Thursday, April 3, 2014

ለእኛ ከዚህ በላይ ጠላትነት ከየትም አይመጣም


(አንድ አድርገን መጋቢት 25  2006 ዓ.ም )፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ብራና ዳምጠው፤ ቀለም በጥብጠው፣ ብዕር ቀርጸው በየአብያተ ክርስቲያናቱ የመቃብር ቤቶች ውስጥ በማስተማር ትውልዱ የሀገር መሪ፣ የቤተክርስቲያን አለኝታ፣ የእግዚአብሔር ቅን አገልጋይ እንዲሆን ያበረከቱት አገልግሎት ከዘመን ዘመን እየተሸጋገረ ለትውልድ ሲተላለፍ የኖረና የሚኖር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሀገራችን ሥልጣኔ በር ከፋች ሆና የኖረች ከመሆኗም በላይ ዛሬ ላለው ዘመናዊ ሥልጣኔም መሠረት የጣለች ባለውለታ ናት፡፡ ቀደምት የቤተክርስቲያን አበው ደከመን፣ ሰለቸን ሳይሉ ዐረፍተ ዘመን እስከገታቸው ድረስ ሲያገለግሉ ኖረው ቤተክርስቲያኒቱ አሁን ከምትገኝበት የዕድገት ደረጃ አድርሰዋታል፡፡

በዚህ ዘመንም የሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ሁሉ ይህን ከአበው የተማሩትን ሃይማኖትና ሥርዓት ጠብቀውና አስጠብቀው ለሚመጣው ትውልድ የማቆየት ሓላፊነት ያለባቸው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም ይሔንን አባቶች ወዛቸውን አንጠፍጥፈው፣ ዐይናቸውን አፍዘው፣ ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው በሰማዕትነትና በተጋድሎ ያቆዩትን ሃይማኖት ለማስጠበቅና ለቀጣዩም ትውልድ በተመቻቸ ሁኔታ ለማስተላለፍ በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ ድጋፍና ዕውቅና የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን በውጪ በአጽራረ ቤተክርስቲያንና በአሕዛብ፣ በውስጥ ዓላማውን ባልተረዱ፣ ዓላማውን ተረድተው የኑፋቄ ትምህርታቸውን እንደልብ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ለማስረግ ሌት ተቀን በሚተጉ አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ እየተከሰሰ እየተወቀሰና ያለ ስሙ ስም እየተሰጠው ይገኛል፡፡ማኅበሩ ወጥ የሆነ ተጠያቂነትና ግልጽነት ያለው ማኀበር ነው ፤ ራሱን ደብቆ እና ሰውሮ ሥራውን የሚሰራ መንፈሳዊ ተቋም አይደለም፡፡ በርካታ በሺዎች የሚቆጠር አባላት ያለውና በተቻለው መጠን ቤተ ክርስቲያንን ለመርዳት ፤ የተዘጉትን አብያተ ክርስቲያናት ለማስከፈት ፤ የሰባኪ ወንጌል ችግር ያለባቸውን መምህር በመመደብ ፤ ለገዳማትና የተቸገሩ አብያተ ክርስቲያናት ፕሮጀክት በመቅረጽ ፤ ምዕመኑ በመንፈሳዊ ህይወቱ ጠንካራ እንዲሆን የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ ትምህርት ከማስተማሩም በላይ በርካታ አሁን ዘርዝረን የማንጨርሳቸውን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ በቅዱስ ሲኖዶስ ፍቃድ የተቋቋመ መንፈሳዊ ተቋም ነው፡፡


እስከ አሁን ብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢፈጠሩም ችግሮችን በመነጋገር መፍትሄ በመስጠት በፈተና ጊዜ ጥንካሬውን አሳይቷል፡፡ የውስጥ ችግር በተፈጠረበት ጊዜም መንፈሳዊ ሕይወትና ወንጌሉ እንደሚያዘውም በወንድሞች መካከል የተፈጠረውን ቅራኔ ይቅር በማስባባል ያጠፋው ይቅርታ እንዲል ፤ የተበደለውም ይቅርታውን እንዲቀበል አድርጓል፡፡ በተቋሙ ላይ ፈተናዎች ተቋሙን በሚፈታተን መልኩ ከግለሰቦች ተነስተዋል ፤ ከማኅበሩ በተቃራኒ መንገድ ከቆሙ ሰዎች ተነስቷል ፤ ከቤተክህነቱም ተነስቷል ፤  ከመንግሥትም ተነስቷል ፤ እንደ ባለፈው ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ጭምር ሳይቀር ተነስቷ፡፡ ነገር ግን ፈተና በየጊዜው መፈጠሩ ሊያስገርመን አይገባም፡፡ በዮሐንስ ወንጌል 16፤33 ‹‹በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።›› ተብሎ ተጽፏል ፡፡ ህልምን ፈርቶ ሳይተኛ እንደማይታደር ሁላ ፈተናን ፈርቶ አገልግሎት ማቆምም አይቻልም ፡፡ ቀድም ፈተና ነበር ፤ ዛሬም አለ ፤ ነገም የሕይወት መስዋእትነት የሚጠይቅ ፈተና ሊመጣ ይችላል ፤ ግን ሁሉም እንደ አመጣጡ ያልፋል፡፡

