሚለው ትርጓሜ ይኸው ዛሬም በበጎነት ጭምር ይጠቀሳል፤ የትምህርት ርእስም ይሆናል። ይህ ማለት ግን የሃና ሀሳብ ከበጎ ኅሊና የመነጨና ለቤተመቅደስ ጥቅም የተነገረ ነው ማለት አይደለም። ግን ሃና ባለበት መቅደስ ጌታችን ሥራውን ፈጽሟል። ጌታችን ቤተመቅደሱን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በሐዲስ ሥርዓተ ክህነትና ሥርዓተ መሥዋዕት እያደሰ፣ ምሥጢረ ሥላሴን እየገለጠ፣ ሐዋርያትን እያከበረ፣ ጸሐፍት ፈሪሳውያንን እንዲመለሱ እየገሰጸ፣ ካልተመለሱም ከነቢያቱ ትንቢት እንደተለዩ እያስረገጠ በመናገሩ ከኦሪት ሊቃውንት እንደነ ገማልያል ያሉ መምህራን የተመለሱበት ሐዋርያትም የዘላለም መንግሥት ካህናት ሆነው በ፲፪ቱ ዙፋን /ነገደ እስራኤል ዘነፍስ/ ላይ የተሾሙበት ፍጻሜ ተገኝቷል።


ዛሬ እንደሃና በየተሾምንበት ሥልጣን አፋችንን ከፍቶ ፊታችነን ጸፍቶ ሳንወደውና ሳንረዳው ደገኛውን ነገር ልንናገር እንችል ይሆናል። ሳንረዳውና ሳንወደው መናገራችን የሚታወቀው ደግሞ በሌላ አጋጣሚ /ያንኑ ሀሳብ ሳንጨርስ ሊሆን ይችላል/ የተናገርነውን የሚቃወም ሀሳብና ተግባር ስንከውን በመገኘታችን ነው። እኔ ፓትርያርክ ጳውሎስን የማያቸው እንደ ሊቀካህናት ሃና ነው። ሀሳባቸውን መርጠን የምንታዘዛቸው በሥራቸው ግን የማንተባበራቸው ኑፋቄን የሚያራምዱ ስመ ካህን፣ እምነታችን በእግዚአብሔር ላይ ስለተመሠረተ የማንናወጽ ሆነን እንጂ ዕቅዳቸው የሁላችንን ድምፅ አሰባስበው ቤ/ክ/ንን ስቀሏት፣ አርጅታለች አድሷት፣ እንድንልላቸው የሚፈልጉ የፍርድ ሰው ሆነው ይታዩኛል።



መምህር ዘመድኩን በቀለ «አርማጌዶን» ቁጥር አንድ ትምህርቱን ባሰራጨ ማግሥት ለተሰበሰቡ ሰባክያነ ወንጌል «ቤተክርስቲያንን እናድሳታለን አትበሉ» እንዳላሉ፤ ነገሩ ፈጥጦ ሊሸነፍባቸው ሲል ደግሞ «ማንንም ተሐድሶ ማለት…አይቻልም። ማንኛውም እንቅስቃሴ ቀኖናን የጣሰ በመሆኑ ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል» ብለው ስለተሐድሶ ግንዛቤ እንዳይሰጥ በደብዳቤ ያግዳሉ። ሌላም ሌላም። ስለዚህ ስለተሾሙ የሚናገሩ፣ ስላልወደዱት የሚያደናግሩ በመሆናቸው እንደ ሃና ብቻ ልናከብራቸውና ልንሰማቸው ይገባ ይሆናል። በተረፈ ግን በተገለጠው ኢ-ሲኖዶሳዊ ተግባራቸው ጥቡዕ እንደ አንበሳ፣ ትሑት እንደ መሬት፣ እንደዮሐንስ አፈወርቅ ጠበቃዋ፣ እንደናቡቴ ሰማዕቷ ሆነን፣ የኪልቂያ ልጅነትን ለመብት፣ ዕብራዊነትን ለማሳፈሪያ ትምክህት፣ መስቀሉን መሸከምን ለመጨረሻው ቁርጥ ፈቃድ ማድረግ ይጠበቅብናል። ምሳሌው ለመንግሥተ ሰማያት ልጆች የተገለጠ ቢሆንም ጥቂት ነጥቦችን ለማብራሪያነትና መፍትሔነት ልግለጥ።


