Monday, April 1, 2013

አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን ለመገናኛ ብዙሀን የላከችው ደብዳቤ



ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ፡፡
“…
ወበሠሉስ፡ዕለት፡አነስኦ፤
“...
በሦስተኛው፡ዕለት፡አነሳዋለሁ፤ዮሐ፤፪

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
፯፼፭፻፭ ዓመተ ፍጥረት ፩፼፸፪ ሱባኤ ፻፶ እዩቤልዩ አመ ፳፭ ለየካቲት፡፡
ለሰው ልጆች በሙሉ

የእናታችሁን የቅድስት ምድር የኢትዮጵያን ጥሪ ተቀበሉ! ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛና መዳኛ መሆንዋ ለዘመናት በተነገረላት ትንቢት በተሰጣት ተስፋ መሰረት ትንሳኤዋን ሊያረጋግጥ ኃያል ባለስልጣን ቅዱስ ኤልያስ ከብሔረ ህያዋን መጥቷል፡፡

ቅዱስ ኤልያስ ከነህይወቱ በእሳት ሠረገላ ያረገ ማንም ሊቃወመው ወይም ሊያስቆመው የማይቻለው ተፈጥሮን የማዘዝ ስልጣን የተሰጠው ታላቅ ነቢይ ነው፡፡ይህ ነው ለቅድስት ሀገሩ ለኢትዮጵያ ቀናኢ ሆኖ የተነሳው፡፡

ይህ የሰው ልጆች ሁሉ ሊያውቁትና ሊገነዘቡት የሚገባ እውነታ ነው፡፡ስለዚህም ይህንን እጅግ ታላቅ አስፈሪና ጥልቅ ሃይማኖታዊ ምስጢር በተመለከተ በታላላቅ አባቶች ትንታኔና ትምህርት የሚሰጥበት፤ጥያቄና መልስ የሚካሄድበት ጉባኤ ከጽዋ ማኅበሬ ጋር በመሆን በመስቀል አደባባይ በኤግዝቢሽን ማእከል በአዳራሽ ቁጥር 3 የካቲት ፳፰ (28) ከቀኑ 800 ሰዓት ታላቅ ጉባኤ አዘጋጅቻለሁና እናንተም በዚህ በአባቶቻችን “…በሦስተኛው ዕለት አስነሳዋለሁተብሎ ተሰይሞ ልዩ ክብር ወደተሰጠው የኢትዮጵያ ትንሣኤ ወደሚታወጅበት የሰንበት እረፍት ፣ሠማያዊትና ዘላለማዊት ተዋህዶ፣ሕግና ነቢያት እና ሌሎች ታላላቅ ቅዱስ ኤልያስ የገለጻቸው ምስጢራት በሚነገሩበት በእዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ እንድትገኙልኝ በአክብሮት ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡


ተዋናይት ጀማነሽ ሰሎሞን (እምነ አስራተ ዳዊት ዘኢትዮጵያ፡፡)

ማኅበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አሐቲ የሰማይ ጉባኤ ዘቅድስት ቤተክርስቲያን ቅድመ መንበሩ ለእግዚእነ ወእመ ኩሉ ፍጥረት ወላዲተ አምላክ የጽዋ ማኅበር፡፡

7 comments:

  1. ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።
    መድህኔዓለም የተመሰገነ ይሁን።

    እስኪ ወደዚህ ስብሰባ ባጋጣሚ የሚሄድ ሰው ካለ ለወይዘሮ ጀማነሽ ጥያቄ ያቅርብልኝ።

    “ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ” ማለት ምን ማለት ነው? “ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ” ናት” ብሎ ነቢዩ ኤልያስ ገለጠልኝ ነው የምትለው? ማለትም ጦጣ በኢቮሉሽን ሉሲ ሆና ክዛም ሰው የሆነችበት አገር ኢትዮጵያ ናት ብሎ ገለጠልኝ ማለቷ ነው? እስኪ ጠይቋት። እኔ ሩቅ አገር ስለምኖር በቅርብ ላገኛት ስለማልችል ነው።

    እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
    ኃይለሚካኤል።

    ReplyDelete
  2. ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።
    መድኃኔዓለም የተመሰገነ ይሁን።

    እስኪ ወደዚህ ስብሰባ ባጋጣሚ የሚሄድ ሰው ካለ ለወይዘሮ ጀማነሽ ጥያቄ ያቅርብልኝ።

    “ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ” ማለት ምን ማለት ነው? “ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ” ናት” ብሎ ነቢዩ ኤልያስ ገለጠልኝ ነው የምትለው? ማለትም ጦጣ በኢቮሉሽን ሉሲ ሆና ክዛም ሰው የሆነችበት አገር ኢትዮጵያ ናት ብሎ ገለጠልኝ ማለቷ ነው? እስኪ ጠይቋት። እኔ ሩቅ አገር ስለምኖር በቅርብ ላገኛት ስለማልችል ነው።

    እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
    ኃይለሚካኤል።

    ReplyDelete
  3. oh my God ! who teach them geez . Guys do you know the problem we didnot teach wongel. that is why these kind of people came. you andeadergen let me tell you the truth if ethiopian people donot learn wongel they will go with this kind of teaching.

