Tuesday, July 17, 2012

“የአቡነ ጳውሎስ ገድል” በ20ኛ በዓለ ሢመት መጽሀፍ



  • ባለፉት 20 ዓመታት በወር በአማካይ 28 ቤተክርስትያኖችን አቡነ ጳውሎስ እንዳሰሩ ይገልጻል (በ20 ዓመት 6800 ቤተክርስትያናት ተስርተዋል ይለናል)

(አንድ አድርገን ሐምሌ ሚካኤል ፤ 2004 ዓ.ም)፡- አንጸባራቂዎቹ 20 ዓመታትን በማስመልከት በጠቅላይ ቤተክህት አንድ መጽሀፍ ተዘጋጅቶ ነበር ፤ ይህን የአቡነ ጳውሎስን ገድል የሚተርክ መጽሀፍ ለማሳተም በርካታ ሺህ ብሮች እንደወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ ፤ የመጽሀፉ አዘጋጆች ምዕመኑ በብር ግዛ ቢባል እንደማይገዛ በማወቃቸው በሺህ የሚቆጠሩ መጻህፍትን በነጻ ሲያድሉ ተመልክተናል ፤ ሐምሌ 5/2004 ዓ.ም አራት ኪሎ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ከመንግስት የተጋበዙ ባለስልጣኖች ፤ የውጭ ጥቂት ዲፕሎማቶች ፤ ፈቅደው ሳይሆን ከየደብሩ የመጡ ካህናትና መዘምራን ፤ ብዛት ያላቸው ጳጳሳት የተገኙበት ስርዓት ነበር፡፡ ምዕመኑ ከ150 የማይበልጥ ሲሆን አብዛኛው ቦታውን የያዙት ተጋባዥ እንግዶች ነበሩ ፤ መሀል ላይ ያለው 10 ሜትር የሚያህል ቦታ ዳር ዳር የቆሙት ምዕመናን ለመታዘብ እንጂ በዓለ ሲመታቸውን ለማክበር የመጡ አይመስሉም ፤ የቅድስት ስላሴ የፊት ለፊቱ ደረጃ በቅጡ በምዕመኑ መሙላት አቅቶት አስተውለናል ፤ አቡነ ጳውሎስ በስተቀኝ እነ ተስፋዬ ውብሸትን ከበስተኋላ ዲፕሎማቶችን ፤ ከበስተቀኝ ደግሞ ሊቃነ ጳጳሳትን አስቀምጠው መሀል ቁጭ ብለዋል፤  በነጻ የሚታደለውን መጽሀፍ በግራ እና በቀኝ የሚያድሉ ሰዎች ተሰማርተው ሰው እጅ ላይ የማድረስ ስራቸውን ተያይዘውታል ፤ ፕሮግራም መሪው የአቡነ ጳውሎስን ፤ የተጋባዥ የመንግስት ባለስልጣናትን ፤ አምባሳደሮችን ስም ሲጠራ ለሰማ ምንድነው ይህ ሁሉ የመዓረግ ጋጋታ ማለቱ አይቀርም ፤የነሱ ስምና መዓረጋቸው ብቻ ከአንድ ገጽ ቢበልጥ እንጂ አያንስም ፤ የሚነበበውን ነገር ጆሮ ሰጥቶ የሚያዳምጥ ሰው ማግኝት መታደል ይመስላል ፤ ማን እንደሚያነብ ስለምን እንደሚነበብ ፤ የጽሁፉ መልዕክትና ይዘት የነበረው እንግዳ ቢጠይቁ ከመቶ አምስቱ አይመልስሎትም ፤ በጣም አሰልቺ ከመሆኑ የተነሳ አንድ ሰው እስከ 5 ገጽ ያነበበበትም ጊዜ ነበር ፤ አቡነ ጳውሎስ አስከ አሁን የሰሩት ወይም ወደፊት የሚሰሩት ስራ አሳስቧቸው ነው መሰል እርሳቸውም ንግግሩን በአጽንዎ እየተከታተሉ አይደሉም ፤ ታዲያ ይህ በዓለ ሲመት ለማነው የተዘጋጀው? የሚያስብል ሁኔታን ይመለከታሉ ፤ እኛ እንኳን የመጣነው 4 ኪሎ ስላሴ ቤተክርስትያን ግቢ ውስጥ እንደ ቦሌው ሌላ ሃውልት ካቆሙ ሃውልቱን ለማፍረስ እንጂ መርሀ ግብሩን ለመሳተፍ አልነበረም ፤ ማን ያውቃል ሀውልቱን እንደማይደግሙት ?

