Tuesday, November 8, 2011

ይህ የቅዱስ ገብርኤል ድንቅ ተዓምር ነው


(አንድ አድርገን ፤ ጥቅምት 28 2004 ዓ.ም):- የመጀመሪያውን ተዓምር ስፅፍ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሁለተኛውን ለመፃፍ ያብቃኝ ብዬ ነበር፡፡ እነሆ ዛሬ የምነግራችሁ ተዓምር እዛው ኮራ ገብርኤል ላይ የተደረገ ነው ፡፡ ይህ ሁለተኛው ተዓምር ሲሆን የመጀመሪያውን እዚህ ቦታ ላይ የተደረገውን የቅዱስ ገብርኤልን ተአምር ካላነበቡ ለሁለተኛው መንደርደሪያ ይሆኖታልና ቢያነቡት መልካም ነው፡፡


የመጀመሪያውን ተአምር ለማንበብ   ይህን ይጫኑ

እነሆ እንደ እርሱ ፍቃድ የኮራውን የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተአምር ለመፃፍ በቅቻለሁ አስተውለው ያንብቡት ፡፡

ከአሰቦት ገዳም ስንመለስ መጀመሪያ እናየዋለን ያልነው ቦታ የኮራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያንን ነበር፡፡ ቦታውም ከአዲስ አበባ ወደ ሐረር መንገድ ሲሄዱ አሰቦት መገንጠያ ሳይደርስ በስተቀኝ በኩል 7 ኪሎ ሜትር ድረስ ገባ ብሎ ይገኛል፡፡ ቦታው አጽራረ ቤተክርስትያን በጣም የበዙበት ስለሆነ እግዚአብሔር እነሱን የሚያስተምረው በተዓምር ይመስላል፡፡ ክርስትያኖቹ ተቆጥረው 30 አይሞሉም፡፡ ለኮራ ገብርኤል ያላቸውን ልዩ ቦታ ስትመለከቱ መንፈሳዊ ቅናት ውስጣችሁን ያነደዋል:: እኛ በሺዎች የምንቆጠር ምዕመናን አካባቢያችን ያለውን አንድ ደብር ከአፅራረ ቤተክርስትያን መጠበቅ ሲያቅተን እዚያ በረሀ ላይ ያለውን አንድ የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ግን 30 የማይሞሉ ክርስትያኖች በ40 እና በ80 ቀን የስላሴን ልጅነት ያገኙባትን፤ የሚያገለግሏትን፤ ሲያርፉ የሚቀበሩባትን ሁሉ ነገራቸው የሆነችውን ቤተክርስትያንን እንዴት እንደሚጠብቁት ሲመለከቱ ይገርሞታል፡፡


በኮራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ሁለተኛው ተዓምር ሲነገረን በመጀመሪያው በተነገረን ተዓምር እየተደመምንና እየተደነቅን ነበር፡፡ ቦታው ላይ 98 በመቶ የሚሆኑት ሙስሊሞች ብቻ ስለሆኑ ቤተክርስትያኗ ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተፅዕኖ መኖሩ እሙን ነው፡፡ እያንዳንዷን ፈተና ከትላልቅ የሀይማኖት አባቶች ጋር በመነጋገርና በመወያየት ሲፈቱት አንዳንዱን ግን በጉልበትና በቁጣ ስለሚመጡባቸው ለእግዚአብሔርና ለቅዱስ ገብርኤል አሳልፎ ከመስጠት ውጪ ሌላ ምንም መፍትሄ የላቸውም፡፡

