Tuesday, February 11, 2020

ለአንዱ ቦታ እያመቻቹ ሌላውን በራሱም ቦታ ማንገላታት

(በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ)
(አንድ አድርገን 02/6 2012 ዓ.ም):-  መምህር ምሕረተ አብን ለማስደንገጥም ይሁን ጉባኤዎችን ለመረበሽ ትላንት ማታ እንደተደረገ የሰማሁት ነገር ብዙ ነገር የሚጠቁም ነው። ሰሞኑን ወንድሞቻችን ሰማዕትነት የተቀበሉበትና አዲስ ቤተ ክርስቲያን የፈረሰበት 24 ቀበሌው ቦታ ያን ሁሉ መዓት ያመጣው ፓስተር ዮናታን ቦታውን እርሱ እመራዋለሁ ለሚለው የመልካም ወጣት ፕሮጄክት በጠየቀው መሠረት ለማስረከብ በጥድፊያ ላይ ስለነበሩ ነው።

ምሕረት የምሕረት ወንጌል ስባኪ እንጂ ፥የወንጀል ስባኪ አይደለም !!


(በዲ/ን ታደሰ ወርቁ)
(አንድ አድርገን 02/6 2012 ዓ.ም):- ወንድማችን መምህር ምሕረተ አብ አሰፋ በእጁ የያዘው የፍቅር እና የስማዕትት ትእምርት የሆነውን ጧፍ እንጂ፥ጎመድና ሰይፍ አይደለም። ከአንደበቱ የሚወጣው ቃል እግዚአብሔር እንጂ ጥላቻና ልዮነት አይደልም። ዘመኑን ለቤተ ክርስቲያን ዘመነ ሰማዕታት ያድረጉባትን እንደ ጃዋር መሐመድ እና እንደ አህመዱን ጀበል ዐይነቱን የስይፍና የጎመድ፤ የሀገራዊ ልዮነትና ጥላቻ፤ የቤተ እምነቶች መቃቃሪያና መጠያያ ምንጮችና የአስተሳስብ አባቶችን የሚከባከብ ፖሊስ ፥መምህራችንን አይደለም የማዋከብ፥ ጠርቶ የማናገር የሞራል እና የሕግ መሠረት የለውም።እገሌ ያስተምር፤ እገሌ አያስተምር የማለት ሙሉ ሥልጣን የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን እንጁ፥የፖሊስ አይደለም

ቅ/ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል።


(አንድ አድርገን 02/6 2012 ዓ.ም)  :-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ለየካቲት 9 ቀን 2012 . አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ማድረጉን ቋሚ ሲኖዶስ አስታውቋል። አስቸኳይ ጉዳይ ካልገጠመው በስተቀር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ (ጥቅምት እና ግንቦት) የሚካሄድ እና በቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ኦርቶዶክሳውያን የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ በሚከተሉት አንኳር ጉዳዮች ላይ እንዲመክር እና ቁርጥ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ይጠብቃሉ።

Thursday, February 6, 2020

እነርሱ እየገደሉን እኛ አስክሬን ልንቆጥር አይገባም ፤ አሁንስ በቃችሁ…


(በዲ/ን ታደሰ ወርቁ)
(አንድ አድርገን ጥር 29 2012 ዓ.ም) ፡-  ትናንት ዳር ዳሩን ሲገድሉን የነበሩት ዛሬ ደግሞ መሐል ከተማ ገብተው ይገድሉን ጀምረዋል፡፡ ትናትም ሆነ ዛሬ እየተገደልን ያለነው በገዳዮቻችን ጥንካሬ ሳይሆን÷በእኛ ልፍስፍስነት፤በአባቶቻችን ጥብዓት አልባነት፤በመንግሥት ይሁንታነት ነው፡፡ ትዕግስታችንን እንደልምጥምጥነት፤ ጨዋነታችንን እንደፍርሐት፤የሀገራዊ አንድነትና ሰላም ጠባቂነታችንን እንደባለዕዳ እየተቆጠረብን ነው፡፡

የትናት ሌሊቱ የኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ግድያ÷የግድያችን ሁሉ ማብቂያ ልናደርገው ይገባል፡፡ ለገዳዮቻችን ንብ በሕይወት የምትቆየው እስከትነድፍና መርዟን እስክትጨርስ ብቻ መሆኑን በተግባር ልናሰተምራቸው ይገባል፡፡ ይኼን ምዕራፍ ዘግተን ወደሌላኛው ምዕራፍ ልንሸጋገር ይገባል፡፡ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጀምሮ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ በተግባር የምንፈተንበት ጊዜና ሰዓት ላይ ደርሰናል፡፡

የመንግሥት ይፋዊ ጦርነት‼

(በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ)
(አንድ አድርገን ጥር 29 2012 ዓ.ም) ፡- ትናንት ሌሊት ላይ በአዲስ አበባ 24 አካባቢ በኦርቶዶክሳውያን ላይ በመንግሥት የተፈጸመው ሽብር በእጅጉ አሳዛኝ እና አሳፋሪ ነው።  ነገሩ በሌሉት የተደረገው ጉዳዩ ሕግ ለማስከበር ሳይሆን መንግሥት ከቤተ ክርስቱያናችንና ከኦርቶዶክሳዊያን ጋር ይፋዊ ጦርነት መጀመሩን ለማወጅ ይመስላል፡፡

