Friday, August 31, 2012

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስከሬን በሙዚየም እንዲቀመጥ ተጠየቀ




አዲስ አበባ ነሃሴ 24/2004የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ማህበር የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስከሬን በሙዚየም እንዲቀመጥና በህይወት ዘመናቸው የሰሩት አኩሪ ስራ እንዲታወስ ጠየቀ። 

Thursday, August 30, 2012

“ኢትዮጵያ ቀኑ ጨለመባት” ተሀድሶያውያን ለአቶ መለስ ዜናዊ ያወጡት መዝሙር


መጀመሪያ ይህን መዝሙር ያድምጡ  Click here
 
(አንድ አድርገን ነሐሴ 24 2004 ዓ.ም)፡- ተሀድሶያውያን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ምክንያት በማድረግ “ኢትዮጵያ ቀኑ ጨለመባት” የሚል መዝሙር በማውጣት ለመንግስት እንደ ገጸበረከት አቅርበዋል ፤  ጥቂት የተሀድሶያውያን አቀንቃኞች አቡነ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ቀኑ ጨልሞባቸው ሊሆን ይችላል ፤ ከአሁን በኋላ በማን አማካኝነት ሲኖዶሱንና ህዝበ ክርስትያኑ መሀል ገብተው የሚበጠብጡበት በራፉ ተዘግቶባቸውም ይሆናል ፤  ነገን ሲያስቡት ጨልሞባቸው ሊሆን ይችላል ፤ ቤተክርስትያን ግን ምዕመኑን እንዲያገለግል የሾመችው ፓትርያርክ አባት በህይወት ቢኖሩም በሞት ቢለዩም ቀኖች  አይጨልሙባትም ፤ ይህ መዝሙር ቤተክርስቲያንን ወክሎ በኦሮሚያ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ ነበር ፤ ይህ በጣም አሳፋሪ ተግባር ነው ፤ ግጥሙ ዜማው ሳይመረመር ስለወጣ ብቻ በቴሌቪዥን ማቅረቡ ትክክል አይደለም ፤ ሰዎቹ ምንፍቅናቸውን ቤተክርስትያኒቱ ላይ ለመጫን ስርዓቷን ለመበረዝ ወደፊት ይመረጣሉ ተብለው የሚጠበቁት አባትን ሲያስቧቸው ሊጨልምባቸው ይችላል ፤ ኢትዮጵያም ብትሆን አንድ መሪ ስለሞተ ጨለመባት ማለት አግባብ አይደለም ፤ ማንም በዚች ምድር ላይ ቋሚ የለም ፤ ሁሉም ጊዜው ሲደርስ ይሸኛል ፤ ዓለም ኮንትራት ነች ፤ በእግዚአብሔር የሚያምን አንድ ሰው በሞት ተስፋ አይቆርጥም ሊጨልምበትም አይገባል ፤ የሚያኖረን የዓለም ብርሀን መድኃኒዓለም ነው፡፡ እኛ ወደፊት ብርሀን ይታየናል ፤ ለጥቅማቸው በቤተክህነቱ ዙሪያ የተሰገሰጉ ተሀድሶያውያን ደግሞ ነገ ጨለማ ሊታያቸው ይችላል ፤ ብርሃናቸውን ተነጥቀዋልና ፤ እንደ ከዚህ በፊቱ ተጽህኖ ፈጣሪ የሆነ አባት ለማግኝት የሚከብድ ስለሚሆንባቸው ጨለማው ይበልጥ ገዝፎና ከብዶ ታይቷቸው ይሆናል፡፡ 
እውን ቀኑ ለኢትዮጵያ ጨልሟል? ወይስ ጨለማው የሚገፈፍበት ቀኑ ደርሷል ? እስከ አሁን በብርሀን እንደኖርን የሚነግረን ሳይኖር ኢትዮጵያ ቀኑ ጨለመባት ይሉናል ፤ ጨለማ ከብርሀን በኋላ የሚመጣ ነው ፤ ብርሀን ደግሞ ከጨለማ በኋላ ፤ አሁን እሆነ ያለው የቱ ነው የሆነው ? ከብርሀን ወደ ጨለማ ? ከጨለማ ወደ ብርሀን ? ወይስ ከጨለማ ወደ ድቅድቅ ጨለማ ? ከጊዜ በኋላ አንዱ ይሆናል ፤ አሁን ግን ምንም የጨለመ ነገር የለም ፡፡ ለቤተክርስትያን ባለፉት 20 ዓመታት ጨለማ ናቸው ባንልም ብርሃን ነው ማለት አንችልም ፤ ነገንም አናውቅም ተስፋችን ግን በብርሀን መመላለስ ነው ፤  ለማንኛውም መንግስትን ለማስደሰት ሲባል የቤተክርስትያኒቱን ስርዓት መናድ ተገቢ አይደለም ፤ 

