Tuesday, September 6, 2011

የጌታችን ክህነትና የመልከ ፄዴቅ ክህነት



ቅዱስ ጳውሎስ ለምን ጠቀሰው? - - - ዕብ.3:1 “ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ” ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ በእብራውያን መልእክቱ ያተኮረው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ማስረዳት ነው፡፡ ይህንንም የሚያስረዳው ደግሞ በንፅፅር ነው፡፡ ከነቢያት ስለመብለጡ የእነሱን ንግግርና የእሱን ንግግር በማነፃፀር አስረዳ፡፡ ከዚያም በኅላ ደግሞ ከመላእክት መብለጡን አስረድቷል፡፡ አሁን ደግሞ ከካህናት መብለጡን ለማስረዳት ያመጣል፡፡ ከካህናት መብለጡንም ሲያስረዳ ዋናወቹ ምክንያቶች 1) በክህነቱ 2) በመስዋእቱ 3) መስዋእቱ በቀረበበት ድንኳን መሆኑን ያስረዳል፡፡ ስለክህነቱም በ ዕብ.5፡1-10 ፣ በዕብ. 6፡20 ፣ 7፡1-28 ፣ 8፡1-3 ባሉት አስረድቷል፡፡

ክህነት ምንድን ነው? - - - አገልግሎት ሲሆን መሾምን መመረጥን ያመለክታል፡፡ በመፅሃፍ ቅዱስም ከአዳም ጀምሮ የተለያዩ ሰወች ለዚህ ክህነት በሰውም በእግዚአብሄርም ሲመረጡ ያሳየናል፡፡ 

መልከ ፄዴቅ ማነው? - - ዕብ.7:3 “አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።” ይህ ሲባል መልከ ፄዴቅ ሰው አይደለም ማለት አይደለም ፡ ዘሩ ከካም ዘር ነበረና በሙሴ መፃህፍት አልተገለፀም ለማለት ነው፡፡ ይህ የተመረጠ ሰው አፅመ አዳምን እንዲጠብቅ የታዘዘ በብህትውና የሚኖር ነው፡፡ የመልከ ፄዴቅ ክህነትም ሙሴ አሮንን በሾመበት ሥርአት ቅብዕ አፍልቶ ፡ መስዋእተ እንስሳ ሰውቶ ፡ልዩ ልዩ ህብር ያላቸውን አልባሳት አልብሶ የሾመው ሰው የለም፡፡ይልቁንም እግዚአብሄር መረጠው ፡ በማይታወቅ ግብርም ሾመው እንጂ፡፡ አሮንና ልጆቹ በሙሴ እጅ ፡ ሙሴም በመልአኩ እጅ እንደተሾሙ (ሐዋ ፡ 6፡6) መልከፄዴቅ ግን ሹመቱ ከእግዚአብሄር ነውና ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ “ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።” ያለው ለዚህ ነው፡፡ “ለዘላለም” ማለቱም እስከ ህይወቱ ፍፃሜ ማለቱ ነው፡፡በዚህም ምክንያት ክህነቱ ከሌዋውያን ክህነት ፍፁም የተለየ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ እንደሌዋውያን ክህነትም የእንስሳት መስዋእት አይሰዋም መስዋእቱ ንፁህ ስንዴና ወይን ነውንጂ፡፡ በዚህም ተነስቶ ቅዱስ ጳውሎስ - - ዕብ.7:11 እንግዲህ ህዝቡ በሌዊ ክህነት የተመሠረተን ሕግ ተቀብለዋልና በዚያ ክህነት ፍጹምነት የተገኘ ቢሆን፥ እንደ አሮን ሹመት የማይቈጠር፥ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ግን የሆነ ሌላ ካህን ሊነሳ ወደፊት ስለ ምን ያስፈልጋል? ብሎ ይጠቅሰዋል፡፡

ጳጉሜ


  • የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው
  • በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው

ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ / Thirty months of sunshine / በመባ ትታወቃች ትለያለች፡፡ ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት / የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡

Monday, September 5, 2011

ይቅር በሉን

ከሳምንት በፊት ‹‹ቤተክርስትያን ትዘጋ›› (http://andadirgen.blogspot.com/2011/08/blog-post_30.html) የሚል ሰላማዊ ሰልፍ August 30 2011 ሐረር መንገድ በቦርደዴ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ላይ አክራሪ የሚባሉ ሙስሊሞች ወጥተው ለአካባቢያቸው ወረዳ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው መጠየቃቸውን እና መንግስት በጊዜው የወሰደውን እርምጃ በመግለፅ መዘገባችን ይታወቃል፡:

