Sunday, October 19, 2014

‹‹አባ ማትያስ አላበደም ፤ መልዕክቱን እያስተላለፈ ነው›› አቡነ ማትያስ ለጉባኤው የተናገሩት



  • እግዚአብሔር ላበዱት አይምሯቸውን ይመልስልን ፤ ላላበዱትና ለማበድ ለተዘጋጁት አይምሯቸውን ይጠብቅልን፡፡

 አንድ አድርገን ጥቅምት 9 2007 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ኻያ አንድ አመታት በርዕሰ አበውነት ‹ሲገዙ› የነበሩትን የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ሞትን አስከትሎ ስድስተኛውን ዘመነ ፕትርክና  የምደባ ያህል  የተረከቡት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀናኢ ሊቃውንትና ምእመናን ለዘመናት ሲያንገሸግሽ የቆየውን አድሏዊ አሠራር ፤ ጎጠኝነትና ሙስና በመጠኑም ቢኾን ይፈታሉ የሚል ግምት ተሰጥቷቸው ነበር፡፡



በበዓለ ሲመታቸው ወቅት ንግግር ሲያደርጉ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሊቃውንትና ምእመናን ብሶትና የዕለት ከዕለት ምሬት የተሰማቸው  በሚመስል ሁኔታ  ትኩረት ሰጥተው ከሚንቀሳቀሱባቸው  የሥራ ዘርፎች  መካከል ፤ በዋነኝነት ሙስናንና ጎጠኝነትን መዋጋት እንደሚሆን መጥቀሳቸው ይታወሳል፡፡


አፍዓዊ መግለጫቸው ተከትሎም በቤተክህነቱ መዋቅራዊ ለውጥ ተደርጎ የአገልግሎት አሰጣጡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዋንኛ ተልእኮ ማስፈጸም የሚያስችል ይሆናል የሚል ግምት በብዙዎች  ዘንድ ተወስዶ ነበር፡፡ ቅዱስነታቸውም  በአንደኛ ዓመታቸው በዓለ ሲመት አከባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ ‹‹የዛሬ ዓመት የተናገርኳቸው ቃላት ኹሉ እንደጸኑ ናቸው ፤ አልተበረዙም ፤ አልተከለሱም ፤ እንዲያውም ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፤ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ከምእመናን ጋር በመሆን አጠነክራቸዋለሁ›› ከማለት አልፈው ለተቋማዊ ለውጡ በቁርጠኝነት የተነሱ በሚመስል ሁኔታ  በለውጡ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች  ላይ የተለያዩ የጥናት ቡድኖች እንዲቋቋሚ በጎ ፍቃዳቸውን ያሳዩ መስለው ‹ተወኑ› ፡፡ በአንዶቻችን ዘንድ አቡኑ ጉዱ ካሳን የሆኑ እስኪመስለን ድረስ የለውጥ አባት ተደርገው ተወስደውም ነበር፡፡

በኋላ ግን ኾነው የተገኙት መስለው የተናገሩትን ሳይሆኑ ከቅድስት ሀገር እየሩሳሌም እስከ አሜሪካ ኖረውታል የሚባለውን ምንነታቸውንና ማንነታቸውን ነው፡፡ መልካም አስተዳደር በማስፈን ኾነ ጎጠኝነትን ኾነ ጥቅመኝነትን መሠረት ያደረጉ አድሏዊ አሠራሮችን በማስቀረት ፤ ሙስናን በመዋጋትም ኾነ በቤተ ክህነቱ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሊቃውንቱንና  የምእመኑን ቅሬታ የሚፈቱና አመኔታቸውን ያተረፉ ኾነውና በቅተው አልተገኙም፡፡

ይባስ ብለው ሞያዊ እውቀታቸውን ለቤተ ክርስቲያን እድገትና ደህንነት አስራት አድርገው ያቀረቡ ሙያተኞችን አግልለው ድጋፍ ነስተው ፤ ከቤተ ክርስቲያን ጥቅም ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ከሚያስቀድሙና  ለቤተ ክርስቲያኒቱ እድገትና ለውጥ የዘመናት እንቅፋቶች የሆኑ አማሳኞችና አድር-ባር ፖለቲከኞች ጋር ማኅበርተኝነት መስርተው ተገኙ ፤ ይባስም ብለው ወጣኒያኑን ‹‹ቀኝ ገዥ›› ብለው አረፉት፡፡ ርእሰ አበውነታቸውን ዘንግተው የስርዓቱ ጭቃ ሹምና ምስለኔ በመሆን የማይገባቸውን ሥልጣን ከሚገባቸው ነጥቀው  ከያዙት ፤ ድኻውን ካህን ባለፉት 23 ዓመታት ሲበዘብዙ እና ሲያሰቃዩት ከኖሩት ፤ የካህኑን ቤተ-ሰብእ ለዘመናት ከእጅ ወደ አፍ የሠቆቃ ኑሮ እንዲገፋ ካደረጉት ፤ ሊቃውንቱን በተዋራጅነት ፤ በድህነት ፤ በእርዛትና በበሽታ እየተሰቃዩ እና እየተጎሳቀሉ አስከፊ ኑሮ እንዲያሳልፉ ያደረገውን አማሳኝና አድር ባይ  ቡድን ጠባቂ ሆነው አረፉት፡፡


ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ 33ኛው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በስብከተ ወንጌል አዳራሽ የተጀመረው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ መልዕክት በማስተላለፍ ነበር፡፡ አቡነ ማትያስ እንደ አሞራ በከበቧቸው ያበዱ መካሪያን ሁለት ድፍን ዓመት በመንበሩ ተክለሃይማኖት ላይ ሳይሞላቸው ቅድስት ቤተክርስቲያን በ‹‹ቅኝ ገዥ›› መያዟን ለጉባኤው አውጀዋል፡፡ እስኪ መልዕክታቸውን ቃል በቃል ለአንባቢያን እንዲህ አቀረብነው፡፡


……..ሁሉንም ማወቅ አለባችሁ ብያለሁ ፤ ስለ ቤተክርስቲያናችን ወቅታዊ ሁኔታ እንድታውቁ እፈልጋለሁ ፤ ወቅታዊም አይደለም ችግሩ የኖረ ነው፡፡ ሰለ ቤተክርስቲያናችን ሁኔታ ያለኝን ለጉባኤው ልገልጽ እፈልጋለሁ፡፡ ይሄ ጉባኤ የሚገኝው በአመት አንድ ጊዜ ነው ፤ ይህ እድል እንዲያመልጠኝ አልፈልግም ፤ ያለውን ችግር ሁሉ ማሰማት አለብኝ ፤ ችግሩ ምንድነው? ትሉኝ እንደሆነ ፤ ችግሩ ቤተ ክርስቲያናችን በቅኝ ግዛት ተይዛለች ፤ ቤተክርስቲያናችን በቅኝ ገዥዎች ተይዛለች  ፤ በቅኝ ግዛት ተይዛለች ይህን ማወቅ መረዳት አለባችሁ ፤ በኋላ አልሰማንም አላየንም እንዳትሉ ፤ ማነው ቀኝ ገዥው? አንድ ሁላችሁም የምታውቁት ማኅበር ነው(……ጭብጨባ…. ) ፤ በምንድነው ወደ ቅኝ ግዛት የተዳረገቸው? ፤ በራስዋ በተሰበሰበ ገንዘብ በቅኝ ግዛት እንድትገዛ አድርገዋታል፡፡ በእውነት ከዚህ የባሰ ክፉ ነገር የለም ፤ እኔ እናገራለሁ ፤ በስራ ላይ መዋል አለማዋሉ የራሳችሁ ጉዳይ ነው፡፡ እኔ ይህን ጉዳይ ከራሴ አወርዳለሁ ፤ ብትወዱም ባትወዱም የቤተ ክርስቲያናችን መብቷ ክብሯ ሀብቷ ሁሉ ተወስዷል ፤ ገንዘቧ ንብረቷ ተወስዷል ፤ ይሄ መመለስ አለበት ፤ ባሳለፍነው ዓመት አንድ ውሳኔ አሳልፏሁ ነበር ፤ ‹‹ማኅበሩ በቁጥጥር ስር ይዋል፤ ቤተ ክርስቲያን ትቆጣጠረው ፤ ወደ ስርዓት ወደ ሕግ ይግባ›› ብሎ ጉባኤው ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ከውሳኔው ውስጥ አንድም አልተደረገም ፤ ምክንያቱም እነሱም ፍቃደኞች አይደሉም ፤ ማንስ ጠይቋቸው?  እና ይህን ጉዳይ ሁላችሁም እንድታውቁት እፈልጋለሁ ፤ እኔ ስራዬ መናገርና ማወጅ ብቻ እንጂ እኔ ብቻዬን የምሰራው ነገር የለም:: ቤተ ክርስቲያናችን ከቅኝ ተገዥነት ትውጣ ፤ ካህናቱ ከችግር ከሰቀቀን ከመከራ ይውጡ ( ….ጭብጨባ….)፡፡ እኔ መልዕክቴን ማስተላለፍ አለብኝ ፤ እኔ ይችን ቤተ ክርስቲያን ለመጠበቅ ነው የተቀመጥኩት ነው ብዬ የማምነው ፤ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁለት ቤተ ክርስቲያን የለም ፤  ፤ እኔ አንዷን ቤተክርስቲያን ብቻ ነው የምመራው ፤ ሌላ ቤተክርስቲያን የለም ፤ ሁለት ቤተ ክርስቲያን ልመራ አይደለም የተቀመጥኩት ፤ ሁለት ቤተክርስቲያን ልመራ አልተቀመጥኩም ፤ አንድ ኦርቶዶክሳዊት ታሪካዊት ቅድስቲቱን ቤተ ክርስቲያን ልመራ ነው የተቀመጥኩት ፤ አሁን ይህን አዋጅ እናንተ በዚህ ሁኔታ እንድታውቁት እና እንድትሰሩበት ነው እየነገርኳችሁ ያለሁት፡፡ አባ ማትያስ አላበደም ፤ መልዕክቱን እያስተላለፈ ነው ፤ ለእናንተ ስለዚህ ይህን መልዕክት በጸጋ ተቀበሉ  ብዬ እማጸናችኋለሁ፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ ችግር ስለሆነ ነው የተናገርኩት፡፡