Wednesday, August 29, 2012

የፈራነው ይህን ነው

  • “መለስ ከሞት ይነሳል ፤ እግዚአብሔር ልኮኛል” የሚል ሰው ብቅ ብሏል
ትላንት 4 ኪሎ ቤተመንግስት የጠቅላይ ሚኒስትሩን አስከሬን ለማየት ብዙዎች ተሰልፈው ነበር ፤ አንድ ሰው ግን ወደ ፊት በመምጣት “መለስ ከሞት ይነሳል ፤ እግዚአብሔር ልኮኝ ነው ፤ ጸሎት አድርግለት ብሎኛል ፤ተውኝ ገብቼ ጸሎት ላድርግና ላስነሳው” በማለት ሲናገር ነበር ፤ በር ላይ ያሉት ዘቦችም ሰልፍ ያዝና ትገባለህ ብለውት ወደ ኋላ ቢወስዱት እሱ ግን “ተውኝ መለስን ከሞት አነሳዋለሁ እግዚአብሔር ልኮኛል” እያለ እምቢታውን ገለጸ ፤ ተፈቅዶለት ወደ ውስጥ እስኪገባ ድረስ ወደ ውስጥ ለመግባት የተዘጋጀውን ሰው ሁላችሁም በሃይማኖታችሁ ጸልዩ  እግዚአብሔር ከሞት እንደሚነሳ ነግሮኛል በማለት ሲናገር ተስተውሏል ፤ ይህም ወሬ ውስጥ ሀዘን ላይ ለተቀመጡት ሰዎች ዘንድም ደርሷል ፤ እውነት የመሰለው በርካታ ነው ፤ እንደ አልአዛር ከሞት እንዲነሳ የሚፈልግም ሰው እንደዛው …. በቦታው ላይ የነበረ ሰው ለዚህ ምስክር ነው፡


ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ መለስ ትዘረጋለች እንዳይባል ሰጋን

ይህ አምልኮ ነው ወይስ ሐዘን? ወደ የት አያመራን እንደሆን እናስብበት!! ሲጀመር ይህ ሀዘን በዛ ብለን ነበር ፤ መጨረሻው ይህ ሆኖ አረፈው ፤ በማን ይፈረዳል? ሀዘንም ይሁን ደስታ መጠኑን ማለፍ የለበትም ፤ ሁላችንም ሟች ነን ፤ በህይወት ለሚለየን ሰው አግባብ ባለው መንገድ ሀዘናችንን መግለጽ ይገባል ፤ ነገር ግን መስመር ከሳተ አደጋ አለው ፤ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴዎቹ ይህ ይመጣል ብለው ላያስቡ ይችላሉ ፤