አእማደ ኅሊናት


ስለዛሬዋ ቤተክርስቲያን ስናስብ መዘንጋት የሌለብን የምላቸው ምሰሶዎች አሉኝ፤ አእማደ ኅሊናት።


ምሰሶ ፩፡ የቤተክርስቲያን አንድነት፡- ፓትርያርክ ጳውሎስ ከእርሳቸው በፊት ጭምር የነበሩትን ክፍተቶች በማስፋትና አዳዲስ በመጨመር የሚያከናውኑት ግልጥ ነገር ባገኙት አጋጣሚ ቤተክርስቲያኗን መቅበር፣ ኅልውናዋን ማስረሳት እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ፤ ይህን ዛሬ በግልጥ ብናወሳው ጥሩ ነው። ለቤተክርስቲያን ኅልውና ወሳኙ ምዕራፏ ደግሞ ከሌሎች የእምነት ተቋማት የተለየ የውስጥ አንድነቷ ነው። ከዚህ አንጻር አባቶች ጳጳሳትንና ሊቃውንትን ሲቀጥልም ምእመናንም በተረዱትና ባልተረዱት ምክንያት እንዲከፋፈሉና የካቶሊክና ፕሮቴስታንቶች አድናቂና ከሳሽ፣ የዘመናዊነት ለምድ ናፋቂና ተቃዋሚ /በእርሳቸው አባባል ዘመናዊና ኋላ ቀር/፣ የተፈላጊ ለውጥ አቀንቃኝና የተቃውሞ ሙሾ አውጪ፣ ወዘተ በማድረግ መከፋፈል ነበረ ሀሳባቸው። ከዚህም የተነሣ ለተወሰኑ ጊዜያት ጥቂት ዘመን ቀመስ የተባሉትን ደጋፊያቸው ለማድረግና ከሌሎች አባቶች ለማለያየት እየተሳካላቸው ነበረ፤ ጥቂት የሰመረላቸው የሚመስለው በአቡነ ፋኑኤል ያልበሰለ መንገድና፣ የእነ አቡነ ጎርጎሪዮስ ላይናገሩ መሸበባቸው ነው። በጸሎትና ትሕርምት ምክንያት እጅግ የዋሕ የሆኑትን አባቶች ሲያደናግሩና ያለተቃውሞ እንዲቆዩላቸው ያስቻለ ቢሆንም እግዚአብሔር ግን እንደነ አቡነ በርናባስ በመጨረሻ ሰዓትም ቢሆን እውነቱን እንዲመሰክሩ አድርጓል። በአማራ ክልል «ማኅበረቅዱሳን የሰላም ጸር ነው» በሚል በመንግሥት አቋም ተወስዶ የነበረው በአቡነ በርናባስ የዋሕነት በባሕርዳሮቹ ተሐድሶዎች አቀናባሪነት ቢሆንም ፓትርያርክ ጳውሎስን ግን ረድቷል፤ የዋሑ አባት ነገሩ ሲገባቸው ግን «ለአንድ ሰው ነው የምንታዘዘው ወይስ ለእግዚአብሔር? እስከመቼ» ብለው አፈረጡት፤ ወዲያውም ዐረፉ።??



ስለዚህም ዛሬም የሚከስቷቸውን አጋጣሚዎች በየዋሕነት ወይም በደመ ሞቃትነት ሳይሆን አንድነታችንን ለማፍረስ የተሸረበ ይሆን ወይ ብለን መጠርጠር ተገቢ ነው። ቤተክህነቱን ያለሥራ ድርሻቸው ማበጣበጥ የያዙትም እንጥፍጣፊ ድጋፍ የሚሰጧቸው ሰዎች የቀሩላቸውና ከውሳኔ ያለፈ ፍሬ ያለው ነገር ሊከውኑበት የሚችሉበት ቦታ ስለሆነ ነው። አንድ «አባ» ሰረቀ እንኳ ይኸው ስንቱን ከወነላቸው አይደል።


