
Thursday, June 29, 2017
የሐዋሳ ተርቦች እየተናደፉ ነው!
By :- D/n Abayneh Kasse
"አምላክህ እግዚአብሔር የቀሩት ከፊትህም የተሸሸጉት እስኪጠፉ ድረስ ተርብ ይሰድድባቸዋል" ዘዳ ፯፥፳።

Tuesday, June 20, 2017
ጠባቂ የሚሹ የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች
17 Jun, 2017
By ምሕረተሥላሴ መኰንን
- << በቅርሶች ጥበቃ ሁሉም አካል መረባረብ ያለበት ሲሆን፣ ትውልዱም ለታሪኩና ለባህሉ ተቆርቋሪ መሆን ይገባዋል፡፡ ከየቤተ ክርስቲያኑና የሚሰበሰቡ ቅርሶች በአግባቡ ካልተጠበቁ ዋጋ የለውም፡፡ አሳልፈን እየሰጠናቸው ያለነው እኛው ነን፤›› አባ ብስራተአብ
ኢትዮጵያ በዓለም የሥነ ጽሑፍ ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው ጥንታውያን መጻሕፍትና የነገሥታት ደብዳቤዎች መካከል የ14ኛው ክፍለ ዘመን አርባዕቱ ወንጌል፣ የ15ኛው ክፍለ ዘመን የጳውሎስ መልዕክቶች፣ የ15ኛው ክፍለ ዘመን ግብረ ህማማትና በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኅትመት መጽሐፍ መዝሙረ ዳዊት ይጠቀሳሉ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በተዘዋዋሪ ከመዘገበው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ ያደረጉት ንግግር በተጨማሪ ሦስት የነገሥታት ደብዳቤዎችም (አፄ ቴዎድሮስ ለእንግሊዝ ንግሥት ቪክቶሪያ የላኩት ደብዳቤ፣ አፄ ምኒልክ ለሞስኮው ቄሳር ዳግማዊ ኒኮላስ የላኩት ደብዳቤና ከሸዋው ንጉሥ ሳህለ ሥላሴ ለእንግሊዟ ንግሥት የተላከው ደብዳቤ) ተመዝግበዋል፡፡ አምስቱ በማይክሮ ፊልም የተቀረፁ ጥንታውያን መጻሕፍት ደግሞ ታሪክ ዘ ምኒልክ፣ መጽሐፈ ሔኖክ፣ ታሪክ ነገሥት፣ ቅዳሴና ፍትሐ ነገሥት ናቸው፡፡
Monday, June 12, 2017
በሰዓሊተ ምሕረት ጉዳይ ያልተመለሱልን ጥያቄዎች!
·
ፓስተር ኦላቭ (Rev.Dr Olav Fyske፣ የኖርዌይ ሉተራን እምነት ፓስተር፣ የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ) ጸሎት አድርጌያለሁ ብሎ ሲፈጽም እየተጠራሩ መቀባባት ተጀመረ።
·
የእኛዋ ቤተ ክርስቲያን ተወካይ ዶ/ር
አባ ኃ/ማርያምም
ቀርበው ተቀቡ:: እርሳቸው ደግሞ ፓስተር ዮናስ ይገዙን (በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የመካነ ኢየሱስ ፕሬዘዳንት) በአደባባይ ቀቡ።
በሀገራችን ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተፈፀመው ድርጊት ይፋ ከሆነ ጀምሮ ብዙ ጥያቄዎችን አስነስቷል። ጉዳዮቹን አድበስብሶ ለማለፍ የሚደረገው ጥረት ደግሞ የበለጠ ለምን እንዴት የሚሉ ጥያቄዎችን በመላው ዓለም በሚገኙ የቤተክርስቲያን ልጆች ላይ ፈጥሯል።

Subscribe to:
Posts (Atom)