በጊዜው መንግስት ይህን ስራ የሰሩትን ሰዎች ገሚሶቹን በማፈስ ወደ እስር ቤት ያስገባቸው ሲሆን በአካባበቢው ላይ የሚገኙ የእስልምና አባቶች መፍትሄ  ለመሻት ይህን ጉዳይ በእርቅ ለመፍታት ከአካባቢው ክርስትያኖች ጋር በመነጋገር ይህን የሰሩት ሰዎች ይቅርታ እንዲሉ እና ክርስትያኖቹም ይቅር እንዲሏቸው ከአሁን በኋላ የዚህ አይነት ነገር በአካባቢያቸው እንደማይከሰት የተነጋገሩ ሲሆን የቤተክርስትያኒቱ አባቶችም ነገሩን በመመልከት ይቅር ብለዋቸው ችግሩን በመፍታት አካባቢው ላይ ሰላም ማውረድ ችለዋል፡፡ 

ሐሰት አንናገርም፤ እውነትንም አንደብቅም 
‹‹እግዚሐብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ ››

ታላቅ የምስራች!!!


ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ድምጸ ተዋሕዶ የሬድዮ ስርጭት 
በኢትዮጵያ በመስቀል በዓል ማግስት ይጀምራል!!
  • የመጀመሪያው ስርጭት መሰከረም 20 ቀን 2004 ዓ ም ነው::
  • የስርጭት ጊዜ ፤ ቅዳሜ ምሽት ከ3:30-4:30(በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ነው::)
  • የስርጭት ሞገድ: 15360 KHZ 19 Meter Band አጭ ር ሞገድ
Contact: radiotewahedo@gmail.com

ከአንድ ወር በፊት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን እምነት ፤ ስርዓት ፤ ትውፊት እና ታሪክ የሚያስተምር አኰቴት ዘተዋሕዶ አዲስ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር እሁድ ከቀኑ 6፡30– 7፡30(በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ነው::) በ EBS ቴሌቪዥን በመላው ዓለም ስርጭት መጀመሩ ይታወቃል፡፡



‹‹እግዚሐብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››

ያለፈው ዘመን ይበቃል ... 1ጴጥ.4፡3፡፡

  • «የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁ በት፡ በመዳራት እና በሥጋ ምኞት፣ በስካርም፣ በዘፈንም ፣ያለልክም በመጠጣት፣ ነውርም ባለበት፣ በጣዎት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና»1ጴጥ.4፡3፡፡ 
  • «ሰውስ ዘመኑ እንደ ሣር ነው እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል፡፡ ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋል» መዝ.102/103፡ 15፡16 
  • በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘን ሁላችን በስካርና በዝሙት፣በስርቆት እና በቅሚያ፣ በመግደልና በምቀኝነት በቅንዓትና በቂመኛነት ያሳለፍነውን ሕይወት ትተን አዲስ ሰው የምንሆንበት ዘመን ሊሆን ይገባል

አባታችን አዳም ጀምሮ ብዙ ትውልድ በዚህች ምድር ላይ ተመላልሷል፡፡ ወጥቷል ወርዷል አልፏል፡፡ ዘመን ሲያልፍ ዘመን ሲተካ ሰው ሲያልፍ ሰው ሲተካ፡ ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ ነቢየ እግዚአሔር ዳዊት በመዝሙሩ«ሰውስ ዘመኑ እንደ ሣር ነው እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል፡፡ ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋል» መዝ.102/103፡ 15፡16 ብሏል፡፡

Sunday, September 4, 2011


 አባ ናትናኤል ወደ ሱዳን ፈረጠጡ”

በሸዊት ገ/ኪዳን (shewitgbrkdn95@gmail.com)
  • ጸሎት በእንተ ማኅበረ ቅዱሳን የሚል አነስተኛ ጽሑፍ በትነዋል፡፡
  • ወደ ሱዳን ለመውጣታቸው የቅዱስ ፓትርያርኩና የአቡነ ፋኑኤል እርዳታ እንዳለበት እየተወራ ነው::
  • አዋሳ ላይ ይኽንን ጽሐፍ የሚያሰራጩት በሕግ አካላት እየታደኑ ነው::ጥቂት የማይባሉ ወዳጆቻቸው በመፈረጠጣቸውና በበተኑት ተራ ጽሑፍ እጅ ግ በጣም አዝነዋል የአዋሳ ምዕመናን ግን ይኽ እንደሚሆነ እናውቅ ነበር ይላሉ::

