Wednesday, November 23, 2011

አባ ሰረቀብርሃን በሎስ አንጀለስ ምን አይነት ሰው ነበሩ?

 • ታቦት ሰርቀዋል ፤ ተይዘዋል፡፡
 • ከገዛናቸው 12 ጸናጽል ያስረከቡን ስድስቱን ሲሆን ፤ ከ 12ቱ መቁዋሚያም 6ቱን ይዘውብን ሄደዋል፡፡
አባ ሰረቀ ማን ናቸው? ከዚህ በፊት ያልተሰሙ ወሬዎች ያንብቡት
ምንም እንኳን የሰሩት ሥራ ያደረጉት አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባር አንቱ ለማለት ቢያስቸግርም የቤተክርስቲያናችን ሥርዓት፣ የሀገራችን ባህል አስገድዶኝ አንቱ በማለቱ እቀጥላላልሁ ። አባ ሰረቀ ብርሃን (እዚህ ባለሁበት ሎሳንጀለስ ከተማ) ታቦታቸውንና ንዋያት ቅዱሳታቸውን ዘርፈዋቸው ስለሄዱ አባ ሰራቂ በማለት ይጠሯቸዋል ። አንዲ የቤተክርስቲያናችን አዛውንትማ ስማቸው እንኳን ሲጠራባቸው ነው የሚያንገሸግሻቸው። 

ወደ ዋናው ቁም ነገር ልግባና አባ ሰረቀ በሎሳንጀለስ እንዴት ነበሩ የሚለውን እስኪ እንመልከት፦ 

አባ ሰረቀ ብርሃን በ1993 መስከረም ላይ ከኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ይህንን መረጃ የሰጡን አባት እንዲህ ያጫውቱናል። ‹‹አባ ሰረቅ ብርሃንን ለማስመጣት ሂደቱን የጀመእኩት እኔ ነኝ። በ1993 እ.ኤ.አ. የእህቴን ባል እባክህ ጥሩ ካህን የተማረና ሰዎችን የሚያስተምር ሰው ፈልግልን ብዬ ነገርኩት። እርሱም ወዲያው አንድ በጣም የተማሩ ሰው አግኝቸልሃልሁ ብሎ አጫወተኝና (በኢትዮጵያም ክረምት አካባቢ ነው) ደስ አለኝ። ደውዬም እንዳነጋግራቸው አመቻቸልኝና አባ ሰረቀን ድውዬ አገኘኋቸው። እርሳቸውም ለመምጣት እፈልጋለሁ ግን ለመጉዋጓዣ 2000 ዶላር ያስፈልገኛል ብለው ነገሩኝ። እኔም ቦርዱን አስፈቅጀ የመምጫቸውን ሁኔታ ጀመርን።2000 ዶላርም ተላክላቸው። ››

በኋላም ስለመምጫቸው ተነጋግረን ንዋያተ ቅዱሳት (ጽናጽልና መቋሚያ ) እንዲሁን ጽላትም ጭምር እንደሌለን ስነግራቸው፤ ሁሉንም ማግኘት እንደሚችሉ፤ ነገር ግን ተጨማሪ 1000 ዶላር እንደሚያስፈልግ ነገሩኝ። ያንንም ቦርዱን አስፈቅጀ ላኩላቸው።  መስከረም 1993 እ.ኤ.አ. 12 ጸናጽል፣ 12 መቋሚያና ጽላት ይዘውልን ሎሳንጀለስ ገቡ። እኛም አባት ናፍቆን ስለነበረ ምንም እንኳን ያወጣነው ወጭ ብዙ ቢሆንም በደስታ ተቀበልናቸው። ስላሁሰንና ዌስት (between Slauson and West) ላይ አንድ የአድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ተከራይትን አገልግሎት ማግኘት ጀመርን። 

ትንሽ ቆይቶም አባ ተከስተ የሚባሉ መነኩሴ (የዛሬው ብጹእ አቡነ ሣᎀኤል) ወደዚህ እነደሚመጡ ተነገረንና እኔው ተቀብዬ አብረው መኖር ጀመሩ። የሚገርመው ግን አባ ሰረቀ ከሰው ጋር ተስማምቶ መኖርን ስለማይፈልጉ፤ አባ ተከስተ ጋር አለመግባባት ፈጠሩና አባ ተክስተ ወደ ሌላ ስቴት ሄዱ። 

ከዚያም እርሳቸውም ብቻቸውን እንዳይሆኑ በማለት ሳንሆዜ የነበረ አንድ ይሥሐቅ የሚባል አገልጋይ ልናመጣልዎት ነበር ብንላቸው ያሉንን እስከ አሁን አስታውሰዋለሁ (እኔ ቤት አንድ ሰው አይገባም ነበር ያሉት።) ያን ጌዜ ነበር አባ ሰረቀ ላይ የነበረው እምነታችን እየተሸራረፈ የመጣው። እንደምንም አግባብተን ልጁን ብናመጣውም አሁንም እርሱም የአባ ተክስተ እጣ ደርሶት አባረሩትና ሄደብን። 