በሕልም ዐለም ውስጥ ያሉ የሚመስሉኝ ኦርቶዶክሳውያን ምንም ያህል ቢሉለት ለእኔ እስከሚገባኝ ድረስ ይህ መንግሥት ጸረ ኦርቶዶክስ መሆኑ ግልጽ ከሆነልኝ ሰነባብቷል።  አንዳንዶቹ ባለሥልጣናት ምንም ያህል ቢያስመስሉም እውነታውን ሊደብቁት አልቻሉም።  በርግጥ ማስመሰላቸው የማይታወቅባቸው አደገኛ ጸረ ኦርቶዶክሶች እንደሚኖሩም እጠረጥራለሁ።  ነገር ግን ጌታ በወንጌል የማይገለጥ የተከደነ ነገር የለም እንዳለ ለጊዜው ነው እንጂ ሁሉም ግልጥ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። የዚያን ጊዜ ደግሞ በሰፈሩት ቁና መሰፈር የማይቀር መሆኑ የተፈጥሮ ሕግ ነው።

ወንድሞቻችንን የነጠቁን ለፓስተሩ ሲሉ ነው?


            ዲያቆን አባይነህ ካሴ
(አንድ አድርገን ጥር 29 2012 ዓ.ም) ፡- አዲስ አበባ ከተማ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል አካባቢ ቀበሌ ፳፬ ላይ የነበረው ክፍት ቦታ በመዋቅራዊ ፕላኑ መሠረት ለመናፈሻነት (Green Area) የተጠበቀ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ መንግሥት ሊያለማ ቀርቶ የቆሻሻ መጣያ እና ለኗሪው የደኅንነት ስጋት እስኪኾን ድረስ ወንጀሎች ይፈጸሙበት የነበረ ቦታ መኾኑ ኗሪውን ሲያሳስበው ቆይቷል፡፡ በዚህም የተነሣ መጠነኛ የማልማት ሥራዎች ማኅበረሰቡ በራሱ ተነሣሺነት ሲያደርግበት የነበረ ቦታ ነው፡፡
 
በዚህ መካከል በቦታው ላይ ለሕዝቡ አገልግሎት ይሰጥ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ለመትከል ምእመናን እንቅስቃሴ ይጀምራሉ፡፡ የሚመለከተው የቤተ ክህነት መዋቅርም ጉዳዩን ዐውቆት አስፈላጊውን ድጋፍ ስላደረገ ጥያቄውን ለመንግሥት አካላት ያቀርባል፡፡ በዚህ መካከል አንድ እሽቅድምድም ይጀመራል፡፡

‹‹ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ››



(አንድ አድርገን ጥር 29 2012 ዓ.ም) ፡- ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት፣ ታሪካዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን  ኢትዮጵያ አሁን ከደረሰችበት  የእድገት ደረጃ ከመድረሷ በፊት ብራና ዳምጣ፣ ቀለም በጥብጣና ፊደል ቀርጻ  ትምህርት ያስጀመረች፣  የፍትሕ ሥርዓቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ መዋቅራዊ አደረጃጀት ሳይኖረው ፍርድ እንዳይጓደልና ደሃ እንዳይበደል በማሰብ የፍትሐ-ነገሥት መምህራኖቿን በዳኝነት መድባ የፍትሕ ሥርዓትን የመሠረተች፣ ዜጎችን በሥነ-ምግባርና በግብረ-ገብነት ትምህርት ኮትኩታ በማሳደግ ሀገር ወዳድ ትውልድ በማፍራት መሠረት የጣለች ቤተክርስቲያን ሆና ሳለ ዛሬ ዛሬ በዘመናችን የምናየው እና የምንሰማው ነገር ‹‹ወርቅ ላበደረ ጠጠር›› በመሆኑ …...ትላንት ከሺ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምንሰማው የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠል እና የምዕመኗ ሞት ዛሬ እጅግ በመበራከቱ ፤  ምዕመና  ስለ  አንዲት  ቅድስት  ቤተክርስቲያንን በሚመለከት ዕለት በዕለት  የሚታየዉ ፤ የወደፊት ስጋት ምን እንደኾነ ኹሉም  የእናት ቤተክርስቲያን ልጆች እንዲያውቁት የበኩላቸውንም መፍትሔ እንዲፈልጉ ሐሳብ እንዲሰጡ በክርስትናቸው የሚጠበቅባቸውን ሓላፊነት እንዲወጡ የክርስቶስን መስቀል ለመሸከም  የማይሰቀቅ ክሣደ ኅሊና አንዲኖራቸው ለስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮዋ መሳካት ፤ ለኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ህልውና መጠበቅና ለፍጹም አንድነቷ እንዲነሡ የበኩላችንን ኃላፊነት እንዲወጡ ‹አንድ አድርን›  blog ወደ ቀደመ ስራዋ  የተመለሰች መሆኗን ለማሳወቅ እወዳለን፡፡ 


Our Official Links :-