   
ስራቸውን የሚያትተው የመጽሀፉ የመጀመሪያ የውሰጥ ገጽ የብጹእ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ብሎ ሙሉ ስማቸውን እስከ ግማሽ ገጽ ድረስ በመጻፍ “ለ20ኛ በዓለ ሲመት ፕትርክና አስመልክቶ የተዘጋጀ ልዩ እትም” በማለት ወደ አዘጋጅ መጋቢ ሚስጢር ወልደ ሩፋኤል ፋታሒ እና ወደ ስነ ፅሁፍ አቅራቢዎች አቶ ተስፋዬ ውብሸት (አስተባባሪ ፤ ይህ ሰው የዋልድባ መነኮሳትን ግድቡን አሳ ያጠምዱበታል ብሎ የተናገረ ሰው ነው) ፤ ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሀ ፤ መልአከ ሰላም አምደ ብርሀን እያለ የ10 ሰዎችን ስም ይዘረዝራል ፤ እኛን በጣም የገረመን ነገር 156 ገጽ የአቡነ ጳውሎስን ገድል ለመጻፍ ይህን ያህል ሰው መረባረብ መቻሉ ነው ፤ እነዚህን የመሰሉ ሰዎች ብር ከተሰጣቸው ሌላም አስገራሚ ስራ እንደሚሰሩ እሙን ነው ፤ በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ካለፉት 4 ጳጳሳት በብዙ ሰዎች በህይወተ ስጋ እያሉ ስራቸውን በደንብ ያጻፉ አባት አቡነ ጳውሎስ ይመስሉናል ፤ ወደ ሚቀጥለው ገጽ ሲገልጡ “ሃያዎቹ አመታ እንዴት አለፉ ?” በማለት ጥያቄ በመጠየቅ ዲስኩራቸውን ይጀምራሉ ….

"የኢትዮዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አምስተኛው ፓትርያርክ የብጹእ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የፓትርያርክነት በዓለ ሲመት ማክበር ከጀመረች እነሆ ሃያ አመታት ተቆጥረዋል ፤ ታዲያ እነዚህ ሃያዎቹ ዓመታት እንዴት ነው ያለፉት? በሰላም ወይስ በፈተና ? በስራ ወይስ በስንፍና ? ብለን ስንጠይቅ የሚከተሉትን መልሶች እናገኛለን ፡፡ ወቅቱ የደርግ መንግስትና የኢህአዴግ መንግስት ለመተካካት የሞት ሽረት ትግል የሚያካሂዱበት ጊዜ ስለነበርና ሰኔና ሰኞ ገጠመና እነዚህ ሃያዎቹ አመታት  በሰላም በጤና አላለፉም” በማለት ይጀምራል ፤ እዚህ ላይ “ሰኔና ሰኞ” ከገጠሙ መልካም ነገር እንደማይከሰት እውነታ የሌለው ልማዳዊ አፈታሪክን መሰረት በማድረግ የደርግን መውደቅ ፤ የኢህአዴግን ስልጣን መረከብ ፤ የአቡነ ጳውሎስ አንድ ላይ መምጣት አያይዞ ያስቀምጣል ፤ ቀጥሎም “በኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብዙ ፈተናዎች ደርሰዋል አያሌ ውጣ ውረዶች ተፈጽመዋል ፤ በተለይም በቅዱስነታቸው ላይ የደረሱት የተለያዩ ፈተናዎች  እጅግ በጣም የሚያስገርሙ እና የሚያሰቅቁ ነበሩ ፤ እንግሊዘኛ ቋንቋ መናገር በወንጀለኝነት አስቆጥሯቸዋል ፤ ታቦት በሴቶች በር ለማስገባት የተገደዱበት ጊዜ ነበር ፤ ከዚህም አልፎ የመግደል ሙከራ ተደርጎባቸዋል” በማለት ሚዛን የማይደፉ ተጋድሎ ያላቸውን ነገሮች ያስቀምጣል ፤ ጽሁፉ “የሚያሰቅቅ” እና “የሚያስገርም” ነገር ምን እንደሆነ ብዥታን ለአንባቢያን ይፈጥራል ፤ ለምሳሌ የሚስገርም ተብሎ መቅረብ የነበረበት የቦሌው የአቡነ ጳውሎስ ሃውልታቸው ቢሆን መልካም ነበር ፤ ለምን ቢባል እስካሁን ያልተደረገ ወደፊትም የሚሾሙ ፓትርያርክ አባቶች ለማድረግ የማያስቡት ተግባር ስለሆነ ገራሚ ቢባል ያንስበታል እንጂ አይበዛበትም ፤ ሌላው ገራሚ ደግሞ ለቢዮንሴ ያደረጉት አቀባበል ነው ፤ ካህናት አባቶች እንዲያቀርቡ የተደረጉበት ወረብ ፤ ታቦት ማውጣት ሲቀራቸው የሲኖዶስ አባላትን ሳያማክሩ በራሳቸው ፍቃድ ያደረጉት ነገር ገራሚ ነው ፤ በጊዜው የነበሩ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችም አቡነ ጳውሎስን ጎን በመቆም የተናገሩት ነገር ትክክል ነው ብለው በሸገር ሬዲዮ ጣቢያ መልስ ሲሰጡ ሰምተናልም አይተናልም ፤ እርሳቸው ላይ የመግደል ሙከራ መቼ እንደተደረገባቸው እኛ አናውቅም ፤ ነገር ግን እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን በጠባቂዎቻቸው ይሁን ከየት እንደመጣ ባልታወቀ ጥይት በበአል ቀን የተገደለውን መነኩሴ ግን እናውቃለን ፤ የሰው ደም ይጮሃል ጊዜ የነጎደ ሊመስል ይችላል ፤ ተበቃይ አምላክ የሚመዝንና የማያዳላ እግዚአብሔር ስለሆነ እርሱ ጊዜ አለው ፤ ዝምም አይልም ፤ ይህ ነው ገራሚ ፤ ስለዚህ ጸሀፊዎቹ ገራሚ ባሉት ነገር ውሃ አይደፋም ፤ እንቀጥል



በአጠቃላይ በብዙ አቅጣጫ አያሌ የጥፋት ነፋሳት ነፍሰው ፤ አያሌ የጥፋት ጎርፎችንም ጎርፈው ቤቱን ሊያናውጡት ሞክረው ነበር ፡፡ ቤቱ ግን ከመሰረቱ በጽኑእ አለት ላይ የተመሰረተ ስለነበረ በቀላሉ ሊነዋወጥ አልቻለም፡፡ ያም ቤት የብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያሪካዊ ሰውነት ነበር ፡፡ ይህ ሰውነት በእምነት ፤ በትሩፋት ፤ በትምህርት ፤ በእስራትና በስደት የተገነባ ስለሆነ እስከ አሁን ድረስ በውስጥም በውጭም የሚደርስበት ዘርፈ ብዙ ፈተና ፈጽሞ ሊበገር አልቻለም” በማለት ያትታል፤ ቤተክርስትያናችን የተመሰረተችው እስከ አሁንም የቆየችም በጌታችን በመድሐኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም መሆኑን እናውቃለን ፤ እኛ  እንደሚገባን እንደ አቡነ ጳውሎስ ያሉ እምነቷን ለሁለት ለመሰንጠቅ ስርዓተ ቤተክርስቲያን እንዳይከበር የሚታትሩ አውሎ ንፋስ የሆነ አባቶች ቢነሱም ቤተክርስትያን ግን በጽኑ አለት ላይ የተመሰረተች ስለሆነች ምንም እንደማትሆን ነው ፤ የተሃድሶ ንፋስ ፤ የሙስና ንፋስ ፤ የዘረኝነት ንፋስ ፤ የጎጠኝነት ንፋስ ፤ የአድሎአዊነት ንፋስ ፤ የጉቦኝነት ንፋስ ፤ የአድርባይነት ንፋስ ፤ የምንፍቅና ንፋስ የተነሱት ቤተክርስትያንም ተቋቁማ እስካሁን ያለችው ባለፉት 20 ዓመታት ጊዜያት ውስጥ ነው ፡፡