መቼም የኛ ቤተክርስቲያን ታሪካዊ ነችና ከአሪዞና አባ ወልደ ሰንበት የሚባሉ አንድ መነኩሴ ደግሞ አስመጣንላቸው። ለካስ ሁለቱም መሰሪ ነበሩና የሚከተለውን ምእመናን የማይረሱትን አሳዛኝ ሥራ ሰሩ። 

አንድ እሁድ ነው አስታውሳለሁ አባ ስረቀና አባ ወልደ ሰንበት ቅዳሴ ቀድሰው ሲያበቁ አባ ሰረቀ ለእኔና ለጓደኞቸ “አባ ወልደ ሰንበት ወንድሙ ስላረፈ ልናረዳው ነው ምን ትላላችሁ” አሉ። እኛም አዝነን አሁን ቅዳሴ ቀድሰው ከምንነግራቸው ለምን ሳምንት ወይንም ነገ አንነግራቸውም አልናቸው። እርሳቸውም እሽ ብለው እኛን ከላኩ በኋላ ረድተዋቸው ነበርና ወዲያው ደውለው አርድቻቸዋለሁና ኑ ተባልን በጣም ሁላችንም ተመልሰን መጣን ። እውነት መስሎን በጣም አዝነን አባ ወልደ ሰንበትንም አጽናንተን ተመለስን። ከዚያም ወደ ሀገራቸ መመልስ እንደሚፈልጉ አባ ሰረቀ ነገሩን እኛም አዝነን ያለንን አዋጥተን ላክናቸው። ትዝ የሚለኝ ለቤተሰቦቻቸውም አምነዋቸው ብር አድርሱልንም ያሉ ሰዎች ነበሩ። ግን አባ ወልደ ሰንበት ሳያደርሱላቸው ብራቸውን በልተው ቀርተዋል። 
ከትንሽ ጊዜ ቆይታ በኋላ የአባ ወለደ ሰንበትን እህት ወይዘሮ አብርኸትን የሚያውቅ አንድ የቤተ ክርስቲያናችነ አባል፤ አዲስ አበባ ሄዶ ወይዘሮ አብርኸትን ያገኝና እባክሽ የወንድማችሁን መሞት ሰምተን እኮ አባን አጽናናቸው ቢሏት የምን ወንድም ነው የምታወራው ትለዋለች። ለካስ አባ ወልደ ሰንበት ወድማቸው ሞተ ትብሎ የተነገረው የውሸት ኑሯል። አባ ሰረቀና እርሳቸው የፈጠሩት ወሸት። ከዚያ በኋላ ይኸው አባ ወልደ ሰንበት ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ እንደዘገበው በወቅቱ የአሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት አቡነ ማትያስ ማኅተም ወስደው በነጭ ወረቀት ላይ እያተሙ የኔን ፊርማ እያስቀመጡ ሰዎችን ብር እየተቀበሉ ከኢትዮጵያ ወደዚህ ሲያመጡ ተደርሶባቸው መጀመርያ ወደ ጀርመን አሁን ደግሞ መቼም ጅብ በማያውቁት ሀገር እንደሚባለው በገለልትኞች ሲኖዶስ ጳጳስ ሆነው ካናዳ ይኖራሉ። 

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ፤ አባ ሰረቀ አባ ወልደ ሰንበትን እንዲህ አድርገው ከአጠገባቸው ካራቁ በኋላ ከቤተ ክርስቲያን አባልት ጋር መግባባት አልቻሉም። ከእለታት አንድ ቀን እንደውም ‹‹ቤተክርስቲያን የለችም ፤ አቡነ አረጋዊም የሚባል ቤተክርስቲያን የለም ፤›› በማለት ሲስብኩ አስታውሳለሁ። ይህ በእምነታችን የሌለ ኑፋቄ ነው። ከዚያም በኋላ ከቤተክርስቲያናችን ተለይቶ የአቡነ ጳውሎስ እንደራሴ ነኝ ፤ እኔ ማንንም መነኩሴ ጳጳስ እንዲሆን አስደርጋለሁ ከሚለውና እዚሁ ሎሳንጀለስ ከሚኖረው ቄስ ጋር ገጠሙና ከእኛ ጋር መጣላት ጀመሩ። ከዚያም አቡነ ማትያስ ለጥቅምት አቡነ አረጋዊ ሲመጡ ምእመናን ክስ አቀረቡ። ውይይቱ የተደረገው ከእነ አቶ ዕቁበ ጽዮን ቤት ነበር። ብጹእ አባታችንም ቢመክሩዋቸው አልሰማ አሉ። አባ ሰረቀንም ብጹእ አቡነ ማትያስ ምእመናኑ ምንም አልበደሉምና ‹‹ተሳስባችሁ አብራችሁ ኑሩ›› ቢሉዋቸው አባ ሰረቀ ከአሁን በኋላ እዚህ አላገልግልም እንደውም ያሉት ቃል ትዝ ይለኛል። “ብርሌ ከነቃ…” አሏቸው። 

