- ጠቅላይ ቤተክህነቱ 2005ዓ.ም በሀገር ውስጥ ብቻ የሚተዳደሩ 50 የሀገረ ስብከቶች ጠቅላላ ገቢ ወደ አንድ ቢሊየን ብር ያገኝ ሲሆን የዚህን ገቢ 1 %(አንድ በመቶ) አስር ሚሊየን ብር በዓመት ለአብነት መምህራት ደመወዝ አይከፍልም፡፡
- በተለያዩ አህጉረ ስብከቶች የአንድ አብነት መምህር የወር ደመወዝ ትክል ከ400 ብር አይበልጥም፡፡

ቤተክህነቱ ዘወትር የበጎ ነገር ተቃራኒ ሆኖ እስከመቼ እንደሚዘልቅ አይታወቅም ፡፡ አንዳንዴ ቤተክህነቱ የማን ነው ?
የማንን ፖሊስ እና ስትራቴጂ ነው ለማስፈጸም የተቀመጠው ? እስከ መቼ ነው በጥቂት ሰዎች አማካኝነት የበጎ ነገር እንቅፋት የሚሆነው?
የሚሉ ሰዎችም አልታጡም ፡፡ ቤተክህነቱ ሥራውን በአግባቡ ቢያውቅ ኖሮ የሱን ሥራ የሚሰሩለትን ሸክሙን ከሚያቀሉለትን
ግለሰቦችም ሆነ ማኅበራት ጋር አብሮ መትጋት ሲገባው በተቃራኒ ጎራ መቆሙ እጅጉን ያሳዝናል፡፡ በዓመት አንድ ቢሊየን የሚጠጋ ብር
ከሀገር ውስጥ ከሚገኙ አህጉረ ስብከቶች ብቻ እየሰበሰበ ለአብነት መምህራት ደመወዝ በአግባቡ የማይከፍል ተቋም በተንኮል መንገድ
ይህን የመሰለ ትልቅ ጉባኤ ሲያደናቅፍ መመልከት አይደለም ለውስጥ ለውጭ ተመልካች ሳይገርም አይቀርም፡፡ ጫናው ከላይ ከሆነም በግልጽ
ማሳወቅ መልካም ነበር ነገር ግን እንዲህ ሲሆን አልተመለከትንም ፤ ዘወትር ውሃ የማያሳ ምክንያት እያቀረቡ ጉባኤያትን መበጥበጥ
ምን ይባላል? እንዴት ቀድሞ መፍቀድም ሆነ አለፍቀድ በእጃቸው ላይ ሳለ ቀኑ ሲደርስ የደብዳቤ መአት በሰዓታት ልዩነት ማዝነብ ምን
ይባላል? እኛስ የቤተክህነቱ በሽታ ሊገባን አልቻለም ፡፡
ከዚህ በፊት ብዙ ዝግጅት ተደርጎበት ፤ ከ5ሺ በላይ ምዕመናን ተመዝግበው ፤ ከመቶ በላይ የህዝብ ማመላለሻ መኪኖች ኪራይ
ተይዞ ፤ ለምዕመኑ የሚሆን በርካታ መሟላት ያለባቸው ነገሮች በበርካታ ሺህ ብሮች ተሟልተው ካበቁ በኋላ ጉዞ ሁለት ቀን ሲቀረው
ጉዞ መከልከሉን የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ ይህን ያህል የህዝብ ገንዘብ ፤ የሰው ጉልበትና እውቀት ከባከነ በኋላ ጉባኤው አንድ
ወይም ሁለት ቀን ሲቀረው መከልከል ምን የሚሉት የክፋት መንገድ ነው ? አባቶች በርካታ ተማሪዎቻቸውን ትተው ከዋልድባ ገዳም ድረስ
እንዲመጡ ተደርገው ይህን አይነት የጉባኤ ክልከላ ከማይጠብቁት የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አካል ሲሰሙ ምን ይሰማቸው ይሆን ? በቤተክህነቱ ውስጥ ለመልካም ነገር እንቅፋት የሆኑ ሰዎችስ ይህ አካሄዳቸው የት ያደርሳቸው ይሆን
? ‹‹የማያድግ ልጅ እናቱ ጀርባ ላይ ሆኖ…›› ማለት ይህን ቤተ ክህነት ነው ፡፡
በዚህ ጉባኤ መደናቀፍ ምክንያት የክፋት ገበዞች ማኅበረ ቅዱሳንን ? የአብነት መምህናንን ወይስ ቤተ ክርስቲያንን ጎዱ
?
Erkuset betekedesew sifra yihonal
ReplyDeletebetam yaszinal betechrstyanachin wedet eyehedech endehone ligeban alchalem????????
ReplyDelete