አቡነ ፋኑኤልም ለዚህ የታሰቡና አሜሪካዊ ተልዕኮ ጭምር የሚጠበቅባቸው ይመስለኛል፤ እርሳቸው ያን ያህል ባይረዱትም። ባይሆን በተጠሪ ጽ/ቤቱ በኩል እንደፈለጉ ሊያሽከረክሯቸው ሲሞክሩ ጥቂቱን እየተግባቡ ሌላውን እየተጨቃጨቁ ሊከውኑት ይችሉ ይሆናል። አሜሪካዊው አሠራር ደግሞ «ሰውን ማመን ቀብሮ ነው» በሚለው የሲ አይ ኤ አማራጭ ጉዳያቸውን ከፈጸሙላቸው በኋላ ወይም ሲከሽፍባቸው ምናልባት ደግሞ ሳይግባቡ ሲቀሩ ሊያስወግዷቸው ይችላሉ። የዚህ አማራጭ ሰለባ ሊሆኑ እንደሚችሉ ለመገመት ደግሞ ቀላሉ ምስክር በአሁኑ ሲኖዶስ በሥውር የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለሲኖዶስ ሲያጋልጡ «ፓትርያርኩ ልከውኝ ነው አሜሪካ የሄድኩት» ሲሉ ያላስተዋሏቸው ብዙ ነገሮች መኖራቸውን ይጠቁማልና ነው። አቡነ ፋኑኤልን ከማዳን አንጻርም ሆነ /ማንስ ቢሆን ለምን ይጎዳ?/ የአሜሪካ ምእመናንን አንድነት ከማስጠበቅ አንጻር በተቃውሞ ከመቀበል ይልቅ በዐዋጁ ሥራቸው /ሐዋርያዊ ልዑክነታቸውን መተባበር ብንችል፣ የተለየ ተግባር ሊከውኑ ሲጀምሩም በአብዮት ሳይሆን በድርሻችን ሥልጣን ብንቃወማቸው በቂ ሊሆን ይችላል። ሰበካውን፣ ሰ/ት/ቤቱን/፣ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን በምእመናኑ በቂ ተሳትፎና በቃለ ዐዋዲው መሠረት እንዲመሩና እንዳያፈርሷቸው ማስገደድ፤ ከዚህ መንገድ ሲያፈነግጡ ደግሞ ባለን ሥልጣን በጥብዓት መከላከል ውጤቱ የተሻለ ሊሆን ይችላል። በአንጻሩም በጥበብ ከተጠቀምንበት የሚሄዱባቸውን «ገለልተኛ» አጥቢያ ምእመናን ወደ ሀገረስብከቱ አስተዳደር እንዲያስገቧቸው «መርዳት» ይቻል ይሆናል። ይህን የመሰለውን ትቶ አሜሪካ እንደገቡ አብዮታዊ እርምጃ ከሞከርን ግን ውጤቱ ማንም የማይፈልገውና የከፋ አንድነት ማጣት፣ ሌላ ትልቅ የቤት ሥራም ሊሆን ይችላል። ሐዋሳ በነበሩበት ወቅት እየታዘዝናቸው ለመፈጸም ከሞከርናቸው ጉዳይ አንጻር ሳስበው ደግሞ ባለማወቅ የሚያጠፉ፣ ለማሸነፍ የማይበቁ፣ ከክፉዎቹ ቀድመውና በልጠው «ከቀረቧቸው» ሌላውን ወገን ትተው ለቤ/ክ/ ሊሠሩ የሚችሉ ዓይነት ሰው ናቸው እንደ እኔ፤ ያም ሆነ ይህ ግን የገንዘብ ነገር ካልተዉት የማይችሉት ጠላት ሊሆንባቸው ይችላል። በቂ መረጃ ካላችሁ አልቃወምም፤ እንዲከፋፍሉን ዕድል ላለመስጠት እናተኩር ነው ነጥቤ። ሌሎች አማራጮችንም በዚህ ምሳሌነት ስለቤተክርስቲያን አንድነት እየታሰበ ቢታይ እላለሁ።


ምሰሶ ፪፡ ያሉና የነበሩት ዛሬ ያልተጀመሩ ችግሮች አስቀድሞም የነበሩ ጥቂት አይደሉም። ልዩነቱ አሁን በመሪ ደረጃ ችግሮቹ ተፈላጊ መሆናቸውና ለጥፋት ዓላማ ለመጠቀም የሚፈልግ ፓትርያርክ መሾሙ ነው። በአንጻሩ ደግሞ በየዋሕነትም ሆነ ባለመረዳት አባቶች ጳጳሳት፣ ሊቃውንትና ምእመናን ለፓትርያርኩ አሳልፈን የሰጠናቸው ሥልጣኖቻችን አሉ። ለቤተክርስቲያን አንድነትና ጥንካሬም ወሳኝ ፍቱን የሆኑ ቀኖናዎችም በሲኖዶስ ባይሻሩም በተግባር ተዘንግተዋል። ጥቂቱን ለመጥቀስ ያህል የተክሊል ጋብቻ እንኳ በሕዝብ ፊት በሰንበት ወይም በበዓል አስቀድሞ እንዲገመገምና ሕዝቡ «ተክሊል አይገባቸውም» ብሎ እንዲበይን መብት የተሰጠበት ቀኖና ተዘንግቶ ጳጳሳትና ፓትርያርክን ሳይቀር በጓዳ መምረጥና የሚሾሙበትን ሀገረስብከት በውል የማያውቁ መልእክተኞች መሆናቸው፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት የሚሾሙበት ቅድመ ሁኔታ /ከራሴ ጭምር/፣ በጳጳሳት መሾም የሚገባቸውና የተዘነጉት መሪጌቶች /በቅዳሴ የሚዘከሩት መዘምራን/፣ ቅዱሳት መጻሕፍት፣ /የዘመኑ ቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጨመር አለበት/ ንዋያተ ቅድሳት፣ መባዎችና መሥዋዕቶች የሚያዘጋጃቸውና የሚያሰራጫቸው ሰው፣ የሚመረቱበት ቦታ ሃይማኖታዊ ይዘት፣ ቀኖናን የሚጥሱ ትእዛዛትን የሚያፈርሱ ካህናትና ምእመናን ላይ የሚበየንበት አማራጭ መጥፋት፣ የሃይማኖት ትምህርት ወይም ቀኖና ልዩነት ያለው ሰው ሀሳቡን አቅርቦ ለመከራከርና ለማመን ወይም ለማሳመን መድረክና ዳኛ አለመኖር ብሎም ችግሩ ቢታወቅ እንኳ ተመሳስሎ ለመኖርና የራስን መርዝ ባላቸው ዕድል ለመርጨት አለመቸገር ወዘተ።


