Monday, February 24, 2014

ወላይታ ሶዶና አቶ በጋሻው ደሳለኝ


(አንድ አድርገን የካቲት 18 2006 ዓ.ም)፡- በወላይታ ሶዶ  ኦቶና ደ/ጽ/ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከጥር 23-25 በተካሄደዉ ጉባኤ ላይ አቶ በጋሻዉ ደሳለኝ የተናገራቸው ነገሮች ብዙዎችን ያስገረመ ከመሆኑ በላይም አሁንም በሌላ የምንፍቅና ክንፍና በልዩ አስተምህሮ መመለሱን ማመስከር ችሏል፡፡ ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ከስርዓተ ቤተክርስቲያን የወጣ በዜማ የታጀበና የረዘመ ‹‹አሜን›› አባባልም ለምዕመኑ አለማምደውት ታይቷል  ፤ ሊቃውንቱ ሲሰብኩ ሰው  ወደ ውስጡ እንዲመለከትና በጥሞና እና በአስተውሎ የእግዚአብሔር ቃል እንዲያደምጥ ሲያደርጉ ነበር እኛ የምናውቀው ፤ አሁን አሁን በአስር ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ከ20 ጊዜ በላይ ‹‹አሜን›› የሚያስብለውን ሆነ ‹‹አሜን›› በማያስብለው ምዕመኑን ጮኻሂ  የማድረግ አዝማሚያ እየታየ ነው ፤  ያ መናፍቃን ቤት የሚገኝው ጩኽት እኛ ቤትም ለመግባት ደጃፍ ላይ እያኮበኮበ ይገኛል፡፡ ለዚህ እማኝ ይሆን ዘንድ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን በቦታው ላይ የተከናወነውን ነገር ይመልከቱ፡፡Click here

አቶ በጋሻው ደሳለኝ በድምጽ ከተቀዳ እማኝ ማስረጃ ላይ በሶስቱ ቀናት ጉባኤ የሚቀጥሉትን መልዕክቶች አስተላልፏል (ወደፊት እንደ አስፈላጊነቱ የድምጽ ቅጅው ፖስት እናደርጋለን)፡፡ አሁንም ቢሆን የድፍረት ቃላቶች የእግዚአብሔር ስም በሚጠራበት ቦታ ላይ ላለመስማት አውደ ምህረት ፈቃጆች ለማን እንደምትፈቅዱ አስተውሉ፡፡


23/05/06 
.

  • ‹‹ቄስ መነኩሴ አትፈልጉ እራሳችሁ ፀልዩ፡፡››
  • ‹‹እኛ ፀልየን ሁለት ህፃናት HIV/AIDS ነፃ ሆኑ፡፡››  
  •  ‹‹ያለ ክርስቶስ ስም ፀሎት አያርግም፡፡››  
  •  ‹‹ክርስቶስ ብቻ ሙሉ ስም ነው፡፡››  
  •  ‹‹ክርስቶስን ብዙ መውደድ ነው እንጅ ብዙ መስገድ አያድንም፡፡››

24/05/06 .
  • በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ይሁዳ ብር ሲያዩ የሚጎመጁ አገልጋዮች አሉ፡፡
  • ‹‹አገልግዬ ወጣቶችን ከብዙ ነገር አስመልጫቸዋለሁ፡፡››
  • ‹‹ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ ነው ለሌላ ለማንም አትስጡ፡፡››
  • ‹‹በነፃነት ለማምለክ መውጣት በክርስቶስ ስም ነው፡፡››
  • ‹‹በትናንትናው የስብከት አገልግሎታችን አንዲት በሽፍቶች ተደብድባ ዓይኗ ጠፍቶ የነበረ እህታችንእኔ እያሰብኩዋት ስለነበር ጉባኤውም እያሰባት ስለነበር ጉባኤው ሲያልቅ ዓይኗ በራ፡፡››
25/05/06 .
  • ‹‹በመዳን ህይወት ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው ኢየሱስ ነው፡፡››
  • ‹‹የመጣችሁ እንግዶች ካላችሁ እኛ የምንሰብከው ኢየሱስ እንደሆነ እወቁ፡፡››




ከእንደዚህ አይነት ስብከት በኋላ ጉዞ ወደ …………………….