ጽሁፉ ይቀጥላል “እንደዚያም ሆኖ ይህ ለፈተና የታደለ ታላቅ ሰውነት የመጀመሪያው ዓመት በአለ ሲመት ፓትርያርክ በሚከበርበት ጊዜ በገባው ቃል ኪዳን መሰረት በእነዚህ በ20ዎቹ ዓመታት ውስጥ በውስጥም በውጭም አያሌ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ በደርግ መንግስት  ተወርሰው የነበሩ ህንጻዎችና ቤቶች ተመልሰው ቤተክርስትያኒቱንና ህብረተሰቡን በመጥቀም ላይ ይገኛሉ፡፡” ይላል ፡፡ መጽሀፉ እንዲህ ቢልም እኛ ባለን ማስረጃ ግን ቤተክርስትያኒቱ አሁንም ከ21 የመንግስት ለውጥ ዓመታት በኋላም ህንጻዎቿ በጠቅላላ አላስመለሰችም ፤ አሁንም መንግስት የቤተክርስትያኒቱን ህንጻዎች ያለምንም ካሳ ያለምንም የቦታም ሆነ የህንጻ ኪራይ በኪራይ ቤቶች እያስተዳደረ ፤ የራሱንም መስሪያ ቤቶች ስራ እያከናወነበት ይገኛል ፤ በተጨማሪ “ቤቶቹ ተመልሰው ቤተክርስትያኒቱንና ህብረተሰቡን በመጥቀም ላይ ይገኛሉ” የሚለው አንቀፅ በተወሰነ መጠን በትንሽ የቤት ኪራይ ቤተክርስትያኒቱ በጣም በትንሹ ተጠቅማለች ፤ ነገር ግን የትኛው ማህበረሰብ ነው ተጠቃሚ የሆነው ? ቤተክህነት ዘመድ ያለው ነው ? የአቡነ ጳውሎስ የስጋ ዘመድ ነው ? እነ ጌታቸው ዶኒ የሚላላኩትን ነው ? እነ እጅጋየሁ ጋር የተጠጋው ነው ? እረ የቱ ማህበረሰብ ነው በቤተክርስትያኒቱ ህንጻ ተጠቃሚ ነው የተባለው ?  ይህን ጉዳይ አስፈላጊ ከሆነ ወደፊት ስማቸውን ፤ ዝምድናቸውን ፤ የሚከፍሉት የቤት ኪራይ አያይዘን እናቀርባለን፡፡ ጽሁፉ ይህን የመሰሉ ነገሮችን ሲጨርስ በ20 ዓመታት ስለተገነቡ መንፈሳዊ ኮሌጆች ፤ ስለ ቅርሶች ፤ ስለ ህጻናት ማሳደጊያዎችን በመዳሰሰስ በስተመጨረሻ “ከጥቂት ዓመታት በፊት ቅዱስነታቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰላም ተሸላሚ ሆነዋል ፤ ከዚህም ባሻገር ቅዱስነታቸው የዓለም አብያተክርስትያናት ምክር ቤትና የዓለም የሃይማኖቶች የሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው ቤተክርስትያነችን የታሪክ እመርታ አሳይታለች ፤ እንግዲህ ሃያዎቹ ዓመታት እንዴት አለፉ ? ለሚለው ጥያቄ ከረጅሙ ባጭሩ ከብዙ በጥቂቱ መልሶቹ እነዚህ ናቸው” በማለት የተነሳበትን ሃሳብ ይቋጫል፡፡

ከብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ መልዕክት
“በቅዱስነትዎ ጥረት የሰበካ ጉባኤ ከምን ጊዜው በላይ እንዲስፋፋና በገጠርም በከተማም የአብያተ ክርስትያናት ቁጥር እንዲጨምር ባደረጉት ጥረት ከ6800 በላይ አዳዲስ አብያተክርስትያናት ባለፉት 20 ዓመታት የተከፈቱ በመሆናቸው በላይ በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ አህጉረ ስብከቶች አጫጭር ስልጠናዎች እንዲሰጡ በማድረግ ሰልጣኝ ካህናት ስብከተ ወንጌል የሚያስፋፉበትን ሁኔታ በማመቻቸት ቤተክርሰትያን ሐዋርያዊት ተልእኮዋን በተሻለ ሁኔታ እንድትፈጽም አድርገዋል፡፡ ቅዱስነትዎ ለተቸገረ እና ለተራበ ሰው በግልዎ ከሚያደርጉት አባታዊ ርህራሄና ስጦታ በተጨማሪ በአበይት በአላት ወቅት ሰንጋዎችን በማሳረድ ከብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን ነዳያንን የሚጋብዙ ከመሆኑም  በላይ “ሰው ለተቸገረ መርዳት ያለበት ሲተርፈው ሳይሆን ካለው ላይ በማካፈል ነው” በማለት በሚሰጡት ትምህርት ህዝበ ክርስትያኑ እርስ በእርስ የሚረዳዳበት እና የሚተጋገዝበት ባህል እንዲጠነክር ለማድረግ ባለፉት20 ዓመታት እጅግ በጣም ጠቃሚ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል” በማለት በጽሁፍ አስፍረውላቸዋል፡፡  ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ እርሳቸው የቱንም ያህል ማሞገስ መብታቸው ነው ነገር ግን ያልተደረገን ነገር ለህዝበ ክርስትያኑ ተደርጓል ብሎ ማቅረብ በሌሎች አባቶችና ዘንዳ ትዝብት ላይ የሚጥላቸው ይመስለናል፡፡

መጽሀፉን በወፍ በረር ሲቃኙት ገጽ 44 ላይ በምስራቅ ሸዋ ናዝሬት ከተማ የተገነባው የደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ጥር 19 ቀን 2004 ዓ.ም በቅዱስነታቸው ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ በታላቅ ስነ ስርዓት ተከብሯል በማለት ያስቀምጣል ፤  የደሴውን የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ምርቃት ግን በመጽሀፉ ላይ መመልከት አልቻልንም ፤ ለምን ቢባል የደሴ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርሰትያን ቅዳሴ ቤቱ ሲከብር ቅዱስነታቸው የጌታቸው ዶኒ ቤት በልጦባቸው የእሱን ቤት ለመመረቅ ስለሄዱ በቦታው መገኝት አለመቻላቸው ነበር ፤ የቅዱስ ገብርኤል ቅዳሴ ቤት ሲከብር የአካባቢው ሙስሊሞች በተጋባዥ እንግድነት ለዘመናት አብሮ የመኖራቸውን ሚስጥር ለማመልከት በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ሲጠሩ ፤ እነርሱም ጥሪያቸውን አክብረው ሲመጡ አቡነ ጳውሎስ ግን የጌታቸው ዶኒ የቤት ምርቃት ሚዛን ደፍቶባቸው በቦታው መገኝት አልቻሉም ፤ ይህ የሆነ በእኛ ዘመን የተደረገ ለመጪው ትውልድ ታሪክ የሚሆን አሳፋሪ ተግባር ነው ፤ የአንድ ሰው ቤት የመልአኩ ከቅዱስ ገብርኤል ቤት የበለጠበት ዘመን .....