በረሀውን እና ቤተክርስትያኗን ብቻ ሲመለከቱ ያሉበትን የቀን እሳት ሲያስተውሉ እንባዎት አይኖትን ሙልት ያደርገዋል፡፡ እኛን ይዞን የሄደው ሹፌር መንገዱ ትንሽ ኮረኮንች መሆኑን ሲያይ እየሰደበን እየተመናጨቀ ነበር ቦታው ያደረሰን፡፡ ቦታው ስንደርስ መጀመሪያ የወረደው እና ቤተክርስትያኑን የሳመው ሹፌሩ ነበር፡፡ አንዴ ቤተክርስትያኑን ዞሮ ከተሳለመ በኋላ ግን ፊቱ ላይ የሚነበበው ነገር ሀዘን እና አይኖቹ እንባ ቋጥረው ልውረድ ልውረድ እያሉት ‹‹ ይቅርታ አድርጉልኝ እንዲህ መሆኑን አላወኩም እኔ ፤ ይቅርታ አድርጉልኝ አጥፍቻለሁ ማመናጨቅ መሳደብ አልነበረብኝም ፤ ማንም ምዕመን መጥቶ ሊያየው የሚገባ ቤተክርስትያን ነው ፤እዚህ በረሀ ላይ ቤተክርስትያን ይኖራል ብይ አስቤ አላውቅም›ብሎ ከኪሱ 100 ብር  አውጥቶ ‹‹ይህው ይህን ለቅዱስ ገብርኤል ሰጥቻለሁ፤ በማንኛውም ጊዜ የፈለጋችሁት ገዳም መሄድ ብትፈልጉ እኔ ከአጠገባችሁ ነኝ ያጠፋሁትን ጥፋት ይቅር በሉኝ›› ብሎ ንስሀውን እዛው አወረደ፡፡ አብረውን የነበሩት አባት ችግር የለም ልጄ ስላላወክ ነው ብለው ይቅርታውን ተቀበሉት፡፡

የደብሩ አስተዳዳሪ ከነገሩን ተአምር ሁለተኛውን እነሆ
ኮራ ቅዱስ ገብርኤል ታቦቱ የሚያርፍበት አንድ ትልቅ ግራር ከቤተክርስትያኑ ብዙም ሳይርቅ ነበር፡፡ አካባቢው ላይ ያለው ሙስሊም ማህበረሰብ ግራር እንጨት ቆርጦ ፤ እንጨቱን አክስሎ(ከሰል አድርጎ) ፤ ገበያ በማውጣት በመሸጥና ገቢውን ለኑሮ ቀዳዳ ማዋል የተለመደ ነው፡፡ ሶስት ወጣቶች አንድ ቀን ይነሱና ፡፡ የቅዱስ ገብርኤል ታቦት ማረፊያን ግራር ካቆረጥን ይላሉ፡፡ አስበውታል..... ለጥምቀት አዲስ አበባ ያሉ ታቦቶችን ለመሸኝት የሚወጣውን ህዝብ ታቦታቱን ማረፊያቸው አድርሰው ወደቤታቸው ይመለሳሉ፡፡ እነዚህ ክርስትያኖች ግን ቢበዛ ቢበዛ 35 ሆነው ነው ታቦቱን ማደሪያው ግራሩ ጋር የሚያደርሱት ፤  4ኪሎ የሚገኝውን የቅዱስ ገብርኤልን ታቦት ወደ ጃል-ሜዳ ሲሸኝ በ10ሺህዎች የሚቆጠሩ ህፃናት፤ ወጣቶች ፤ አባቶች ምዕመን ከፊት በሰንበት ተማሪዎች በዝማሬ፤ ከኋላ በካህናት ታጅቦ ማደሪያው ይደርሳል፡፡ ኮራ ቅዱስ ገብርኤልን ግን 35 የማይበልጡ ምዕመኖች  አጅበውት ነው ማደሪያው ጋር የሚያደርሱት፡፡ አዛው ድንኳን ይጣላል ያድራል በሚቀጥለው ቀን እየዘመሩ ታቦቱን ወደ ማደሪያው ይመልሳሉ፡፡ ይህን ግራር ነው ሶስት ሙስሊሞች  ካልቆረጥን ያሉት፡፡ ክርስትያቹ ‹‹ ይህ የቅዱስ ገብርኤል ማደሪያ ግራር ነው አትቁረጡብን ቦታው የኛ ነው›ሲሏቸው ‹‹እረ እባካችሁ በፈጣሪያችሁ ይህ ግራር ለረዥም ጊዜ የቅዱስ ገብርኤልን ታቦት የምናሳርፍበት ቦታ ነው አትቁረጡብን› ብለው ቢለምኗቸው ፤ ቢያስለምኗቸው ልመናቸውን የሚሰማ ጆሮ አልነበራቸውም፡፡ ‹‹ማነው ይህን ቦታ ለናንተ የሰጣችሁ እኛ ሀገር መጥታችሁ ቤተክርስትያን ሰርታችሁ ፤ እኛው ሀገር እየኖራችሁ ፤ የእኛ ነው ትላላችሁ እንዴ›› በማለት በቁጣ በማስፈራሪያ በዛቻ መለሱላቸው ለያዥ ለገናዥ አስቸገሩ፡፡ ‹‹ለመስማትም እንቢ አሉ፥ ›› መጽሐፈ ነህምያ 9፤7 ፡፡ በሙስሊም አባቶች ተው ቢባሉ እነዚህ ሰዎች ግን ሊሰሞ አልፈለጉም ‹‹አንገታቸውንም አደንደኑ፥›› መጽሐፈ ነህምያ 9፤7 ፡፡ ‹‹በቃ ተዋቸው በግራር እንጨት አማካኝነት ሌላ ነገር ውስጥ ከምንገባ ይቁረጡት›› አሏቸው ፡፡ይህን ሲሏቸው ነገሩን ማጠፊያ ቦታ ጠፍቷቸው ነበር፡፡ ክርስትያኖቹ በጣም እያዘኑ ከእግዚአብሔር በቀር ታዳጊ ጌታ ፤ ከረድኤቱም በቀር ሰግደድ ያለ ቦታ ፤ ከሃይማኖት የበለጠ ጋሻ ፤ ከእርሱም ውጪ የበለጠ አምባ፤ መጠጊያ ፤ እንደሌላቸው አውቀው ‹‹ቅዱስ ገብርኤል ይፋረዳቸው›› ብለው አልቅሰው አይናቸው እያየ ግራሩን በረዥም መጋዝ መቁረጡን ተያያዙት፡፡ እዛው በአካባቢው ያሉት ክርስትያኖች ስለ ነገሩ አለቀሱ ፤ እንደ ራሄል እንባቸውን ወደ ላይ ረጩት፡፡ የደብሩ አስተዳዳሪም ለምዕመናኑ እንዲህ አሏቸው፡፡ ‹‹ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል›› ትንቢተ ኢሳይያስ 25፤8 እግዚአብሔር ይህን እንባችንን የሚያብስበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ብለው አፅናኗቸው ፡፡ ይህን ነግረውን ሳይጨርሱ ሁላችንም ላይ የሀዘን ስሜት ይነበብብን ነበር ፡፡

