Tuesday, April 2, 2013

የአዲርቃይ ፍርድ ቤት ‹‹ዋልድባ አይታረስ›› ያሉትን ወጣቶች በአሸባሪነት ከሰሰ

  • የአዲርቃይ ፍርድ ቤት ገዳማችን አይታረስም በማለታቸው ወጣቶችን በአሸባሪነት ከሰሰ
  • በዛሬማ የሚገኙ ነዋሪዎች በወጣቶቹ ላይ ምስክርነት አንሰጥም በማለታቸው እንግልት እየደረሰባቸው ነው
  • የሰሜን ጎንደር ጸጥታ ክፍል ክሱ በአሸባሪነት መሆን አለበት በማለት ትዕዛዝ አስተላልፏል
  • የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከገዳሙ በረከት ለመቀበል የመጡት ማስፈራሪያ እና ፍተሻ (strip search) ተደረገባቸው
  • የጣሊያኑ ኮንስትራክሽን ሌላ አማራጮችን እንፈልግ ብሏል
  • የወልቃይት ነዋሪም እርሻውን እንዲቀጥል እስከሚመጣው ዓመት ምንም ነገር እንደማይኖር እየተነገረው ነው
(From Save Waldeba):- የዛሬ ዓመት አካባቢ ይሆናል የዛሬማ ወጣቶች ከመንግሥት ጋር ገዳማችን አይታረስም፣ የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም በማለት ከመንግሥት ታጣቂዎች ጋር ግብግብ የተፈጠረው፥ በወቅቱ የክልሉ ባለሥልጣናት በቦታው ተገኝተው ከዛሬማ ነዋሪዎች ጋር ስብሰባ አድርገው የዛሬማን ነዋሪ ውሳኔ እንዲሰጥ እያስፈራሩ ባሉበት ወቅት ነበር ጥቂት ወጣቶች የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም፣ ገዳማችንንም ፈቅደን አናሳርስም በማለታቸው ጥቂቶቹን በወቅቱ ወደ እስር ቤት ሲከቷቸው የተቀሩት አምልጠው ጫካ ገብተው ገዳማችንን ማንም ሊነካውም፣ ሊደፍረው፣ ሊረግጠውም አይገባም በማለት ጥሪያቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል የአካባቢውንም ገበሬ ማኅበራት፣ የሃገር ሽማግሌዎችን በማነጋገር እንዴት ዓይናችን እያየ ገዳማችንን የማንም አማቄላውያን (አረማውያን) መፈንጫ ይሆናል፣ ይሄ ቦታ እኮ የቅዱሳን ማረፊያ፣ የግዑሳን መጠጊያ ለእኛ ለተዳደፍነው እረፍት፣ በረከት፣ ቅድስና ለማግኘት የምንሄድበት እንጂ እንዴት እነዜህ አረማውያን ዛሬ እንደፈለጉት ያደርጉታል በማለት ተቃውሟቸውን በከተማው አስተዳደር /ቤት ከሃገረ ስብከቱ ሃላፊዎች ቢያቀርቡም የተወሰኑ የመንግሥት ሃላፊዎች በሃገር ሽማግሌዎች ምከሯቸው እና ወደ ቤታቸው እና ቤተሰባቸው ይመለሱ በማለት አግባብተው ወደ ሃገራቸው እና ቤተሰባቸው ከተቀላቀሉ የሦስት ወይም ሁለት ወር አይበልጣቸውም ነበር።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያስገነባቸው ያሰባቸው የስኳር ፋብሪካዎች ወጣቶቹም ወደ ሃገራቸው እና ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደተመለሱ ብዙም ሳይቆይ የአዲርቃይ ከተማ አቃቤ ሕግ ቢሮ ደብዳቤ ከሰሜን ጎንደር የጸጥታው ቢሮ ይደርሰዋል በደብዳቤውም ላይከዚህ በፊት ታስረስው እና በምሕረት የተመለሱት ወጣቶች በሙሉ በአሸባሪነት፣ በመንግሥት ላይ በመነሳት፣ እና ከግንቦት 7 ታጣቂዎች ጋር በመተባበርበአስቸኳይ እንዲከሰሱ እና የፍርዱንም ሄደት እንደሚከታተሉት ጠቅሰው ደብዳቤ ይጽፋሉ። ደብዳቤ የደረሳቸው የአቃቢ ሕጉ ቢሮ ሰራተኞች ወደ ዛሬማ በመሄደ ከከተማው የመንግሥት ተወካዮች