Wednesday, August 29, 2012

የፈራነው ይህን ነው

  • “መለስ ከሞት ይነሳል ፤ እግዚአብሔር ልኮኛል” የሚል ሰው ብቅ ብሏል
ትላንት 4 ኪሎ ቤተመንግስት የጠቅላይ ሚኒስትሩን አስከሬን ለማየት ብዙዎች ተሰልፈው ነበር ፤ አንድ ሰው ግን ወደ ፊት በመምጣት “መለስ ከሞት ይነሳል ፤ እግዚአብሔር ልኮኝ ነው ፤ ጸሎት አድርግለት ብሎኛል ፤ተውኝ ገብቼ ጸሎት ላድርግና ላስነሳው” በማለት ሲናገር ነበር ፤ በር ላይ ያሉት ዘቦችም ሰልፍ ያዝና ትገባለህ ብለውት ወደ ኋላ ቢወስዱት እሱ ግን “ተውኝ መለስን ከሞት አነሳዋለሁ እግዚአብሔር ልኮኛል” እያለ እምቢታውን ገለጸ ፤ ተፈቅዶለት ወደ ውስጥ እስኪገባ ድረስ ወደ ውስጥ ለመግባት የተዘጋጀውን ሰው ሁላችሁም በሃይማኖታችሁ ጸልዩ  እግዚአብሔር ከሞት እንደሚነሳ ነግሮኛል በማለት ሲናገር ተስተውሏል ፤ ይህም ወሬ ውስጥ ሀዘን ላይ ለተቀመጡት ሰዎች ዘንድም ደርሷል ፤ እውነት የመሰለው በርካታ ነው ፤ እንደ አልአዛር ከሞት እንዲነሳ የሚፈልግም ሰው እንደዛው …. በቦታው ላይ የነበረ ሰው ለዚህ ምስክር ነው፡


ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ መለስ ትዘረጋለች እንዳይባል ሰጋን

ይህ አምልኮ ነው ወይስ ሐዘን? ወደ የት አያመራን እንደሆን እናስብበት!! ሲጀመር ይህ ሀዘን በዛ ብለን ነበር ፤ መጨረሻው ይህ ሆኖ አረፈው ፤ በማን ይፈረዳል? ሀዘንም ይሁን ደስታ መጠኑን ማለፍ የለበትም ፤ ሁላችንም ሟች ነን ፤ በህይወት ለሚለየን ሰው አግባብ ባለው መንገድ ሀዘናችንን መግለጽ ይገባል ፤ ነገር ግን መስመር ከሳተ አደጋ አለው ፤ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴዎቹ ይህ ይመጣል ብለው ላያስቡ ይችላሉ ፤

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ  ጥሩ ከሚባሉ የአፍሪካ መሪዎች ግንባር ቀደም ናቸው ፤ አሁን እግዚአብሔር ፈቅዶ  በሞት ተለይተውናል ፤  እሳቸውን የመመለስ አቅም የሌለውን እንባ ከምናፈስላቸው ይልቅ ሀገራችን ቅን ፤ አስተዋይ ፤ አርቆ አሳቢ ፤ ህዝብን የሚያከብር ፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያደረበት ፤ ችግሮችንን የሚፈታ ፤ ማስተዋልና ጥበብን ተሰጠው መሪ እንዲሰጠን ብንጸልይ መልካም ነው፡፡

9 comments:

  1. የማቴዎስ ወንጌል 4/9 ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።

    10 ያን ጊዜ ኢየሱስ። ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።፤---------------ትንቢተ ኢሳይያስ 6/1 ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።

    ReplyDelete
  2. Er bkachu hazenu beza nge degemo beged wetach shma aberu tebelenal yeh hulu le nefse men yetkmatale?

    ReplyDelete
  3. yemtesegdu sewoche be carful besew ytamn ergum new ymil

    ReplyDelete
  4. eyasagadachew yalew le Geta new wayes le Askerenu yehenen layeten enewek majameriya. Askerenu fit wadeka/ tanbarekeko le fetari matsaley ayechalem ende koy lamin wedelela techet lamagebat enechakulalen gobez??? Tenesh ken astesaseb binoren betam yeshalal... ergetegna negn enazih sewoch askerenu fit wadekew le amlak eyamalakatu new yamihonew nafsun marew belew ena yatefut nager yalem tenesh lenekefa yachakolen ayemaselachehum....

    ReplyDelete
    Replies
    1. አምላክም ቤተ ክርስቲያን ቀርቶ ቤተ መንግስት መገኘት ጀመረ?

      Delete
  5. Yehe Hezeb Me'at Endayametaben.....Egazbhair yetagesen!

    AMEN!
    HM - NY

    ReplyDelete
  6. I am a born-again believer & my religion is Meles Zenawi.

    ለማንበብ ከፈለጉ ጠቅ የምትደረግ አድራሻ እነኋት
    http://www.aigaforum.com/articles/There-is-nothing-left-for-me-to-say.pdf

    ReplyDelete
  7. Egziabher mastewalin ysten

    ReplyDelete
  8. Gobez ...yihin euit eski. Abayin yalaye alu .. http://www.aigaforum.com/articles/There-is-nothing-left-for-me-to-say.pdf

    The one who wrote "eyasagadachew yalew le Geta new wayes le Askerenu yehenen layeten enewek majameriya"...aye gud..ahun demo min til yihon?

    ReplyDelete