አንድ አድርገን ጥቅምት 10
2007 ዓ.ም
ቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያንን የመሩ ከአጸደ ሥጋ ዓለም በሞት ተለይተው በአጸደ ነፍስ የሚገኙ ቅዱሳን ፓትርያኮችና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ ጥቅምት
9 ቀን 2007 ዓ.ም በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ጸሎተ ፍትሐት ተደርጎላቸዋል፡፡ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ፣ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ለብፁዕ
ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እንዲሁም ለብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳትን በጊዜው ጸሎተ ፍትሐት ተደርጎላቸዋል፡፡
ያለፉትን አባቶቻችንን እንዲህ ለማስታወስ ሞከርን፡፡
1.
ቀዳማዊ አቡነ
ባስልዮስ (፲፰፻፹፬ዓ/ም (ሚዳ ሚካኤል) - ፲፱፻፷፫ ዓ/ም (አዲስ አበባ)) የመጀመሪያው
ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና
የመጀመሪያው ፓትርያርክ ነበሩ።የመናገሻ አምባ ማርያምን ገዳም እያስተዳደሩ ሳሉ፤ ከዚህ ሥልጣናቸው በተጨማሪ የአዲስ አበባ መንበረ
መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መምህርነት በየካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ/ም ተሰጣቸው። ከዚያም ቀጥሎ መጋቢት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፭ዓ/ም በኢየሩሳሌም ያሉ የኢትዮጵያን ገዳማት በመንፈሳዊ መሪነት አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመው ለሁለት ዓመታት ካገለገሉ
በኋላ ወደአገራቸው ተመለሱ።