እና የጸጥታው ሃላፊዎች ጋር መመካከር ይጀምራሉ፥ የዛሬማ ከተማ መስተዳደር እና የጸጥታው ሃላፊዎች እንዴት ብለን ነው በአሸባሪነት የምንከሳቸው? በምን መረጃ ነው ብለው ሲጠይቁ ሰዎችን አስመስክሩባቸው በማለት የአቃቢ ሕጉ ሰራተኞች ቢጠይቁም ጥቂት የአካባቢው ነዋሪዎች ተጠርተው የምስክርነት ቃላቸውን እነሱ በሚፈልጉት መልኩ ቢመሰክሩ ወሮታውን መንግሥት እንደሚሰጣቸው ቢያብሏቸውምእኛ በልጆቻችን ላይ የሃሰት ምስክር ልንሆን አንችልም፣ የምናውቀው ነገር ቢኖር ገዳማችንን አትንኩ ማለታቸውን ነው በማለት እንቢታቸውን ገልጸዋልየአካባቢው ነዋሪዎችም ‹‹እስከ ዛሬ ድረስ ሰዎችን እንዲህ እየደረጉ ነው ለካ በሃሰት እየከሰሱ ያሉት›› እነኝህ ወጣቶች ያደረጉት ነገር ቢኖር ገዳማችን አትንኩ ከማለት በስተቀር፡፡ እንኳን አሸባሪ ሊሆኑ ጭራሽ እንዴት እንዲህ ዓይነት ክስ ሊመሰርትባቸው ይችላል?  በማለት ቅሬታቸውን ደጋግመው በማሰማት የአካባቢው የጸጥታ ቢሮ እና የአዲርቃይ የአቃቢ ሕግ ሰራተኞች ተመካክረው ወጣቶቹን በአሸባሪነት ቀርቶ በሌላ ክስ ሊመሰርቱባቸው ተስማምተው እንደነበር ለማውቅ ተችሏል፡፡
መጋቢት ፲፮ ቀን ፳፻፭ .. በአዲርቃይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የዛሬማ ወጣቶች ለቤተክርስቲያናቸው፣ ለገዳመ ዋልድባ፣ እንዲሁም ለቅርስ እና ለሃገራቸው ሃብት በመቆርቆራቸው የተነሳ እንደ ወንጀለኛ ተከሰው በፍርድ ቤት ቀርበው የአዲርቃይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
፩ኛ/ ወጣት ደስታው   ብር 3000.00 ብር እንዲቀጣ
፪ኛ/ ወጣት ደፋሩ ታከለ ብር 2000.00
፫ኛ/ ወጣት ማሙሽ አሰፋ በብር 800.00
፬ኛ/ ወጣት ስሙን ያላገኘነው በብር1800.00 ብር እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡
የአካባቢው ማኅበረሰብ በወጣቶቹ ላይ የተወሰነውንም ውሳኔ በጥብቅ ተቃውመውታል።
በተያየዘ ዜና ከተለያየ የጎንደር ከተማ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ወደ 70 የሚጠጉ ተማሪዎች በየዓመቱ እንደሚያደርጉት ወደዋልድባ ገዳም በመሄድ ከገዳሙ በረከት ለመቀበል፣ በዮርዳኖስ ጸበል ለመጠመቅ፣ እንዲሁም ከመጋቢት መድኅኒዓለም ዋዜማ ጀምሮ በበዓሉ  በረከት ተካፋይ ለመሆን ጉዞ እንደሚያደርጉ ይታወቃል፥ ዘንድሮም እንደ አምናው እነዚህን ተማሪዎች ታጣቂዎች ከመንገድ አስወጥተው ምን ልታደርጉ መጣችሁ በማለት ብዙ ማንገላታታቸውንም የደረሰን መረጃ ያሳያል፣ ተማሪዎቹንም የተጠየቁት ጥያቄዎች
  • ከአካባቢው ሃገረ ስብከት ደብዳቤ ይዛችኃል ወይ?
  • እናንተ ባለፈው ጎንደር ላይ አመጽ ልታስነሱ ስትሞክሩ የነበራችሁ ናቸሁ፥
  • ዘራችሁ ምንድነው? አማሮች ከሆናችሁ ወደ ትግራይ ክልል መግባት አትችሉም፥
  • የግንቦት 7 ቡድን ናችሁ፣ ደፈጣ ለማድረግ ነው የመጣችሁት ፤ ጸረ ልማት እና ጸረ ሰላም ናችሁ