“አባ” ናትናኤል
እነ በጋሻውና ትዝታው ባለቤቱ አይታወቅም እያሉ ማስተባበያ ለመስጠት ላይ ታች የሚሉለትና ነገር ግን በአዋሳ ምዕመናን እንደተዘጋጀና አዲስ አበባ ለአቤቱታ በሚመላለሱበት ጊዜ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዱስነታቸውን ጨምሮ ለብፁዐን አበው በነጻና በስፍራው ለተገኘው ምዕመን በአነስተኛ ዋጋ ያሰራጩት ቁጥር አንድ ቪሲዲ ካሴት ላይ ሦስቱ ወፎቹ ተበለው ከተጠቀሱት “መነኮሳት” አንዱ የሆነውና በወቅቱ  የአዋሳ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን “አስተዳዳሪ”የነበረው “አባ” ናትናኤል በቅርቡ ምእመናን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ይጸልዩበት በሚል “ጸሎት በእንተ ማኅበረ ቅዱሳን”የሚል በይዘትም ሆነ በቅርጽ  አነስተኛ የሆነ ጽሑፍ አዘጋጅቶ በመበተን የሚከተለውን በመገመት ይመስላል ወደ ሱዳን ኮብልሏል ሲሉ የአዋሳዎቹ ገብርኄራውያን ገልጸውልናል፡

Friday, September 2, 2011

ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ እና ፊሊጶስ



  • የፊልጶስ ጥያቄ እና የጃንደረባው መልስን በሚገባ ማስተዋል ያስፈልጋል፡
  • እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች ሲጀመርም ለአገልጋዮችም ሆነ ለምእመናኑ አርአያ ሊሆኑ አልቻሉም
  • ስለአንዳንድ ሰባኪያኖች ግን ከፈጣሪ መንገድ ይልቅ አለማዊ (አጋንታዊ) መንገድን እየተከተሉ ነው
  • የሚደረገው ክርክር መሰል ምልልስ የእየራሳቸውን እምነት ተከታዮች ከማደናገሩም ባሻገር እናገለግለዋለን የሚሉትን ፈጣሪያቸውን ጭምር የሚያሳዝን እየሆነ ነው
  • ማንም ሰው ወደ አምልኮ ስፍራዎች የሚሄደው እንደ ጃንደረባው ተደስቶ ለመመለስ እንጂ ልቡ ተሰብሮ ለመመለስ አይደለም
  • የሁሉም እምነት ተከታይ የፊልጶስን አይነት ሰባኪን (አስተማሪን) እንጂ እርስ በእርሱ የማይከባበር እና የሚሰዳደብ ሰባኪን አይፈልግም
  • የተጠቀሱት ሃይማኖት መሪዎች በሙሉ ከእግዚአብሔር ይልቅ ቄሳርን የሚያገለግሉ እና የሚፈሩ ናቸው፡የእረኝነት ተልእኮአቸውን ከመውጣት ይልቅ የገዥው ፓርቲ የፖለቲካ አስፈፃሚ በመሆን ጊዜያቸውን የሚያጠፉ ናቸው
  • አንዱ አንዱን ለማውገዝ ካሴት እስከማውጣት እና መጽሐፍ እስከማሳተምም ደርሰዋል
  • ሀገሪቱ የሚያምነውም የማያምነውም መሆኗን በቅድሚያ መገንዘብ ያስፈልጋል

‹‹ለቤተክርስትያን አገልጋዮች›› የተሐድሶ ሠራዊትነት ስልጠና ተሰጠ


በምስራቅ ኢትዮጵያ ከሚገኙ አራት ሀገረ ስብከቶች ለተውጣጡ ‹‹ለቤተክርስትያን አገልጋዮች›› የተሐድሶ ሠራዊትነት ስልጠና ተሰጠ



  • የሥልጠናው ዋና ርዕሰ ጉዳይ ኢየሱስን ማለመመድ የሚል ነበር
  • ስልተ በጋሻው በዝርዝር ቀርቦላቸው እንዲጠቀሙበት መመሪያ ተሰጥቷቸዋል
  • ፓስተር መስፍን ፤ገበየሁ ይስማውና  በጋሻው ደሳለኝ ከነሐሴ 13-15 ሐረር በቆየበት ጊዜ በሥልጠናው ዙርያ መምከራቸውን ለመረዳት ተችሏል
  • ለሥልጠናው ተሳታፊዎች ኢየሱስ አማላጅ ነው የሚል ማስታዎሻ እና መጸሐፍ ተሰቷቸዋል
  • ከሠልጣኞቹ መካከል ቀደም ሲል ማኅበረ ቅዱሳን በክረምት ተተኪ መምህራን ሥልጠና አሰልጠኗቸው ከነበሩት ሠልጣኞች አንድ ግለሰብ ተገኝቷል
ከድሬዳዋ ፤ ከሱማሌ ፤ ከምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ አህጉረ ስብከቶች የኦርቶዶክስ  አብያተ ክርስቲያናት ለተውጣጡ ‹‹የቤተክርስቲያን አገልጋዮች›› ግበረ ተሐድሶን በሚያስፋፉበት ስልት ዙርያ ሥልጠና መሰጠቱን  በሰነድ እና በድምጽ ወምስል የደረሰው መረጃ አመለከተ፡፡

ተዋህዶ በእመቤታችን ልጅ ስም አፍራ ታውቃለችን?