እነዚህ ወጣቶች ግራሩን ቆርጠው ለከሰል እንዲሆን እንዲሆን አድርገው ካዘጋጁት በኋላ ከወንዝ መውረጃ ማዶ ከሰል ማክሰሉን ተያያዙት ፤ ግራሩ ከሰል ከሆነ በኋላ ከሶስቱ አንዱ በማዳበሪያ አድርጎ ከሰሉን ለማምጣት ወንዙን ተሻገረ፡፡ በረሀ ላይ ያለ ወንዝ ሁሌም ደረቅ ነው፡፡ ነገር ግን መቼ ውሀ እንደሚኖረው ፤ ጎርፍ መቼ ይዞ እንደሚመጣ አይታወቅም ፡፡ በላይኛው አካባቢ ዝናብ ዘንቦ ኖሮ ከሰሉን ትከሻው ላይ ጣል አድርጎ እየተሻገረ ያለውን ወጣት ውሀው ተሸክሞት ነጎደ፤ ‹‹የእግዚአብሔር ቍጣ በላያቸው መጣ›› መዝሙረ ዳዊት 78፤31 ቢጮህ ቢጮህ ማንም ሊደርስ እና ሊያተርፈው አልቻለም ፤ በዳይ እና ተበዳይ አንድ ላይ ስለሁኔታው አዘኑ ፤ ውሀው የወሰደውን ወጣት ለመፈለግ ሰዎች ተሰበሰቡ ፤ ውሀው መጉደል ስላለበት ውሀው እስኪጉድል ድረስ ጠበቁ ፤ ወንዙን ተከትለው ቢፈልጉ ቢፈልጉ ልጁን በህይወት ማግኝት አልተቻለም ፤ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እያጋደለች ስለሄደች የልጁን ሬሳ ፍለጋ በሚቀጥለው ቀን ሙስሊም ክርስትያኑ ለመፈለግ በሁለተኛው ቀን በማለዳ ወጡ ፤ ሬሳውን ግን አሸዋ ደብቆታልና በቀላሉ ማግኝት አልተቻለም ፤ ሬሳው ሲፈለግ ሶስት ቀን አለፈ ፤ ፈላጊዎቹም ተስፋ ቆርጠው መፈለጉን እርግፍ አድርገው ተውት፡ ቤተሰቦቹ በጣም አዘኑ ‹‹ይህ የአላህ ቁጣ ነው›› አሉ፡፡ የዚህን ልጅ ሬሳ ከ5 ቀን በኋላ እንደ እግዚሐብሔር መልካም ፍቃድ አሸዋው ተፍቶት ተገኝ፡፡ ግብአተ መሬትም ተፈፀመለት ፡፡እኛም በጣም አዘንን