መንግሥት ለምን ማበሩን ጠምዶ ያዘው?
ከ97 ዓ.ም በፊት ነገሮች ሁሉ መልካም ይመስሉ ነበር ፡፡ መንግሥት ሌሎች ሲያደርጉ ተመልክቶ እኔም ለምን ይቅርብኝ ? በማለት ‹ዲሞክራሲያው ምርጫ› አደርጋለሁ ብሎ ተነሳ፡፡ እንደታሰበው ጥሩ የሆነ ሂደት ያለው የፖለቲካ ቅስቀሳ በመላው ሀገሪቱ ተካሄደ ፤ መጨረሻ ግን ሁላችን እንደምናውቀው ውጤቱ መንግሥት እንዳልጠበቀው ስለሆነ የምርጫውን አቅጣጫ የሚያስቀይር ስራ ተሰርቶ ፤ ኮሮጆ ተገልብጦ ፤ ብዙ ሰዎች ሞተው ሁሉም ነገር እንዳልሆነ ሆነ፡፡ ከዚህ በኋላ መንግሥት የሰራው ስራ ቢኖር ለመሸነፌ ምክንያት ምንድነው? ብሎ በመነሳት ከበታችኛው አመራር ጀምሮ እስከ ላይኛው ባለስልጣናት ድረስ ሂስና ግለ ሂስ ፤ ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶችን ማውጣት ማውረድ ተያያዙት ፤ በርካቶች ላይ ግልጽ እርምጃ በመውሰድ ከመስመር አስወጧቸው ፤ በርካታ መንግሥታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለ97 ምርጫ ለኢህአዴግ ውጤት ማጣት የራሳቸውን ሚና መጫወታቸው በስመጨረሻ ደረስንበት አሉ፡፡ ለመያዶች ሕጉ በሀገሪቱ ውስጥ የማያሰራቸው በማድረግ ከጨዋታ ውጪ እንዲሆኑ አደረጓቸው፡፡ በዚህ ማኅበራትን በማክሰም ዘመቻ በርካቶች የተመሰረቱበትን ፍቃድ ከወሰዱበት መንግሥታዊ ተቋም በግልጽ ፍቃዳቸውን መለሱ፡፡ በዚህ ጥናት ወቅት ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› ለመሸነፋችን አንዱ ምክንያት ነው የሚል ኢህአዴግ የውስጥ አቋም ያዘ ፡፡ ይህን የምንለው ሂደቱን ስለምናውቅ ጭምር ነው፡፡ በምን ሚዛን ላይ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን››ን አስቀምጠውት ይህን ሊሉ እንደቻሉ አናውቅም፡፡ በወቅቱ ይህ የፍረጃ ጉዳይ የእነሱም የህልውና እና ስልጣንን ከራስ ጋር የማቆየት ነገር ስለሆነም የፈለጉትን ቢሉ ተሳስታችኋል ማለት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ነበርን፡፡ በጊዜው መፍረስ ያለበት ተቋም ሁሉ እንዲፈርስ ተደርጓል፡፡ ነገር ግን ማኅበረ ቅዱሳን የተቋቋመበት መንገድ ለማፍረስ ቢፈልጉ ቀላል እንደማይሆንላቸው ከማወቃቸው በላይም ሌላ ከድጡ ወደ ማጡ እንደሚከታቸው ፤ ተጨማሪ ጫና እደሚፈጥርባቸው ስለተገነዘቡ በውስጥ እና በውጭ አካሄዱን በሰዎቻቸው አማካኝነት መከታተል ተያያዙት ፡፡  በዚህ መሰረት ማኅበሩ የሚያወጣቸው መጽሔቶች ፤ ጋዜጦች ፤ ሲዲዎች እና የድረ-ገጽ ጽሁፎች ከመንግስት ሰዎች አምልጠው አያውቅም፡፡  ህትመቶቹን ሁላ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ መረጃ ባይኖረንም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላይብረሪ ተጠርዘው በአግባቡ ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ ኢህአዴግ ጽ/ቤት ፤ መንግሥት ተጠሪ ፤ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ያላቸው ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር ሕትመቶቹን አያጧቸውም፡፡  የሚጽፉቸው መንፈሳዊ ጽሁፎች ሁላ የሚታዩበት መነጽር እንደተመልካቹ እና እንደ ወቅታዊ ሁኔታዎች ይለያያሉ ፡፡ ማኅበሩ ራሱን የሚያይበት መስታወት እንዳለ ሁላ መንግሥትም ማኅበሩን የሚመለከትበት የራሱ የሆኑ መስታወት አለው ፤ ከመስታወቱ ውስጥ ያለውን ምስል እንደተመልካቹ ሊቀያየር ይችላል፡፡

