Thursday, October 31, 2013

ተሀድሶያውያን ‹‹ ቅዱስ አትናቴዎስ የወንጌል አገልግሎት›› የሚል የእምነት ተቋም ሊያቋቁሙ ነው

(አንድ አድርገን ጥቅምት 21 2006 ዓ.ም)፡- THE ETHIOPIAN HERALD TUESDAY 29 OCTOBER 2013 ዕትም ገጽ 7 ላይ ይህን ነገር ይዞ ወጥቷል ፡፡
Notice 
“KIDUS ATNATEWOS YEWENGEL AGELEGELOT has applied use this name as a religious institution. Any individual or organization opposing the name is here by requested to report to the Ministry of Federal Affairs and Religious Organization and Association Registration directorate, Office on November 11/2013 at 9:00 AM  
Ministry of Federal Affairs
  
Notice
“KIDUS ATNATEWOS YEWENGEL AGELEGELOT has applied use the under indicated symbol.

(ቅዱስ አትናቴዎስ የወንጌል አገልግሎትየሚል መስቀል ያለው ክብ ምልክት)
Any individual or organization opposing the symbol is here by requested to report to the Ministry of Federal Affairs and Religious Organization and Association Registration directorate, Office on November 11/2013 at 9:00 AM  
                   Ministry of Federal Affairs

በጋዜጣው ላይ በእለቱ ከወጡ አዲስ ለመመስረት መንገድ ላይ ያሉ ስድስት የእምነት ተቋማት ውስጥ አንዱ ‹‹ ቅዱስ አትናቴዎስ የወንጌል አገልግሎት›› የሚል ነው፡፡ በዚህ ስምም ሆነ የእምነት መጠቀሚያ ምልክት ላይ ተቃውሞ ያለው አካል ካለ ሰኞ ህዳር 2 2006 ዓ.ም (November 11/2013 at 9:00 AM) ላይ እንዲቀርብ ያሳስባል፡፡

የተሀድሶ ርዝራዥ በደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን


  • ቅዳሴን በ45 ደቂቃ እንዲያልቅ አድርገዋል፡፡
  • ‹‹ሥላሴ ግቢ ውስጥ እሾህ ተከላችሁብኝ ፤ ማህበረ ቅዱሳንን የሚያጠፋልኝ ካለ ደሜን እለግሳለሁ፡፡››
  • የራሳቸውን ደመወዝ 5000 ብር አድርሰዋል ፤ ድርሳናት ገድላት እና ተዓምራት በጸበል ቤት እንዳይነበብ ከልክለዋል፡፡
  • በአስተዳዳሪነት ዓመታቸው በቦታው ታይቶ አና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ መብረቅ ከሰማይ በመውረድ ረዥም እድሜ ያላቸውን ጽዶችን አቃጥሏል ፡፡(በአጼ ዘርዓያቆብ ዘመነ መንግሥት ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ከሰማይ ብርሃን የወረደበት ቤተክርስቲያን ነው፡፡ )
  • ‹‹የማርያም ስም ሲጠራላችሁ ደስ ይላችኋል ፤ ኢየሱስን ስሰብክላችሁ ግን ቦታ አትሰጡትም ፤ ማርያም እኮ ከእግዲህ ዋጋ የላትም ፤ የኛ ጌታ ሁሉን ፈጽሞልናል›› አባ ማርቆስ በአውደ ምህረት ከተናገሩት የተወሰደ
  • ‹‹መጽሀፍ ቅዱስን በደንብ የተመራመረው ፕሮቴስታንት ሆነ ፤ ከታቦት ወንጌል ይቀድማል ፤ ኪዳን ከምትመጡና ቅዳሴ ከምታስቀድሱ መጽሐፍ ቅዱስ ብታነቡ ይሻላል›› የአባ ማርቆስ የጠርዝ ምንፍቅና አስተምህሮ


(አንድ አድርገን ጥቅምት 21 2005 ዓ.ም)፡-  ተሀድሶያውያን አውደ ምህረቱን ካጡ  አመት አልፏቸዋል ፡፡ የዛሬ ዓመት  ጉዳያቸው በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሊታይ የተጀመረ መሆኑ ይታወቃል በዚህ አስተምህሮ ፊት አውራሪዎቹ አዲስ አበባ ውስጥም ሆነ በመላ ሀገሪቱ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ተቀባይነትን ስላጡ አይናቸውን ከሀገር ውጪ አብያተ ክርስቲያናት ላይ አድርገዋል በቅርቡም በአንዱ የአረብ ሀገር የሶስት ቀን ጉባኤ አካሂደዋል ከዚህ ቀደም በጉባኤ ብር ኪሳቸውን ሲሞሉ የነበሩት ሰዎች አሁን ላይ የገቢ ምንጫቸው መሟጠጡን ተገንዝበት በሌላ ሙያ በመሰማራት ከሀገር ውጪ የወጡም ይገኛሉ በዚህ መንገድ ላይ የሚገኙት አውራዎቹ ግን በማህበረሰቡ ዘንድ ያጡትን ተቀባይነት ለማደስ ያስችላቸው ዘንድ በዘመሪት ፋንቱ አማካኝነት የይቅርታ እና የመታረቅ ጥያቄ ማቅረብ መፈለጋቸው ይታወቃል እንደ እኛ እምነት ለመታረቅ ያሰቡት ከአስተምህሯቸው ጋር ቢሆን መልካም ነበር የእነዚህ ሰዎች ርዝራዦቻቸው ግን አሁንም በየቦታው በግለሰብ ደረጃ በቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ ተቀምጠው አመቺ ቀን እየጠበቁ ይገኛሉ ከእነዚህም መካከል የደብረ ብርሃኑ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አስተዳዳር አባ ማርቆር ብርሃኑ አንዱ ናቸው፡፡