ይህ እንዲህ እያለ  የሁለተኛውን ወጣት እጣ ፋንታ የደረሰበትን ነገር እንዲህ ብለው ነገሩን
የዚህ ልጅ ሀዘን ገና ለአካባቢው መፅናናት ሳይደርስ  ‹‹የእግዚአብሔር ቍጣ በዚህች ምድር ነደደ››  ኦሪት ዘዳግም  2927 ሌላ ነገር ደግሞ በሁለተኛው ላይ ተከሰተ ፡፡ ሁለተኛው ልጅ ‹‹ብርሃን የለበሰ  ሰው የሚመስል ፤ በጣም ረዥም ፤ መስቀል በእጁ የያዘ መጥቶ ተቆጥቶት ለምን ማደሪያዬን ቆረጣችሁ›› ብሎ በጥፊ እንደመታው ለቤተሰቦቹ መስክሮ ከጨረሰ በኋላ ሙሉ ሰውነቱን ማዘዝ ተስኖት ፓራላይዝ መሆኑ ሲሰማ ሁሉም ሰው ደነገጠ ፡፡ ‹‹እኔም በተዘረጋች እጅና በብርቱ ክንድ፥ በቍጣና በመዓት በታላቅም መቅሠፍት እወጋችኋለሁ። ትንቢተ ኤርምያስ 21፤5 ልጁ አይሰማም ፤ አይናገርም ፤ ምግብ በአግባቡ መመገብ አይችልም ፤ ሰውነቱን እንደ ከዚያ በፊቱ ማዘዝ ተሳነው :: ሞቷል እንዳይባል እስትንፋስ አለው ፤ ለተመለከተውም ሆነ ለሚሰማው ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ነበር ፡፡ ‹‹አሕዛብ ሁሉ። እግዚአብሔር በዚህች ምድር ስለ ምን እንደዚህ አደረገ? ይህስ የቍጣው ታላቅ መቅሠፍት ምንድር ነው? ይላሉ።›› ኦሪት ዘዳግም 2924

እስላም ክርስትያኑም በሆነው ነገር ደንግጠው ነበር፡፡ ከዚያ ቀን በፊት እንዲህ አይነት ነገር በአካባቢያቸው አይተውም ሰምተውም ስለማያውቁ ምን እንደሚያደርጉ ግራ ገባቸው፡፡ ቤተሰቦቹ ልጁን ለማሳከም ብዙ ቦታ ይዘውት ቢሄዱም ካለበት ሁኔታ ግን አንዳች ሊነቃ አልቻለም፡፡ ሙስሊሞቹ ‹‹ዱአ›› የሚሉት ነገር አላቸው፡፡ አንድ ሰው ሲታመም ጫት እየተቃመ ‹ዱአ›› ይደረግለታል ፈጣሪያቸውን ይለማመኑለታል ፡፡ ገጠር ወሰዱት‹ዱአ›› አደረጉለት ፤ አሰበ ተፈሪ ወሰዱት ‹ዱአ›› ተደረገለት ፤ አለ የሚሉት ቦታ ሁሉ ወሰዱት ነገር ግን ምንም አንዳች ለውጥ ሊያመጣ አልቻለም፡፡ መጨረሻም ላይ የክርስትያኖቹ ቄሶች ጋር ይዘውት ይሂዱ ተብለው አባትየው ልጃቸውን ይዘው ወደ ቤታቸው ተመለሱ አሁን ቤት ነው ያለው ብለው ነገሩን …. ወላጆች ‹‹ልጄ ደረሰልኝ ስራ ይዞ ይጦረኛል ብለው ተስፋ በሚያደርጉበት ሰዓት በእንደዚህ አይነት ቁጣ ልጆች ላይ ሲያጋጥም ስሜቱን የሚረዱት ወላጆች ብቻ ናቸው›› ካሉን በኋላ  ‹‹ቆይ ልጆቼ አባትየው እየመጡ ነው እሳቸውው የሆነውንና ልጁ ያለበትን ነገር ይንገሩአችሁ›› አሉን፡፡  ለካ ቤተክርስያን እኛ መምጣታችን ተነግሯቸው ኖሯል እኛል ለማየት አባትየው እየመጡ ነበሩ፡፡

