Tuesday, April 23, 2013

‹‹በውጭ ሲኖዶስ ሠራን የሚሉት ከአቡነ ጳውሎስ የባሱ ፥ ሃይማኖትን ጭራሽ የቀየሩ፣ ኃይማኖትንም የሚሳደቡና ከእግዚአብሔር መንገድ የወጡ ሰዎች ናቸው››


ከዚህ በፊት የተለያዩ ሰዎችን አስተያየት ብሎጋችን ላይ ምንም አይነት ማስተካከያ ሳናደርግ እንደወረደ ለአንባቢዎች ማቅረባችን ይታወቃል ፤ ከእነዚህ ጸሀፊዎች አንዱ የሆነውን የሰዓሊ አምሳሉ ሶስት ጽሁፎች ይጠቀሳሉ ፤ የሰዓሊ አምሳሉን ፅሁፍ መልስ የሚሆን ጽሁፍ ከሀገር ውጪ ከሚኖር ኃይለሚካኤል ከሚባል አንባቢ ስለደረሰን ጽፉን እንዲህ በማድረግ ለአንባቢያን አቅርበነዋል፡፡

(አንድ አድርገን ሚያዚያ 15 2005 ዓ.ም)፡- ሰዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን አርጋው የተባለ ሰው ባለፈው አንድ ሰውፖለቲከኛ ነው” ሲለው ለካ አውቆት ኖሯል። እኔ እኮ ምንም የእውቀት ችግር እንደነበረበት ባውቅም ከልቡ ለቤተክርስቲያን የሚያስብ ሰው መስሎኝ ነበር። በመጀመሪያ ባለፈው ጊዜ አምሳሉ ፓለቲከኛ ነው ሲል የተቃወምኩትን ሰው ይቅርታ እጠይቃለሁ። ከዛ በተረፈ ግን የአንድ አድርገን ብሎግ አዘጋጆች ከዚህ በታች ያለውን አስተያየት ለአንባቢያን ታደርሱልኝ ዘንድ እጠይቃለሁ።
ሰዓሊ አምሳሉ ሆይ፥


