Wednesday, August 22, 2012

የአቡነ ዮሀንስ ነገር



(አንድ አድርገን ነሐሴ 17 2004 ዓ.ም)፡-በትላንትናው እለት የአቡነ ጳውሎስን አስከሬን ከሆስፒታል እስከ ጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ አጅበን ከመጣን በኋላ ቀጥታ ወደ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት ነበር ያመራነው ፤ በጊዜውም ቅዳሴ ሳይገቡ በመድረስ ቅዳሴ ማስቀደስ ችለን ነበር ፤ በቅዳሴው ላይ የአቡነ ጳውሎስ ፤ የመለስ ዜናዊ እና የአቡነ ዮሃንስ ስም ተጠርቶ ነፍስ ይማር ለሶስት ጊዜ ተብሎ ነበር ፤ ቅዳሴው ካለቀ በኋም ከአቡነ ጳውሎስ ሞት ቀጥሎ አቡነ ዮሃንስ አርፈዋል በማለት በአውደ ምህረት ላይ ተነግሯል ፤ እኛም ይህን ይዘን ከሰዓታት በኃላ ትላንት ማታ ላይ አቡነ ዮሃንስ ማረፋቸውን ገልጸን ጽፈን ነበር ፤ ነገር ግን ከወደ መቀሌ እንዳረጋገጥነው አቡነ ዮሃንስ በህይወት እንዳሉ ለማወቅ ችለናል ፤  በመኖሪያ ቤታቸው ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል አባ ፍሬምናጦስ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ ፤


ታቦት ወጥቶ እስኪገባ ፤ ቅዳሴ ተጀምሮ እንከሚያልቅ የገብረእግዚአብሔር(መለስ ዜናዊ) ፤ አቡነ ጳውሎስ ፤ አቡነ ዮሀንስ ስም ተጠርቶ ነፍስ ይማር ተብሏል ፤ በአቡኑ ሞት እንባቸውን ያፈሰሱም በጊዜው ነበረ ፤ ይህ ነገር የተነገረው በሺህ ለሚቆጠር ሰው ነው ፤ እኛም ይህን ሰምተን በጊዜው መጻፋችን ስህተት መስሎ አይታየንም ፤ ችግሩ ያለው ከአስተዳዳሪው እንጂ ከእኛ አይደለም ፤ አሁንም የአቡነ ዮሀንሰ ቀብር መቼ ነው እያለ ሰው እያወራ ይገኛል ፤ ማንም ኦፊሺያሊ ያስተባበለ አካል ስለሌለ ኢንተርኔት ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች በእንጦጦ ኪዳነምህረት የነበሩ እናቶችና አባቶች እንደሞቱ ነው የሚያውቁት፡፡ በጊዜው በአውደ ምህረት ላይ ለህዝብ የተነገረን ዜና ማነው ለማመን ከሶስተኛ አካል እማኝ የሚፈልግ? ለዛውም ቤተክርስትያን … 

አብያተ ክርስትያናት የመረጃ ምንጫቸው ምንድነው ?

2 comments:

  1. Whatever the sources of information of the Churches, as a blogger you should excuse yourself and say "I am sorry". It natural to make mistake. you are a blogger, brother/sister.

    ReplyDelete
  2. ትክክል ነው እኔም ቅዳሴው ላይ ሰምቼ እንደገና ደግሞ አጣራጣሪ ነገር ስሰማ ግራ ተጋብቻለሁ።

    ReplyDelete