Monday, November 7, 2011

አሁንስ የአምላክን እጅ ናፈቅን


  • አቡነ ጳውሎስ አባ ሰረቀን የጠ/ቤ/ክ/ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾሙ
  • ሹመቱን የተቃወሙት ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ መልቀቂያ አስገቡ!!!
  • አቡነ ሕዝቅኤልም ከዋና ጸሐፊነት በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለፓትርያርኩ ለማስገባት በዝግጅት ላይ ናቸው::
  • የሹመቱ ደብዳቤ ፓትርያርኩ በሚቆጣጠሩት ጽ/ቤት በኩል የወጣ ነው::
(በሸዊት ገ/ኪዳን; http://www.gebrher.com ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ እና የኢሉባቦር እና ጋምቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ‹‹ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በማይከበርበት ሁኔታ ሥራ አስኪያጅ ሁኜ አልቀጥልም›› በማለት በራሳቸው ፈቃድ ከሥራ አስኪያጅነት መልቀቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ዛሬ ጠዋት ለፓትርያርኩ በእጃቸው አስረክበዋቸዋል፡፡ ይህን ዜና እያጠናቀርን ባለንበት ሰዓት ፓትርያርኩ ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስን በመጥራት ሃሳባቸውን ለማስቀየር እየተነጋገሩ ይገኛሉ፡፡


ከአባ ሠረቀብርሃን ሹመት ጋር በተያያዘ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤልም ከዋና ጸሐፊነት በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለፓትርያርኩ ለማስገባት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል መልቀቂያ ከማስገባታቸው በተጨማሪ የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባዔ ይጠራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ታዛቢዎች ድርጊቱ የፓትርያርኩ አምባገነንነት የት እንደረሰ እና ባልቴት እጅጋየሁ የሚመሩት አጉራ ዘለል ቡድን የቤተክርስቲያኗን መዋቅር ምን ያህል እንደተቆጣጠረው የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 27/2004 ዓ.ምባለባቸው ከፍተኛ የአቅም ማነስ እና በተጠረጠሩበት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነት ሤራ ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊነት ተወግደው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በሚገኙበት የሊቃውንት ጉባኤ ምርመራ እንዲካሄድባቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተወሰነባቸው አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ዛሬ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው መሾማቸውን የሚገልጽ ደብዳቤበፓትርያሪኩ ማኅተም እና ፓትርያሪኩ በብቸኝነት በሚቆጣጠሩት ልዩ ጽ/ቤት በኩልደርሷቸዋል፤ ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሹመቱን በአድራሻ ለ‹አባ› ሰረቀ በደረሳቸው ደብዳቤ ግልባጭ እንዲያውቁት መደረጉ ተዘግቧል፡፡
ሕገ ቤተ ክርስቲያንን፣ የቋሚ ሲኖዶስን እና የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤን ሥልጣን ባስተሐቀረ ሁናቴ ለተጠርጣሪው አባ ሰረቀ የተሰጠውን ሹመት አጥብቀው ሲቃወሙ የቆዩት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በቅዱስ ሲኖዶስ ከተሾሙበት የጠቅላይ ሥራ አስኪያጅነት ሥልጣናቸው እንደሚለቁ ተናግረዋል፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 29 ንዑስ አንቀጽ አራት መሠረት ሦስት ዓመት የአገልግሎት ዘመን ያላቸውና ለተጨማሪ አንድ የምርጫ ዘመን መቆየት የሚችሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ አባ ሰረቀን የመሾም ጉዳይ ከተነሣበት ጊዜ ጀምሮ ተቃውሟቸውን ሲያቀርቡ መቆየታቸው ታውቋል - ልዩነታቸው እንደ ዛሬው በግልጽ ጎልቶ/louder and bolder/  ባይሰማም፡፡

የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ በሚጠናቀቅበት ዋዜማ፣ ጥቅምት 24 ቀን 2004 ዓ.ም፣ አባ ሰረቀን ምክትል ሥራ አስኪያጅ ለማድረግ ሐሳብ ላነሡት አቡነ ጳውሎስ “አይሆንም”የሚል ተቃውሞ ላሳዩት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ፣ “እኔ አዝዛለሁ፤ የማዝዘው እኔ ነኝ” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ምንጮች ተናግረዋል፡፡ አቡነ ፊልጶስም፣ “የሚያዝዙት እርስዎ ከሆኑ እኔ ለሾመኝ ሲኖዶስ ሥልጣኔን አስረክባለሁ፤ አባቶች ሳይሄዱ [የምልአተ ጉባኤው ስብሰባ ሳይጠናቀቅ ማለታቸው ነው] የሚሆን ም/ሥራ አስኪያጅ እንሹም” የሚል ጥያቄ አዘል ምላሽ ያቀርባሉ፡፡ ሌሎችም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም፣ “የሃይማኖት ችግር እያለባቸው አንሾማቸውም፤ ሃይማኖቱን ነው እንጂ ቅድሚያ የምንመረምረው ሥራ አንሰጠውም፤ ስንኳን ም/ሥራ አስኪያጅ ሊሆን ስድስት ዓመት ሙሉ የሠራው ሥራ የለም፤ ከማበጣበጥ በቀር፡፡ ሥራው ይህን የሚያጠናው ኮሚቴ ሪፖርት ካቀረበ በኋላ የምናየው ነገር ነው” በማለት ከብፁዕ ሥራ አስኪያጁ ጎን ቆመው እንደ ነበር ተገልጧል፡፡
አቡነ ጳውሎስ እና አቡነ ፊሊጶስ (በመካከል ያሉት አቡነ ገሪማ ናቸው)
በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ሰባት ንኡስ አንቀጽ 15 መሠረት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅንና ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅን፣ የልማት ኮሚሽን ኮሚሽነርን፣ የውጭ ጉዳይ መምሪያ ሓላፊንና የልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎችን ቦርድ አባላት እየመረጠ የመሾም የቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣንና ተግባር እንደሆነ ተደንግጓል:: ፓትርያሪኩ ይህን ሕግ ተላልፈው ለ‹አባ› ሰረቀ የማይገባቸውን ሥልጣን ቢሰጡም ከሕገ ወጡ ተሽዋሚው ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጋራ የተያያዘውን ሂደት በተመለከተም ያለሥልጣናቸው በሰው ኀይል አስተዳደሩ ላይ ጣልቃ በመግባት መጨረሻ የሌለው ስሕተት መሥራታቸውን ይቀጥላሉ፡፡

ይኸው የአባ ሰረቀ ሕገ ወጥ ሹመት ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ከምልአተ ጉባኤው ስብሰባ አስቀድሞ ጀምሮ፣ በስብሰባው ሂደት እና ፍጻሜ ለሕገ ቤተ ክርስቲያን እና ለቅዱስ ሲኖዶሱ ሥልጣን ባለመገዛት፣ የተለያዩ የማዳከሚያ ስልቶችን በመጠቀም እንደ አባ ሰረቀ ያሉ ጥቅመኛ እና በሃይማኖታዊ ደዌ የተለከፉ ግለሰቦችን በመከላከል የሚያሳዩትን ያልተገባ አቋምና አካሄድ ወደ ከፋ ደረጃ ያደረሱበት አሳሳቢ ሁኔታ ተደርጎ ተወስዷል፤ ከፕሪንስተን ኮሌጅ የፒ.ኤች.ዲ የመመረቂያ ጽሑፋቸው ጋር በተያያዘ ወደ ራሳቸው ወደ ፓትርያሪኩ የሚያነጣጥርና በሃይማኖታዊ ሕጸጽ ከአባ ሰረቀ ጋራ የሚያመሳስላቸው ሌላም የሚፈራ ነገር መኖሩ አልቀረም፡፡

