Tuesday, January 17, 2012

አሁን እዚህ ሀገር ህግ አለ?


(አንድ አድገን ጥር 8 2004 ዓ.ም)፡በደብረዘይት የሚገኘውን የመድሀኒዓለም የጥምቀት ቦታ መንግስት ከአቡኑ ጋር በመስማማት ቆርሰው ለባለሀብት በመስጠት ሪዞርት ሲያሰሩበት ማንም ያልተናገራቸው ‹‹ለምን ለአንድ ቀን ያለ መንግስት ፍቃድ በ2003ዓ.ም ለጥምቀት ታቦታችሁን እዚህ ቦታ አሳረፋችሁ››  በሚል ሰበብ በኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ ዙሪያ ቡራዩ ከተማ የሚገኝው ፊሊዶሮ ቅድስት ልደታ ገዳም አስተዳዳሪ የሆኑት ቆሞስ አባ ሳሙኤል ግዛቸው  ህገወጥ የመሬት ወረራ ፈፅመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው የ3 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል፡፡  ታቦተ ህጉን 2000 ካሬ በማትሞላ ቦታ ላይ የዛሬ ዓመት 2003ዓ.ም ላይ ነበር አርፎ ምዕመኑ በዓሉን ያከበረው ፤ በዓመት 1 ጊዜ የሚመጣውን የጥምቀት በዓልን ለማክበር ታቦተ ህጉን መንግስት ቦታ ካልሰጠን የት እናሳርፍ ? እንዴት ይሄ ከህገ ወጥ መሬት ወረራ ጋር ይያያዛል ? አንድ ቀን ታቦት ስላሳረፍንበት ህገ ወጥ የመሬት ወረራ አደረግን ማለት ነው እንዴ? ህጉስ እንዴት ያየዋል? ቤተክህነቱስ ምን ይላል?

የመንግስትን መሬት እንደ ግል ንብረታቸው ተጠቅመው ሸንሽነው ለማህበራት መሰሎች ያከፋፈሉ ፤ 280 ሚሊየን ብር መንግስት ማግኝት ያለበትን ገቢ ያስቀሩ ሰዎች  የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ እና የላፍቶ ክፍለ ከተማ ባለስልጣናት  የነበሩ ሹሞች በ 7 ዓመት የእስራት ፍርድ ሲፈረድባቸው ፊሊዶሮ ቅድስት ልደታ ገዳም አስተዳዳሪ የሆኑት ቆሞስ አባ ሳሙኤል ግዛቸው ግን ለምን ያለ መንግስት ፍቃድ በ2003ዓ.ም የጥምቀት በዓል ቀን የመንግስት ቦታ ላይ ታቦት ያሳርፋሉ በሚል ተልካሻ ምክንያት 3 ዓመት ሊፈርዱባቸው ችለዋል፡፡ 

3 comments:

  1. egezyabehyer yefaredelen leman abet yibalale

    ReplyDelete
  2. Becherinetu enji yalenew Ezi hagrima Hig yelem

    ReplyDelete
  3. egezyabher yeker yebalen

    ReplyDelete