    ReplyDelete
  4. የቀረቡልን ሦስቱ የወይዘሮ ጀማነሽ የመጽሐፍ ቅዱስ ክህደቶች ከነማስረጃ ኃይለ ቃሎች ፡-
    1. መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው ይላል እንጅ ሥፍራውን ከኢትዮጵያ ምድር ይሁን ከሌላ ቦታ ለይቶ አልገለጸም ፡፡
    * “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።” ዘፍ 1፡1
    * “እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።” ዘፍ 1፡27
    * “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።” ዘፍ 2፡7

    2. የመጽሐፍ ቅዱሱ ኤልያስ ቴስብያዊ እንጅ ኢትዮጵያዊ አይደለም ፡፡
    *“በገለዓድ ቴስቢ የነበረው ቴስብያዊው ኤልያስ አክዓብን፦ በፊቱ የቆምሁት የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ጠልና ዝናብ አይሆንም አለው።” 1 ነገ 17፡1

    3. የመጽሐፍ ቅዱሱ ኤልያስ መምጣቱን ኢየሱስ ራሱ ተናግሯል ፤ በዳግምና ሳልስ የሚመጣ ቢሆን ሌላ ጊዜም ይመጣል ብሎ ለጠያቂዎቹ በመለሰላቸው ነበር ፡፡
    *“እነርሱም። ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ እንዲገባው ጻፎች ስለ ምን ይላሉ? ብለው ጠየቁት። እርሱም መልሶ። ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናናል፤ ስለ ሰው ልጅም እንዴት ተብሎ ተጽፎአል? ብዙ መከራ እንዲቀበል እንዲናቅም። ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ደግሞ መጥቶአል፥ ስለ እርሱም እንደ ተጸፈ የወደዱትን ሁሉ አደረጉበት አላቸው።” ማር 9፡11-13

    እንግዲህ እንዲህ እንዳመለከትኩት ስምን ብቻ ይዘው ቀጣጥፈው ቀጣጥፈው የሆነ የንግድ መስክ ለመጀመር አቅደው የተነሱ (መጽሐፍና ሌላም ነገር ለመነገድ) አለያም ከክርስትና እምነት ውጭ የሆነ አዲስ ሃይማኖትን ለመፍጠርና መባ ለመሰብሰብ አስበው ካልሆነ በስተቀር መጽሐፍ ቅዱስን የተከተለ እምነት አይደለም ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. ሰለም ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።
      መድኃኔዓለም የተመሰገነ ይሁን።

      አሁን መልካም የሆነ አስተያየት ሰጡ። በዚህ እንስማማለን።

      እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ተብሎ ነው የተጻፈው። ከዚህ ውጭ ያለ ፀረ እግዚአብሔር የሆነ ሰው ሠራሽ ኦሪት ዘፍጥረት በተቀደሰው የኢትዮጵያ ምድር መሰበክ አልነበረበትም። ከእርሷ የማብራሪያ መልስ እስክንሰማ መጠበቅ ሊይስፈልግ ይችላል እንጂ ወይዘሮ ጀማነሽ “ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ” ብላ በጻፈችው ዐረፍተ ነገር እጅግ በጣም አዝኛለሁ። “ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ ናት” የሚለው ቋንቋ የኃሳውያንና የኢቮሉሺኒስቶች ቋንቋ ነው። የዚህ መሠሪ ቋንቋ አላማ እግዚአብሔርን ከሰው ልጅ እምነት ማስወጣት ነው። ብዙ የኛ አገር ሰዎች የሉሲን ሚስጢር አያውቁትም። ብቻ የአውሬውን ንግግር እየተከተሉ፥ “ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ” እያሉ አውሬውን እየተከተሉ ያጨበጭባሉ። ካህናቶችም ሳይቀሩ ነው ይህን የሚያደርጉት። የሉሲ ፕሮጄክት ሚስጢር በኦሪት ዘፍጥረት ለተጻፈው የሰው ልጅ አፈጣጠር ታሪክ እግዚአብሔርን የሚሰድብና የሚፃረር የሰው የሆነ አማራጭ ማቅረብ ነው። ለዚህ እኩይ አላማ ኢትዮጵያ የተመረጠችበት ምክንያት ቅድስናዋን ለማጥፋት እና የአውሬው ተገዢ ለማድረግ ነው። በነገራችን ላይ አውሬው ለጦጣዋ የሰጠው የራሱን ስም ነው። ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፲፬ ቁጥር ፲፪ አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ! ተብሎ እንደተጻፈ “አጥቢያ ኮከብ” በእንግሊዝኛ “ሉሲፈር” ይባላል። የምእራባውያንን ኢሳይያስ ም ፲፬ ቁ ፲፪ ትርጉም ቢመለከቱ “How art thou fallen from heaven, O Lucifer, son of the morning!” ይላል። ስለዚህ ስሙ ሉሲፈር ሲሆን አውሬው ለጦጣዋ የሰጠው የራሱን ስም ምህጻረ ቃል “ሉሲ” ብሎ ነው።