ከዓመት በፊት በአቡነ ሳሙኤል የተጻፈው ‹‹እውን የሀይማኖት መቻቻል አለን? ›› የሚል ባሳተሙት መጽሐፍ እውታውን ስላወጡ መንግሥት ፊት ለፊትም ሆነ በቤተክህነቱ በኩል ያሳደረባቸው ተጽህኖ ቀላል የሚባል አልነበረም፡፡ በተጨማሪ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን በጅማ ሲጨፈጨፉ ሁኔታው በሲዲ እንዳይወጣ ክርስትያኑ እንዳያውቀው ፤ ተደባብሶ እንዲያልፍ መንግሥት በሰዎች እና ማኅበሩን በመሰሉ ማኅበራት ላይ ያሳደረውን ተጽህኖ ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡ የእምነቱ ተከታዮች ሆኑ ማኅበራት በወቅቱ ሰው እንግደል አላሉም ፤ ባይሆን የተደረገውን ነገር ለሕዝበ ክርስትያኑ ይወቀው ነው የተባለው ፤ በጊዜው የ6ወር ህጻን የእናቱን ጡት ያልጨረሰ ልጅን ትታ የተሰዋች እናት ነበረች፡፡ ከዓመት በኋላ ልጁን አንድ መነኩሴ ጋር አግኝተነው ታሪኩን ነግረውኝ እጁን ስንጨብጠው ሰውነቱ ውስጥ አጥንት ያለ አይመስልም ነበር፡፡ በወቅቱ የተሰማንንስሜት በቃላት መግለጽ አይቻልም፡፡ የእናት ጡት በአግባቡ ስላላገኝ ፤ እናቱም ስለሞተችበትና ምግብ እንዳስቸገራቸው በጊዜው ካገኝናቸው አባት ማወቅ ችለናል፡፡ በጣም አዘንን ፤ ግን የመፍትሄ ሰው ባለመሆናችን ክፉኛ አዘንን ፡፡ በጊዜው ይህን ችግር ሕዝቡ እንዳያውቀው መንግሥት እንቅፋት ሆኖ ተነሳ ፤ ነገሩ ፖለቲካው ላይ ችግር እንደሚያመጣ ይታወቃል ፤ የሞቱትን መመለስ ባይቻል እንኳን ነገ ይህን መሰል አደጋ እንዳይከሰት ማድረግ በተቻለ ነበር፡፡ መንግሥትም ሀገሪቱ ውስጥ ለሚከናወኑ ነገሮች ትከሻ ለትከሻ እኩል የሚቆም ተቋም ማየት ካለመፈለግ የተነሳ በወቅቱ ይህን በመሰሉ ሁኔታዎች መረጃዎችን ማኅበሩ ሊያወጣ ይችላል በሚል ስጋት በመንግሥት በኩል ፍርሀት ሰፍኖ ነበር …….  

የ97 ምርጫ ላይ ልክ እንደ አንድ ነጥብ የተያዘበት በጊዜው ማኅበሩ 13 ዓመት ሙሉ  ከሰንበት ትምህርት ቤት አንስቶ እስከ ዩኒቨርሲቲዎች ያለው የግንኙነት መረብ እስከ ወረዳ ደረጃ ድረስ ሰፊ ግንኙነት መኖሩ መረጃዎችንም በቀላሉ ይወርዳሉ ብለው በማሰባቸው በተለየ አይን እንዲታይ አድርጎታል፡፡ መንግስት በ14 ዓመት ውስጥ በሀገሪቱ ላይ ሊሰራ ያልቻለውን ስራ ማኅበሩ በጥቂት ጊዜያት መስራት ችሎ መታየቱ በኢሕአዴግ  በጥሩ አይን እንዲታይ አላደረገውም፡፡ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› የዘረጋውን ኔትወርክ ለአላማቸው ማስፈጸሚያ ተጠቅመውበታል የሚል አቋም በወቅቱ ይዟል፡፡ ይህ ግን የፖለቲከኞቹ  የተሳሳተ ግምት እንጂ እውነታው የኢህአዴግ አቅም ማነስና ሕዝብን ያለማድመጥ መሰረታዊ ችግር ነበር ፡፡ በወቅቱ አንድ ሰው የኢሕአዴግ አባል የሚሆነው አንድም ልኑርት በሚል ዘዬ ፤ በሌላም በኩል በአቋጭ ወደ ስልጣን በመጠጋት የመበልጸጊያ መንገድ አድርጎት እንጂ ርዕዮተ ዓለሙ ገብቷቸው የፓርቲውን ግብ  ለማስፈጸም አልነበረም ፤ ኢህአዴግ በጊዜው በየመድረኩ ያጨበጨበ ሁላ ደጋፊ መስሎት ነበር፡፡