ከዚህ አንጻር ስናይ ፓትርያርክ ጳውሎስ ያስፋፉትና የጀመሩት የጥፋት መንገድ ብዙ ቢሆንም የተወሰኑት ከግራኝ አሕመድ ሌሎች ጥቂቶቹም ከንጉሠ ነገሥት ምኒሊክ ዘመን በኋላ የተከሠቱ ናቸው። ስለዚህ የራሳችን ሲኖዶስ ባገኘንበት ዘመን አሁን ሁሉንም ማስተካከል ስለምንችል የሲኖዶሱን አንድነትና አቅም የሚያውኩ ጉዳዮችን እየተጠነቀቅን በመሥራት ለተናጠል ክስተቶች /events/ ስንቸኩል ሊፈጠሩ የሚችሉ ጉዳቶችን መቀነስ አለብን።


አማራጭ መፍትሔ

እኔ ፓትርያርክን ማውረድ ወይም ሥልጣናቸውን ለመነካካት /እንደ ሥራአስፈጻሚው/ ቀኖና ወይም ዶግማ ማጣቀስ ከወቅቱ አለመመቸት አንጻር ጥቅሙ ብዙ አይመስለኝም። ከጊዜያዊ ድል አያልፍም ባይ ነኝ፤ በተለይ የሰሞኑ አካሄዳቸው «ያውግዙኝና እኔም አውግዤያቸው የራሴን ድርሻ እካፈላለሁ» ለማለት የፈለጉ ነው የመሰለኝ። ከዚህ አንጻር መፍትሔዎች በሚገባ መጠናት አለባቸው እላለሁ። በአማራጭነት ከሚቀጥሉት ሁለት መፍትሔዎች አንዱ ወይም ሁለቱ በጋራ ቢወሰዱ የተሻለ ነው ብዬ አምናለሁ። የውሳኔ ተግባራዊነት ላይ ተስፋችን ከጸና ሐውልቱን ለማፍረስ ማን ከለከለን? የሲኖዶስን ውሳኔ ተከትሎ ሃይማኖትን መጠበቅና ማስጠበቅ የሁላችን ሥራ አይደል? አታፍርሱ ብሎ ሊቃወመን የሚችል ሕጋዊ አካል አለ? ያው ስለፈራን ወይም ዘላቂ ስለማይሆን እንጂ።