አባትየው እድሜያቸው ከ60 የዘለለ ሲሆን የሙስሊሞቹ ሼካዎች አይነት ዕይታ አላቸው ፡፡ ቤተክርስትን መጥተው ሁላችንንም ሰላምታ ከሰጡን በኋላ እኛን ተቀላቀሉን፡፡ ምን ብለን እሳቸውን ማውራት እንዳለብን እንዴት መጠየቅ እንዳለብን ምንም የምናውቀው ነገር የለም፡፡ አባ ‹‹ልጁ እንዴት ነው›› አሏቸው ‹‹ደህና ነው›› ብለው መለሱ ፡፡ በዚያው አባ የነገሩንን ሁሉ ነገር ከልጁ አባት ደግመን ሰማነው፡፡ እኛም ‹‹ እይዞት አባባ እግዚአብሔር መሐሪ ነው ይምረዋል እያመጡ እዚህ ልጁን ፀበል ያስጠምቁት እግዚአብሔር በፈቀደና በወደደ ቀን ምህረቱን ይልክለታል አይዘኑ›› በማለት ትንሽ ልናፅናናቸው ሞከርን፡፡ እሳቸውም ‹‹እሺ ›› አሉን፡፡ ይህ ልጅ በቅርብ ጊዜ ነበር እግዚአብሔር ምህረቱን ልኮለት ከረዥም ጊዜ በኋላ ሊድንና ወደ መጀመሪያ ጤናማ ሁኔታው ሊመለስ የቻለው፡፡

በጣም ይገርማል. . .በጣም እኔ ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ነገር ሰምቼ ስለማላውቅ በቃ አይኔም ጆሮዬም ልቦናዬም እያንዳንዷን ነገር በማስተዋል ነበር የማየው ፤ የምሰማው ፤ የሰዎችን ስሜት የምመለከተው ፡፡ የቤተክርስትያኑ አስተዳዳሪ ቤተክርስትያኑ ጧፍ ፤እጣን፤ ፤ የቤተክርስትያን መገልገያዎች እንደሚቸገሩና እነሱን እንኳን አሟልተው ማገልገል ከባድና በጣም አስቸጋሪ መሆኑን ነገሩን ፡፡ እኛም መጀመሪያ ከአዲስ አበባ ስንነሳ በረሀ መሆኑን ጧፍ እና እጣን እንደሚቸገሩ ነግረውን ትንሽ ይዘን ነበር፡፡ ከሱ በተጨማሪ ሁላችንም ኪሳችንን ዳበስ ዳበስ አድርገን 700 ብር ያህል አንድ ላይ ከመጣነው ከ30 የማንበልጥ ሰዎች ሰበሰብንና ለቤተክርስትያኗ አስተዳዳሪ አስረከብን፡፡ በጣም ደስ አላቸው አመስግነው ተቀበሉን ፡፡