ምርጫው አልፎ ነገሮች ወደ መስመራቸው ከተመለሱ ከዓመታት በኋላ የመንግስት ባለስልጣን አቶ አቦይ ስብሀት በማን አለብኝነት በነጋድረስ ጋዜጣ እና በተለያዩ መጽሄቶች ላይ ‹‹የኦርቶዶክስ ጳጳሳቱ አይረቡም ›› ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክህበት እዳ ነው›› በማለት ቀድሞ የቋጠሯትን ቂም ግልጽ አድርገው በሚዲያ ተናግረዋል፡፡ በመሰረቱ ስብሀት ነጋ ማለት የወረደ ብቻ ሳይሆን የዘቀጠ አመለካከት ያላቸው ሰው መሆናቸውን በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይመሰክራሉ ፡፡ እንደ እኛ እምነት ይህ ከመሬት የተነሳና መሰረት የሌለው ቂም አይደለም፡፡ሰውየው ጤነኛ ናቸው ብሎ መናገር ይከብዳል፡፡ በማኅበረሰቡ ዘንድ ተሰሚነት ያለው ሰው ፤ ስብእናው ኢትዮጵያዊ ኢትዮያዊ የሚሸት ፤ አንቱታን የተላበሰ ሰው ቢሆን ኖሮ በወቅቱ በእሳቸው ንግግር እና ስድቦች በርካቶች በተሰናከሉ ነበር፡፡ ግን አይደለም ፡፡ ይችን ክፍተት በመጠቀም ተሀድሶያውያኑ የአቦይ ስብሀትን ቃል ለመጽሀፍ አርዕስት አድርገው የዲ/ን ዳንኤል ክብረትን 20 ገጽ ማኅበሩ ላይ የጻፈውን ወቀሳ አንድ ላይ በማድረግ መጽሐፍ መጻፋቸውን እናስታውሳለን ፡፡ የመጽሐፉ ስም ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክህነት እዳ›› የሚል ነበር ፤ ጠላትም አንዳንዴ ጥሩነቱ  ምን ያህል እንደተኛን ከማመላከቱም በላይ ከተኛንበት እድንነቃ በር ይከፍትልናል፡፡ ምን ያህል መሥራት እንዳለብንም ትምህርት ይሰጠናል፡፡

በሕግ አግባብ ካየነው አቦይ ስብሀትም ሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለ አግባብ አይደለም አንድን  ማኅበር ያለመረጃ ይቅርና ግለሰብን የመናገር መብት የላቸውም (ይህ በእኛ ሀገር ደረጃ አይደለም) ፡፡ ነገር ግን ሙልጭ አድርገው  ማኅበሩ የማይገባውን ስም በመስጠት ሲናገሩ ማንም እረፉ ያላቸው ሰው አልነበረም ፡፡ አሁንም ይሁን በወቅቱ እኛም የመንግሥት ባለስልጣን ይቅርና የቀበሌ ተራ ሹም ለመቃወም የሚበቃ ወኔ የለንም፡፡ ይባስ ተብሎ ሰው ዘንድ እንዲደርስ ምዕመኑ ለማኅበሩ መልካም አመለካከቱ እንዲቀየር ሥራ በመስራት ሰው አንቅሮ እንዲተፋው ያልተሳካ ሥራ አከናውነዋል ፤ ግን አልተሳካላቸውም ፡፡

እኛ የማናውቃቸው በጣም ብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ መናፍቃን ቤተ ክርስትያኒቱን ለማፍረስ ከሚገነቧት ጋር አብረው ቆመዋል ፡፡እኛ ስለምናውቃቸው ሰዎች ብቻ እንከራከራለን እኛ የማናውቃቸውን እርሱ አንድ አምላክ ስለ ‹‹አንዲት እምነታችን›› እና ስለ ‹‹አንዲት ቤተክርስትያን›› ብሎ ክፉ ስራቸውን ይያዝልን ፡፡ በርካቶች ከውስጥም ይሁን ከውጭ  ለምን ‹‹ማኀበረ ቅዱሳን›› ላይ ብቻ እጃቸውን ይጠቁማሉ ? ሌሎች ማኅበሮች በቤተ ክርስቲያኒቱ ጥላ ስር የሉምን? ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ከተበተነ ሌላው ገለባ ነው›› በማለት የሚሰሩ ይመስለናል፡፡