መፍትሔ ፩ ሥራቸውን በየደቂቃው መከታተልና መቆጣጠር

ይኼ አማራጭ እጅግ አድካሚና ለቤተክርስቲያን መልካም ስም ሲባል ብቻ የሚደረግ እንጂ ቅድሚያ አይወስድም። በአንጻሩ ግን ግልጽ ሕግጋትና ቀኖና ላላት ቤተክርስቲያን ልበ ሰፊና ጥበበኛ የእሳቸውንም ተንኮል ቀድሞ የሚረዳ ሰው አብሮ ከሠራ የእሳቸውን ቁማር የሚበልጥ ጥበብ መጠቀም /በእሳቸው ላይ ቁማር መጫወት/ ሊባል የሚችል ነው። ይህም በዋናነት በቋሚ ሲኖዶስ፣ በሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ፣ በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና በየሀገረ ስብከቱና የጠቅላይ ቤተክህነት አመራሮች ሊፈጸም የሚችል ሲሆን የሚራመዱበት እግራቸው የሚሰዱት እጃቸው ከሚገባው አልፎ በሥልጣናቸው ሥር ባሉ ጉዳዮች እንዳይደርሱ ለማድረግ ሳይሰለቹ መታገል ነው። እርግጡ ነገር ይኼ በመንፈሳዊው ዐውድ ብዙ የሚያስደስት ተግባር አይደለም፤ ተማምኖና አምኖ ለበረከት መሽቀዳደም ሲገባ አንዱ አጥፊ ሌላው ጠበቃ ሆኖ መሳደድ ያበሳጫል። በምን ዓይነት መድኃኒት በምን ያህል ወጪ የየዕለት ሕይወታቸውን እንደሚቀጥሉና እስከመቼ እንደሚያዛልቃቸው ባይገባኝም ቀናቸውን በሚያሳጥር ጋንግሪንና የጭንቅላት ዕጢ ከሌሎች ተደራራቢ በሽታዎች ጋር ለሚሰቃዩ ጳውሎስ እያንዳንዷን ደቂቃን በሰጠናቸው ቁጥር ለእኛ ባንረዳውም በፈጣሪም በሰውም የሚፈለግ ንስሐ ገብተው ወደልባቸው ተመልሰው ቢሞቱ ስለሚሻል ለአንድ ሰው ሲባል የሚከፈል ከባድ መሥዋዕትነት ነው። ያም ሆኖ ከታች በዘረዘርኳቸው ምክንያቶች ከሌላ ወገን የተላኩ የትሮይ ፈረስ ስለሚመስሉ ንስሐ ቢገቡ እንኳ የላካቸው አካል ደቂቃም ሕይወት አይሰጣቸውምና ይህ አማራጭ ጥቅሙ እምብዛም ሊሆን ይችላል።


መፍትሔ ፪ የፓትርያርኩን ጥፋቶች ለዳኝነት ማቅረብ

በ፲፱፻፺፯ ምርጫ ወቅት ይመስለኛል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተከሰው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ታይቶ ነበረ። በተደጋጋሚ በፕሮቴስታንትነት የተከሰሰው አሰግድ ሣህሉም ለግል ጥቅሙ ብፁዕ አቡነ ጢሞቲዎስን ፍርድ ቤት አቁሟቸዋል። ወንጀሎች በያይነቱ በሚጠቀሱባቸውና ከበቂ በላይ መረጃዎች በየአደባባዩ ሊቀርብባቸው በሚቻልባቸው ፓትርያርክ ላይ ለቤተክርስቲያን ሰላምና ጥቅም ሲባል ብቻ ክስ መመሥረትና በፍርድ ቤት እንዲታይ ማድረግ ለምን አይሞከርም? አዋጭ ይመስለኛል፤ አፈጻጸሙ ምንም ይሁን ምን። ይልቁንም ዝም በመባላቸው የተዘፈቁበትን ተራና ዘርፈ ብዙ የውንብድና ሥራ ቢያንስ ለማስቆም ከተሳካም ለቤተክርስቲያን ጥቅም የሚሆን ውጤት ሊያመጣ ይችላል። ምእመናኑን በየጊዜው የሚያስበረግገውና ጥርሱን ነክሶባቸው ከቤ/ክ ያራቀው አልጠግብ ባይ ዝርፊያቸው በምሁራንም ሆነ በሊቃውንት በግልጥ የታወቀ ነው። ተሿሚዎቻቸውም የሚያስፈጽሙት ይህንኑ አጠናክረው መሆኑን የአዲስ አበባና የታላላቅ አድባራትና ገዳማት ምእመናን የሚያውቁት የአደባባይ ምስጢር ነው። ይህንም ወንጀል ማንኛውም ግለሰብና ቡድን ለሕግ ሊያቀርበው፣ መረጃውም ከየጓዳው ሊገኝ፣ የክስ ሂደቱም በፌደራል ፍርድ ቤቶች በቀጥታ ሊታይ የሚችል ምንም ቅድመሁኔታ የማይፈልግ ነው። ውሳኔውን ለዳኞቹ እንተወውና ፓትርያርኩ በሥልጣን ዘመናቸው ከሚከሰሱባቸው ጉዳዮች ጥቂቶቹን ለማንሳት እንሞክር።