“የሌለውን ፍለጋ” ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ለተስፋዬ ገብረአብ የሰጠው ምላሽ

(Read in Pdf ) ተስፋየ ገብረ አብ ‹የስደተኛውማስተዋሻ› የተሰኘ መጽሐፍ ማውጣቱንና ባነበውመልካም እንደሆነ ገልጦ አንድ ወዳጄ ‹ስስ ቅጅውን› ከሀገረ አሜሪካ ላከልኝ፡፡ ከዚህ በፊት ሌሎች መጻሕፍቱን አንብቤያቸዋለሁ፤በአጻጻፍ ችሎታው የምደሰተውን ያህል እንደ አበሻ መድኃኒት ነገሩን ሁሉ እርሱ ብቻ የሚያውቀው ምስጢር ስለሚያደርገው፤ በአንዳንድጉዳዮችም ሆን ብሎም ሊያናጋቸው የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ እሴቶች ያሉ ስለሚመስለኝ፤ ተስፋዬ ለምን እንደዚህ ይጽፋል? እያልኩ የምጠይቃቸው ነገሮች ነበሩ፡፡

በዚህ መጽሐፉ ውስጥም ያንን ጥርጣሬየን አጉልቶ ሥጋ ነሥቶ እንዳየውየሚያደርገኝ ነገር ገጠመኝ፡፡ ተስፋየ በገጽ 306 ላይ ‹‹የፍስሐ ጽዮን ፖለቲካ› በሚል ርእስ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የማያውቀውንነገር ጽፏል፡፡ ስለማያውቀው ነገር የጻፈው ባለማወቁ ብቻ አይመስለኝም፡፡ አንድም ለማወቅ ባለመፈለጉ፣ አለያም ሆን ብሎ የማፍረስዓላማ ይዞ ይመስለኛል፡፡

ይህን የምለው በሁለት ምክንያት ነው፡፡ ተስፋዬ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖትለመጻፍ ሲፈልግ ሊያነባቸው የሚችላቸው መጻሕፍት በምድረ አውሮፓ እንደ ማክዶናልድ በዝተው ሞልተው ይገኛሉ፡፡ አብዛኞቹ ደግሞ ኢትዮጵያውያንባልሆኑ ሰዎች የተጻፉ ናቸው፡፡ ሌላው ቢቀር ኤንሪኮ ቼሩሊ የደብረ ሊባኖስ አበ ምኔቶች ታሪክ(GliAbbati di Dabra Libanos, 1945)፣ ኮንቲ ሮሲኒ ከሐተታ ጋር ያሳተመውን ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣በዋልድባ ቅጅ (IlGadla Takla Haimanot secondo la redazione Waldebbana, 1896)፣ የዊልያም በጅን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕይወትና ተአምር (The Life and Miraclesof Takla Haymanot, 1906)፡፡ ከኢትዮጵያውያን ጸሐፍትም ውስጥ የታደሰ ታምራትንChurch and State in Ethiopia, ማንበብ በተገባው ነበር፡፡

የሃይማኖት አክራሪነት ንፋስ በቤተ ክርስቲያን “አታስቆጡን!”


Sunday, October 27, 2013

“መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ ኦሮምኛ ተተረጎመ


በመልካሙ ተክሌ
(አዲስ አድማስ ጥቅምት 16 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን “መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተተረጎመ፡፡ ለብዙ ዘመናት “መጽሐፈ ቅዳሴ”ን በግእዝ እና በአማርኛ ስትጠቀምበት የቆየችው ቤተክርስትያኗ፤መፅሃፉን በኦሮምኛ ማስተርጎም የጀመረችው በ1999 ዓ.ም እንደሆነ ታውቋል፡፡ የመጽሐፉ መተርጎም በኦሮሚያ ክልል ላሉ አብያተ ክርስትያናት በኦሮምኛ ለመቀደስ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡ የቤተክርስትያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ እያካሄደ ባለው የጥቅምት ምልዐተ ጉባዔው ትኩረት ከሰጣቸው ዋና አጀንዳዎቹ አንዱ ስብከተ ወንጌልን ማዳረስ እንደሆነ የገለፁት ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ የመጽሐፉ  ሕትመት እንዲቀላጠፍ ትዕዛዝ እንዳስተላለፉም  ለማወቅ ተችሏል፡፡ “መጫፈ ቂዳሴ” በሚል ርዕስ የተተረጎመው የኦሮምኛ መጽሐፉ፤በቅርቡ ዝግጅቱን የተቀላቀሉትን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍን ጨምሮ፣ በርካታ ጳጳሳት ተሳትፈውበታል፡፡ መጽሐፉ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እየታተመ ሲሆን በዚህ ሳምንት ከተጠናቀቀ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ መዝጊያ ላይ ሊመረቅ እንደሚችል ታውቋል፡፡ 


Tuesday, October 22, 2013

በእናቴ ጠባሳ አላፍርም!