በሚል ክስ ወደ በረሃ ወስደው አንድ ቀን ሙሉ ልብሳቸውን ሲበረብሩ፣ ሻንጣቸውን ሲፈትሹ ውለው እጅግ ብዙ እንግልት እና ድብደባም ደርሶባቸው በመጨረሻ ከአንድ ቀን ሙሉ እንግልት በኃላ ወደሚፈልጉበት እንዲሄዱ ፈቅደውላቸዋል፤ ተማሪዎቹም እኛ ከገዳማችን በረከት ለመቀበል የማንንም ፈቃድ አንጠይቅም፣ የሃገረ ስብከት ተወካዮችም ሂዱ ወይም አትሂዱ ሊሉን የሚችሉበት ስልጣን የላቸውም እንደ ክርስቲያን ቤተክርስቲያንን ለመሳም እና በረከት ለመቀበል ፈቃድ ልንጠይቅ አይገባም በማለት ቁጣቸውን ቢገልጹም ታጣቂዎቹ ብዙ ማስፈራራት እና እንግልት አንዳደረሱባቸው ለመረዳት ችለናል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ እስከ ዛሬ ድረስ በገዳሙ ክልል ሊገነባ የታሰበውን ግድብ (እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ውዝግብ ያስነሳው ግድብ) የኮንስትራክሽኑ ሃላፊ የሆነው የጣሊያን ኩባንያ ለመጭው ሁለት ወራት ስራውን በደንብ ጥናት እንዲያደርግ እና መልሱን ለባለሥልጣናቱ እንደሚያሳውቅ አስታወቀ። ባለፉት 13 ወራት 4 የተለያዩ ኩባንያዎች ግንባታውን ለመሥራት ጥረት ሲያደረጉ መቆየታቸው ይታወቃል። ነገር ግን የሰው ሕይወት ከመጥፋት በስተቀር፣ ምንም አይነት ስራ መስራት ባለመቻላቸው ተስፋ መቁረጥ የሚታይባቸው የጣሊያን ኩባንያ ባለሥልጣናት ተጨማሪ የሆኑ ቦታዎችን ተመልክተው የቦታ ለውጥ ለማድረግም ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ይገመታል። የጣሊያኑ ኩባንያ ከህንዱ ኪባንያ ተቀብሎ ስራዎችን ለመሥራት ያደረገው 4 ወራት ጥረት ምንም መስራት ባለመቻላቸው ከመንግሥት ባለሥልጣናት ነቀፋ ቢደርስባቸውም ቀን ከሌሊት ቢሰሩም በመድኅኒዓለም ጥበቃ ግድቡ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ መስራት ባለመቻሉ ተስፋ መቁረጥ፣ እልህ፣ እና በቀል የሚታይባቸው የስኳር ፋብሪካ ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር አቶ አባይ ጸሐዬ ተጨማሪ ወይም ተለዋጭ ሃሳቦችን ከጣሊያኑ ኩባንያ እንደሚቀበሉ አስታውቀዋል።
የወልቃይት ገበሬ ማኅበራት እና በፕሮጀክቱ ምክንያት ከአካባቢው ትፈናቀላላችሁ ተብለው በስጋት ላይ ነበሩት አርሶ አደሮችም ለጊዜው ኑሮአቸውን መቀጠል እንደሚችሉ እና እርሻም ማረስ እንደሚችሉ የክልሉ ባለሥልጣናት ሲናገሩ ሰንብተዋል፥ የክልሉ ነዋሪም እምነቱን በእግዚአብሔር አድርጎ የእለት ተእለት ኑሮውን ቀጥሏል ፤ ነገ ምን ሊመጣ እንደሚችል ስለማይታወቅ ሁልጊዜም ባጣዳፊ ትነሳለህ ቢባል እንኳ ዝግጁ ሆኖ የነገን ስለማያውቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል። እርሻውንም ለማረስ ምንም አማራጭ ያጡት የወልቃይት ገበሬዎችነገ ተነሱ ብንባል ደግሞ፥ ለከርሞ ቤተሰባችንን የምናበላው የለንምእንዴት እንሁን? በማለት ምሬታቸውን አሰምተዋል አንዳንዶችም እጃቸውን ወደ ሰማይ በመዘርጋትአንተ ታውቃለሃበማለት አቤቱታቸውን ለአምላካቸው አቅርበዋል።
እኛም ለቤተክርስቲያናችን ፍጹም ሰላምን፣ በክፋት እና በድፍረት በአባቶቻችን ላይ ግፍ እና በደል ለሚያደርሱት ልቦን እንዲሰጥልን እንመኛልን።
የጻድቁ አባታችን አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ በረከት ይደርብን፥ እግዚአብሔር አምላካችን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን፣ ቅድስት ሃገራችንን፣ ሕዝባችንን በረደኤት ይጠብቅልን