ከባድ ሙስናዎች፣ ሥልጣንን አላግባብ መጠቀም፣ ከባድ የእምነት ማጉደል፣ በኃላፊነት ቸልተኛነት ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ። በዝምድናና አላግባብ ከሚሰጡ ቅጥር፣ ዝውውር፣ ዕድገት፣ ሹመትና ጥቅማ ጥቅሞች ጀምሮ ከመሥሪያ ቤቱ ዕቅድና ዓላማ ውጪ ለግላቸው ጥቅም የሚባክነው ግዙፍ መጠን ያለው የገንዘብ ዝርፊያ፣ ተያይዞም እሳቸው አላግባብ በሾሟቸው ሰዎች የሚፈጸሙ ሙስናዎች እሳቸውን ከሚያስጠይቁ ሙስናዎች ጥቂቶቹ ናቸው። ሥልጣንን አላግባብ በመጠቀም የመሥሪያ ቤቱን ጥቅም ከመጉዳት ጀምሮ በፓትርያርክነት ስም የበላያቸውንና የበታቻቸውን የሲኖዶሱንና የወከላቸውን መሪዎች ሥልጣን በመጋፋት የተሠሩ ሥራዎች ብዙ ናቸው። በፓትርያርክነት ሥልጣናቸው ሊያስጠብቁት የሚገባውን የቤተክርስቲያን /የመሥሪያ ቤታቸውን/ ጥቅምና ዝና የቤተክርስቲያን ወገን ወይም ወዳጅ ያልሆኑ ሲጠቀሙበት ዝም ማለትና ይህም በብዙ ምክረ ሀሳብ ሲቀርብላቸው እንዲዘነጋ ማድረግ አንዳንዴም መተባበር ለታመኑበትና ለተሾሙበት ሥልጣን ያልታመኑ እምነት አጉዳይ የሚያደርጋቸው ይመስለኛል። አሜን ብለው በተቀበሉት ኃላፊነት ላይ ተቀምጠው የማይገባውን ከመሥራት ባሻገር ሊሠሩት የሚገባውን ባለመሥራትም ምክንያት የተፈጠረ ጉዳት ካለ በቸልተኝነትና ኃላፊነትን ባለመወጣት መጠየቃቸው እውነታውን ሊያስገኝ የሚችል ዕድል አለው። ሌሎቹን እንርሳቸውና የሚከብዱትን የቸልተኝነት ጉዳቶች እንመልከት። ቤተክርስቲያንን በግልጥ ቋንቋ ሲዘልፉ የሚታዩ ግለሰቦችና መንግሥታት በዝምታ መታለፍ አልነበረባቸውም። አቶ ተፈራ ዋልዋ እንዳሉት ቤተክርስቲያን «የአማራና የጉራጌ ትምክህተኞች ዋሻ» ነች? የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው ቤተክርስቲያን የዓለም /የአሜሪካ ስጋትና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ እኩልነት አደናቃፊ ልትባል ይችላል? ፒኤችዲያቸው ለዚህ መልስ አጣ? ብፁዐን አባቶች ያረፉበት የማያሳምን አሟሟት ሲደጋገም የሀገሪቱ ሕግ ምን ነበረ የሚለው? ለምሳሌ በአደባባይ እየታየ መኪና ገጭቶ የገደለውን ሰው እንኳ የሞተበትን ምክንያት በሕክምና ተቋም እንዲረጋገጥ ማድረግ በሚቻልበት ዘመን የአባቶች አሟሟት አለመመርመሩ አሳሳቢ ነው። ታመው በማያውቁት የጉበት በሽታ ለወሬ በማይመች ምክንያት ጉበታቸው አልቋል ተብለው ሳይመረመሩ የተቀበሩት አቡነ መልከጸዴቅ፣ ቅዳሴ እንዲገቡ ለመጋበዝና ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ውጪ ሀገር ለመጓዝ ብቁ የነበሩት ከሰዓት ከቅዳሴ ወጥተው ለሠርክ ጸሎት ሳይደርሱ ሞት ያጣደፋቸው አቡነ ይስሐቅ ፣ በሀኪሞች አስተያየት ቀላል የሚባለውና በተሳካ ሁኔታ የተከናወነው የሀሞት ጠጠር ቀዶ ጥገና አብቅቶ ከኦፕሬሽን ክፍል ከወጡ በኋላ ከሰመመን ሳይነቁ ያሸለቡት አቡነ ሚካኤል፣ በጤንነትና በሰላም መጽሐፍ ቅዱስ ለመተርጎም ከጉባኤ ቤታቸው መጥተው ባልታወቀ ምክንያት የቀሩት እነ ሊቀ ሊቃውንት መንክር፣ ማታ 11፡00 ሰዓት ድረስ ጤናማና ሰላም የነበሩት አዲሱ የቤተክህነት አደረጃጀት የአስተዳደር መምሪያው ተሿሚ ጠዋት እንዲቀብሯቸው ለቤተክህነቱ መርዶ ሲነገር በድምፅ አልባ ለቅሶ የተሸኙት አቶ ነገደ ስዩም ፣ ያው ፍንጩ ወደራሳቸው ጠቁሟል ተባለ እንጂ የ፳፻፩ዱ የአባቶች ቤት ሰበራና የአባቶች መደብደብ ቤተክርስቲያንን ወክለው ያሉ መሪዎች እንደመሆናቸው አሟሟታቸው ሳይጣራ መቅረቱ ከፍተኛ ቸልተኝነት ነው። ይህም ሁሉ ሲሆን ፓትርያርኩ የአንዳቸውን ሬሳ እንኳ ወደ ምኒሊክ ቢያስልኩ ምናልባት የቤተክርስቲያን ሥራ ሲሠሩ የጠላቸው አጥቅቷቸው ከሆነ ይታወቅና ለሌሎችም አባቶች ለራሳቸውም ጭምር ደህንነት የሚያግዝ መረጃ ይገኝ ነበረ። አሳማኝ ምክንያት ሊቀርብ የማይችልበት የ፲፮ ጳጳሳት በመኪና አደጋ ማለቅ፣ የቤተክርስቲያን መሪዋና ቸር ጠባቂዋ ለሆነ ፓትርያርክ ዝም ብሎ ለጥቂቶቹ ሐውልት በመመረቅና ሂዶ በመቅበር መታለፉ ከቸልተኝነትም በላይ ነው ብዬ አምናለሁ። እነዚህ ሁሉ ሲደማመሩ ለቤተክርስቲያንና መሪዎቿ በቂ ጠበቃ ባለመሆን ኃላፊነታቸውን ላለመወጣት ቸልተኛ ነበሩ ብሎ በሕግ ፊት እንዲዳኝ ማድረግ ቀጣይ ጥፋትን ይታደግ ይሆናል። ጥፋተኝነታቸው ከተረጋገጠም ከቀኖናና ዘዴ ምርምር የቀለለ መፍትሔና ሥልጣናቸውን ወዲያው /by default/ ሊያሳጣ የሚችል ይሆናል።



