‹‹ዛሬ በከፍተኛ አዘቅት ውስጥ የወደቀችው አገራችሁን ኢትዮጵያን እና ሃይማኖታችሁን ለመታደግ በሃይማኖት ጸንታችሁ መንፈሳዊ ተጋድሎ አድርጉ›› አለቃ አያሌው ታምሩ ሚያዚያ 23 ቀን 1983 የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአል በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በሚከበርበት ጊዜ በቦታው ተገኝተው ያስተማሩት ትምህርት፡፡
(አንድ አድርገን ሚያዝያ 23 2004 ዓ.ም )-
የዛሬ 22 ዓመት መንግሥትና ቤተክህነት ሁለቱም የተሳሳተ ጎዳና ላይ ሳሉ አለቃ አያሌው ታምሩ በቅዱስ ጊዮርጊስ አውደ ምህረት
ላይ ያስተማሩትን ትምህርት እንመልከት::
1983 ዓ.ም ደርግ በህዝቡ ላይ ሲሰራ የነበረው ግፍ ሁሉ ዘንግቶ ከመጣበት የውድቀት ጥሪ
ለመዳን በከፍተኛ ደረጃ በተፍጨረጨረበት ዓመት ነበር ።። በቀደሙትዓመታት ሙልጭ አድርጎ ሲሰድባቸው የነበሩት ቀደምት የኢትዮጵያ
ነገስታት ይልቁንም እነ አጤ ቴዎድሮስን ፡ እነ አጤ ዮሐንስን ፣ አጤ ምንይልክን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን እያነሳ የህዝቡን
ወኔ መቀስቀሻ እና የዘመቻ ማዘጋጃ ዘዴ ብሎ ይዞት ነበር።። ነጋ ጠባ ስለ እነዚህ ቀደምት ነገስታት ጀብዱና ሀገር ወዳድነት
አትንኩኝ ባይነት ብዙ ይባል ነበር። ሚያዚያ
23 ቀን 1983 የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአል በአራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በሚከበርበት ጊዜ አለቃ አያሌው ታምሩ በቤተክርስቲያኑ
ተገኝተው እንዲያስተምሩ ተጋብዘው ነበር። እሳቸው ስለ ሰማዕቱ ተጋድሎና በሃይማኖት ስላገኝው የድል አክሊል ዘርዝረው እንዲህ
ብለው አስተማሩ።