19 comments:

  1. በቃ ይሄ ሰውዬ ለየለት ማለት ነው አይይይይ በቃኮ በቁሙ ሞተኮ ሊያውም እኮ ነፍስ ይማር የማይባልበት

    ReplyDelete
  2. what is going on inside a Church and no one stop him if his is talking like these evil words; please no leader for church??? I guess we should have pray hardly before this guy kill everybody .Him and his follower have a long term plane so that please, please, please inform for others Orthodox family's to aware about him what he has been doing.

    ReplyDelete
    Replies
    1. I hope all those words which are said by him are not evil at all. They may be evil if we think that all our practices are right. But our brother is saying that Orthodox is a Christian faith special our tewahido church Ethiopian I mean follows Our Lord and Savior Jesus Christ. If so we all should follow the same. God is always God if worked by our fore fathers he also can work by us his followers and believers even sons and daughters according to our Holy Bible. Therefore my brother go back to your bible and read it the Holy Spirit will teach you many great things then you will be amazed how our practice or religion is far from the Holy Word of God. But I still appreciate your concern about the Church. God bless you

      Delete
  3. ‹‹ቄስ መነኩሴ አትፈልጉ እራሳችሁ ፀልዩ፡፡›› He is right! what is wrong with that? do you think it is a requirement to have middle man to reach our prayer to God? Absolutely not. Trust me Thadiso will control Orthodox Church very soon! We need that!

    ReplyDelete
    Replies
    1. what about mosse, eyob abereham ,yeshak did they not intermediate with God if u doesnt know bible come to church and learn what it say else keeping the mouth shut is wisdom

      Delete
  4. hi guys it is good sibekit

    ReplyDelete
  5. በመዳን ህይወት ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው ኢየሱስ ነው፡ this is wrong because jesus is the only saviour. the lion part means 90 10% 10% for others .this is wrong jesus only saviour not others.

    ReplyDelete
  6. በደምህ ዋጅተህ ያፀናሃትን
    ጠብቅልን ቤተክርስቲያንን
    አብዛልን ማስተዋልና ጥበብን

    ReplyDelete
  7. egzer yinkelew kebete kiristinachin. yetereme!!!!!!!!! yebeg lemid lebisoo yemeta kifu newe. gin egzer yizegey yihonal enji ayikerim wagawin yagnal. His backbone is from betekihinet, those guys they don't represent orthodox... but they do represent tehadiso.

    ReplyDelete
  8. ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።

    ReplyDelete
  9. ወንድማችን ዲያቆን በጋሻው የኑፋቄ ንጝሮች የተሰራጨባቸውን ቪሲዲዎች እና መጻሕፍት የበተነው መች ነው?
    ብቻውን አምላክ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ እሱን ብቻ ኣአክብሩ ስላለ ነው ? ቃሉ የሚለው እኮ
    እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።ትንቢተ ኢሳይያስ ፬፫፥፩፩

    መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። የሐዋርያት ሥራ ፬፥፩፪

    ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።ወደ ሮሜ ሰዎች ፩፥፫፡፬

    ReplyDelete
    Replies
    1. ሄኖክ ቁጭትMarch 11, 2014 at 1:24 AM

      እንደጋሩሪ ፈረስ ቀጥታ አትመልከት እሱ ለማለት የፈለገው " ፃድቃን ሰማዕታት አትበሉ፤ አታክብሩ፤ ለፃድቃን ቦታ አትስጡ ነው እንጂ " መፅሀፉ እኮ ክብር ለሚገባው ሁሉ ክብርን ስጡ ይላል።

      Delete
  10. Egziabher Kebetecheresiyanachin ley Kene nufakewu yigfawu enji Besewuma altechalem edme LEBETEKIHINE Mindegnoch legenzeb belewu fekad lemisetut egzer gize alewu atesgu bizu alkesenal balefewu 20 amet ena keziya belay gin ye 3 ken besheta begizewu yiseta aytenal ene alsegam lebetechrestiyan yalat Yebetechrestiyan amlak becha newu esu meftehe selalewu egna entseleyalen metseley metseley!!!

