Monday, April 29, 2013

አርቲስት ጀማነሽና ግብር አበሮቿ ዘብጥያ ወረዱ


(አንድ አድርገን ሚያዚያ 21 2005 ዓ.ም )፡- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሳቸውን ማህበረ ስላሴ ደቂቀ ኤልያስ የሚል ስም በመስጠት ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ሰዎች ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ በተነሳባቸው ተቃውሞ ምክንያት ዘብጥያ ሊወርዱ ችለዋል ፤ አራት ኪሎ አካባቢ በተከራዩት አዳራሽ አማካኝነት ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ ውድቅት ለሊት ድረስ በሚያካሂዱት ጉባኤ መሳይ ስብሰባ የአካባቢው ማህበረሰብ ስራቸውን በመቃወማቸው  ፤ ሰላማችንን አሳጡን በማለት ለፖሊስ በማመልከታቸውና ይህን ተከትሎ በተነሳው ውዥንብርና ግርግር ፖሊስ አርቲስት ጀማነሽን ፤ አንድን የእምነቱን ፈልሳፊ ሰው እና ቤቱን ለመስብሰቢያ ያከራየውን ሰው እስር ቤት ሊያስገባቸው ችሏል፡፡





የአዲስ አድማስ ጋዜጣ የቅዳሜ ዘገባ
(አዲስ አድማስ ሚያዚያ 19 2005 ዓ.ም) አርቲስቷ ማክሰኞ ማታ ተይዛ አራት ኪሎ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረች በኋላ ረቡዕ አመሻሽ ላይ ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ መዛወሯንና ከእርሷ ጋር ሌላ አንዲት ሴትና ሁለት ወንዶች መታሰራቸውን በስፍራው ተገኝተን አረጋግጠናል፡፡ አርቲስት ጀማነሽና አብረዋት የታሰሩት ግለሰቦች ሃሙስ እለት አፍንጮ በር መንገድ አዲስ አበባ ሬስቶራንት አካባቢ በሚገኝ የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው የታየ ሲሆን የፊታችን በድጋሚ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡

አርቲስቷንና አብረዋት የታሰሩትን ሰዎች ለመጠየቅ ወደ ስፍራው ከመጡ ግለሰቦች ለመረዳት እንደቻልነው፤ አርቲስቷና አብረዋት ያሉት ሰዎች የታሰሩትማህበረ ስላሴ ደቂቀ ኤልያስከተባለው ማህበራቸውና ከሀይማኖት ጉዳይ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ጠቁመው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ከአርቲስቷ ጋር የታሰሩት አንድ የሃይማኖት አባት፤ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ በመሆኑ ከፍርድ ሂደቱ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ፣ አሁን ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ነግረውናል፡፡
አርቲስት ጀማነሽን ሊጠይቋት የመጡ ሰዎችን ለማነጋገር ስትወጣ በተመለከትናት ጊዜ በፈገግታ የታጀበች ሲሆን ጠያቂዎቿእንዴት ነሽ ተመቸሽ?” ብለው ሲጠይቋትእግዚአብሔር ያለበት ቦታ ሁሉ ምቹ ነውስትል ምላሽ ሰጥታለች፡፡ አርቲስቷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህተዋህዶበሚል ሃይማኖት ውስጥ ተሣታፊ በመሆን አነጋጋሪ ሆና መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡

ወረዳ ዘጠኝ ፖሊስ ጣቢያ በተገኘን ጊዜ የሃይማኖቱ ተከታዮች የሚለብሱት የቀስተደመና ቀለማት ያሉት ነጠላ አጣፍታ፣ ፀጉሯንም የቀስተ ደመና ቀለም ዙሪያውን ባቀለመው ሻሽ አስራለች፡፡ ማህበረ ስላሴ ደቂቀ ኤልያስየኢትዮጵያን ትንሣኤ ሊያረጋግጥ ሃያል ባለስልጣን ነብዩ ኤልያስ ከብሔረ ህያዋን ጳጉሜ 1/2003 . ወደ ምድር መጥቶ በመካከላችን ይገኛል፣ ኦርቶዶክስ የሚባለው የሃይማኖት ስም ስህተት ነው ተዋህዶ ነው መባል ያለበት፣ ሰንበት ቅዳሜ ብቻ ነው፣ መለበስ ያለበት እግዚአብሔር ለኖህ ቃል ኪዳን የገባበትን ቀስተ ደመና ቀለማት ያካተተ ጥለት ያላቸው ነጭ አልባሳት ናቸውየሚሉትን የተለያዩ ጉባኤዎችን እያዘጋጀ የሚያስተምር ማህበር መሆኑን ያነጋገርናቸው የማህበሩ አባላት ገልፀውልናል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ከፖሊስ መረጃ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም፣ ከመምሪያው የተፃፈ ፈቃድ ያስፈልጋል በሚል የወረዳው ፖሊስ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

No comments:

Post a Comment