 በገጽ 81 ላይ “በአብያተክርስቲያናት መስፋፋትና መጠናከር ዘርፍም ቤተክርስቲያኒቱ ተዐምር ሊያሰኝ የሚችል ለውጥ ባለፉት 20 ዓመታት አስመዝግባለች፡፡ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ምዕመናን በቅርበት የሚገለገሉባቸው በ594 ወረዳዎች ፤ በ1273 ገዳማት ፤ 4510 አድባራትና 16441 የገጠር አብያተ ክርስቲያናት በድምሩ 23738 ገዳማትና አድባራት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስያን ስር የሚገኙ ሲሆን በተለይ ባለፉት 20 ዓመታት ከ6800 በላይ አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት የተተከሉና ቅዳሴ ቤታቸው የተከበረ ሲሆን አገልጋይ ካህናትም ቅጥርም ከሁለትና ከሶስት እጥፍ በላይ በመጨመሩ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ስታስቲክስ ያስረዳል” በማለት ያትታል ፤ በጠቅላላው የአብያተክርስትያናት ብዛት ላይ ምንም ጥያቄ ላይኖረን ይችላል ፤ ለምን ቢባል ባሳለፍናቸው 1600 ዓመታት ውስጥ በመላ ሃገሪቱ ውስጥ 17ሺህ ገዳማትና አድባራት አሉ ቢባል የበዛ ቁጥር መስሎ ስለማይታየን ነው ፤ በግራኝ መሃመድ እና በዩዲት ጉዲት ዘመን የተካሄደው ወረራ ባይኖር ባይከሰት ኖሮ የዚህን አምስት ቁጥር አብያተ ክርስቲያናትና ፤ አድባራትና ገዳማት በኖሩ ነበር ፡፡ አሁን እኛን ግራ ያጋባን 6800 ቤተክርስትያናት በ20 ዓመታት ተሰሩ መባላቸው ነው ፤ 20 ዓመት 20 x 365 = 7300 ቀኖችን ይይዛል ፤  ተሰሩት የተባሉት በ6800 ቤተክርስትያናትን በ7300 ቀናት ስናካፍላቸው በአማካይ በቀን 0.93 ይመጣልናል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ በአንድ ወር በአማካይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ 28 ቤተክርስትያናትን በሀገሪቱ እየሰራች መሆኑን ያመላክታል ፤ ይህ ስታስቲክስ ብላችሁ ያቀረባችሁትን መረጃ ለራሳችሁ ዞር በሉና እዩት ፤ ባሳለፉት 20 ዓመታት የዚህን  አስር እጥፍ ሰርተው ብንመለከት ደስታችን ወደር የለው ነበር ፤ ነገር ግን ለአቡነ ጳውሎስ ሞገስና ክብር ተብሎ የሚደረግ ተግባር እንቃወማለን ፤  ባለፉት 20 ዓመታት በሺህ የሚቆጠሩ አብያተክርስቲያናት እንደተሰሩ የሚታወቅ ነው እናንተ እንዳላችሁት ግን አይደለም ፤ ባሳለፍናቸው 1600 ዓመታት 17ሺህ ቤተክርስትያን በመላ ሀገሪቱ ላይ አባቶቻችን ሰርተው ለእኛ ሲያወርሱን አቡነ ጳውሎስ ደግሞ በ20 ዓመት ውስጥ 6800 ቤተክርስትያናትን ሰርቻለሁ እያሉን ነው፡፡ ቢሰሩ መልካም ነገር ግን ቁጥሩ ለአንባቢ ያለ አሳማኝ መረጃ ከመቅረቡ ጋር ተያይዞ ተዓማኒነት ይጎድለዋል ፡፡

ለመጽሀፉ ጸሀፊዎችን አንድ መነኩሴ

የአህያ በሬ የጅብ ገበሬ ፤
የጦጣ ጎልጓይ የዝንዥሮ ዘር አቀባይ.... አይተን አናውቅም ያሉትን ተረት ትዝ አስባሉን፡፡

ቸር ሰንብቱ

ሌሎች ነጥቦችን በቀጣይ ለመጻፍ እንሞክራለን

16 comments:

