Friday, October 3, 2014

ስምንት ጊዜ ባንዲራዋን የቀየረች ሀገር “ኢትዮጵያ”

(አንድ አድርገን መስከረም 24 2006 ዓ.ም)፡-

ኢትዮጵያ ዘመን ተሻጋሪ የሰንደቅ አላማ ታሪክ ካላቸው ሃገራት መካከል አንዷ ናት  ፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እስከ 1890ዎቹ ሁለተኛ አጋማሽ ድረስ በቀለማትም አንድ ወጥ አልነበረም ፤ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ  ቀለማት ያሉት ሰንደቅ አላማ ቀለማት ወጥነት ባለው በተያያዙ አራትማእዘናት በጥቅም ላይ የዋሉት 1890ዎቹ መጨረሻ ነው ፤ በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሰንደቅ አላማ ልዩትርጓሜና ስርፀት የተሰጠው 1898 እንደሆነ ይነገራል ፤ ቢጫ የብርሃን፣ ቀይ የመስዋዕትነትና አረንጓዴ የተስፋምልክት ተደርጐ ይወሰዳል፡፡   


ከዚህ በኋላ ሰንደቅ  አላማችን  አንድ  ጊዜ መንፈሳዊ ሌላ ጊዜ ፖለቲካዊ ትርጓሜ እየታከለበት ዘመን ተሻግሯል ፤  እኛ ኢትዮጵያውያን በሰንደቅ አላማችን ስም በጐም ሆነ መጥፎ ተግባራት በተፈፀሙባቸው ዘመነ መንግስታት ጭምር ለሰንደቅ አላማችን ያለን ፍቅርና ክብር እጅግ ጥልቅ ነው ፤ ጥንታውያንጀግኖች ወላጆቻችን ሰንደቅ አላማችንን ይዘው አስደናቂ ትግልና ውጊያ በማካሄድ ከባዕዳውያን ቀጥተኛ ተፅዕኖ ነፃ የሆነች ሃገር አስረክበውናል ፤ በአንዲት ባንዲራቸው ጥላ ስር በመሆን ወራሪውን ሃይል በእግዚአብሔር ረዳትነትና እና በታማኝ አርበኞች ጀግንነት ከቀኝ ግዛት ነጻ የሆነች ሀገር አቆይተውልናል ፡፡

ኢትዮጵያውያን ለአያሌ ዘመናት ብሔራዊ ክብራችንን ባዋረደና እንደ ህዝብ አንገታችንን ባስደፋን አስከፊ የድህነትማቅ ውስጥ ኖረናል ፡፡ አሁን ሰንደቅ አላማችን የጭቆናም የጭፍጨፋ  አርማ አይደለም።  የሰንደቅ አላማችን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት እንደ ዱሮው ሁሉ የልምላሜ የተስፋና ለነፃነት የሚከፈል መስዋዕትነት ምልክቶቻችን ናቸው ። 

“አፍ ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም” እንደሚባለው ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አውቀው ይሁን ሳያውቁ “ባንዲራ ጨርቅ ነው” በማለት በአደባባይ ሲናገሩ ጆሯን ሰምቷል ፤ በዚህ ንግግራቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን የባዲራው ነገር የገባቸው እጅጉን ውስጣቸው ተጎድቷል ፤ እድሜ ልካቸውን ለሀገር ብለው ከጠላት ጋር ጦር ሜዳ ለተዋደቁ አባቶቻችን ይህ አባባል አጥንት ዘልቆ የሚሰማ ስሜት ፈጥሮባቸው አልፏል ፤ አቶ መለስ ይህን በተናገሩ በሳምንታት ውስጥ አፋቸውን ሞልተው “ይቅርታ መናገር አልነበረብኝም ተሳስቻለሁ” የማይሉ ሰው ስለሆኑ ምን ማለት እንደፈለጉ በሌላ አባባል ንግግራቸውን መስመሩን ማቀየር ችለው ነበር ፡፡

የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ቀን በዓል መከበር የጀመረው በአዲሱ ሚሊኒየም መጀመሪያ ላይ ነው ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀው የሰንደቅ አላማ አዋጅ በዓሉ በየአመቱ በመስከረም ሁለተኛ ሳምንት ሰኞ እንዲከበር ይደነግጋል ፤ አዋጁ መስከረምን የመረጠው ወሩ ለሃገራችን የዘመን መለወጫና አዲስ የተስፋ የስራና የለውጥ መንፈስ የሚፈጠርበት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ይመስላል ፤  