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ  ጥሩ ከሚባሉ የአፍሪካ መሪዎች ግንባር ቀደም ናቸው ፤ አሁን እግዚአብሔር ፈቅዶ  በሞት ተለይተውናል ፤  እሳቸውን የመመለስ አቅም የሌለውን እንባ ከምናፈስላቸው ይልቅ ሀገራችን ቅን ፤ አስተዋይ ፤ አርቆ አሳቢ ፤ ህዝብን የሚያከብር ፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያደረበት ፤ ችግሮችንን የሚፈታ ፤ ማስተዋልና ጥበብን ተሰጠው መሪ እንዲሰጠን ብንጸልይ መልካም ነው፡፡

Tuesday, August 28, 2012

“መንግስት በአደባባይ የሚሰራቸውን ስህተቶች ቤተክርስትያን የእርምት እርምጃ እንዲወስድ የጠየቀችበት ጊዜ የለም” አቡነ ጢሞቲዎስ

  •   “የቤተክርስቲያን መሪዎች መንግስት እንዳይነቀፍ ብለው ቤተክርስትያኒቱና ክርስትያኖች መብታቸው ሲነካ ዝም ብለው ካዩ የእግዚአብሔርን አደራ አልጠበቁም ፤ መንግስትንም ባለመምከራቸው ጎዱት እንጂ አልጠቀሙትም” አቡነ ጢሞቲዎ
  •    “ከእግዚአብሔር የመጣው መዓት እግዚአብሔር መዓቱን እስኪመልሰው ድረስ ከመጸለይ በስተቀር ምንም ለማድረግ አይቻልም” አቡነ ጢሞቲዎ
  •   “መንግስት ሃይማኖታችሁን ልንካ ካለ ግን ለሃይማኖታችሁ ፤ ለክብራችሁ ለመብታችሁ መሟገት እንዳለባችሁ እመክራችኋለሁ” አለቃ አያሌው ታምሩ
  •  “እውር ገደለ ታሰኝኛለህ እንጂ አንተን እዚህ እደፋ ነበር፡፡” ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም ለአለቃ አያሌው ታምሩ የተናገረው
(አንድ አድርገን ነሐሴ 22 2004 ዓ.ም)፡- ከዛሬ 12 ዓመት በፊት ህዳር 8 1992 ዓ.ም አቡነ ጢሞቲዎስ ከ”ምኒልክ መጽሄት” ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ዘወር ብለን ለናንተው ለማቅረብ ወደድን ፤ ይህ መጽሄት በጊዜው ለአቡነ ጢሞቲዎስ ያቀረበላቸው ጥያቄና እሳቸው የሰጡት መልስ ጥቂቱን አሁን ካለንበት ሁኔታ ጋር ምን እንደሚመስል ለማየት እንሞክራለን ፤  በጊዜው አቡነ ጢሞቲዎስ የቅድሥት ሥላሴ  መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሃላፊ ሆነው ያስተዳድሩ ነበር፡፡

Sunday, August 26, 2012

ድህረ አቡነ ጳውሎስ ሰዎች ምን ይላሉ?


  • “ስለ ሁሉም ግን መስማትና ማመዛዘን የሚችል አባት እንዲሰጠን ጸሎት ይዘናል” የተሀድሶ አቀንቃኝ ፊት አውራሪ 
  •  “ሞት ርስታችን ነው ፤ ጉዳዩ የቅደም ተከተል ነው ፤ የአቡነ ጳውሎስ ሞት ባያስደስተኝም  እግዚአብሔር ግን ይችን ቤተክርስትያን አሳረፋት” አንድ ሊቀ ጠበብት አባት