  1. አሁን እኛን ግራ ያጋባን 6800 ቤተክርስትያናት በ20 ዓመታት ተሰሩ መባላቸው ነው ፤ 20 ዓመት 20 x 365 = 7300 ቀኖችን ይይዛን ፤ ተሰሩት የተባሉት በ6800 ቤተክርስትያናትን በ7300 ቀናት ስናካፍላቸው በአማካይ በቀን 0.93 ይመጣልናል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ በአንድ ወር በአማካይ 28 ቤተክርስትያናትን በሀገሪቱ እየሰራች መሆኑን ያመላክታል ፤ ይህ ስታስቲክስ ብላችሁ ያቀረባችሁትን መረጃ ለራሳችሁ ዞር በሉና እዩት ፤ ባሳለፉት 20 ዓመታት የዚህን አስር እጥፍ ሰርተው ብንመለከት ደስታችን ወደር የለው ነበር ፤ ነገር ግን ለአቡነ ጳውሎስ ሞገስና ክብር ተብሎ የሚደረግ ተግባር እንቃወማለን ፤ ባለፉት 20 ዓመታት በሺህ የሚቆጠሩ አብያተክርስቲያናት እንደተሰሩ የሚታወቅ ነው እናንተ እንዳላችሁት ግን አይደለም ፤ ባሳለፍናቸው 1600 ዓመታት 17ሺህ ቤተክርስትያን በመላ ሀገሪቱ ላይ አባቶቻችን ሰርተው ለእኛ ሲያወርሱን አቡነ ጳውሎስ ደግሞ በ20 ዓመት ውስጥ 6800 ቤተክርስትያናትን ሰርቻለሁ እያሉን ነው፡፡ ቢሰሩ መልካም ነገር ግን ቁጥሩ ለአንባቢ ያለ አሳማኝ መረጃ ከመቅረቡ ጋር ተያይዞ ተዓማኒነት ይጎድለዋል ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. yaferesutin, meqedesha tefto yetezegutin, lemenafiqan mefencha yaderegutin yihonala be 20 ametat yetebalelachew. and teret lastawsachihu sewyew mistu minim aynet neger beqetita atadergim neber enam hule teqarani neberech. .ot ayiqermina weraj wuha (wenz) dinget yizoat hede. yakababiw newarina balebetua filega jemeru. yezihin gize balebetua filegawin wedelay aderegew (aqebetun) ende min nekah wenzu eko eyefesese yalew wedetach new silezih etach askerenuan enagegnalen silut ayihonim ale yesuan neger atawqutim " qegn sitibal gira, tiqur sibal nech" newna negerua ahunim yemitigegnew kezih ke aqebetu new alachew.
      Dirom sitifeter temama neberech
      Arib motechina hamus teqeberech
      teblo teleqeselat. fichiein engidih le enantew biyalehu.

      Delete
  2. betekiristianat Yeteserute beme`menan Tiret new.enersum tikit nachew.

    ReplyDelete
  3. betam des yemel new menew sel waldeba zekola asebot ena lelochem seletezegu bet crstian ena gedamat seletekatelut betcrstian ena sel hezbu mebet matat betcrstian west< betcrstian end mesria bet tekotera hulum eyezerefat mehonun man yenager men yebalal egzeabhir meles yesten ayzochehu tegtachehu agelgelu hulum befeker yehun

    ReplyDelete
  4. የእናንተ መጨበጫ የሌለው ወሬ እያለ በየት በኩል ቸር እንሰነብታለን፡፡ የመንግሥት ማስጠንቀቂያ ካላሳረፋችሁ ቀጣዩ እርምጃ ይመጣባችኋል፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. manehe demo ante fesame menafe

      Delete
    2. ashqabach arfeh gize yesetehin bila kentu

      Delete
    3. Yikirta Ato Anonymous Ohhh sorry, Kabene Anonymous Keyet Atasferaruwachew Hasabachewin begiltse yitsafubet enje; endeee minekawot Aleka .

      Delete
  5. liars, liars, liars......


    Nice try but numbers don't lie. 6,800 churches in 7,300 days means (.93) church in a day.
    If we round it up it is close to one church per day continously for 20 years/ 7,300 days. What are they thinking? Who can believe them?

    ReplyDelete
  6. betekikekele!!!
    he and his supporters had been closing many churches perhaps they may have plan to close more!!!


    God will save the people and the true °Tewahedo°

    ReplyDelete
  7. ebakachu be semien America sint abyate krstyan tekftewal bilow yaqerebutn masreja kemetshetu lay bitasefrulin

    ReplyDelete
  8. What I am thinking is we have to cross check each hagere-sebket's report. From where they get this data? Is it really reported from each hagere-sebket? We don't have to keep silent, we should ask seriously. There is no way that Aba paulos can build one church each day. This is not only exaduration, it is the sign of what has been don in our church.

    ReplyDelete
  9. የአህያ በሬ የጅብ ገበሬ ፤
    የጦጣ ጎልጓይ የዝንዥሮ ዘር አቀባይ

    ReplyDelete
  10. Dear Andadrgen

    What a fantastic report review, it shows the writer has a deep knowledge of reviewing the book and knows everything what is going on in the church. I admired all the contributers for this link , GOD bless u all.

    Andadrgen you are ahead of other links getting the news , reporting , etc which I followed.Good on u keep up the good job guys.

    I and all my friends are proud of you. You are truly the son and daughter of Ethiopian Orthodox Tewahedo church.