ከአባ ዮሐንስ


የእናቴ ጠባሳም ይሁን ማድያት አያሳፍረኝም ውለታዋን ቢያስታውሰኝ እንጂ!!

(አንድ አድርገን ጥቅምት 13 2006 ዓ.ም)፡- ቤተ ክርስቲያን የመከራን ጽዋ መጨለጥ አዲስ ባይሆንባትም የሚያስገርመው በውስጥ ሰው ምቹ ጊዜ ተፈልጎ የላምና የጊደር መስዋእት አቅራቢዎች ለነበሩት የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ተላልፎ መሰጠቱ ነው። ከአምስት ገበያ ህዝብ መካከል የአንድ ገበያ ህዝብ ያህሉ የመልኩን ደም ግባት ለመመልከት የሚመላለስ እንደነበረ ታላቁ መጽሓፍ ያወሳል በአንጻሩም የቤተክርስቲያን መስራች የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ምን ያህል ደም ግባቱ ያማረ መሆኑንም ያስጨብጣል።

Sunday, October 20, 2013

እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ


እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
የምንኩስና ግብር ምን ነበር ምሥጢሩ
የክርስትና ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ
መቃብሩን ክፈቱና አበው ይመስክሩ፡፡

እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ
ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ፡፡

ነብያት በመጋዝ የተሰነጠቁት
ሐዋርያት ቁልቁል የተዘቀዘቁት
ሰማዕታት በእሳት የተለበለቡት
ቅዱሳን በገዳም ደርቀው የተገኙት
ምሥጢሩ ምን ነበር? አበው ይናገሩት፡፡

Thursday, October 17, 2013

እነ ‹‹ጀማነሽ› ጭፍራዎቻቸውን በገዳማት ማሰማራት ጀምረዋል


(አንድ አድርገን ጥቅምት 8 2006 ዓ.ም)፡- ከሶስት ዓመት በፊት በአራት ኪሎ ከስላሴ ጀርባ የመሽገው ‹ማህበረ ስላሴ ዘ ደቂቀ ኤልያስ› በመባል የሚታወቀው ማኅበር ምዕመኑን በተለያየ የተሳሳተ አስምህሮዎች በማጥመድ ስራቸውን ሲሰሩ የነበሩት የ‹‹ተዋህዶ ክርስቲያን›› ነን ባዮች በአሁኑ ሰዓት ለጭፍራዎቻቸው የ‹‹ተዋህዶ ክርስቲያን›› እምነት ተከታይና ሰባኪ መሆናቸውን የሚገልጽ መታወቂያ በመስጠት ፤ የሚያስፈልጉ ውሎ አበል እና የተለያዩ ወጪዎችን በመሸፈን ወደ ተለያዩ ገዳማት እያሰረጉና እያስገቡ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ 

Saturday, October 12, 2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመገኝት ጸሎት አደረጉ

(አንድ አድርገኝ ጥቅምት 2 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ነገ ጥቅምት 3 2006 ዓ.ም ከናይጄሪያ  ጋር ላለባቸው ወሳኝ ጨዋታ ትላንትና አርብ አመሻሹ ላይ ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመሄድ አምላክ ድሉን እንዲያጎናጽፋቸው ጸሎት አድርገው ወደ ማረፊያቸው ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ተመልሰዋል ፡፡ ከሳምንት በፊት ዴቪድ ማርክ የተባሉ የናይጄሪያ ሴናተር መላው ናይጄርያዊ ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገውን ጨዋታ ለማሸነፍ እንዲያበረታታ በካቶሊክ አማኞች ለ9 ቀናት የሚዘልቅ የፀሎት ስነስርዓት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ በአሁኑ ሰዓት በርካቶች በአዲስ አበባ እና በበርካታ ክልል ከተማዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ማሊያ ስካርፍ እና እጅ ላይ የሚደረጉ ማጌጫዎችን በመግዛት ቡድኑን ለመደገፍ ከፍተኛ ዝግጅቶችን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ባሳለፍነው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አንዲት ጎልን ብቻ አግብቶ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጎሏ መገኛ የቅዱስ ገብርኤል ወዳጅ 19 ቁጥር በመልበስ የሚጫወተው አዳነ ግርማ መሆኑ አይረሳም፡፡ 

የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳችሁ