በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት፣ በዲታ ወረዳ፣ ጋና ደሬ ቀበሌ፣ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ከሌሊቱ በስድስት ሰዓት አካባቢ በእሳት ከተቃጠለ በኋላ የምእመኑ ለቅሶ ….
Friday, February 10, 2012
ፈተናችን በዝቷል
Thursday, February 9, 2012
Wednesday, February 8, 2012
ሐውልቱ ስር ምን አለ?
‘ Ethiopia shall soon stretch out her hands unto God.’
(አንድ አድርገን ጥር 30 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ቅዳሜ ጥር 17 ቀን 2004 ዓ.ም. አዲስ አበባ አንድ ዓቢይ ታሪካዊ ክሥተት አስተናገደች ፤ በ “ዓለም በቃኝ” (ከርቸሌ) መቃብር ላይ የተገነባው አዲሱ የበረከተ ቻይና ሕንፃ ፤ የአፍሪካ ኅብረት ለወለደው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት (አአድ) ጠንሳሿ ኢትዮጵያ ብኵርናዋን አሳልፋ የሰጠችበት መሪዎቿም አባሪና ተባባሪ ኾነው ያጸደቁበትን ፣ በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት ሕንፃ የተተከለውን የጋና ቀዳማዊ ፕሬዚዳንት ክዋሜ ንኩሩማ ሐውልት ቄጠማ ተነስንሶ እልል ተብሎ ሲመረቅ አይታ አንገቷን የደፋችበትን ትዕይንት አስተናግዳለች፡
Tuesday, February 7, 2012
የሰበካ ጉባኤ ምርጫና ኮሮጆ ግልበጣ
(አንድ አድርገን ጥር 28 ፤ 2004ዓ.ም )፡- የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ምርጫ በ27/5/2004 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን ምርጫው ግን የተጭበረበረ መሆኑን ከቦታው የደረሰን በአይን እማኝ ተገልፆልናል ፡፡ መጭበርበሩን የተገነዘቡ ምእመናን ጥያቄ ቢያቀርቡም የደብሩ አስተዳዳሪ ግን የምእመኑን ጩኸት ወደ ጎን በመተው ምርጫው ሳይፈጸም ቅዳሴው እንዲዘጋ ቀጭን ትዕዛዝ በማስተላለፍ ሁሉም ምዕመን ሳያምንበት ምርጫውን ቋጭተውታል፡፡ ሁሉም ክርስትያን ማወቅ ያለበት ስለ ዛሬ ተመራጮች ብቻ ሳይሆን እነዚህ ያለ አግባብ የተመረጡ ሰዎች ነገ በቤተክርስትያናችን ላይ ስለሚያደርሱት ጉዳትም ጭምር ነው ፤ ለዓመታት ሲያበጣብጥ የነበረው የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ላይ በፊት እነሱ የሚመስሏቸውን ሰዎችን በመምረጥ ለምእመኑ ህጋዊ በመምሰል ለብዙ ወራት እሾህ ሆነው መቆየታቸው ፤ በመጨረሻም ጉዳዩ ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር በመድረስ እልባት ያገኝበትን ሁኔታ የቅርብ ትውስታችን ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የእኛ ችግር የተመረጠውን የሰበካ ጉባኤ ችግር ሲፈጥር መጮህ እንጂ መጀመሪያ ላይ እኛው ያገባናል ይመለከተናል ብለን በሰበካ ጉባኤ ምርጫ ቀን ቤተክርስትያን በመሄድ ሀላፊነታችንን አንወጣም ፤ በዚህም ምክንያት ምእመኑ የማያውቃቸው የሰበካ ጉባኤ አባላት ተመርጠው ሲያበቁ ፤ ስርአተ ቤተክርስትያን ሳያከብሩ ሲቀሩ ፤ ሙዳየ ምጽዋት ሲገለብጡ ፤ እጃቸው በሙስና ሲጨማለቅ ፤ በብልሹ አሰራር ሲተበተቡ የዛኔ እኛ እንነቃለን ፤ እነርሱን ከተሰጣቸው የሀላፊነት ቦታ ለመቀየርም እንቸገራለን ፤ እና መፍትሄው ሲጀመር ነውና ይህን ጉዳይ አፅንኦት ብንሰጠው ጥሩ ነው የሚል ሀሳብ አለን፡፡
Monday, February 6, 2012
ስለ ብርሃን እንዲመሰክር ስለ ተላከው መብራት
(የዮሐንስ ወንጌል የሦስተኛው ሳምንት ጥናት)!
“ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክርዘንድ ለምስክር መጣ። ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ፥ እርሱ ብርሃን አልነበረም። ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛውብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።” ዮሐ.1፡6-9
አካላዊ ቃል ከአባቱ ዕሪና ሳይለይ ሰው ሆኖ ተገልጧልና ስለዚሁ ድንቅ ነገር ይመሰክር ዘንድ መልአክ ሳይሆን ዮሐንስ የሚባል ሰው ተላከ /አውግስጢኖስ/፡፡ ሌሎች ነብያት ክርስቶስ “ይወርዳል ይወለዳል” ብለው ትንቢት ቢናገሩም ክርስቶስን ሊያዩት ወደዱ እንጂ አላዩትም /ማቴ.13፡16-17/፤ ሐዋርያትም “ወረደ ተወለደ” ብለው አስተማሩ እንጂ “ከእኛ በኋላ ይመጣል” አላሉም /ሐዋ.4፡2/፡፡ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከእርሱ የሚበልጥ የሌለ መጥምቁ ዮሐንስ ግን እንደ ነብይ “ከእኔ በኋላ ይመጣል”፤ እንደ ሐዋርያም “ይመጣል ያልኳችሁ እርሱ ነው” እያለ ያስተምር ነበር /ዮሐ.1፡15፣30፣ ሄሬኔዎስ/፡፡ ወንጌላዊው ስለ አካላዊ ቃል ቀዳማዊነት እየመሰከረልን ቆይቶ አሁን ደግሞ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ምስክርነት ጨምሮ የሚነግረን ምስክርነት በሁለት ወይም በሦስት ስለሚጸና ነው /ዘዳ.19:15፣ ቅ.ቄርሎስ/፡፡
Sunday, February 5, 2012
‹‹ትንቢተ ዮናስ›› በዶ/ር ከበደ ሚካኤል

(አንድ አድርገን ጥር 28 ፤ 2004ዓ.ም)፡- የነነዌ ፆም በደረሰ ቁጥር የከበደ ሚካኤል ይችህ ግጥም ትዝ ትለኛለች ፤ የትንቢተ ዮናስን ምዕራፍ እንዴት በግጥም መልክ ማስቀመጣቸውን ሳስበው ይገርመኛል ፤ ይህኛውን ግጥማቸውን ሳነብ መጽሀፍ ቅዱስ ያነበብኩ ይመስለኛል ፤ ከበደ ሚካኤል በርካታ መጽሀፍትን በነበሩበት የህይወት ጊዜያት ለማህበረሰባችን አበርክተዋል ፤ በስነ ፅሁፍ ታሪክ ውስጥ ገናና ከሆኑ ደራሲያን አንዱ ናቸው ፤ ትምህርታቸውን ከቤተክህነት ቢጀምሩም በ1990 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ሊቀበሉ የቻሉ ታላቅ የስነ ፅሁፍ ባለሙያ ናቸው ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስራቸውን መዝኖ የክብር ዶክትሬት በሰጠበት ወቅት ‹‹ በድርሰቶቻቸው ውስጥ የሚታዩት የእኒህ ታላቅ ደራሲ የሀሳብ መግለጫዎች ፤ ቃላት ዘይቤዎች ፤ ሌሎች የአፃፃፍ ስልቶች በኋላ ለመጡ ደራሲዎች ያደረጉት አስተዋፅኦ ቀላል አይደለም ፤ ›› ብሏል ፡፡
Friday, February 3, 2012
ጾመ ነነዌ!!
እንኳን አደረሳችሁ!!