አባ ሰረቀ
አባ ሰረቀ ከሓላፊነታቸው ተወግደው ምርመራ እንዲካሄድባቸው ከተወሰነባቸው ቀን አንሥቶ “በበሉበት ሆዳቸው የወሰኑት ውሳኔ ነው” እያሉ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ስም በየመንገዱ ሲያጠፉ ሰንብተዋል፤ በአንዳንዶቹ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ማረፊያ ቤት ጎራ እያሉም ለሊቃነ ጳጳሳቱ ‹ጉቦ አብልቶ አስወሰነብኝ› በሚል የሚከሱትን ማኅበረ ቅዱሳንን “የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እና የዘርዐ ያዕቆብ ናፋቂ ነው” በሚል ሲወነጅሉ መደመጣቸው ታውቋል፡፡ 
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነገረ መለኮታዊ ይዘቱ ተደፍቆ የወቅቱ ፖሊቲካዊ ቀለም የተሰጠው ይኸው የውንጀላ አነጋገራቸው ዐይነተኞቹ መናፍቃንና መፍቀሬ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎጎች ከሚያቀነቅኑት ጋር በይዘቱ አንድ መሆኑን ልብ ይሏል፤ በሕገ ወጥ መንገድ በሚያገኙት ሥልጣናቸው እንዲቀጥሉ ከተፈቀደላቸውም የመጀመሪያ ዒላማቸው ማኅበረ ቅዱሳንንና ከማኅበሩ ጋር ፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ የሚያካሂዱ አደረጃጀቶችን የማዳከም የቤት ሥራን ማከናወን እንደሚሆን የታዛቢዎች አስተያየት ይጠቁማል፡፡
በጉዳዩ ላይ ከመጪው ኅዳር ወር ጀምሮ እስከ ጥር መጨረሻ የሚቆየውና አቡነ አረጋዊ፣ አቡነ ስምዖን፣ አቡነ ዮሴፍ እና አቡነ እንድርያስ በአባልነት የሚገኙበት ቋሚ ሲኖዶስ ምን አቋም እንደሚወስድ ለማወቅ ባይቻልም አሁን የሥራ ጊዜውን በማጠናቀቅ ላይ የሚገኘው ቋሚ ሲኖዶስ፣ ያለጽ/ቤቱ እና ዋና ጸሐፊው ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ዕውቅና ስለተፈጸመው የማናለብኝነት ድርጊት ከአቡነ ጳውሎስ ጋራ ከፍተኛ ንትርክ እንደሚጠብቀው ተገምቷል፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስም ሥልጣን ከመልቀቅ ይልቅ፣ የ‹አባ› ሰረቀ ሹመት ሕገ ወጥ መሆኑን በመግለጽ ለመንግሥት ደብዳቤ እንዲጽፉ፣ ግለሰቡ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ለሃያ አራቱም መምሪያዎች እና አህጉረ ስብከት ሰርኩላር ደብዳቤ እንዲያስተላልፉ፣ የሹመቱን ደብዳቤ ውድቅ በማድረግ ‹አባ› ሰረቀን ከሥልጣን እንዲያግዱ፣ በሕገ ወጥ ሹመታቸው አንዳችም ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም እንዳያገኙ ማድረግ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

የሆነው ሆኖ ፓትርያሪኩ ያለተጠያቂነት በጥፋት ጎዳና/Impunity/ ተጨልጠው በቀጠሉበትና ዛሬ ከቀትር በኋላ ለ‹አባ› ሰረቀ የቤተ ክህነቱን ከፍተኛ የሥራ አስፈጻሚ ሥልጣንበመስጠት ባሳዩት ወደር የለሽ ዕብሪት ከፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ቤተሰቦች/አካላት የማያባራ ተቃውሞ እንደሚጠብቃቸው፣ ዋጋም እንደሚከፍሉበት እየተገለጸ ነው፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

6 comments:

  1. «ዛሬ ካለው የቤተ ክርስቲያን አመራር ጋራ ወደ ትግል ሰልፍ እንድገባ ያደረገኝ የኔ ፈቃድ፥ ዐቅምም አይደለም። በ፲፱፻፹፭ ዓመተ ምሕረት ሐምሌ ፭ ቀን ኦፕራሲዮን ሆኜ በሰመመን ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ በሥርዓተ ሙታን ወደ አምላኬ ፊት ቀርቤ የተሰጠኝ ትእዛዝ ነው። በዚያች ሰዓት፤ ከቅዱስ ማርቆስ እስከ ሳድሳዊ ቄርሎስ የነበሩ የእስክንድርያ ፓትርያርኮችና ሊቃነ ጳጳሳት፤ ከአትናቴዎስ፥ ከሰላማ እስከ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የነበሩ የኢትዮጵያ ሊቃነ ጳጳሳትና ፓትርያርኮች የእሳት ነበልባል በከበበው፥ የእሳት ልሳን ያለው መጋረጃ በተንጣለለበት በዚያ አዳራሽ፥ በዚያ የግርማ ዙፋን ግራና ቀኝ ተሰልፈው ቁመው ነበር። በኤፌሶን ጉባኤ ንስጥሮስን ያወገዘው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ቄርሎስ በመንበሩ ፊት ለፊት ቆሟል። ቀድሞ የተወገዘው ንስጥሮስ የማዕረግ ልብሱን ተገፎ በስተጀርባው ቆሟል። አባ ጳውሎስ በማዕረጋቸው እንዳሉ ተከስሰው ከንስጥሮስ ጎን ቁመዋል። በዐጸደ ነፍስ የሚገኙት የእስክንድርያና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አበው፤ «አባ ጳውሎስ ሺ ስድስት መቶ ዓመት የኖረ ውግዘት ጥሰው፥ በሥጋው በደሙ የማሉትን መሓላ አፍርሰው የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን የሮም ቅኝ ግዛት ስላደረጉ፤ ፍርድ ይሰጥልን፤» ሲሉ ለኀያሉ አምላክ አቤቱታ አቀረቡ። ከዙፋኑ የመጣው መልስ ግን፤ «እስከ ዕለተ ምጽአት ፍርድ የቤተ ክርስቲያን ነው፤» የሚል ነበረ። ይህ ሁሉ በሚከናወንበት ጊዜ የማላውቀው ኀይል ከዚህ ዓለም ነጥቆ ከቅዱስ ቄርሎስ ጎን አሰልፎኝ ከቆየ በኋላ ከዙፋኑ የመጣው ድምፅ፤ «አንተ ያየኸውን፥ የሰማኸውን ለቤተ ክርስቲያን፥ ለምእመናን ንገር፤» ሲል አዝዞ ወደ ነበርኩበት መለሰኝ። ይህ ትእዛዝ ነው እዚህ ሰልፍ ውስጥ ያስገባኝ። ኢትዮጵያዊ፥ ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉም ስለ ቤተ ክርስቲያኑ አጥብቆ መታገል አለበት።» አለቃ አያሌው ታምሩ።