አዲሱ ክስ ‹‹አንድ ሀይማኖት አንዲት ሀገር››           
እኛ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች   ‹‹አንድ ሀይማኖት አንዲት ሀገር ብለን እናውቃለን?›› አይመስለንም፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ‹‹ይህችን ሀገር ክርስቲያን ብቻ ይኑርባት›› ብላ አላስተማረችንም፡፡ እንዲህ ቢሆንማ መጀመሪያም ከአረብ ሀገር የመጡትን የመጀመሪያዎቹን የእስልምና እምነት ተከታይ ስደተኞች አባቶቻችን ባልተቀበሏቸው በጦርም ወደመጡበት በገፏቸው ነበር፡፡ ይህ ግን አልሆነም ፤ አባቶቻችን ለእኛ ያስተማሩን ከሁሉ ጋር በሰላም እንድንኖር ብቻ ነው፡፡  ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፤5 ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት›› ነው የሚለው የወንጌሉን ቃል  የጥምቀት ወጣቶችም ይህን ነው የለበሱት፡፡ ኢህአዴግና ኢህአዴጋውያን ከ134 በላይ በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉትን ማተሚያ ቤቶች ከመቆጣጠር ይልቅ ይህን የሰራው በመስራትም ላይ የሚገኝው ይህ ማኅበር ነው ብለው ነው የተነሱበት፡፡ ሕገ መንግስቱን ተጋፋ የሚለው ‹‹አንዲት እምነት›› የሚለው ነገር ነው፡፡ ‹‹እንዴት ከ80 በላይ ብሔር ያለባት ኢትዮጵያ እና በርካታ የእምነት ተቋማት ያላት ሀገር ላይ የኦርቶዶክስ  እምነት ተከታዮች ይህን ነገር ያራምዳሉ?›› የሚል ሀሳብ ነው ያለው፡፡ መንግሥት ስለ ብሔር ብሄረሰብ ነጻነት እንደቆመ ሀገሪቱም ሁሉም እንደሆነች ባገኝው አጋጣሚ ሁላ እየደሰኮረ ይገኛል፡፡  ሕገ-መንግሥቱ መግቢያ ላይ ‹‹ የግለሰብና የብሔር ብሔረሰብ መሰረታዊ መብቶች መከበራቸው ፤  ኃይማኖቶች ካለ አንዳች ልዩነት እንዲያራመዱ የማድረግ አስፈላጊነት ጽኑ እምነታችን ነው…›› በማለትም ይዘረዝራል:: ነገር ግን መንግሥት እንደ መንግሥት ሕገ-መንግስቱን ብቻ ማክበርና ማስከበር ሲገባው ባልሆነበት ቦታ እየገባ ለሰላም እጦት ዋና ተዋናይ ሆኖ ይገኛል፡፡ 

ይህን የቲሸርት ጽሁፍ ኢህአዴግ በማኅበሩ ጓዳ የሚሰራው መስሎ ነው የሚታየው፡፡ የዚህ ሀረግ አላማ አንዲት እምነት ስለ አንድ ጌታ እና ስለ አንዲት ጥምቀት  መናገር ነው ፡፡ ድንገት ይህ የእምነት አቋማችን ይሆናል ሌሎችን ብስጭት ውስጥ ከቷቸው ሌላ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የሚያደርጓቸው፡፡ እና እኛ ምን እናድርግ? ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለን የወንጌሉን ቃል አንቀይር?  የአምላክን ቃል አናጥፍ ፡፡

‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤›› የሚለውን የወንጌል ቃል ህገ መንግሥቱን ስለሚጋፋ ብቻ እናንተን ደስ እንዲላችሁ መቀየር አይቻልም፡፡ የጌታ ቃል የሚታጠፍ አይደለም ፡፡ ይህን ነገር ሲያስረግጥልን ‹‹ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።›› የማርቆስ ወንጌል 13፤31 ታዲያ እኛን ምን እናድርግ ? ስለዚህ የምናብንበት መጽሐፍ ሰማይና ምድር እንደሚያልፉ ቃ ግን እንደማያልፍ እየተናገረ ሳለ እኛ ማን ሆነን ነው ይህ አመለካከት ኢህአዴግን ደስ አላሰኝውም እና ብለን መቀየር የምንችለው? በመጽሀፍ ቅዱስ አትመኑ ማለት አንድ ነገር ነው ፡፡ በተጨማሪ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ‹‹ይህን ነገር የሚያራምዱ ወጣቶች ህገ መንግሥቱ ያልገባቸው በትምህርት የሚመለሱ ናቸው›› ብለዋል፡፡ ወጣቶቹ ህገ-መንግሥቱ ባይገባቸው ወንጌል ግን ገብቷቸው ታቦታቱን ለማጀብ በረከትም ለማግኝት ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤›› የሚል ቲሸርት ለብሰው ሊታዩ ችለዋል ፡፡ እኛ ጌታ ያልነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ አንዲት እምነት ያልናት ‹‹ኦርቶዶክስ ተዋህዶ››ን ፤ አንዲት ጥምቀት ያልናት ደግሞ ‹‹እኛም እናንተም በ40 በ80 የተጠመቅን ፤ የስላሴ ልጅነትን ያገኝንባት ጥምቀት›› ብለን እናምናለን ፡፡