    ReplyDelete
  11. ጸሐፊው የሚለውን የሚያውቅ አይመስለኝም። አረ እየተስተዋለ! ከአንተ ሃሳብ ጋር ስለተቃረነ ብቻ አባባሎቹ ሁሉ የተሳሳቱ ናቸው ማለት ነው? እንዲህ ስል ሰውየው የተናገረውን ሁሉ እንቀበላለን ማለት አይደለም።

    ዝም ብለህ ስትቃወም ከመጽሐፉ ቃል ጋር ስትጋጭ እንዳትገኝ ተጠንቀቅ!

    እኔ ግን በ1984ቱ የመጽሐፍ ቅዱስ እትም ላይ እንደታየው በጥቂት ዘመናት ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ንጹህ መልእክት ሙሉ በሙሉ (ለጆሯቸው በሚስማሙ ቃላት ብቻ) እንደሚቀየሩ ምንም ጥርጥር የለኝም። በዚህ እትም ላይ ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ውጪ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች (አዲስ ኪዳን ላይ ያሉ) እንዲቀየሩ ተደርገዋል። መስተካከል የሚገባው ማን ነው? መጽሐፉ ወይስ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ?

    እግዚአብሔር ንጹህ ልብን ያድለን።

    ReplyDelete
  12. betam yigerimal sebel yasifeligewal

    ReplyDelete
  13. የአንድ አድርገን ፀሓፊ መቼ ነው እራስህን በእግዚአብሔር ቃል የምትመልከተው:: ሃይማኖት እኮ ሕይወት ሲሆን እንጂ ሞትን አይናገርም መጋቢ አዲስ በጋሻው ደሳለኝ ብለህ በክብር ስሙ ልትጠራው እንካን አልወደድከው ቢሳሳት እንካን ፀልይለት እንጂ አትግፋው ጌታችንስ
    "
    ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፥ ቢጸጸትም ይቅር በለው።" ሉቃስ 17፥3
    ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፥12

    ReplyDelete
  14. ራሥህ ይኸው ማሥረጃ ብለህ አስቀምጠህ : አንተው ራሥህ ደግሞ ማሥረጃ ጠቃሹ ትዋሻለህ :: ነው ራሥህን ለማጋለጥ ነው ? ሠውን ሥትወነጅል ሙሉ ቃሉን ጠቅሰሕ እንጂ : እንደ ካድሬ ቃል አትምዘዝ :: ለማሥተማር ሳይሆን ነገር ፍለጋ እያደረግከው እንደሆነ ግልፅ ነው ፥፥ ሌላ የተሻለ አቀራረብ ፈልግ ፥፥ ለምሳሌ በጋሻው ፥
    ቤታችሁ በሽተኛ አስተኝታችሁ እናንተም መፀለይ ኣየቻላችሁ በግድ የቄሥና የመነኩሴ ፀሎት ብቻ አያስፈልጋችሁም ፥ የናንተም በእምነት የሆነ ፀሎት በእግዚአብሄር ፊት ዋጋ አለው ፥፥ የሚል መልእክት እየተናገረ ‹‹ቄስ መነኩሴ አትፈልጉ እራሳችሁ ፀልዩ፡፡›› አለ እንዴት ትለናለህ ? ይልቁን አንተ የምዕመናን ፀሎት ዋጋቢስ ነው እያልከን እኮ ነው ::

    ReplyDelete
  15. let alone he is correct he has no spiritual gesture(he looks a gambler)

    ReplyDelete