
“የማህበረ ስላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ”
ማህበር አባላት አሁንም ድረስ ከፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሕጋዊነቱን የሚያረጋግጥና በመንግስት ዘንድ እውቅና ያለው የእምነት ተቋም
ሳይሆን ስሙን ከመሬት በማንሳት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተክርስቲያናት እና ገዳማት ላይ አስተምህሯቸውን ለመጫን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
በአሁኑ ሰዓት በባለፉት ሦስት ዓመታት በሰሩት ስራ ባፈሯቸው ጭፍራዎቻቸው አማካኝነት ጊዜን እየጠበቁ በየቦታው ሁከት እያስነሱ ይገኛሉ፡፡
ቤተክርስቲያኒቱ እነዚህ ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች ላይ እያደረሱት ያለውን ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሕጋዊ መንገድ የምትጠይቅበት
ምዕመኑንም ከውዥንብር የምትታደግበት ጊዜ እስኪመጣ ድረስ ሁሉም በያለበት እነዚህን ሰዎች ሊቃወማቸውና ከተቻለም እንደ ደብረ ብርሃን
ወጣቶች ከነሥራቸው ወደ ፍርድ አደባባይ ሊያቀርባቸው ይገባል እንላለን፡፡
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን
No comments:
Post a Comment