ለእኛ ከዚህ በላይ ጠላትነት የለም
ቤተ ክርሰቲያኒቱ በዘመናት በርካታ ጠላቶች ተነስተውባታል ፤ ነገር ግን መሰረቷ የማይናወፅ በመሆኗ ጠላቶቿ እንደ አይን ጥቅሻ ሲያልፉ ቤተ ክርስያኒቱ ግን የማይታለፉ የሚመስሉትን ዘመናት ተሻግራ አሁን እኛ ዘመን ላይ ደርሳለች ፡፡ አሁንም ቢሆን ከፈተና ያልተላቀቀችው ቤተ ክርስቲያን በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ጠላቶቿ የሚተኙላት ሆነው አልተገኙም፡፡ በአሁኑ ሰዓት የሚሰማው ነገር እውን የሚሆን ከሆነ ለእኛ ከዚህ በላይ ጠላትነት አይኖርም ፤ በሰላማዊ ሁኔታ እምነታችንን እንዳናካሄድ ከተደረገ ፤ ለመጥፋት የተዘጋጁትን በእምነት የሚመስሉንን ወገኖቻችንን እንዳናበረታ ከተደረግን ፤ ቤተ ክርስቲያን ተተኪ እንዳይኖራት ምንጩን የማድረቅ ሥራ ከተሰራ ፤ ዓይናማዎች ብጹአን አባቶች የሚፈልቁበት የአድባራትና ገዳማት የአብነት ተማሪ ቤቶች በአግባቡ እንዳይረዱና አደራቸውን የሚቀበሉበት ትከሻ እንዳይኖራቸው ከተደረገ ፤ የቤተክርስቲያኒቱን ቀዳዳ ለመሙላት እና ምዕመኑ በሃይማኖቱ በመኖር ለራሱ ፤ ለቤተሰቡ ፤ ለእምነቱ እና ለሃገሩ ጥሩ ዜጋ እንዲሆን የሚያስችለው በር የመዝጋት ሥራ ከተሰራ  ለእኛ ከዚህ በላይ የሚሆን ጠላትነት የለም፡፡  

የቤተ ክርስቲያን የድሮ  ጠላቶቿ ባሕር ተሻግረው ፤ መሳሪያ ይዘው ፤ ጦር አስከትለው ነበር የሚመጡት፡፡ እነዚህ ጠላቶች ቤተክርስያኒቱን ወደ አመድ ለመቀየር ፤ ሕዝቡን እምነቱን ለማስለወጥ ፤ በገንዘብ የማይተኩትን ወርቃማዎቹን ድርሳናትና ገድላት በመመዝበር ከውስጣቸው የሚገኙትን እውቀቶች ለራሳቸው ለማድረግ ፤ የማኅረሰቡን ቋንቋ ፤ ባህል ፤ እምነትና ትውፊት በመናድ የራሳቸውን ለመጫን ብለው ባሕር አቋርጠው እንደሚመጡ እናውቃለን፡፡ የአሁኖቹ ግን እንደ ቀድሞዎቹ ባሕር ተሻግረው የሚመጡ አይደሉም ፤ እነዚህኞቹ ፍቅረ ነዋይ ያሳበዳቸው ፤ ደመወዛቸው አልበቃ ያላቸው እና እጅግ ብዙ በመመኝት ፓትርያርኩን እንደ ትኋን በመክበብ በተዘዋዋሪ ቤተክርስያኒቱን የተጣበቁ እና ስልጣን ካሳወራቸው ከእግዚአብሐየር በላይ ከሚያከብሯቸው እና ከሚፈሯቸው ምድራዊ ባለስልጣናት ጋር በመሆን የቀድዎቹን ጠላቶች አይነት ሥራ ለመስራት የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ለእኛ ጠላት ከውጭም መጣ ከውስጥ ጠላት ሁሌም ጠላት ነው፡፡  አሁንም ቢሆን እነዚህ ሁለቱ የጥፋት ነጋሪት ጎሳሚዎች ያሰቡት ነገር ብቻ ለእኛ ጠላትነት ነው ፡፡ለእኛ ከዚህም የበለጠ ጠላትነት ከየትም አይመጣም

