ድጋሚ የቀረበ
አንድ አድርገን መስከረም 2
2006 ዓ.ም)፤-
የልዑል እግዚአብሔር ቸርነትና አዳኝነት ከሚገለጥባቸው ምክንያቶች ወይም መንገዶች አንዱ ጠበል ነው፡፡ በገዳማትና አድባራት ቅጽር፣ በቅጽሩ ዙርያና በአካባቢው ሰበካዎች ባሉ የጠበል ቦታዎች በፍጹም እምነት የሚቀርቡ ምእመናን በጠበል እየተጠመቁ ፈውስ ያገኛሉ፤ የእግዚአብሔር ደገኛ ተኣምራት እየተገለጸ ምሕረቱ የተደረገላቸው ሁሉ በየጊዜው ድንቅ ሥራውን እየመሰከሩ ይገኛሉ፡፡
በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ማጥመቅ የሚችለው የቅስና ሥልጣነ ክህነት ያለው አባት ብቻ ነው፡፡ ቅስና የሌለው ሰው አያጠምቅም፤ አያናዝዝም፤ አይባርክም /ፍት.ነ.ፍ.መ.አን.3 ቁ.21/ ቅዱሱን ቅባት መቀባት የሚችለው የክህነት ሥልጣን ያለው ብቻ ነው፡፡ /ያዕ.5÷14/ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በገንዘብ አይሸጥምና አጥማቂው ካህን መማለጃ መቀበል አይገባውም፡፡ /ፍ.ነ.ፍ.መ.አን.7/