20 comments:

  1. I do not agree with the way you posted his picture. Even though they are not working properly, we are not expected to post their picture in such a way. Please do not try to post such ugly pictures in the future. Just try to post the real picture and criticize the way that they are acting.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Am seeing a different picture? what's wrong with it?

      Delete
  2. Abune Matias is a great leader....to have the church finance centralized is a good idea. Mahbere kidusan yefres altebalem. Genzebun be betekerestian ser yarg new yetebalew. Mahberu yetemeseretew begenzeb adelem....mitefawem begenzeb adelm. ENDEWEM MINAFEKEW YE MAHBERU AGELGLOT YALEW GENZEB SAYNOREW YENEBEREW AGELGLOT NEW. To have its money through church administration is correct. Mahbere Kidusan is a good mahber.....it will live...endewem MAHBERU GENZEBEN BEBETEKERESTIAN WEST ALAREGEM MALETU TARIKAWI TEZEBT NEW MIHONEW. Egziabher Abune Matiasen le ethioia atriarch adrerego simert miadergewen YAWKAL. Demo tsehufachehun Beseme Selalle Jemru.....kerestian endezi new miaregew....amatbo jemro amatbo yecheresal....alebelezia tsehufachu menfesu kefu yehonal.

    ReplyDelete
    Replies
    1. let me simple question what is the relation b/n money religion.who come first? which one is the big point concerning to the meeing?

      Delete
  3. በአንዶቻችን ዘንድ አቡኑ ጉዱ ካሳን የሆኑ እስኪመስለን ድረስ የለውጥ አባት ተደርገው ተወስደውም ነበር

    ReplyDelete
  4. jiraf erasu gerfo erasu yichohal ayidel yemibalew mezbariw gotegnaw yerasun gibr lelela asalifo liset yirotal yefrdu balebet firdun yist

    ReplyDelete
  5. so is the patriarch is crazy ? if you say crazy, you guys are not belive in orthodox sucession

    ReplyDelete
  6. እኛም እንዲያብዱ አንፈልግም፡፡ የምንፈልገው እንደ እብዶች እንዳይሆኑ ብቻ ሳይሆን እብዶችንም እንዳይመስሉ ነው፡፡ መምሰልና መሆን የሚለያይ መሆኑን ያዉቁት አይደል፡፡ “አንተ አልክ”….አለ ጌታ !

    ReplyDelete
  7. ለአባቶቻችን በእውነት ማሳተዋልን ይስጥልን፡፡ የህዝብ ጠባቂ ናቸውና
    በእውኑ የማህበሩ ነገር ለእሳቸው እንዲት ታያቸው?

    ReplyDelete
  8. In order to accuse that Mk is collecting 10% of the church the must be sure that the members of the church are really giving 10%. do the make them to dos so first. on some of the MK members are doing and some members

    ReplyDelete
  9. woy gode Besintu enseqayi

    ReplyDelete
  10. ''አባ ማቲያስ አላበደም'' እርስዎ አሉ?

    ReplyDelete
  11. yetenagerut esachew kehonu! bayabdum tenegna gin aymeslum! mahibere kidusanin beftsum ayawikutim! weyis lela mahibern lemalet felgew yihon? Egiziabher betekirstianin yitebkilin! le Abunu Ye abatochin libona yistlin!!