ብጹእ አቡነ ማትያስም እንግዲያውስ እናንተም ሌላ ካህን ፈልጉ እርሳቸውንም መጉዋጉዋዣ ከፍላችሁ ላኳቸው እርሳቸውም ንዋያተ ቅዱሳቱን፤ ታቦቱን ጭምር ያስረክቧችሁ (ይህንንም በዚያን ጊዜ አባ ኢሳይያስ- የሳንዲያጎ ገብርኤል አስተዳዳሪ የነበሩ- የአሁኑ ብጹእ አቡነ ኢሳይያስ ያረካክቡዋችሁ ተባለ)።  እኛም አዝነን እሽ ብለን 700 ዶላር ከምዕመናን ሰበሰብንና ዶ/ር ኃይሉ ፤ አቶ ጥላሁንና አንድ ሌላ ሰው ወክለን አባ ኢሳይያስን ይዘው እንዲረከቡ ላክናቸው። 

ከዚያም አባ ሰረቀ በለመዱት አንደበታቸው የተወከሉ ምእመናንን ታቦቱን ነው የያዝኩት ብለው ብሪፍ ኬዝ ይዘው መጡና ፤ ይህንን ለመነኩሴው ለአባ ኢሳይያስ ብቻ ነው የማስረክበው በማለት ወደ ውስጥ ሁለቱ ብቻ ገቡ። ብዙ ቆይተው ሲወጡ አባ ኢሳይያስን የተወከሉት ሰዎች ‹‹ታቦቱን ተረከቡ ወይ›› ሲሉዋቸው “ታቦት ተረከብኩም አልተረከብኩም አይባልም” አሉዋቸው። 

ተወካዮችም ግራ ግብቷቸው ሲመለሱ አባ ኢሳይያስም ፤ ለብጹእ አቡነ ማትያስ ደውለው ታቦቱን እንዳልተረከቡ እንደውም ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ አባ ሰረቀ ብሪፍ ኬዙን ሳይከፍቱ ይረከቡ ይሏቸዋል። አባ ኢሳይያስም ይክፈቱት እንጂ እንዴት ዝም ብዬ እረከባለሁ ይሉና ተቀብለው ቢከፍቱት የተገኘው ታቦት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ፤ ከዚያም አባ ሰረቀ እግራቸው ላይ ወድቀው ‹‹እባክዎን አልተቀበልኩም ብለው ለተወካዮች አይንገሩብኝ፤ ታቦቱን ዲሲ ልኬዋለሁ እዚያ ሄጄ ለአቡነ ማትያስ እሰጣለሁ ወይንም እልከዋለሁ›› ብለዋል ይሏቸዋል። 

ይህንን ነገር አቡነ ማትያስ ሲሰሙ በጣም አዝነውና ተናድደው ነገሩን ምእመናን እንዲሰሙ ያደርጋሉ። ሁለቱም አባቶች (አቡነ ማትያስና አቡነ ኢሳይያስ በሕይዎት ስላሉ ህያው ምሥክር ናቸውና ስለ እውነትነቱ እነሱው ሊጠየቁ ይችላሉ።) ከገዛናቸው 12 ጸናጽል ያስረከቡን ስድስቱን ሲሆን ፤ ከ 12ቱ መቁዋሚያም 6ቱን ይዘውብን ሄደዋል። ምእመናንም በዚህ ተናድደን ያዋጣነውን ገንዝብ ሳንሰጣቸው ቀርተናል። 

ከሁሉ የሚገርመኝ ሲሄዱ አንዲት ምዕመን ለቤተ ክርስቲያን የሰጠችውን ሰንና ብርት ይስጡን ብለን ስንጠይቃቸው፤ መልሳ ወስዳዋለች አሉን። ይህ ሁሉ እንግዲህ በሎሳንጀለስ የነበራቸው ታሪክ ነው። 