፩ኛ - ካህናትን መሳደብን እግዚብሔር እንደከለከለ አታውቅምን? ኃይማኖትን ሲቀይሩ ወይም ሲያጎድፉ ስታይ ፊት ለፊት ኃይማኖቴን አትንኩ ብሎ መናገር መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ማስረጃ ሳይኖርህ ካህናትን በጅምላ የግራ ክንፍ እያልክ መሳደብ አጸያፊ ነው። ከነሱ ውስጥ ድጎችም ሊኖሩ ይችላሉ፣ ሰርገው የገቡ አስመሳዮችም ሊኖሩ ይችላሉ። ሆኖም ግን በጅምላ ስድብ እንኩ ማለት መልካም አይደለም። ወይም እገሌ ኃይማኖትን እንዲህ አጓድሏልና ኃይማኖቴን ለመጠበቅ ይህን ማድረግ አለብኝ ብለህ የሚታይ፣ የሚጨበጥ ነገር ማቅረብ አንድ ነገር ነው። አንተ ግን የምታወራው ነገር ምን እንደሆነ እንኳን በትክክል የማታውቅ ሆነህ በዛ ላይ ስድብ ስታክልበት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል።
፪ኛ - አቡነ ጳውሎስ ቤተክርስቲያንን ብዙ በድለዋል። ኃይማኖታችን ሊያጎድፉ ከካቶሊኮች፣ ከኃሳውያን መሢሕ ፕሮቴስታንቶችና ከእምነተቢስ ህዝባዊ ወያን ሓርነት ትግራይ ወንበዴዎች ጋር ተባብረው ቤተክርስቲያናችን ለማጥፋት የወሰዷቸው እርምጃዎች የሚረሱ አይደሉም። በተለይ ደግሞ ከእምነተቢሶች ጋር እጅና ጓንት ሆነው የተቀደሰውን የዋልድባ ገዳም ለማፍረስ ያደረጉት ዘመቻ ለዘመናት የሚዘነጋ አይደለም። በዚህም ሥራቸው ከጥፋት መሪያቸው ከመለስ ዜናዊ ጋር ሁላችንም ዓይናችን እያየ ኃያሉ አምላክ እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ እንደ ፈርኦንና እንደ ግብጽ በኩሮች እንደቀሰፋቸው በቅርቡ ያየነው ተዓምር ነው። ሆኖም ግን የአቡነ ጳውሎስ ጥፋት በውጭ የሚገኙትን በአሜሪካን ሴኩላር ህግ የተመሠረተ የተለየ ሲኖዶስ ሠራን የሚሉትን ንጹሕ አያደርጋቸውም። አሜሪካን የሚገኙት የውጭ ሲኖዶስ ሠራን የሚሉት ከአቡነ ጳውሎስ የባሱ ፥ ሃይማኖትን ጭራሽ የቀየሩ፣ ኃይማኖትንም የሚሳደቡና ከእግዚአብሔር መንገድ የወጡ ሰዎች መሆናቸውን ሰዓሊው አምሳሉ አታውቅም የምታውቅ ከሆነ ደግ፡፡ እንደሚመስለኝ ፎቶህንም የለጠፍከው አሜሪካ የመምጣት ተስፈኛ ሆነህ በዚህ አስተያየትህ ስፖንሰር የሚያደርጉህ መስሎህ ሊሆን ይችላል። ተሞኝተሃል። አንተን ከኢትዮጵያ ማስወጣት ይቅርና አያገኙትም እንጂ እነሱ ወደ ኢትዮጵያ መመለስን የሚለምኑበት ቀን እሩቅ አይደለም።
፫ኛ - በፓትርያርክ ላይ ፓትሪያርክ አይሾምም የሚለው ሕግ የሠፈረው በፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ነው። እኒህ አንተ ይገባቸዋል የምትላቸው የውጭ ሲኖዶስ ሠራን የሚሉት ፍትሐ ነገሥትን አንቀበልም የሚል አስተያየት ከዚህ ቀደም ethiopianorthodox በሚባለው ድህረ ገጻቸው ላይ አውጥተውት ነበር። ፍትሐ ነገሥትን አንቀበልም ካሉ የሠሩት የአሸዋ ግንብ እንደሚፈራርስባቸው ሲገነዘቡ በኋላ ጽሁፏን አነሷት። ማን እንደሆኑ ለማወቅ በቂ ነው። ፍትሐ ነገሥትን ሳያምኑበት በፍትሐ ነገሥት ሕግ መሠረት ሥልጣን የኛ መሆን አለበት የሚባል አቤቱታ አለ ወይ? ይህን እግዚአብሔር ይቀበለዋል ወይ?
፬ኛ - በአሜሪካን አገር ያሉ የውጭ ሲኖዶስ ሠርተናል የሚሉት ሴቶች በግዳጃቸው ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲገቡ አድርገዋል፣ ግቡ ብለውም በየስቴቱ አስተምረዋል። ፍትሐ ነግሥት በነሱ ላይ የሰጠውን ፍርድ እነሆ ተመልከት።
ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ወገን አንዱስ እንኳ ተደፋፍሮ ከግዳጅዋ (ከደሟ) ያልነጻችውን ሴት ወደ ቤተ ክርስቲያን ያስገባ :- በደሟም ወራት ሥጋውንና ደሙን ያቀበላት ቢኖር ከሹመቱ ይሻር :: ምንም ከነገሥታት ሴቶች ወገን ብትሆን :: ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ቁጥር ፪፻፴፭
እንግዲህ እንደምታየው ያንተን ካህናቶች ፍትሐ ነገስት ሽሯቸዋል። ፍትሐ ነገስት የሻራቸው ፍትሃ ነገስትን ጠቅሰው ስልጣን ይገባናል ሊሉ ይችላሉ ወይ?
፭ኛ - እነዚህ ያንተ የውጭ ሲኖዶሶች ዋልድባ በተደፈረ ማግሥት የሲኖዶስ ስብሰባ አደረግን ብለው በስብሰባው መደምደሚያ የዋልድባ ጉዳይ ሳይቆጫቸው እስላሞችን በመደገፍ መግለጫ አውጥተዋል። የዋልድባን ገዳም ለማዳን ሎሳንጀለስ ላይ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ኢትዮጵያውያን እንዳይሳተፉ በመሰብሰቢያቸው ጥሪውን እንዳይነገር ከልክለዋል። ከነሱ መካከል አንድም ሰው አልተገኝም። የውጭ ሲኖዶስ የሚባለው መንገዱ ውጭ አገር ባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚቀየስ በመሆኑ ምክንያት የፖለቲካ ሰዎቹ ለፖለቲካ ሲሉ አንዳንዶቹን ገፋፍተው ያስወጧቸው ቢሆንም ውጭ አገር ሲኖዶስ መስርተናል የሚሉት የማያምኑት በፍትሐ ነገሥት ብቻ ሳይሆን በገዳምም አያምኑም። የገዳምን ነገርም ሆነ የፍትሐ ነገስትን (የቅዳሴንም ጭምር) ለፖለቲካ አኪያሄድ ስላመቻቸው እንጂ እኛ ውጭ አገር ያለን ሰዎች በአንዱም እንደማያምኑ እናውቃለን።
፮ኛ - ‹‹፭ኛ ሳይባል ፮ኛ አይባልም›› ያልከው ከሁለተኛ በኋላ ሥራአት እንደፈረሰ አታውቅምን? ሦስተኛ ሳይባል አራተኛም እኮ የለም። ያለ ጥርጥር ምንም ሦስተኛ ቅዱስ መሆናቸውን ብናውቅም በደርግ ሥርአት እንደተጣሰ እኮ መዘንጋት የለብህም።
፯ኛ - ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ቁጥር ፻፺፱ ኤጲስ ቆጶስ እራሱን ከክርስቶስ አገልጋይ አውጥቶ ለንጉሥ ከሚሠሩ ሥራዎች በማናቸውም ሥፍራ መሾም አይገባውም። በዚህ ጸንቶ ቢኖር ከሹመቱ ይሻር። ጌታችን አንድ ባሪያ ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻለውም አለዛም ግን አንዱን ያሳዝነዋል ሌላውንም ደስ ያሰኘዋል ብሏልና (ማቴ ፮፡ ፳፬) - ይላል። አሁን የውጭ ሲኖዶስ መሥራች አባ መልከጸዴቅ የጻፉትን ‹‹የቋሚ ምስክርነት›› የሚለውን መጽሐፍ አንብብና እንደገናም በደርግ ሸንጎ ውስጥ የያኔው ኤጲስቆጶሳት የነበራቸውን ተሳትፎ መርምርና ውጭ አገር እንኳን ሲኖዶስ ካህን እንኳን እንደሌለ ትረዳለህ። ሁለቱ በውጭ አገር ያሉ የውጭ ሲኖዶስ መሠረትን የሚሉትን ክህነት ሰው ሳይሆን ፍትሐ ነገሥት እራሱ ሽሮባቸዋል። መጽሐፍ የሻረውን አንተ ወደ መንበር ልታመጣ ትደክማለህ። እኔ ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ አቡነ መርቆሬዎስን ፓትርያርክ ያደርጋሉ ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበረ። ይህን የፈለኩት ትክክል ነው ብዬ ሳይሆን በውጭ አገር ብዙ የተዋህዶ ልጆች በዚህ የውጭ ሲኖዶስ በሚባለው ትምህርት እምነታቸው ወደ ፕሮቴስታንትነት እየተለወጠ ስለመጣ እነሱን በተኩላ ከመበላት ለማዳን መንገድ ይገኝበታል ብዬ ስላሰብኩ ነበረ። ወንድሜ ሆይ፥ ይልቁንስ የቤተክርስቲያን ቅንአት ካለህ ዋልድባን ሄደህ ተመልከትና ስለዋልድባ ጻፍ። አለቃ አያሌው የተናገሩትን ሁሉ ደግሞ ፈላልገህ አድምጥ። ብዙ ትምህርት ታገኝበታለህ።