    ReplyDelete
  12. We Thank You your holiness, indeed MK should be put under strong regulatory law. unless it will divide us because they are now led by those politics power mongers&hidden elites of Ankober province

    ReplyDelete
  13. AG from Virginia,USAOctober 21, 2014 at 6:41 PM

    To start with, I am the holy trinity theology college first graduate, I never got a chance to serve in or with MK. but I can assured everyone, I born and raised in the church. when I see all this mess in the church I want to challenge every fellow orthodox tewahedo Christians, by the following questions:-
    1) is it the time to quarrel each other while the lion /devil is roaring to eat us?
    2) who is making the believers and church minsters cry by doing corruption, and by doing so diminishing the power of church and number of believers?
    3) is it appropriate behavior to church father to demonize his own children ?
    Egzeabher hoy lementachen tsenaten , le abatochachen areko maseben lebetekrstyanachen mesfafaten tadelen zend be dengle Maryam sem tematsegnehalehu.

    ReplyDelete
  14. ኃይማኖቱን የካደ የሃገር መሪና አገሩን የካደ የኃይማኖት መሪ በአንድ ላይ የመምጣታቸው ምስጢሩ እየታየ አይደለም ወይ? ኃይለሚካኤል።

    ReplyDelete
  15. This is not true, they have no political agenda. They are blessed Orthodox children who save this "Tiwlid" when our religious fathers slept. They save,
    1. Mengaw betekula endaybela,
    2. yehaymanotachin tiwfit enditebek,
    3. Gedamat ena adbarat kelimena endiwetu ena gedamu beteleyaye sira project tekersolet leza bemigegn sitota gedamun belemat sira tesatfo rasun endichilna kelimena endiweta,
    4. Asrat bekurat lebetekristian endiset,
    5. Gedamatin miemanan endigobegnu bemadreg
    - miemenu bereket endiagegn,
    - miemenu gedamatuna adbaratu tuaf, etan, mekedesha albasat, yegenzeb digaf
    bebotaw tegegnto endiaderg,
    - yetezegu abiyate kirstianat endikefetu,
    - mekedesha tuaf etan, albasat yatu ena bemefres lay yalu betekristiant endiredu
    yaderegu,
    - miemenu limarbachew ena yeminorewn tiyake limelslet yemichil metshaftin,
    gazatochin bemesafina bemasatem lehizbu yabereketu,
    - yeuniversity ena college temariwoch kebeteseb rikew sihadu be emnet endaytefu ena
    betekula endaybelu yetemariwoch gubaie leuniversity kirb behone beyeatbiya
    betechristian yehaymanotachinin timhirt yastemaru,
    - beyesamntu friday Lunch time serategnochin beakrabiyachew bale Betechristian
    astemari bememedeb beserategna gubaie yehamonotachinin timihirt yastemaru,
    - Yemehaberu abalat kedemewezachew befikadegninet bemiyawatut genzeb
    yemahberu agliglot yemikenawen ena yemitedader,
    - Yemahaberu hinsa beabalat ena bemiemenan mewacho yetesera,
    - Betekristian beguyawa tehadsowoch tekemitew mengawan siyasadidu yeabatochin
    zimta sebrew hunatawin bemasawek betechiristian ermiga enditwosed yaderegu

    lelochim yaltetekesu ageliglotochin yabereketu nachew. Yih hulu yediablos wigiya newna ennkabet. Kalawekin eniteyik zim bilen anfred, sileageliglotachewm hone sileasserarachew beglits yasredalu.

    Amlak hoye endegna hatiat sayhon lekidisinah ena lekibrih enduhum belejochih lay lemidersew fetena ena mengelatat sitil ewnetun firediline. Seytanin kemehalachin arikeh megbabatin fiterilin.

    We sibhat LeEGZIABHERE.




    ReplyDelete
  16. Ergit meliktachewn new eyastelalefu yalut. ke Aboy sibhat nega ena ke Abay tsehaye yetesetachewn melikt. Egzeabher libona yistachew.

    ReplyDelete
  17. ይህ የአንድ እድርገን ጽሑፍና የሰዎቹ ኮሜንቶች የማህበረ ቅዱሳን ውጤት ያሳያል። ይገርማል

    ReplyDelete
  18. er bakachehu koy enes yegeremegn feragu man endehon new?ferd le egzeabher becha new bakachehu atferedu?
    MANAN ENEMEN ???????blogu hulu besew mefered hone temehiretu...egzeabher ethiopian yibark
    wosebhat le egzeabher

    ReplyDelete