ትናንት የማደራጃ መምሪያው ዋና ሓላፊ እንዲሆኑ ‹በፓትርያሪኩ እና በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ስምምነት ተመርጠዋል› የተባሉት አባ ኅሩይ መሸሻ መምሪያውን በሲኖዶሱ ከተላለፉት ውሳኔዎች አኳያ አስተባብሮ የመምራት ጉዳይ ጥያቄ ቢነሣባቸውም ለጊዜው የተሰማባቸው ለውጥ እንደሌለ ተጠቁሟል፡፡
ዛሬ ከቀትር በፊት በነበረው የስብሰባው ማጠናቀቂያ ላይ በተላለፈው በዚሁ ውሳኔ የፓትርያርኩ የምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅነት ሹመት ሐሳብ በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት በቋሚ ሲኖዶስ ተመርጦ እስኪቀርብ ድረስ እንዲቆይ፣ የቀድሞው ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ኤልያስ ግን ቀደም ሲል እንደተገለጸው ወደ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት በሥራ አስኪያጅነት የመዘዋወራቸው ጉዳይ አይቀሬ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 25/2004 ዓ.ም)
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
No comments:
Post a Comment