ከዚያም እንዲህ አሉን
‹ቁልቢ ገብርኤል በዓመት ሁለት ጊዜ ሲከብር በሺህ የሚቆጠር ምዕመንና በሺህ የሚቆጠር መኪና ነው እኛን አልፎ የሚሄደው፡፡ ቢያንስ እንኳን ምንም አያድርጉንል ጧፍም፤ እጣንም ፤ የቤቱ መገልገያም ፤ብርም አይስጡን ፤ ግን ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለን እንኳን አይተውን ቢያልፉ ለእኛ እርሱ ነው ትልቁ ስጦታ ፤ አይዟችሁ ቢሉን ፤ እኛም የእናንተ ወገን ነን ቢሉን ፤ ይበቃን ነበር ብለው ፊታቸው ላይ አንዳች ሀዘን ይዟቸው ረዘም ያለ ጊዜ ዝም አሉ፡፡ እንዲህ ሲሉ ለካ ‹‹አይዟችሁ ቢሉን ፤ እኛም የእናንተው ወገን ነን ቢሉን› ያሉት ነገር ውስጤ ቀርቶ ኖሮ እንባዬ እንኳን በአይኔ ላይ ሲፈስ አላውቀውም ነበር፡፡
ስንት ቤተክርስትያኖች በበረሀ ላይ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ እንደሚኖሩ ለአንድ ጊዜ እንኳን አስበን አናውቅም ፡፡ እኛ ከተማ ላይ የምንኖር ምዕመናኖች የገጠሪቱን ቤተክርስትያን ጧፍ እጣን የቤቱ መገልገያዎችን የማሟላት ግዴታው አለብን፡፡ ስንቶቻችን ነን ግሸን ማርያም፤ አክሱም ፅዮን ፤ ቁልቢ ገብርኤል ስንሔድ መንገድ ላይ ያሉትን ቤተክርስትያኖች ጧፍና እጣን የምንሰጠው? ለአንዲት ደቂቃ እንኳን ያሉበትን ሁኔታ የምናስታውሰው?  ችግራቸው ችግራችን መስሎ የሚታየን ? በየገጠሩ ስንሔድ እንደ ኮራ ገብርኤል በረሀ ላይ ያሉ ምዕመኖች የአፅራረ ቤተክርስትያን ተቋቁመው ሲኖሩ ፤ ካህናት ደግሞ ቅዳሴ ለመቀደስ  ጧፍና እጣን በጣም ይቸገራሉ :: እዚህው አካባቢ የሚገኝ የፃድቁ አባታችን የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤ/ን አንዲት ጧፍ በቅዳሴ ሰዓት አጥተው በጋዝ ብርሀን(ኩራዝ) ወንጌል እንደተነበበ ሲነግሩን በጣም ነው ያዘነው፡፡ ምን ያህል ችግር እንዳለባቸው ለመረዳት ብዙ ነጋሪ አያሻም፡፡ ችግራቸው አንዲት ጧፍ እስከማጣት ይደርሳል፡፡ አንዲት ጧፍ 1ብር ናት ይችም ለካ የምትቸግርበት ጊዜ አለ?  የእነዚህን ቤተክርስትያኖች ችግር የእኛ ችግር አድርገን በመውሰድ የአቅማችንን ብንረዳቸው መልሱን ከእግዚአብሔር እናገኝዋለን፡፡

የሶስተኛው ጓደኛቸው እጣፈንታ ደግሞ የቤተክርስትያኑ አስተዳዳሪ እንዲህ ብለው ነገሩን
‹‹በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም›› ትንቢተ ኢሳይያስ 9፤21 ሶስተኛው የደረሰበት  እንኳን ከቀደሙት ከሁለቱ ብዙም አይለይም እሱም ይህው ጨርቁን ጥሎ ሀገር ጥሎ ከጠፋ ቆየት እንዳለና የት እንደሚገኝ ቤተሰቦቹ እንኳን አያውቁም፡፡ ›› ብለው የሶስተኛውን ወጣት የደረሰበትን ነገር ነገሩን፡፡ ‹‹ተመክሮ ካለመስማት ፤ አይቶ ካለመማር ፤ ሰምቶ ካለማስተዋል ፤ልብን ከማደንደን እግዚአብሔር ይጠብቀን ›› ብለው መከሩን፡፡ምን ይባላል ? እኛ ዝምታን ነበር የመረጥነው፡፡ኦሪት ዘጸአት 32፤9 ላይ ‹‹እኔ ይህን ሕዝብ አየሁት፥ እነሆም አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነው።›› ይላል፡፡  ይህ ሁሉ ነገር በቦታው ላይ ሲደረግ፤ ይህን ሁሉ ተዓምር እግዚአብሔር ቢያሳያቸው ፤ ቤተክርስትያኗን እንዳይተናኮሏት ቢያስተምራቸው ልባቸው አንዴ ደንድኗልና እነሱም ከመተናኮል አርፈው የሚያውቁበት ጊዜ የለም፡፡

እኛ ሁሌ እንበድላለን ፤ ሁሌ እሱን እናሳዝናለን ፤ መደረግ የማይገባቸው ነገሮችን እናደርጋለን እንሰራለን ፤ ለምን ‹‹በደልን ይቅር የሚል›› ትንቢተ ሚክያስ 7፤18 አምላክ እግዚአብሔር የቁጣ ሰይፉን እንዳልመዘዘብን አስበነው እናውቃለን?  ለምን እንደ ሎጥ ሚስት(ዘፍ 19፤27)እንደ ኤሳው (ዘፍ 25፤32)፤ እንደ ዳታንና አቤሮን ፤ ቄሬ ነገደ ሌዊ (ዘኁ 16 ፤1-50)፤ የኤሊ ልጆች (1ኛ ሳሙኤል 2፤11-22) ፤ ንጉስ አዝያን (2ኛ ዜና 26፤16-21) ፤ የናቡከደነፆር ልጅ ብልታሶር (ዳን 5፤1-31) ስናጠፋ የቁጣ ሰይፉን አልመዘዘብንም?