(አንድ አድርገን ነሐሴ 21 2004 ዓ.ም )፡- ባሳለፍነው ሳምንት በተከሰቱት ሁለት ትልልቅ ክስተቶች ላይ ሰዎች ትንሽ የመደናገጥ ስሜት ተፈጥሮባቸው ተስተውለዋል ፤ አንዱ ክስተት የአቡነ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ነበር ፤ የፓትርያርኩ ሞት ከተሰማ ጀምሮ በርካታ ሰዎች ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ወደ አዲስ አበባ ገብተው ነበር ፤ የፓትርያርኩን ስንብት ላይ የአርመን ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን 3 ሊቃነ ጳጳሳት ፤ 2 የግሪክ ኦርቶዶክስ  ሊቃነ ጳጳሳት ፤ በተጨማሪ በአሜሪካ ኒውስተን ዩኒቨርሲቲ 4 ተወካዮችን ጨምሮ የግብጽ ኮፕት ቤተክርስትያን 10 ሊቃነ ጳጳሳት ፤ ከህንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን 5 አባላት ያሉት ቡድን ፤ የአለም አብያተ ክርስትያናት ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ ዶ/ር ኦላቭ እና 3 ሊቀ ጳጳሳት ፤ የአፍሪካ አብያተክርስትያናት ጸሀፊ  ዶ/ር አንድሪ ካራቫጋ እንዲሁም የዓለም ሀይማኖት ለሰላም 4 ሊቀጳጳሳት የአቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነስርዓት ላይ ለመታደም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል  ተገኝተዋል፡፡

Thursday, August 23, 2012

ተፈጸመ

የመጨረሻውን ስንብት ለማየት ይህን ይጫኑ

(አንድ አድርገን ነሐሴ 17 2004 ዓ.ም)፡- የብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ስርዓተ ቀብር መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተከናወነ ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ፤ የህዝብ ተወካች ምክር ቤት አፈጉባ አባ ዱላ ገመዳ ፤ ምክትል አፈጉባዬ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ፤ የአኅት ቤተክርስትያን አባቶች ፤ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ መንግስት አምባሳደሮች ፤ እና የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት በዛሬው እለት ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል ፡፡

ትላንት ማታ በሰረገላ ታጅቦ ከመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል በርካታ በብጹዓን ጳጳሳት በክቡራን ሚኒስትሮችና የመንግስት ባለስልጣናት ፤ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፤ በሊቃውንተ ቤተክርስትያን በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ፤ በአዲስ አበባ ፖሊስ ሰራዊት ባንድ ፤ በምዕመናንና በምዕመናት በክብር ታጅቦ መሄዱ ይታወቃል ፤ ረቡዕ ለሊት ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ እስከ ንጋቱ ድረስ ለሊቱን በሙሉ ጸሎተ ማህሌት ሲከናወን አድሯል ፤ ንጋት 12፡30 ላይ አስከሬኑ ባለፈበት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል በብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና አኅት አብያተክርስትያን ተወካዮች ባሉበት ስርዓተ ቅዳሴው ተከናውኗል ፤ ጸሎቱ እንዳበቀ የቅዱስነታቸው አስከሬን በክብር ታጅቦ ወደ አውደ ምህረት ወጥቷል በተዘጋጀለት ቦታ ላይ ለሰዓታት አርፏ ፡፡

የወጣው መርሀ ግብር በተቀመጠለት ሰዓት በአግባቡ በማከናወን ዛሬ ነሐሴ 17 ፤ 2004 ዓ.ም የብጹዕ ወቅዱስ ደ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የአለም የአብያተክርስትያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፤ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ፤ የዓለም ሰላም አምባሳደር ስርዓተ ቀብር ከቀኑ 7፡30 ተፈጽሟል፡፡