    ReplyDelete
  2. By Aleqa Ayalew Tamiru(the true martyr of this age. )

    ReplyDelete
  3. we all say something or write just to express our anger and sadness. But why someone doesn't organize us and do something fruitful instead of just talking and talking. Can someone(who can reach a lot of christians) please do something to do something organized that can bring change? Zim belen mekatel bicha honeko negeru.

    ReplyDelete
  4. ርብቃ ከጀርመንNovember 8, 2011 at 9:39 AM

    የቅዱሱ አባታችን ያባጊዮርጊስ አምላክና የዘረያእቆብ እመቤት የድንግል ማርያም ልጅ እውነትን ይፍረድባቸው እንዲህ በቤተክርስትያን ላይ እንደዘበቱባት ከጸረማርያሞችጋር ወግነው እንደወጉዋት እንዲቀጥሉ የምንተዋቸው እስከመቸእንደሆነ ነው ያልገባኝ?

    ReplyDelete
  5. አይዞአችሁ የናፈቃችሁት የአምላካችሁ እጅ በቅርብ ዘመን ለያንዳንዳችሁ ትገለጣለች፡፡ እግዚአብሔር በሥራ ላይ ነው፡፡ እንደዚሁ በብዥታ አትኖሩም፡፡ እውነቱ አንድ ቀን ለሁላችሁም ይገለጥላችኋል፡፡ በሐዋ ሥራ 9፡1 ላይ ሳዉል (በኋላ ሐዋሪያው ጳውሎስ የተባለው) ስለ ህግና ስለ እግዚአብሔር ቀንቶ የክርስቶስን ሐዋሪያት ሲያሳድድና ሲገድል ነበር፡፡ ተመልከቱ፤ ሳውልን ለምንድነው ይህንን ምታደርገው ቢትሉት ስለ እግዚአብሔር ነው ብሎ ነው ምመልስላችሁ፡፡ ይህ እግዚአብሔርን ስለ እግዚአብሔር ማሳደድ ይባላል፡፡ ስለዚህ እናንተም እንደዚህ የምትሉት አሁን ስለ ክርስቶስ ቀንታችሁ ስለቤተክርስቲያን ተቆርቁራችሁ ይመስላችኋል፤ ከእግዚአብሔር ከራሱ ጋር እየታገላችሁ እንደሆነ አላወቃችሁም፡፡ ይህንን የተሐድሶ ሥራ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የጀመረው ጌታ እራሱ ነው፡፡ ስለዚህ ልትቋቋሙት አትችሉም፡፡ የጀመረው እሳት መቼም አይጠፋም፡፡ ሊታጠፉት ቢትሞክሩ እንኩዋን ይጨምራል እንጂ አይጠፋም፡፡ ምክንያቱም ሰው አይደለም የጀመረው፡፡

    ReplyDelete
  6. አይዞአችሁ የናፈቃችሁት የአምላካችሁ እጅ በቅርብ ዘመን ለያንዳንዳችሁ ትገለጣለች፡፡ እግዚአብሔር በሥራ ላይ ነው፡፡

    ReplyDelete