ኃይለሚካኤል።

6 comments:

  1. ወያኔ እና ዘረኛ የሆነ ሰው እውነትን አይቀበልም አቶ አምሳሉ እውነትን ቁልጭ አድርገው አስፍተውና አምልተው በማስረጃ አስደግፈው ለአንባብያን አቅርበዋል አንተ ደግሞ የግለሰብ ጥላቻ እነጂ እውነቱን መቀበል እንደ እሬት መሮሃል ልቡና ይስጥህ

    ReplyDelete
    Replies
    1. AnonymousApril 23, 2013 at 12:03 PM እርስዎስ ገና ወያኔ ሚለውን ቃል መናገር ሲጀምሩ ራስዎ ፖለቲከኛ ከፖለቲካም የደርግ ወይም የሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች ደጋፊ ወይም አባል መሆንዎ ያስታውቅብዎታል። ስለዚህ አርስዎም እውነቱን መቀበል ወይም ማየት ተስኖታል በዚህ መንገድ የምንመላለስ ከሆነ ለምን በቤተክርስትያን ስም እንነግዳለን። ወንድማችን/እህታችን እውነት ስለሃይማኖት አስበው መናገር ከፈለጉ የርስዎንም ፖለቲካ የተቀባ አስተያየት በሃይማኖታዊ ስፍራ/ውይይት መድረክ ሲደርሱ ከነሰንኮፉ አውልቀው መጣል ይኖርብዎታል።

      ፖለቲካን ለማራመድ በሃይማኖት መድረክና በቤተክርስትያን ስር ለምትታከኩ ለምትሽሎኮሎኩ ለምትደበቁ ለምትመሽጉ ወዘተ እባካችሁ ፖለቲካ ሰፊው ዓለም አለላችሁ ቤተክርስትያን፡ገብታችሁ አትበጥብጡን እናንተም፡አትቀሰፉ፡በየተክርስትያንን፡የደፈረ ለኩነኘየ ይዳረጋልና፡

      Delete
  2. Thanks a lot the writer you very well Aba Melkesadik, He is the one who makes all this mess, he is the one who brought Organ to TRINITY church while he was on power. Now he is doing it in his own Co-operated organisation. and alot..... and please find out also how he left to America their is a big reason (He has got ESES, He is one of the TEHADESO memeber. Even go back and try to find who was his master(MESERETE Sebeat Leab) was his mentor he died. He was one of the protestant affiliate to expand Tehadeso in Ethiopia 1940,50,60. pls u will get from the church do research people who like to know the truth.

    አሁን የውጭ ሲኖዶስ መሥራች አባ መልከጸዴቅ የጻፉትን ‹‹የቋሚ ምስክርነት›› የሚለውን መጽሐፍ አንብብና እንደገናም በደርግ ሸንጎ ውስጥ የያኔው ኤጲስቆጶሳት የነበራቸውን ተሳትፎ መርምርና ውጭ አገር እንኳን ሲኖዶስ ካህን እንኳን እንደሌለ ትረዳለህ።

    ReplyDelete
  3. Kale eywet yasemalen melkame melse new

    ReplyDelete
  4. ቁጥር አንድ አስተያየት ሰጪ ከወያኔ በላይ ዘረኞች እነሱ እንደሆኑ
    አገር ያወቀው ጸሃይ የሞቀው ነውና የራስዎትን ማንነት ባያስተዋውቁ ጥሩ ነው

    ReplyDelete
  5. አገር ቤት ያለው በሊቀ ጻጻስ አባይ ጸሀዬ ከሚመራው ሲኖዶሰ ጋር ወደፊት እንበል አሜሪካማ ሩቅ ነው ሀይማኖት ከቀየሩ ሥርዓት ካፈረሱ ለምንስ ኦርቶዶክስ እንላቸዋለን

    ReplyDelete