“አንድ አድርገን”፡- የአባታችንን ነፍስ እግዚአብሔር ከአብርሀም ከይስሀቅ እና ከያቆብ ጎን ያሳርፍልን 

የአቡነ ጳውሎስ ሽኝት በፎቶ


Wednesday, August 22, 2012

የአቡነ ዮሀንስ ነገር



(አንድ አድርገን ነሐሴ 17 2004 ዓ.ም)፡-በትላንትናው እለት የአቡነ ጳውሎስን አስከሬን ከሆስፒታል እስከ ጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ አጅበን ከመጣን በኋላ ቀጥታ ወደ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት ነበር ያመራነው ፤ በጊዜውም ቅዳሴ ሳይገቡ በመድረስ ቅዳሴ ማስቀደስ ችለን ነበር ፤ በቅዳሴው ላይ የአቡነ ጳውሎስ ፤ የመለስ ዜናዊ እና የአቡነ ዮሃንስ ስም ተጠርቶ ነፍስ ይማር ለሶስት ጊዜ ተብሎ ነበር ፤ ቅዳሴው ካለቀ በኋም ከአቡነ ጳውሎስ ሞት ቀጥሎ አቡነ ዮሃንስ አርፈዋል በማለት በአውደ ምህረት ላይ ተነግሯል ፤ እኛም ይህን ይዘን ከሰዓታት በኃላ ትላንት ማታ ላይ አቡነ ዮሃንስ ማረፋቸውን ገልጸን ጽፈን ነበር ፤ ነገር ግን ከወደ መቀሌ እንዳረጋገጥነው አቡነ ዮሃንስ በህይወት እንዳሉ ለማወቅ ችለናል ፤  በመኖሪያ ቤታቸው ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል አባ ፍሬምናጦስ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ ፤


ታቦት ወጥቶ እስኪገባ ፤ ቅዳሴ ተጀምሮ እንከሚያልቅ የገብረእግዚአብሔር(መለስ ዜናዊ) ፤ አቡነ ጳውሎስ ፤ አቡነ ዮሀንስ ስም ተጠርቶ ነፍስ ይማር ተብሏል ፤ በአቡኑ ሞት እንባቸውን ያፈሰሱም በጊዜው ነበረ ፤ ይህ ነገር የተነገረው በሺህ ለሚቆጠር ሰው ነው ፤ እኛም ይህን ሰምተን በጊዜው መጻፋችን ስህተት መስሎ አይታየንም ፤ ችግሩ ያለው ከአስተዳዳሪው እንጂ ከእኛ አይደለም ፤ አሁንም የአቡነ ዮሀንሰ ቀብር መቼ ነው እያለ ሰው እያወራ ይገኛል ፤ ማንም ኦፊሺያሊ ያስተባበለ አካል ስለሌለ ኢንተርኔት ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች በእንጦጦ ኪዳነምህረት የነበሩ እናቶችና አባቶች እንደሞቱ ነው የሚያውቁት፡፡ በጊዜው በአውደ ምህረት ላይ ለህዝብ የተነገረን ዜና ማነው ለማመን ከሶስተኛ አካል እማኝ የሚፈልግ? ለዛውም ቤተክርስትያን … 

አብያተ ክርስትያናት የመረጃ ምንጫቸው ምንድነው ?

የአቡነ ጳውሎስ አስከሬን እንደ አቡነ ሺኖዳ በመስታወት ሬሳ ሳጥን ቤተክህነት ደርሷል

Photographer:- LAMBDA


























Tuesday, August 21, 2012

የአቡነ ጳውሎስ የቀብር ስርዓት እና የመለስ ዜናዊ አስከሬን አቀባበል



  • የአቶ መለስ ዜናዊ አስከሬናቸው ቢያንስ ለአንድ ሳምንት በብሔራዊ ቤተመንግስት ይቆያል ፤ ህዝቡም በቦታው በመገኝት ይሰናበታቸዋል ተብሎ ይጠበቃል