ነገ አይደግሙት፤ ለሰሩት በደል ‹‹ንስሐ ቢገቡ ›› መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 6፤37 በንስሀ ይመለሳሉ ፤ የንስሀ እድሜ ልጨምርላቸው ብሎ እንጂ እንደ እኛ ስራ አይደለም በህይወታችን ላይ ይች ቀን የተጨመረችልን፡፡  ‹‹እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ። ›› መዝሙረ ዳዊት 103፤3 ስለሆነ ነው፡፡  እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጠው 10ቱ ትዛዛት በቀን ስንቱን ስንት ጊዜ እንተላለፋቸዋለን? ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ ይላል፡፡ እኛ ገንዘብ አምላካችን ከሆነ ሰንበትበት ብሏል፡፡ ‹‹ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ባርያ ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላልና ሁለተኛውንም ይወዳል፥ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል። ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።›› የሉቃስ ወንጌል 16፤13 ስለገንዘብ ብለን የማናደርገው ነገር ምን አለ? ከዚህስ በላይ አምላክ ሊሆን የሚችል ምን አለ? በወንጌል እንደተነገረን አንዱ አምላክ የተባለው ገንዘብ መሆኑን ምን ያህላችን እናውቃለን?


ይህን ሁሉ ካየው ከሰማው በኋላ ለራሴ እንዲህ ስል ጠየኩት
‹‹እግዚአብሔር ለምን ይህ ተአምር ሊያሳየኝም ሆነ ሊያሰማኝ ወደደ? ከዚህ በኋላ ከእኔ ምን ይጠብቃል? ገዳም መመላለሴ ጥቅሙ ምንድነው? አሰቦት ገዳም ፤ ዋልድባ ፤ ደብረሊባኖስ ገዳም እያልኩ መሽከርከር? ወደ ህይወት ቀይረህ ካልተጠቀምክበት ፤ ክርስትና ህይወትህን አንድ ደረጃ ከፍ ካላደረገልህ ፤ የበፊት ክፋትህን ትተህ ለህጉ ካልተገዛህለት ፤በንስሀ ህይወት ካልተመላለስክበት ፤ ስጋውን ለመብላት ደሙን ለመጠጣት ካልበቃህበት ፤ ትህንና ፤ ቅንነትን፤ ርህራሄን ገንዘብ ማድረግ ካልቻልክ ምንድነው ጥቅሙ ?›› ለጊዜው መልስ ያላገኝሁለት ጥያቄ ነበር፡፡

በተነገረን ሁሉ  የእግዚአብሔርን ስራ እየገረመን ፤ እነደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሌላ ጊዜ እንደምንመለስ ቃል ገብተን የቦርደ የአቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስን ቤተክርስትያን  ለማየት ተንቀሳቀስን፡፡

ቦርደዴ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን በ12 እና በ13ተኛው ክፍለ ዘመን በኢቲሳ ተክተኃይማኖት የነበረ ፅላት ሲሆን ሙሉ ታሪኩን እንዴት ወደ ቦርደዴ(አዋሽ አካባቢ) ሊመጣ የቻለበትን ሁኔታ ፤ አመጣጡን ፤ መቼ ቅዳሴ ቤቱ እንደከበረ ፤ ቦታው ላይ ስለተደረጉ ገቢረ ተዓምራት ፤ የክርስትያኖቹን ብዛት ፤ የአፅራረ ቤተከርስትያን እያደረሱ ያለውን ፈተና ከቤተክርስትያኑ አስተዳዳሪ ጠይቄ ያወኩትን ለናንተ በሰፊው ለመፃፍ የእግዚአብሔር መልካም ፍቃዱ ይሁንልኝ፡፡አሜን


በነዚህ ጊዜያት ቤተክርስትያኖቹን ማየት ይችላሉ
  • ጥቅምት 29:-  የአባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ እረፍታቸው
  • ግንቦት 27:- የአባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ፍልሰተ አጽም
  • ሀምሌ 10:- የአባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ልደታቸው
  • ጥር 7 እና ሐምሌ 7:-  የአሰቦት ስላሴ አመታዊ ክብረ በአል
  • ጥቅምት 5 :-  የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አመታዊ በአል
  • ታህሳስ 19 እና ሐምሌ 19 ፡ የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በአል 


እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ መፃፍ ጀመርኩ እንጂ አልጨረስኩም በቦርደዴ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ታሪክና የተደረጉ ገቢረ ተአምራትን ደግሞ ቀጥዬ ለናንተው ለመፃፍ የእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ይሁንልኝ፡፡

‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ››

For Donation and additional information call 0913-833532

16 comments:

  1. አሜን ቃለ ህይወትን ያሰማልን፣ እኛም የሰማነውን ለህይወታችን እንድንጠቀምበት የአምላካችን መልካም ፈቃድ ይሁንልን።

    ReplyDelete
  2. AMEN kale hiyiwet yasemalin tesifa menigisite semayatin yawirisilin. Legnam asabi libunan yadilen.

    ReplyDelete
  3. ርብቃ ከጀርመንNovember 8, 2011 at 9:25 AM

    ሰላም አንድ አድርገኖች የምታቀርቡት ጽሁፍ እጅግ በጣም የሚያሳዝን እና በገጠሩ የሀገራችን ክፍል ቤተክርስትያናችን ያለችበትን ሁኔታ ቁልጭአድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ በጣም ተወዳግ ያደርጋችሁ ነገርነው በርቱ እማምላክ ስራችሁን ድካማችሁን ትባርከላችሁ የቅዱሳን አምላክ ቤተክርስትያንን ከቀሳጥያንና ካህዛብ ምክር ይጠብቅልን!

    ReplyDelete
  4. thanks wondmachin. kale hiwot yasemaln

    ReplyDelete
  5. amen kaleyiwot yasemalen, please please please tell us more, it really shows us the practical committment of our fathers, mothers, elder brothers and sisters to the orthodox tewahedo betekerestian even now a days.

    ReplyDelete
  6. KALE HIYWET YASEMALN EGZIABHER YITEBKEN AMEN.

    ReplyDelete
  7. ቃለ ህይወት ያሰማል

    ከቻላችሁ አንድ ጉዞ አዘጋጁ ብዙ ሰውም በብሎጋችሁ አማካኝነት ለማግኘት ስለምትችሉ። ከተጓዘዡም ጋር በቋሚ ንብረት ወይም ገቢ እንዲኖር ወይይት ተደርጎ ገቢ የሚሰባሰብበትን ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ ቢጀምር በአንድ አመት ፕሮጀክት ተደርጎ ተጓዘዡ አስራቱን እያወጣ ገቢ ማስገኛ እያካሄደ ቢከናወን መልካም ነው እላለሁ። ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን የሚችል የተሻለ ሀሳብ የሚያመጡና የማስፈፀም ብቃት ያላች ወንድሞችና እህቶች እንዳሉ አምናለው። ያለ አንድ ጻድቅ አገርን(ቤተክርስትያንን) አይተውምና። በተናጠል የምናደርገው ደጋፍ አመርቂ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም።

    ወስብሐት ለእግዚአብሔር
    ኪዳነማርያም ዘደብረይድራስ
    kidargaw@gamil.com

    ReplyDelete
  8. kale heiwet yasemahe.ende ene lalu betekerestyan bakabayachew lelele sedetegoche metenaga kale new.ebakachehu atakwaretuben.hulunem neger asawekun.tigist from canada.

    ReplyDelete
  9. ቢያንስ እንኳን ምንም አያድርጉንል ጧፍም፤ እጣንም ፤ የቤቱ መገልገያም ፤ብርም አይስጡን ፤ ግን ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለን እንኳን አይተውን ቢያልፉ ለእኛ እርሱ ነው ትልቁ ስጦታ ፤ አይዟችሁ ቢሉን ፤ እኛም የእናንተ ወገን ነን ቢሉን ፤ ይበቃን ነበር

    ReplyDelete
  10. kale hiwot yasemalin

    ReplyDelete
  11. kale hiwot Yasemalen Be edme ena betsga yetebikilen

    ReplyDelete
  12. Kale hiwot Yasemalen be edme ena betsega yetebikilen

    ReplyDelete
  13. kale hiwoten yasemalen yesemanewen belebachen yasadereben lenatem yagelegelote zemenachehun yarezemelachu tsegaeen yabezalachu

    ReplyDelete
  14. solomon beshahwredJuly 5, 2014 at 1:35 PM

    Amen kale hiwot yasemalin, be ewnet betam yemigerm teamir new..Egziabher betekrstiyanuwan yitebik!

    ReplyDelete