የሰንደቅ አላማችን አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ህብረ-ቀለማት ያለፈውም ሆነ የመጪው ጊዜ በልማት የመለወጥ ፣ በነፃነትና በተስፋ የመኖር ራዕያችን አሻራዎች ናቸው፡፡ የአግድም ቀለሞች አረንዴ- ስራ፣ ልምላሜና እድገት  ፤ቢጫ -የተስፋ፣የፍትህና የእኩልነት ቀይ- ለነጻነትና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመስዋዕትነትና የጀግንነት ምልክት ነው፡፡ ይህን የቀለም ህብረት ኢትዮጵያ መጠቀም የጀመረችው ከአድዋ ጦርነት በፊት መሆኑን ታሪክ ይናገራል ፤ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ይህን የቀለም ህብረት መጠቀም የጀመሩት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ ይታወቃል ፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነጻነትና የቅኝ አለመገዛት ተምሳሌት የሆነች ሀገር በመሆኗ በርካቶች ይህን ለመጠቀማቸው ቀዳሚ ምክንያን  መሆኑን የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ፡፡



በተለያዩ ጊዜያት በሃገራችን የነበሩ የሰንደቅ አላማዎች
እንደሚከተለው እንመልከት 









ይህ ኮከብ ምንድነው?
አሁን የኢፌድሪ መንግስት የሚጠቀምበት ባንዲራ ላይ መሀሉ ላይ የተቀመጠው ኮከብ ፤ ቀለምና መግለጫ የተለያዩ አመለካከቶች በተለያዩ የህብረተሰቦች ዘንድ ሲንጸባረቅ ይታያል ፡፡ ኮከቡንና ፤ የሚያቋርጠው መስመር ምን ማለት እንደሆነ በተለያዩ አመለካከቶች ይገለጻል፤ መንግስት የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነትን የሚያንጸባርቅ መሆኑን ሲናገር ሌሎች ደግሞ ፍጹም የሆነ ስህተት ነው በማለት አስተያየታቸውን በመስጠት ኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ ያለውን ኮከብ Satanism ጋር ግንኙነት እንዳለው ያትታሉ፡፡
 pentagram is often used to represent Satanism.

Satanism is a broad term referring to a group of Western religions comprising diverse ideological and philosophical beliefs. Their shared features include symbolic association with, or admiration for the character of, Satan, or similar rebellious,promethean, and, in their view, liberating figures.

Satanist groups that appeared after the 1960s are widely diverse, but two major trends are Theistic Satanism and Atheistic Satanism. Theistic Satanists venerate Satan as a supernatural deity. In contrast, Atheistic Satanists[2] consider themselvesatheistsagnosticsignostics or apatheists and regard Satan as merely symbolic of certain human traits. This categorization of Satanism (which could be categorized in other ways, for example "Traditional" versus "Modern"), is not necessarily adopted by Satanists themselves, who usually do not specify which type of Satanism they adhere to.[citation needed] Some Satanists believe in a god in the sense of a Prime Mover but, like Atheistic Satanists, do not worship it, due to the deist belief that a god plays no part in mortal lives.


በዚህ ላይ እርስዎ ምን ይላሉ? 
እውን ይህ ኮከብ ትክክለኛው ትርጓሜ መንግስት እንደነገረን ነውን ?


LION OF JUDAH IN ETHIOPIA

Ethiopia's traditions, recorded and elaborated in a 5th century treatise, the "Kebre Negest", assert descent from a retinue of Israelites who returned with Makeda, the Queen of Sheba from her visit to King Solomon in Jerusalem, by whom she had conceived the Solomonic dynasty's founder, Menelik I. As Solomon was of the tribe of Judah, his son Menelik I would continue the line, which according to Ethiopian tradition was passed directly down from King to King until Emperor Haile Selassie was deposed in 1974. Both Christian and Jewish Ethiopian tradition has it that there were also immigrants of the Tribes of Dan and Judah that accompanied Makeda (Queen of Sheba) back from her visit to Solomon; hence the Ge'ez motto Mo`a 'Anbessa Ze'imnegede Yihuda ("The Lion of the Tribe of Judah has conquered"), included among the titles of the Emperor (King of Kings) throughout the Solomonic Dynasty. It is unknown whether John of Patmos was directly aware of this hereditary title when he penned it into the text of the prophecy. The Lion of Judah motif figured prominently on the old imperial flag, currency, stamps, etc. and may still be seen gracing the terrace of the capital as a national symbol. After the collapse of theCommunist Derg in 1990 and the increase of Western-style political freedoms, a minor political party bearing the name Mo'a Anbessa made its appearance.

source :- http://en.wikipedia.org/wiki/Lion_of_Judah

1 comment:

  1. Why are you lying look at the difference between the flag and the pentagram, the flag has the shape of a star and the pentagram is a star upside down.

    ReplyDelete