Saturday, February 28, 2015

የሆሳዕና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በእሳት ቃጠሎ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባት

(አንድ አድርገን የካቲት 21 2007 ዓ.ም)፡- በየካቲት ማርያም ቀን 2007 . በሃድያ እና ስልጤ ሃገረ ስብከት በሆሳዕና ከተማ የምትገኘውና 1901 . እንደተተከለች የሚነገርላት የ106 ዓመት ባለቤት ሆነች   የሆሳዕና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በእሳት ቃጠሎ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባት፡፡

ይህች ቤተ ክርስቲያን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ብቻ ሳይሆኑ ለማያምኑትም እና መናፍቅና አህዛብ ለሆኑትም የአካባቢው ሕዝቦች ጭምር ምሥክር እንደሆነች ይነገርላታል፡ የሀድያ አካባቢ ምዕመን የዕድሜ ባለፀጋ የሆኑ የብዙ አብያተ ክርቲያናት ባለቤት ነው፡፡ ሆሳዕና ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሆሳዕና አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ሆሳዕና ቅዱስ ሚካኤል፣ ሆሳዕና እግዚአብሔር ወልድ /በዓለ ወልድ/ መስመስ ቅዱስ ሚካኤል /1034 . አካባቢ እንደተተለ የሚነገርለት/ እኝህና ሌሎችንም ጨምሮ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠሩ ቅዱሳት መካናት በአካባቢው እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

/የጎርባቾቭ የካቲት 21 ቀን 2007 ./


Monday, February 23, 2015

ሃያ አንደኛው ሰማዕት



አንድ አድርገን የካቲት 16 2007 ዓ.ም
/ ሄኖክ ኃይሌ
 henoktsehafi@gmail.com

  •   '' ክርስቲያንና ዕጣን አንድ ናቸው:: ሁለቱም መዓዛቸው የሚታወቀው እሳት ውስጥ ሲገቡ ነው'' ፓትርያርክ ታዋድሮስ

ሰሞኑን በሊቢያ ባሕር ዳርቻ ላይ የግብፅ ኦርቶዶክስ ምእመናን የሆኑ ወጣቶች አምላካችንን አንክድም ብለው እንደ በግ ተነድተው ሲታረዱ ተመልክተናል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ራስ ክርስቶስ ነው፡፡ አንዱ አካል ሲሰቃይ ሌላው አካል መታመሙ አይቀርምና የእነርሱ ስቃይ የክርስቶስ አካል ክፍሎች ለሆንን ሁላችም ተሰምቶናል፡፡ የአምላካቸውን ስም እየጠሩ የታረዱት ምእመናን በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚገኙ ሥራ ፍለጋ ወደ ሊቢያ የሔዱና አንዳንዶቹም ጋብቻ ለመመሥረት እየተዘጋጁ የነበሩ ናቸው፡፡ ሆኖም የአምላካቸውን ስም ጠርተው ሰማያዊ ሙሽሮች ሆኑ፡፡ ምንም እንኳን በምድራዊ ዓይን ስናየው እጅግ አሰቃቂ ቢሆንም እነዚህ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ያለ አንዳች ተቃውሞ በፈቃደነት የተቀበሉት ሰማዕትነት እጅግ የሚያስቀና እና ሰማያዊ አክሊል የሚያጎናጽፋቸው ነው፡፡ በሰማይም ከመሰዊያው አጠገብ ቆመው ከሚያማልዱ ቅዱሳን ሰማዕታት ማኅበር ተደምረው ‹‹በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም›› እንደሚሉ ነጭ ልብስም ተሰጥቷቸው እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንደሚያርፉ›› እናምናለን:: /ራእ 6:11/

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የፓትርያርኩን እገዳ ተቃወሙ



አንድ አድርገን የካቲት 16 2007 ዓ.ም
From:- Addis Admass
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን /ሲኖዶስ፣ ‹‹ቤተ ክርስቲያንን አዋርደዋል፤ አባቶችን ዘልፈዋል›› ያላቸው አለቆች ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው ያሳለፈው ውሳኔ በፓትርያርኩ ትእዛዝ መታገዱ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት ሰንበት /ቤቶች ተቃውሞ ገጠመው፡፡
የአ/አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት /ቤቶች አንድነት ባለፈው ሳምንት እሑድ በሀገረ ስብከቱ /ቤት አዳራሽ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባካሔደው የግማሽ ቀን ውይይት ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት፤ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምቱ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባው ‹‹አማሳኝ አለቆች›› ተግሣጽና ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ያሳለፈው ውሳኔ ባለመፈጸሙ ቤተ ክርስቲያኒቱ በከፋ ኹኔታ እየታወከችና እየተመዘበረች እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡
ፓትርያርኩ ውሳኔ እንዲቆዩ ማዘዛቸውን ተከትሎ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውሳኔውን ለማስፈጸም ባለመቻሉ፣ ‹‹አማሳኝ አለቆች›› በሚል የተገለጹ የአድባራት ኃላፊዎች እንቅስቃሴያቸውን ለሚቃወሙ አገልጋዮች ስም እያወጡ፣ በገንዘብ ኃይል ከሥራቸው እንዲፈናቀሉና ያለፈቃዳቸው እንዲዘዋወሩ፤ የሰንበት /ቤት ወጣቶች የድርሻቸውን እንዳይወጡ ከመዋቅር ውጭ ባደራጇቸው አካላት እየከፋፈሉና በፖሊቲከኛነት እየወነጀሉ ከአገልግሎት በማገድ ለእስርና እንግልት እየዳረጉ እንደኾነ በውይይቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