Wednesday, April 9, 2014

ገብረ ጉንዳኖችና የአይጥ መንጋዎች



(አንድ አድርገን ሚያዚያ 1 2006 ዓ.ም)፡- በዓለማየሁ ገላጋይ “ለውድቀት እንደግስ?” የሚለው ጽሑፉ ላይ መንግሥት በየጊዜው በሰበብ አስባቡ ለሚያከናውናቸው ሥርዓትን ያልተከተሉ ነገሮችን በመተቸት በስተመጨረሻ ይኽችን ሀረግ አስቀምጧል ‹‹ ትላልቅ ጉንዳኖች ፤ የአይጥ መንጋዎች ብዙ እህል ፈጁ …. ከዚህ ሁሉ መቅሰፍት የባሰው ግን መጥፎ መንግሥትና አስተዳደር ነው፡፡ መጥፎ መንግሥት ሕዝቡ ከተፈጥሮ  ፤ ከተመክሮ ያገኝውን ንብረቱንና ማንነቱን ከመቀጽበት ያወድምበታል፡፡›› (Travel to discover the source of Nile).



ለዘመናት የገነባነውን ማንነት ፤ የተላበስነውን ስብዕና ፤ ያቆየነውን ግብረ ገብነት ፤ ያቆዩልንን ሀገር የኖርንበትን ሃይማኖት ፤ የተረከብነውን ትውፊት እና በአል ከዘመኑ ጉንዳኖችና የአይጥ መንጋዎች መጠበቅ የሁላችንም ግዴታ መሆን መቻል አለበት፡፡ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ አልፋ አሁን ለእኔ እና ለእናተ ቋንቋ ፤ ዜማ ፤ ሥርዓት ፤ ትውፊትና እምነትን አስተላልፋልናለች ፡፡ እኛም ይህን የተረከብነውን ላለማስተላለፍ እንቅፋት የሚሆኑብንን ከበላያችን ያሉ ገብረ ጉንዳኖችና በውስጣችን ያሉ የአይጥ መንጋዎችን ሳንፈራ ለልጆቻችን ማውረስ ሃይማኖታዊ እና ሀገራዊ ግዴታ አለብን፡፡ ትላንት ቤተ ክርስቲያን ህልውናዋን በሚያናጋ መልኩ በብርቱ ፈተና አልፋለች፡፡ ዛሬም እንደ ቀድሞ ያህል ባይሆን እንኳን የዛሬ ከርሳቸው እንጂ የነገ ክስረታቸው ባልታያቸው ዙሪያዋን በከበቧት የአይጥ መንጋዎች ፤ በጎውን በማይመኙላት ገብረ ጉንዳኖች ዘንድም እየተፈተነች ትገኛለች፡፡ ነገም ይባስ ወይም ይቅለል አሁን ላይ በማናውቀው ፈተና ውስጥ ቤተክርስቲያኒቱ ታልፋለች፡፡ ታዲያ በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ከአንድ ኦርቶዶክሳዊ አማኝ የሚጠበቀው የራሱን ክርስቲያናዊ ሃላፊነት መወጣት ብቻ ነው፡፡ የዛኔ ፈተናውን ማስቀረት ባንችል እንኳን ፈተናውን የምንቋቋምበትን ትከሻ እንገነባለን፡፡ ገብረ ጉንዳኖቹም ሆኑ የአይጥ መንጋዎቹ ዛሬ ላይ መቅበር በሚፈልጓት ቤተክርስቲያን ነገ መቀበራቸው አይቀርምና…..

2 comments:

  1. እናንተስ የሰዎችን ምልካም ስም ስታጠፉ፣ ሕልውናቸውን ስትፈታተኑ፣ ክብራውን ስታጎድፉ የምን መንጋ ናችሁ፣ የእናንተ መንደር ተወላጅ ስላልሆነ/ች፣ የእናንተ የሙስና ሥራ ተባባሪና አዳማቂ ስላልሆነ/ች፣ አይዟችሁ የሁሉም ፈራጅ አለ እውነቱ ነፃ ያወጣችኋል፡፡

    ReplyDelete
  2. M.k zendro mechem geta jrafun sianesa temesgen new

    ReplyDelete