ሰው በልጇ ስም እያፈረ እንዴት አማልጂኝ ብሎ ይለምናል እንዴትስ በረከቷን  ይሻል....ቀሲስ አሽናፊ ገብረማርያም
“(ከቀሲስ አሽናፊ ገብረማርያም )ሰላም ለሁሉ፤-እንኳን አደረሳችሁ፡፡ እመቤታችን በምድር ላይ ጌታችን ኢየሱስን ወልዳ አቅፋ አጥብታው አዛው ታዛው እቅፏ ውስጥ አስተኝታው አጥባው አልብሳው አጉርሳው ስማው…. በተግባር በኑሮ ሰብካው አገልግላው በብዙ መከራ ለኛ ሰጥታናለች፡፡ ኢየሱስን የምትወዱ ከእመቤታችን ጋር በተግባር እየተባበራችሁ ነውና በርቱ! ተሰድባለች ከመቅደስ ተባራለች ከሃገር ተሰዳለች በትትና ስለራሷ ስላልተናገረች በዙ ነቀፌታን ታግሳለች፡፡ ሰው በልጇ ስም እያፈረ እንዴት አማልጂኝ ብሎ ይለምናል እንዴትስ በረከቷን  ይሻል

 መልስ ከታምራት ፍስሀ
በእውነት ይህን መልእክት አንድ የፌስቡክ ጉደኛየ እንድመለከተው ሲፅፍልኝና ሳነበው በጣም  አዘንኩ በተለይ የፅሁፉ ባለቤት የቤተክርስቲያናችን መምህር መሆኑን ሳስብ ደግሞ ተናደድኩ፡፡ እውነት ግን እንዲህ ብሎ መልእክትን ማስተላለፍ ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው? እንደዚህስ ማለት ምን ይሰራል? ይህስ በስህተት የተባለ ይሆን? ወይንስ ይህ በማር የተለወሰ መርዝ ነውን? በዚህም ምክንያት በአንድ ወቅት “ኢየሱስ የሚለውን ስም ሽሽት” በሚል የሰጠሁትን አስተያየት ትንሽ አሻሽየ አወጣሁት፡፡ “ኢየሱስ” ብሎ መጥራት እውቀት የሚመስላቸው ነገር ግን

Thursday, September 1, 2011

ሦስቱ መምህራን ፍርድ ቤት ቀረቡ


  • በጋሻው ደሳለኝ ስሜን በማጥፋት ከሰው ልቡና እንድወጣ አድርገውኛል በማለት አቤቱታ ያቀረበባቸው እነ መምህር ዘመንድኩን በቀለ ፍርድ ቤት ቀረቡ
  • የአቡነ ጳውሎስ ደብዳቤ ማስረጃ ሆኖ ቀርቧል
  • ለአቶ በጋሻው ‹‹አደባባይ ከመውጣት ተወግዶ ተቀምጦ እንዲማርና ለፈጸመው ስሕተቱ ንስሐ እንዲገባ መክረዋል››
  • እነ በጋሻው የተሐድሶ መናፍቅነት አቀንቃኝ በሆነው‹‹ አሸናፊ ቦሻ ›› ላይ ተስፋቸውን ጥለዋል
  • በጋሻውና ትዝታው ‹‹የተከሳሾቹ ጓደኞች በመኪና ሊገጩን ነበረ›› በማለት ጉዳዩን ለያዘው ዐቃቤ ሕግ መናገራቸው ተሰምቷል
  • / ዘመድኩን በቀለም በቅርቡ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄን አስመልክቶ በተለያዩ መጽሔቶች ላይ በሰጣቸው ቃለ ምልልሶቹ ነው የተከሰሰው(ይህን ቃለ ምልልስ አንድ አድርገን ላይ ከሳምንት በፊት ፖስት ተደርጓል)
የተከሰሱበት መፃህፍቶቻቸው
በሜቲ ኤጀታ (memettiej1@gmail.com)
ዲ.ን ደስታ ጌታሁን  የሰባኪው ሕጸጽ”  ፤ መ/ር ሣህሉ አድማሱ  በጋሻው ኦርቶዶክሳዊ ነውን?”  የተሰኙ መጻሕፍትን በመጻፋቸው እንዲሁም መ/ር ዘመድኩን በቀለ ከማራኪ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ስሜ ጠፋቷል በማለት በጋሻው ደሳለኝ ባቀረበው አቤቱታ መሠረት በተጣራው የምርመራ መዝገብ በስም ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱት ሦስቱ መምህራን ትላንት ነሐሴ 25 ቀን 2003 ዓ.ም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ወንጀል ችሎት ቀረቡ፡፡