ሥርዐቱ አሁን የያዘው መንገድ  እንደማያዋጣው እና ያለምንም ጥርጥር የተቃውሞውን ጎራ እንደሚያጠነክረው ሊያስበት ይገባል፡፡ አገሪቱን በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ የአውራ ፓርቲ ሥርዐት  ወደፊት እመራለው ለሚለው ገዥው ፓርቲ ግብዓተ መሬት አፋጣኝ ምክንያት ሊኾን እንደሚችል ሊገነዘቡ ይባል፡፡ ይህ አካሄድ የማኅሩን መጨረሻ ለማየት በመጓጓት የራስን የመጨረሻ መጀመሪያ መንገድ መጀመር ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህም ባሻገር ማኅበሩ ትውልዱ ሃይማኖቱን ተረድቶ ፤ ቤተክርስቲያኑን አውቆ ፤ ማንነቱን እንዲገነዘብና  በመልካም ሥነ ምግባር ያነጸው ብቁ ዜጋ ሥርዐቱን ከአገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ደምሮ ማየቱ አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህ መንግሥት መካሪ እንደሌለው የእብድ ሥራ ከመሥራቱ በፊት ነገሮችን ማጤን  ይበጀዋል ብለን እናምናለን ፤ ለእኛም ከዚህ በላይ ጠላትነት ከየትመ አይመጣም፡፡

ቸር ሰንብቱ
ይህ ጽሁፍ የግሌ ኣስተያዬት ነዉ

16 comments:

  1. እኔ እምለው ''አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት'' የሚለው ተርጉም በየትኛው ትርጉም ነው አንድ ሃይምኖት አንድ ሃገር ከሚለው ጋር ያመሳሰላችሁት ??

    ReplyDelete
  2. ለእኛም ከዚህ በላይ ጠላትነት ከየትመ አይመጣም፡፡

    ReplyDelete
  3. ሥርዐቱ አሁን የያዘው መንገድ እንደማያዋጣው እና ያለምንም ጥርጥር የተቃውሞውን ጎራ እንደሚያጠነክረው ሊያስበት ይገባል፡፡ አገሪቱን በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ የአውራ ፓርቲ ሥርዐት ወደፊት እመራለው ለሚለው ገዥው ፓርቲ ግብዓተ መሬት አፋጣኝ ምክንያት ሊኾን እንደሚችል ሊገነዘቡ ይባል፡፡ ይህ አካሄድ የማኅሩን መጨረሻ ለማየት በመጓጓት የራስን የመጨረሻ መጀመሪያ መንገድ መጀመር ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህም ባሻገር ማኅበሩ ትውልዱ ሃይማኖቱን ተረድቶ ፤ ቤተክርስቲያኑን አውቆ ፤ ማንነቱን እንዲገነዘብና በመልካም ሥነ ምግባር ያነጸው ብቁ ዜጋ ሥርዐቱን ከአገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ደምሮ ማየቱ አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህ መንግሥት መካሪ እንደሌለው የእብድ ሥራ ከመሥራቱ በፊት ነገሮችን ማጤን ይበጀዋል ብለን እናምናለን ፤ ለእኛም ከዚህ በላይ ጠላትነት ከየትመ አይመጣም፡፡

    ReplyDelete
  4. ዝም ሲሉት የተፈራ ይመስለዋል-ነዉ ነገሩ፤-ማ/ቅዱሳን ተከሰሰ ማለት ቢተ-ክርስቲያን ተከሰሰች ማለት ነዉ ፤ቢተ-ክርስቲያን ተከሰሰች ማለትደግሞ መስራቹ ጊ/መ/ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም በ21ኛዉ መ/ክ/ዘመን ተከሰሰ ማለት ነዉና፡እባካችሁን አእምሮ ካላችሁ እጃችሁን ከማ/ቅ ላይ አንሱ፤ እምቢ የምትሉ ከሆነ ፀባችሁ ከእግዚአብሂር ገር ስለሆነ አወዳደቃችሁ የከፋ ይሆናል!!!

    ReplyDelete
  5. Bless u more u r on ur side.

    ReplyDelete
  6. መንግሥት መካሪ እንደሌለው የእብድ ሥራ ከመሥራቱ በፊት ነገሮችን ማጤን ይበጀዋል!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  7. laba ciserke ayetalame cikafele new yemitalawe laboch tawekebach tenekabach beterach alekesu enanete betekerestianen atewekelume laboch

    ReplyDelete
  8. bmelaw alem yeminoru krstianoch tekawmo self mewtat yinoribnal tetenkek lemalet yahl. we have to do this faster

    ReplyDelete
  9. ማህበረ ቅዱሳን ሁልግዜ በፈተና ዉስጥ ያለ ማህበር ነዉ። ጽሁፍህ እውነትነት ቢሆረዉም በርካታ የማህበሩ ያልሆነ የግል ኣስተያዬት ኣካተህበታልና፥ ይህ ጽሁፍ የግሌ ኣስተያዬት ነዉ የሚል ማስታወሻ ብታክልበት ጥሩ ነዉ። ኣለበለዚያ ለማህበሩ ኣመራሮች ተጨማሪ ፈተና ነዉ የምት ሆነው፥ ምክንያቱም የማህበሩ ኣቁም ተደርጎ ስለሚወሰድባቸዉ። የሁሉም ሰዉ የግል ኣስተያዬት በዚህ መልክ ከተተረጎመ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ኣስበዉ...

