Monday, November 11, 2013

በሳውዲ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግሥት ኃፊነቱን ይወጣ


(አንድ አድርገን ህዳር 3 2006 ዓ.ም)፡- ከወራት በፊት የሳውዲ መንግሥት በህገወጥነት ስራ የተሰማሩ የማንኛውም ሃገር ሰዎች አንድም ህጋዊ እንዲሆኑ ያለበለዚያ ከሀገር እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር ፤ ብዙ የፊሊፒንስ ፤ የኢንዲኒዥያ ፤ የህንድ እና የፓኪስታን ዜጎን መንግሥታቸው ጊዜ ገደቡ ሳይጠናቀቅ በኢምባሲዎቻቸው አማካኝነት አንድም ሕጋዊ የማድረግ ሥራ ሲሰሩ ነበር ያልሆኑትም በርካቶችን ወደ ሃገራቸው ሲመልሱ ነበር ፡፡ የኛ ሃገር መንግሥት ግን ተኝቶ ሲያበቃ የቤት ለቤት አፈሳው ሲጀመር ፤ የሰዎች ደም እንደ ከንቱ ሲፈስ ፤ የኢትዮጵያውያን ሞት ከውሾች እኩል ሲታይ ፤ አፈናው ፤ ዱላው ፤ ግድያው ፤ አስገድዶ መድፈሩ ሲባባስ አቤት እንኳን ማለት አለመቻሉ እጅጉን ያሳዝናል ፡፡ በተለያዩ የዓለም የመገናኛ ብዙሃን በግልጽ የኢዮጵያኖችን መከራ ሲያስተላፉ  የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ በኤፍ ኤም 97.1 ላይ ቀርበው ‹‹ኢትዮጵያኖች ላይ እየደረሰ ያለው ነገር እንደሚወራው አይደለም ፤ ኢትዮጵያውያ ሳውዲ ውስጥ በቁጥር እዚህ ግቡ የሚባሉ አይደሉም›› ብለው አስተያየታቸው ሲሰጡ መስማት ውስጥን ያደማል፡፡ እስኪ አሁንም ጊዜው አልረፈደም ፤ ከዚህም የባሰ ጉዳት ሳይደርስ መንግሥት አቤት ይበላቸው ፡፡ ወደ ሀገራቸው ለመምጣት ያሰቡትን በእስር ላይ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን ከሰዓታት እድሜ ውስጥ ይድረስላቸው ፡፡ ከዚህ የባሰ ሰብአዊ መብት ረገጣ እንዳይካሄድባቸው ሁሉም በያለበት ድምጹን ያሰማላቸው፡፡  

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በስደት ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሌም ታስታውሳለች ታስባለችም። ይልቁንም በአሁኑ ሰዓት በአረማውያኑ ሃገር የሚሰቃዩትንና ሕይወታቸውም ያለፈውን እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን ከአብርሀም ከይሳቅ ወገን እንዲያሳርፍና ለወገኖቻቸውም መጽናናትን ይህንንም አስከፊ ግፍ ለሚፈጽሙባቸውም ልቦናን ይሰጥ ዘንድ ዘውትር ትጸልያለች። እግዚአብሔር በስደት ያሉትን ወገኖቻችንን ያስብልን፡፡ መድኃኒዓለም ይድረስላቸው፡፡


እስኪ ስለነዚህ ወገኖች ሁላችን እንጸልይ

1 comment:

  1. lemehonu yih site yemanewu? kebetekirtsian alfen wede yemingistin aserar metenkos mesmerun yesatin ayimeslim?

    ReplyDelete