ነነዌ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪካቸው በስፋት ከተጻፈላቸው የሜሶፖታምያ ከተሞች አንዷ ናት፡፡ ብዙ የሥነ መለኰት ምሁራን ከዛሬዋ የሞሱል ከተማ በተቃራኒ ከባግዳድ ሰሜን ምዕራብ 350 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ እንደ ነበረች ይስማማሉ፡፡ ምንም እንኳን በ4000 ቅ.ል.ክ. ገደማ በናምሩድ በኵል ብትቆረቆርም /ዘፍ.10፡11-12/ የአሦራውያን ዋና ከተማ የሆነችው ግን በ1400 ቅ.ል.ክ. ነው /2ነገ.19፡36/፡፡ በከተማዋ በጣም ታዋቂ የነበረው የጣዖት ቤተ መቅደስ የአስታሮት ቤተ መቅደስ ይባላል፡፡
የአዲሱ ሚካኤል ምዕመን አስተዳሪውን አገዱ
- አቡነ ጳውሎስና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቃላቸውን አልጠበቁም
(አንድ አድርገን ጥር 25 2004ዓ.ም )፡- የደብረ መዊዕ ቅ/ሚካኤል ካቴድራል ካህናት እና ምዕመናን የካቴድራሉን ንብረት ለግል ጥቅማቸው አውለዋል ፤ ከተባባሪዎቻቸው ጋር በመመሳጠር በብዙ ሺህ የሚቆጠር የካቴድራሉን ገንዘብ አጉለዋል፤ በካቴድራሉ አስተዳደር እና በሀገረ ስብከቱ የማይታወቁ ተገቢ ያልሆኑ ቅጥሮችንና ዝውውሮችን ፈፅመዋል፡፡ ገቢዎችን በተደጋጋሚ ዘርፈዋ ያላቸውን አስተዳዳሪ ከሀላፊነታቸው አገደ፡፡
Wednesday, February 1, 2012
ቤተክህነቱ አዳራሹን ለተሀድሶ አቀንቃኞች ሳይፈቅድ ቀረ
(አንድ አድርገን ጥር 23 2004 ዓ.ም)፡- ጥር 20 /2004 ዓ.ም የተሀድሶያውያን ስብስብ ሊያደርጉት የነበረው ጉባኤ ከለባት የቤተክህነቱ ጥያቄ መመለስ ስላልቻሉ ጉባኤው ሳይደረግ እንደዋለ ለማወቅ ችለናል ፤ የቤተክህነቱ ሀላፊዎች ቀደም ብለው አዳራሹን ለጉባኤ የፈቀዱ መሆኑ ቢታወቅም በመጨረሻ ጉባኤውን ሊያደርጉ ያሰቡትን ሰዎች ‹‹ እዚህ ቤተክህነት አዳራሻ ላይ ቤተክርስትያንን የሚወክሉ መምህራን ከሆነ እንደሚፈቅዱ ያለበለዚያ ግን በስመ እርዳታ ቤተክርስትያንን የማይወክሉ በሲኖዶስ ጉባኤ የታገዱ ሰዎች ከሆኑ እንደማይፈቅዱላቸው›› እርግጡን ነግረዋቸው ጉባኤው ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ ከጉባኤው ሁለት ቀናት በፊት ጉባኤው እንደተሰረዘ በቤተክህነት ሰሌዳ ላይ ቤተክህነቱ ማስታወቂያ ለጥፏል፡፡ በዚህ ጉባኤ አለመካሄድ ጥቂት ሰዎች ከእነርሱ ወገን የሆኑ ሰዎች መካሄድ አለበት ብለው ብዙ ቢሮዎች ቢያንኳኩም በበሬ ወለደ ድህረ ገፃቸው አማካኝነት ቢፅፉን በሩን የሚከፍት ሰው ሊያገኙ አልቻሉም፡፡
300ሺህ ብሩ የት ገባ ?
- በዝግ ሂሳብ ባንክ ገብቷል - ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኢጲፋንዮስ
(አንድ አድርገን ጥር 23 ፤ 2004ዓ.ም)፡- በምዕራብ ሸዋ ሐገረ ስብከት (ዞን) የሚገኙ ምዕመናን ለገጠር አብያተክርስትያናት ተብሎ የተዋጣ ከ300ሺ ብር በላይ የት እንደገባ እንደማያውቁና ሳይመዘበር እንዳልቀረ ሰሞኑን ተናገሩ፡፡ ገንዘቡ የተዋጣበት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በዞኑ ዋና ከተማ በአምቦ አለመከናወኑ ጥርጣሬ አሳድሮብናል ብለዋል - ምዕመናኑ፡፡ በምዕራብ ሸዋ ሐገረ ስብከት (ዞን) የአስተዳደር ችግር እንዳለ የጠቆሙት ምዕመናኑ፤ ሥራቸውን በአግባቡ ሲወጡ የነበሩት ከሃላፊነት ተነስተው መሾም የማይገባቸው ተሹመዋል እንዲሁም አምቦ አካባቢ የሚገኘው የአዋሮ ቅዱስ ሚካኤል መሬት ተሸንሽኖ ለግለሰቦች እየተሸጠ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)