      ኤልያስ “ኢትዮጵያዊ” ነበር ወይ? ማን ያውቃል? ቅዱስ መጽሐፍ ቴስብያዊ ይለዋል ትርጉሙም እንግዳ ማለት ነው። ቴስቢያዊ የሚለው የአማርኛ ትርጉም ችግር ያለበት ይመስላል (etymological)። ግዕዙ በቅርብ ያላችሁ የግእዙን አገላለጽ ብታስረዱን ይረዳናል። ቅዱስ ኤልያስ በገለዓድ የኖረ እንግዳ ሊሆን ይችላል። ከዛ አረፍተ ነገር ተነስቶ ኢትዮጵያዊ ነበር ማለት አይቻልም። ኢትዮጵያዊ አልነበረም ማለትም አይቻልም። የሙሴ ቤተሰቦች የነበሩ ብዙ ኢትዮጵያውያንና ከሳባ ንግሥት ከማክዳ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ሄደው ንጉሡ ሰሎሞን ለንግሥቷ በሰጣት መሬቶች ላይ የሠፈሩ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። ቅዱስ እልያስ ኢትዮጵያዊ ነው ካለች ወይዘሮ ጀማነሽ ማብራሪያ መስጠት ይጠበቅባታል። በመጨረሻው ዘመን ይመጣል አይመጣም እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው። ኤልያስ ደግሞ እንደመጣ ክርስቶስ ተናግሯል። የክርስቶስ ቅኔ ስለ መጥምቁ ዮሃንስ ነበር። የእግዚአብሔር ቅኔ ብዙ ዘርፍ አለው፥ አሁንም ይመጣ እንደሆነ ለማወቅ ቅኔ አዋቂዎች (ቅዱሳን) ያስፈለጋሉ።

      እኔ እንደሚመስለኝ “የሰው ዘር መገኛ” ያለችው ቃል ከማህበሯ ከሆነ ማህበሯ ከእግዚአብሔር እንዳልሆነ የሚያሳይ አቢይ ምልክት ስለሆነ ኢትዮጵያውያን ይህን እንዲያውቁት ማድረግ ይጠቅማል።

      ምስጋና ለመድኃኔዓለም ይሁን።
      ኃይለሚካኤል።

      Delete
    2. ስለማብራሪያዎ አመሰግናለሁ ፡፡

      Delete
    3. ስለ ቴስቢና ቴስቢያዊ ይህንንም አነበብኩ ፡፡
      Tishbe: a town in Gilead
      Tishbite: a resident of the town of Tishbe
      Tishbite (Hebrew) = "captivity"

      "Prophet Elias, also known as Elijah was born in a remote and little known Village called Tishbe, which lies among the mountains of Gilead, on the other side of the Jordan River. This area is not too far from the country of the Gergesenes, where, in the time of our Lord the devils entered into the swine. (Luke. 8:26-39) The book of Kings of the Bible, make the following record about Elias“And Elijah the Tishbite, who was of the inhabitants of Gilead” (I Kings, 17:1) He was born and raised by a Jewish family of which we know nothing. His birth place Tishbe, is interpreted to mean a converter and the name Elijah as “My God of power” or “Jehovah is my strength”. We know nothing about his childhood and his life. Most probably Elias was a child with no education or schooling. His fathers name was Sadok while we know nothing about his mother. In the Book of Kings, we find Elias entering the stage of history, abruptly out of nowhere, with a word of faith and power presenting himself to the king saying“And Elijah the Tishbite said Unto Ahab. “As the Lord God of Israel lives, before whom I stand, there shall not be dew or rain these years, but according to my word.” (1st Kings, 17:1)"
      ምንጭ፡- http://ocarm.org/en/content/ocarm/prophet-elias-elijah-tishbite-life-and-times

      Delete