Friday, September 18, 2015

የግብፅ ኦርቶዶክስ ፓትያርክ ከመስከረም 15 ጀምሮ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ




የግብፅ ኮፒት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ቴዎድሮስ 2 ከመስከረም 15 ቀን 2008 . ጀምሮ የአምስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ወደኢትዮጵያ እንደሚመጡ ታወቀ።
ፓትርያርኩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ታሪካዊው የመስቀል በዓል ላይ የሚታደሙ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣትን ጨምሮ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ፓትርያርክ ቴዎድሮስ 2 መንፈሳዊና ታሪካዊ ቦታዎችንም እንደሚጎበኙ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ጋርም እንደሚመክሩ ታውቋል።
ፓትያርኩ ወደኢትዮጵያ የሚመጡት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አቡነ ማቲያስ በቀረበላቸው ግብዣ መሠረት መሆኑ ተጠቁሟል። 

Source :- http://www.sendeknewspaper.com

No comments:

Post a Comment