    ReplyDelete
  10. ማኀበረ ቅዱሳን የያዘውን አቋም ለማደናቀፍ የሚሞክር ሁሉ ያውም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አባቶች ስም
    የሚደረግ ሙከራ የቤተክርስቲያንዋን መጠናከር የማይፈልጉ ድብቅ አጀንዳ ያላቸው ስለሚሆኑ እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሃይማኖት ምዕመናን ሁሉ አንድነት ሆነን ልንታገላቸው ይገባል።
    ማሕበረ ቅዱሳኖች ባቋማችሁ ጠንክሩ፤ መስዋት በመሆን የሐዋርያቶች ምሳሌ ሆናችሁ ሌላዉን አስተምሩ።
    እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እናንተን የመሰለ ልጆች አያሳጣት።
    አግዚአብሔር ይርዳችሁ።

    ReplyDelete
  11. ማ/ቅ ቤተ ክርስቲያን ለወያኔ አሳልፋችሁ ስትሰጡ ኑራችሁ አሁንም በውጭ ሀገር በነጻነት የሚኖረውን ምእምናን እያሰቃያችሁ ፡እና ከወያኔ ጎን ሁናችሁ ቤ/ክ ለማፍረስ ስትተባበሩ ቆይታችሁ አሁን ምን አጣላችሁ ቤ/ክ የ ማ/ቅ ወይም የወያኔ አይደለችም ።የክርስቶስ ናት።ማንም አያጠፋት በደሙ ለዘላለም አጽንቷታል።


    ReplyDelete
  12. I believe beside making the youth in higher education loyal and active participant in EOTC, MK has also contributed hard working and corruption proof young professionals. But also there are few who have left their association and became politicians and journalist and bloggers of Dejeselam, Hara and Andadirgen. These self-proclaimed supporter are posting of actual or so called sin of individuals which is unchristian and post what th press press is writing about EOTC and MK in their website. It shall be noted press like Fact are not neutral, they are exaggerating errors that are committed intentionally or being partisan ( ant-orthodox elements)! Hence, they can write article to rally the youth to the opposition! As you are self-proclaimed supporters of the association, the Government will definitely no have good view of the Association. Hence, these website will have the major share for creating inflamed situation. the motive behind them might be confusing earthly and spiritual world or promoting individual political opinion or unethical and sentimental character of individuals.

    The solution is thus to pray to God sothat He can resolve the situation and also pray for those who don not know what they are doing, make peace with those who have antagonistic views with association and the association shall officially excommunicate these websites and announce to its members.

    Christians can continue to serve GOD only by respecting the teaching of our Lord!


    ReplyDelete
    Replies
    1. ከዚህም ባሻገር ማኅበሩ ትውልዱ ሃይማኖቱን ተረድቶ ፤ ቤተክርስቲያኑን አውቆ ፤ ማንነቱን እንዲገነዘብና በመልካም ሥነ ምግባር ያነጸው ብቁ ዜጋ ሥርዐቱን ከአገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ደምሮ ማየቱ አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህ መንግሥት መካሪ እንደሌለው የእብድ ሥራ ከመሥራቱ በፊት ነገሮችን ማጤን ይበጀዋል ብለን እናምናለን ፤ ለእኛም

      Delete
    2. ከዚህም ባሻገር ማኅበሩ ትውልዱ ሃይማኖቱን ተረድቶ ፤ ቤተክርስቲያኑን አውቆ ፤ ማንነቱን እንዲገነዘብና በመልካም ሥነ ምግባር ያነጸው ብቁ ዜጋ ሥርዐቱን ከአገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ደምሮ ማየቱ አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህ መንግሥት መካሪ እንደሌለው የእብድ ሥራ ከመሥራቱ በፊት ነገሮችን ማጤን ይበጀዋል ብለን እናምናለን ፤ ለእኛም

      Delete
  13. ከዚህም ባሻገር ማኅበሩ ትውልዱ ሃይማኖቱን ተረድቶ ፤ ቤተክርስቲያኑን አውቆ ፤ ማንነቱን እንዲገነዘብና በመልካም ሥነ ምግባር ያነጸው ብቁ ዜጋ ሥርዐቱን ከአገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ደምሮ ማየቱ አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህ መንግሥት መካሪ እንደሌለው የእብድ ሥራ ከመሥራቱ በፊት ነገሮችን ማጤን ይበጀዋል ብለን እናምናለን ፤ ለእኛም

    ReplyDelete