- ምእመናን ለሚከፍሉትና ለሚሰጡት ገንዘብ ደረሰኝ የመጠየቅ ልማድ ሊኖራቸው ይገባል
- ድብቅሙዳየምጽዋትማስቀመጥ፣በዣንጥላናበምንጣፍገንዘብመለመንይከለከላል
(አዲስ አድማስ
ታኅሣሥ 12 2006 ዓ.ም)፡- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት የካሽ
ሬጅስተር ማሽንን ለገቢ መሰብሰቢያነት ለመጠቀም ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
ዘመኑን ያልዋጀውንና ጥራት የጎደለውን፣ ለሙስናና ብክነት የተጋለጠውን የቤተ ክርስቲያኒቱን የፋይናንስ አሠራርና ቁጥጥር ችግር፤ ግልጽነት፣ ወጥነት፣ ተቀባይነትና ተጠያቂነት ባለው የፋይናንስ አያያዝ ሥርዐት ለመቅረፍና ለማድረቅ ያስችላል፤ በሚል በቀረበው የሀገረ ስብከቱ የሒሳብ አያያዝ ፖሊሲና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ ረቂቅ ላይ እንደተጠቀሰው÷ በማንኛውም መንገድ የተሰበሰበ ገንዘብ፣ ሕጋዊ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወዲያውኑ ሊቆረጥለት የሚገባ ሲኾን
ይህም በዋናነት በካሽ ሬጅስትር ማሽን
እንደሚከናወን ተመልክቷል፡፡