3 comments:

  1. Amlakachen yetmesgene yehun , Geta hoy tebark!
    Enanten Andadrgen be Waldba guday eytegachehu newena tebarku

    ReplyDelete
  2. ግልጽ አቤቱታ።

    ለብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፥ ቀዳማዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት።

    ስለ ብፅእት ቅድስት ድንግል ማርያም
    ስለ ቅዱስ ሚካኤል
    ስለ ቅዱስ ገብርኤል
    ስለ ቅዱስ ሩፋኤል
    ስለ ቅዱስ ኡራኤል
    ስለ ቅዱስ ራጉኤል
    ስለ ቅዱስ ፋኑኤል
    እልፍ አእላፍ ስለሚሆኑ ስለቅዱሳን መላእክት በሙሉ
    በአፀደ ሕይወትም በአፀደ ነፍስም ስላሉ ቅዱሳን በሙሉ
    ስለ ቅዱሳን ሰማእታት በሙሉ

    አቤት ተበደልን፣ አቤት የኃያሉ አምላካችን የመድኃኔዓለም እርስት ተደፈረ፣ አቤት ዋልድባ ታረሰ። አቤቱ ለአስተዳዳሪ፣ አቤቱ ለመሪ፣ አቤቱ ለሊቀ ጳጳስ።

    ማመልከቻ ያስገቡልን፣ ስለ መዳህኔዓለም ቆመው ይከራከሩልን። ቅጂ ለመዳህኔዓለም።

    መረጃው ይሄውልዎ።

    https://docs.google.com/file/d/0B08ihe6dWn9Hcm96Q1p2c2VoWGc/edit?pli=1


    ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለ ወላዲቱ ድንግል፤ ወለ መስቀሉ ክቡር። አሜን።
    ኃይለሚካኤል።

    ReplyDelete
  3. we will be arrest you soon,we have got enough security information about you. Unless shout your mouth.

    ReplyDelete