ሲጠቃለል፡



እንግዲህ አንዱም አማራጭ በአንዴ የሚጠናቀቅ ስላልሆነ ሁለቱንም አማራጭ እያስኬዱ የቤተክርስቲያንን ጉዳት መቀነስና የበለጠ የችግሮቹ ዓይነት ግልጥ እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል። በሂደትም የራሳቸውን መጨረሻ ሳያውቁ የሚላላኳቸውንና የሚራዷቸውን ሰዎችም መቀነስና ለቤተክርስቲያን የሚያግዙ ማድረግ ይቻል ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

ሁላችንም የምንስማማው ግን ፓትርያርክ ጳውሎስ በቤተክርስቲያን ውስጥ የዘሩት እሾኽና አሜከላ በአጭር ጊዜ ተነቅሎ የማይጠናቀቅ፣ ነገር ግን እሾኽነቱን ከመኮነን ጀምሮ ለመንቀስና ለማረም ሰፊና አሠራር/ሀሳብ ላይ ያተኮረ /idea & system/ ሥራ መጠናከር እንዳለበት ነው። የየዕለት ጉዳዮችን /events/ ትኩረት ስንሰጥላቸውም ደስታቸው ወደር የለውም፤ ዓላማቸውን ከበጣም መጥፎ በመጥፎው እያጽናኑና ያልተተኮረበትን እያስፋፉ ዓላማቸውን /የትሮይ ፈረስነቱን ወይም የኑፋቄውን ካልሆነም የተራና ሌጣ ውንብድናውን/ ተግባር በበለጠ ዐቅም ሊሠሩት ስለሚችሉ። ምነው ኮራ ብለን የቤተክርስቲያንን በዳይ ለመፋረድ ሕጋዊ አማራጭን ብንጠቀም፤ ጥላቻችንን ወይም ቁጣችንን ለመግለጥ ድንጋይና የገማ ዕንቁላል መወርወር ወይም ይሁዳ ብሎ ብቻ መሳደብ የፈሪ ዱላ እንጂ እውነተኛ ፍርድ ፈላጊ አያደርገንም ብዬ አምናለሁ። ይቆየን።

‹‹ከረባት ያሰረ መነኩሴ ሆነን ነው የኖርነው›› ቄስ በሪሁን


(ነጋድረስ  ጋዜጣ ዛሬ አርብ ጥቅምት 10 2004 ዓ.ም ያስነበበን ዜና)

ቄስ በሪሁን እባላለሁ ተወልጄ ያደኩት ወሎ ክፍለ ሀገር ነው ፡፡ እንደ ማንኛውም ወጣት ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያ ነው ያገለገልኩት ፤ መካነ እየሱስ አካባቢዬ ስለነበረች እሷ የወንጌል ሙቀት ሰጠችኝ፡፡ በደሴ ቄስ ሆኜ አገልግያለሁ ፤ የማዕከላዊ ሲኖዶስ የወንጌል መምሪያ ዳይሬክተር ሆኜ አገልግያለሁ፤ የማዕከላዊ ሰሜን ኢትዮጵያ ሲኖዶስ ጳጳስ  ሆኜ መርቻለሁ ፤ አሁን የስነ መለኮት ትምህርት ለመማር አሜሪካ እገኛለሁ … እያለ ስለ ራሱ ብዙ ይነግረናል፡፡ አስተውሉ ይህን ሁሉ ሲሰራ የነበረው የመካነ እየሱስ አማኝ የሆነ አንድ ግለሰብ ነው፡፡