    GOD BLESS U ALL

    ReplyDelete
  11. ይህ ብሎግ እንደ ብሎግ ተነባቢ ሆኖ መቀጠል ካለበት ጸሐፊዎቹ ፅንፍ ይዞ መጻፍን ማቆም አለባቸው እላለሁ፡፡ የእንናንተ ሞያ የተጻፈውንና የተባለውን በጥሬው ከተገቢ ማብራሪያ ጋር ማቅረብ ሲሆን የመፍረድና ሐሳቡን የመቀበልና ያለመቀበል ድርሻ ደግሞ የኛ የአንባቢያን ነው፡፡ ስለሁሉም ነገር ፅንፍ ይዞ መጻፍ (ድጋፍም ከሆነ በመደገፍ ብቻ ፣ ተቃውሞም ከሆነ በመቃወም ብቻ) የጸሐፊውን ማንነት የሚያሳብቅ ነው፡፡ በዘመኑ ያለው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሁሉም ነገር ኮንኖ ስለጻፈ ያተረፈው ትርፍ ወይም ለሀገሪትዋ ያበረከተው ምንም ዓይነት አስተዋጽኦ የለም፡፡ ስለዚህ እናንተም ሁሉም ነገር የውስጣችሁ ስሜት ብቻ በሚገልጽ መልኩ ጠምዝዛችሁ ከመጻፍ ይልቅ ሚዛናው ሆናችሁ ስትደግፉም ስትቃወሙም በምክንያት አስደግፋችሁ መሆን አለበት፡፡ እኛ ከሁሉም የተሻለ መረጃ ወይም እውቀት አለን ብሎ በሁሉም ነገር ላይ ፅንፍ ይዞ መጻፍ አላዋቂነት ነው፡፡ አንባቢው በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ከእናንተ የተሻለ መረጃም ግንዛቤም ሊኖረው እንደሚችል እያሰባችሁ ብትጽፉ ጥሩ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ብሎጋችሁ ሩቅ በማይባል ጊዜ ማንም የማይመለከተው ዲስኩር ሆኖ ሊቀር ይችላልና ብታስቡበት፡፡ይህ ብሎግ እንደ ብሎግ ተነባቢ ሆኖ መቀጠል ካለበት ጸሐፊዎቹ ፅንፍ ይዞ መጻፍን ማቆም አለባቸው እላለሁ፡፡ የእንናንተ ሞያ የተጻፈውንና የተባለውን በጥሬው ከተገቢ ማብራሪያ ጋር ማቅረብ ሲሆን የመፍረድና ሐሳቡን የመቀበልና ያለመቀበል ድርሻ ደግሞ የኛ የአንባቢያን ነው፡፡ ስለሁሉም ነገር ፅንፍ ይዞ መጻፍ (ድጋፍም ከሆነ በመደገፍ ብቻ ፣ ተቃውሞም ከሆነ በመቃወም ብቻ) የጸሐፊውን ማንነት የሚያሳብቅ ነው፡፡ በዘመኑ ያለው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሁሉም ነገር ኮንኖ ስለጻፈ ያተረፈው ትርፍ ወይም ለሀገሪትዋ ያበረከተው ምንም ዓይነት አስተዋጽኦ የለም፡፡ ስለዚህ እናንተም ሁሉም ነገር የውስጣችሁ ስሜት ብቻ በሚገልጽ መልኩ ጠምዝዛችሁ ከመጻፍ ይልቅ ሚዛናው ሆናችሁ ስትደግፉም ስትቃወሙም በምክንያት አስደግፋችሁ መሆን አለበት፡፡ እኛ ከሁሉም የተሻለ መረጃ ወይም እውቀት አለን ብሎ በሁሉም ነገር ላይ ፅንፍ ይዞ መጻፍ አላዋቂነት ነው፡፡ አንባቢው በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ከእናንተ የተሻለ መረጃም ግንዛቤም ሊኖረው እንደሚችል እያሰባችሁ ብትጽፉ ጥሩ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ብሎጋችሁ ሩቅ በማይባል ጊዜ ማንም የማይመለከተው ዲስኩር ሆኖ ሊቀር ይችላልና ብታስቡበት፡፡

    ReplyDelete