Saturday, May 10, 2014

መንግሥት በዋልድባ ገዳም በመስራት ላይ ላለው የሥኳር ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከቻይና መንግሥት የገንዘብ ብድር አገኝ

(አንድ አድርገን ግንቦት 3 2006 .)- መንግሥት በአምስት አመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ 32 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ  አስር የሥኳር ፋብሪካዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ እገነባለሁ ብሎ በእቅድ መያዙ ይታወቃል፡፡ መንግሥት ከፍተኛ አትኩሮት ከሰጣቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኋላ በሀገሪቱ የተጀመሩት 10 የሥኳር ልማት ፕሮጀክቶቹ በሁለተኝነት ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ ብዙ ውዝግብ ያስነሳው የሥኳር ፋብሪካ ውስጥ በዋልድባ ገዳም አካባቢ የሚገነባው መሆኑ ይታወቃል፡፡  ፕሮጀክቶች በበላይነት የሚመራው ሚኒስትር መስሪያ ቤት ከሚቆጣጠራቸው ፕሮጀክቶቹ ውስጥ አንዱ እና ዋንኛው የሆነውን የዋልድባን የስኳር ፋብሪካ ግንባታን ለመስራት በየጊዜው የሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የመጡ ኮንትራክተሮች ውል በመቋጠርና በመፍታት አሁን ላይ ሶስተኛው ስራ ተቋራጭ ስራው እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡  ለሚገነባው የስኳር ልማት ፕሮጀክት በመጀመሪያ ዙር 1800 አባወራዎች ከቦታቸው በማንሳት መንግሥት 127.5 ሚሊዮን ብር የካሳ ክፍያ መክፈሉ ይታወቃል፡፡ በሁለተኛ ዙር የሰፈራ ፕሮግራሙ ላይ 4ሺህ ሰዎች ከቦታው ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሰፈራውም የሚቀጥል ሲሆን ለሚነሱት አብያተ ክርስቲያናት ቅድመ የማግባባት ስራ በአካባቢ አስተዳደር በኩል እንዲሰራ ትዕዛዝ መውረዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡


የማይፀብሪ የመንግሥት ባለሥልጣናት የገዳሙን መነኮሳት በመሰብሰብ የመነኮሳቱን ውሳኔ ለመጨረሻ ጊዜ  በግንቦት 6 2006 ዓ.ም እንዲያሳውቁ ጥብቅ ውሳኔ ከበላይ አካል ተላልፏል፡፡ ለስኳር ፋብሪካው ግንባታ እንቅፋት ይሆናሉ ተብለው በዲዛይኑ መሰረት መነሳት አለባቸው የተባሉት መኅር ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ደለሳ ቆቃ አቡነ አረጋዊ፣ እጣኖ ቅድስት ማርያም አብያተ ክርስቲያናት እንደሚነሱም ተወስኗል፡፡
አቶ አባይ ጸሃዬ የ2005 ዓ.ም በጀት ዓመት የሥኳር ኮርፖሬሽኑን ዓመታዊ አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት መንግሥት በበጀት እጥረት  የሰፈራ ፕሮግራሙንና ፕሮጀክቱን በአግባቡ ለማስኬድ እንቅፋት እንደሆነበት ለፓርላማ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ቦታው ድረስ በመሄድ ስራውን የሚሰራ የተማረ የሰው ኃይል እጥረት እና ረዥም ጊዜ አለመቆየት መቻልን ለፕሮጀክቱ መጓተት እንደ ሁለተኛ ምክንያት አቅርበው ነበር፡፡ ይህንም ችግር ለመፍታት ከአበዳሪ ሀገራት እና ዓለማቀፍ ተቋማት ፕሮጀክቱን ለማስፈጸም የሚስችል ብድር እየተፈለገ መሆኑን ጠቁመው ነበር፡፡
በዚህ መሰረት የቻይናው ጠቅላይ ሚንስትር ሊ ኪዩኪያንግ ከሚያዚያ 26 20006 ዓ.ም  ጀምሮ በኢትዮጵያ የ 3 ቀናት ይፋዊ ጉብኝት  ባደረጉበት ወቅት ከኢትዮጵያ ከመንግሥት ጋር 17 የተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡ ከተፈራረሙት ስምምነቶች አንዱ በዋልድባ ገዳም ተጀምሮ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ሥራ ተስተጓጉሏል ተብሎ ለሚታሰበው የዋልድባ አካባቢ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚሆን የፋይናንስ ብድር እንደሚገኝበት ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህም መሰረት ከቻይና መንግሥት ሊሰጥ የታሰበው ብድር እንደተለቀቀ ሥራው እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡
ጥቂት ምንጭ ፡- የኢቲቪ ዜና

7 comments:

  1. አቤቱ ሕዝብህን አድን፤ ርስትህን ኢትዮጵያንም ባርክ፤ ጠብቀን ከፍ ከፍም አድርገን፤ ጨነቀን ምን እናድርግ፤ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እንዳንወጣ፡ ከመንግስት ሰላማዊ መልስ አናገኝም፤ አቤቱታ እንዳናሰማ የሚሰማ ጆሮ የለም፤ ቤተክርስቲያንን ይጠብቋት ዘንድ አደራ የሰጠሃቸው አባቶችም ዝምታን መርጠዋልና አቤቱ አንተ ስማን፤ ተለመነን፤ በደላችንንም ይቅር በለንና ገዳማችንን፣ ቤተክርስቲያናችንን ጠብቅልን፡፡ አሜን!!

    ReplyDelete
  2. AYISERAM, AYISAKALACHEWUM FETSIMO

    ReplyDelete
    Replies
    1. I don't understand why Dim-witted leaders are focusing on WALDEBA. IT WOULD HAVE BEEN BETTER TO BUILD THE PROJECT NEXT TO NILE DAM SIDE BY SIDE FOR A BETTER WATER FLOW. Two years from now the two leaders "the so called spiritual" and non spiritual gone because of THEIR AWFUL DECISION ON WALDEBA. Today their "ancestors" next to their foot. if they are don't quit TODAY- they will go TOMORROW including the chinene leader. YOU CAN'T FIGHT WITH ALMIGHTY GOD. ORTHODOX CHURCH REMAINS TILL resurgence.

      Delete
    2. do you have enough information about it or information is skindeep information. i am christian from that place, but all the information posed by anumber of peoples is quite emotional including the bloger. there is one fuct that both he ruling party and the peoples living in the monastry( am not refering to the real monks who live he spirtual life). former members of the derg regime were hidden there these are the people even who have satelite telephones and used to call every day o norh america. don' believe every murmur. but it is tirue tha the project inforce the people and the three mentioned churche whic are out of the so called holly area of he monastry to be desplaced.

      Delete
  3. አቤቱ ሕዝብህን አድን፤ ርስትህን ኢትዮጵያንም ባርክ፤ ጠብቀን ከፍ ከፍም አድርገን፤ ጨነቀን ምን እናድርግ፤ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እንዳንወጣ፡ ከመንግስት ሰላማዊ መልስ አናገኝም፤ አቤቱታ እንዳናሰማ የሚሰማ ጆሮ የለም፤ ቤተክርስቲያንን ይጠብቋት ዘንድ አደራ የሰጠሃቸው አባቶችም ዝምታን መርጠዋልና አቤቱ አንተ ስማን፤ ተለመነን፤ በደላችንንም ይቅር በለንና ገዳማችንን፣ ቤተክርስቲያናችንን ጠብቅልን፡፡ አሜን!!

    ReplyDelete
  4. Mad government.

    ReplyDelete