ጥያቄ :- እርስዎ በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አድገው ከዚያ በመካነ እየሱስ ጌታን እንዳገኙ ነው የነገሩኝ?
በሪሁን ሲመልስ፡- የለም ሙቀት ነው ያገኝሁት

ጥያቄ :- ማለት ? ጥቄው ይቀጥላል
በሪሁን ሲመልስ:- እየሱስ ክርቶስ ስለ ሐጥያቴ በመስቀል ላይ እንደሞተ ግልጽ ሆኖልኝ በአማርኛ የተማርኩት ለማለት ነው(ቤተክርስትያን በጀርመንኛ ነው እንዴ የምታስተምረው?)

ጥያቄ ፡- ቀደም ሲል የነበሩበት ቤተክርስትያን ሙቀት አልነበረም ?
በሪሁን ሲመልስ:-ተው ተው የሚያቀራርብ ነገር እንነጋገር እኔ ለእናት ቤተክርስትያን ጥሩ አክብሮት አለኝ

አሁንም ያሉት የተሀድሶና መናፍቃን አካሄድ እንደዚ እንደምታዩት ነው ፡፡ ሲጀመር ማርያም ታማልዳለች አታማልድም ብለው የሞኝ መናፍቅ አካሄድ አያነሱም ፡፡ አሁን መስሎ ገብቶ ዲያቆን ሆነው ቀድሰው ፤ ቄስ ሆነው አሳልመው ፤ የእኛን የመምህራን ልብስ ለብሰው በአውደ ምህረታችን ላይ አስተምረው ፤ ‹‹የለበሱት የኛ ውስጣቸው የነኛ››  መስለው ነው እየተገዳደሩን  ያሉት


እስቲ ሙሉውን እርስዎ ያንብቡት ብለናል
To Read by Pdf format

Read by image format Click Read more

ተኩላዎቹ የአመፅ ጥሪ አካሔዱ


በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት ከሆኑት ወዳጆቼ ያገኘሁት መረጃ ቀንደኞቹ የተሐድሶ አቀንቃኞች በጋሻው አሰግድ እና ግብርአበሮቹ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መጀመሩን አስመልክቶ በሚደረገው የብጹአን አባቶች የጸሎት ስነስርዐት ላይ አመፅ ሊወጡ ነው፡፡ የኮሌጁ መደበኛ ተማሪዎች የደንብ ልብስ የሆነውን ጥቁር ቀሚስ በመልበስ እንደሚደረግም ሲገለጽ የአመፅ ሰልፉን አሰግድ እያስተባበረና “ለሚመስሏችሁ አገልጋዮች ብቻ ተናገሩ” በማለት ለአንዳንድ አገልጋዮች መናገሩም ተሰምቷል፡፡ ነገ 10፡00 ፊደል ካፌ እንገናኝ የሚለው ጥሪ የካፌው ባለቤት የሆነውን አቶ ኤፍሬም ኤርሚያስ በአዲስ አበባ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ምዕመናን ዓይን በጥርጣሬ እንዲታይ አድርጎታል፡፡ ጥቅምት 12 ቀን 2004 ዓ.ም. ቀን 10፡00 የተጠራው ስብሰባ እውን ከሆነ ካፌው አካባቢ አጓጉል ነገር እንደሚፈጠር ወጣቶቹ እየዛቱ ሲሆን በተያያዘ ዜና የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ህብረት በተመሳሳይ ሁኔታ የተሐድሶን እንቅስቃሴ አስመልቶ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲያሳልፍ በሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠይቁ ይጠበቃል፡፡ የነበጋሻው፣ አሰግድ እና ግብረ አበሮቹ በአመፅ ሰልፉ የሚያነሱት ሐሳብ መናፍቅ እየተባልን አናስተምርም፣ ስማችን ጠፍቷል ቅዱስ ሲኖዶስ ስማችንን ያድስልን የሚል እንደሆነም ታውቋል፡፡ ቤተክርስቲያንን የማደስ ስውር ተልዕኮአቸው ያልተሳካላቸው በጋሻው እና አሰግድ ስማቸውን ለማደስ መነሳታቸው ምን ያህል በተሐድሶ ሱሰኞች መሆናቸውን የሚያሳይ መሆኑን አንዳንድ ጥሪው የደረሳቸው የኮሌጁ ደቀመዛሙርት ገልጸዋል፡፡

Posted on  by ገብር ኄር
በማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com)