አንድ መነኩሴ ከሰረቀ፤ ከዋሸ፤ ከቤተክርስቲያን ይልቅ ስልጣን ፤ገንዝብና ፤ ክብርን ከፈለገ እንዴት መነኩሴ ይሆናል። በአሁኑ ሰዓት የሚያደርጉት ብጥብጣ እኔ ከአባ ሰረቀ የማልጠብቀው አይደለም። እርሳቸው፤ ከሰው ጋር ተስማምተው የማይሰሩ፣ የሚዋሹና ፤ በሃሰት ማንኛውንም ኃጢያት ሁሉ ሊሰሩ የሚችሉ ሰው ናቸው። ለዚህ ደግሞ አቡነ ማትያስ በአሁኑ ሰዓት የኢየሩሳሌም ሊቀጳጳስ፣ አቡነ ሣᎀኤል፤ አቡነ ኢሳይያስ ህያው ምስክሮች ናቸውና ፡፡ እነሱን በመጠየቅ ወይንም ለእኔም በመደወል የበለጠ መረጃ ማግኝት ይቻላል ብለውናል። 

በአጠቃላይ አባ ሰረቀ፡ 
1. ለእምነታቸው ሳይሆን ለሆዳቸውና ለገንዘብ የሚኖሩ
2. ካለ ፍርኃት የሚዋሹ
3. ካለ ሃፍረት የሚሰርቁ
4. ከሰው ጋር ተባብረውና ተግባብተው መኖርን የማያውቁ ሰው ናቸው። 
እርሳቸው ከሄዱ በኋላ ስድስት ወራት ሙሉ ካለ ካህን እሁድ እሁድ ምእመናን ብቻችንን ተሰብስበን አቶ እቁባይ መጽሐፍ ቅዱስ እያነበቡልን እንበተን ነበር። በኋላ ይኼው እስከ አሁን የሚያገለግሉንን ታላቅ አባቶች አግኝተን እንገለገላለን... እንደውም ባለፈው ዓመት ቤተ ክርስቲያን ገዝተን ገብተናል። በአሁኑ ሰዓትም ከልብ የሚያገለግሉ ካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ታላላቅ ም ምእመናን ያላት ቤት ክርስቲያን በማግኘታችን ደስትኞች ነን። 

ከአንድ የሎስ አንጀለስ ምዕመን የደረሰን መልዕክት ነው። 

from:- የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ 

5 comments:

 1. I knew another Priest from Belgium who did the same as Aba Sereke. Surprising.

  ReplyDelete
 2. he is always such a stupid person to commit such kind of mistakes. Now let's start to work with the comint "aba's" EVENTOUGH THEY ARE SIMILAR IN THEIR PRACTICE.

  ReplyDelete
 3. አንድ አድርገን ስለ አባ ሠረቀ ያስነበባችሁን ከእውነት የራቀ ነው ይህም የነአባ ኃይለ ሥላሴ ተንኮልና ሸር ነው።
  አባ ሠረቀን ያለ ስሙ የምታጠፉት ሰረቀ አላችሁት እናንተ ደግሞ ርኩሳን ናችሁ እንደ ሠረቀ ብርሃን የመሰለ አባትና ወንድም ሊቅና ትጉህ የለም እናንተን ስለ ወቀሰ ነው የምትጠሉት እሱ መምሕር ወመገሥጽ ወመገሥጽ ዘኢያደሉ ለገጽ ነው። ሰሙም ሠረቀ ማለት በግእዙ በራ ፤ ብርሃን ወጣ ሲሆን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሐየ ጽድቅ ዘበአማን ሠረቀ ይለዋል እንደ አጥቢያ ኮከብ በጨለማ የሚበራ እንጂ እናንተ እንደምትሉት አይደለም። ስምን አጣሞ መተርጉም የእውቀት ማነስንና የጥመት ፤የክፋትና የቅናት ያልመታዘዝ ፤ከሳሶችና ነፍሰ ገዳዮች ፤ ቤተ ክርስቲያንን የሚመዘብሩ በአሥራትና በልዩ ልዩ አሽከላ የሚያጠምዱ ናቸው፡ እና እነዚህን አትስሙ አንደበት ሁሉ ልጌታ የሚታዘዝ የናንተን አንደበት አምላክ ይዝጋው አንደብታችሁ አይታዘዝላችሁ ዘር አይውጣላችሁ ከሥር ማንዘራችሁ ይንቀላችሁ አሜን በተ ክርስቲያናችንና ቅድስት ተዋህዶ እምነታችንን ይጠብቅልን ደቂቀ አስቂዋን ይንቀላቸው አሜን ወአሜን ልይኪን ልይኩን፡

  ReplyDelete
 4. The anonymous above on November 24, 2011 8:17 AM .
  አንድ አድርገንን ሳይሆን ሎስ አንጀለሶችን ይጠይቁ

  ReplyDelete
 5. አንተ ነሐ ወራኀው ስም አጥፊ ወሬኛ ባንዳ

  ReplyDelete