(አንድ አድርገን ነሐሴ 16 ፤ 2004 ዓ.ም) ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አስከሬን ከባልቻ ሆስፒታው ወደ ሐያት ጠቅላላ ሆስፒታል መሸጋገሩ ይታወቃል ፤ ቀድሞ የታሰበው ብጹእነታቸው አስከሬን ረቡዕ ከሰዓት ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ከተወሰደ በኋላ ጸሎት ተደርጎለት ከመንበረ ፓትርያርክ ወጥቶ ወደ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስትያን በሰረገላ በመውሰድ ለሊቱን ሙሉ ጸሎት በማድረግ ጠዋት ቅዳሴ በማድረግ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ግድም ወደ ውጭ አውጥቶ ስርዓቱን ለማከናወን ታስቦ ነበር ፤ ነገር ግን አሁን በደረሰን መረጃ የብጹእነታቸው አስከሬን ዛሬ ጠዋት 3 ሰዓት ከሐያት ሆስፒታል ወደ መንበረ ፓትርያርክ በመውሰድ የከሰዓት በኋላ ቅዳሴውን በማድረግ አመሻሹ ላይ ወደ ቅድስት ስላሴ እንደሚሄድ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በነገው እለት የቀብር ስነስርዓታቸው እንደሚፈጸም ይታወቃል ፤ 

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ተከትሎ የከሚሴ የጦር መሳሪያ ግምዣ ቤት በውሀቢያ ሙስሊም አክራሪዎች ተዘረፈ



·        "We are very glad about Meles' death. Ethiopia is sure to collapse," Sheikh Ali Mohamud Rage, the spokesman for Al Shabaab told Reuters.

(አንድ አድርገን ነሐሴ 15 2004 ዓ.ም)፡- ቀናት አልፈው ቀናት ሲተኩ የሚሰማው እና የሚታየው ነገር ማህበረሰቡን እያስገረመው መጥቷል ፤ አዲስ ቀን በመጣ ቁጥር አዲስ ነገር ጠባቂ ጆሮዎች ተበራክተዋል ፤  አሁን የሰማው ግን አስደንጋጭ  ነው ፤ ሀገሪቱ በአሁኑ ሰዓት መተንፈስ እስኪሳናት ድረስ ውጥረት ውስጥ ገብታለች ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ፤ የፓትርያርኩ ዜና እረፍት እና ቀጣይ ከመንግስት እጅ ነጻ የሆነ የፓትርያርክ ምርጫ ፤ የተለያዩ ባለስልጣናት የጤና መታወክ ፤ በሙስሊም ማህበረሰቦች ዘንድ የተነሳው የመጅሊስ ይውረድ ጥያቄ ፤ ጥያቄውን መሰረት በማድረግ መንግስት ያሰራቸው የሙስሊም ተወካዮች ፤ ሞያሌ አካባቢ የተነሳው ከ30 ሺህ ሰዎች በላይ ወደ ጎረቤት ሃገር የተሰደዱበት የጎሳ ግጭት ፤ በአዲስ አበባ አንዋር መስኪድ ውስጥ በየጊዜው የሚነሳው ተቃውሞ ፤ በየቦታው ጊዜ የሚጠብቁ የታፈኑ የመብት ጥያቄዎች ፤ በይበልጥ በዋልድባ ገዳም ተፋጠው ያሉት የአካባቢው ምዕመናን እና የመንግስት ወታደሮች ሀገሪቱ ወደ የት እየሄደች መሆኑ  አመላካች ምልክቶች ናቸው ፡፡ 

በቅርቡ በአንዋር መስኪድ በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት በእለተ ቅዳሜ ከ700 በላይ ሰዎች በአዲስ አበባ እና በፌደራል ፖሊስ አባላት አማካኝነት መታፈሳቸው እና የይቅርታ ሰነዱን ፈርመው መውጣታቸው ይታወቃል ፤ ይህ እንዲህ እያለ ሙስሊም ማህበረሰብን ወክለው ከመንግስት ጋር ሲነጋገሩ የነበሩ 18 የሚያህሉ መሪዎቻቸው በፖሊስ ተይዘው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ፖሊስ ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ዳግም ወደ እስር ቤት መልሷቸዋል፡፡ 

አሁን ግን ከወደ ከሚሴ የተሰማው ዜና በአካባቢው የሚገኝን የመንግስት የጦር መሳሪያ ግምዣ ቤት ሙሉ በሙሉ በአካባቢው አክረሪ ሙስሊም ማህበረሰብ በተለይ ውሀቢዝምን የሚያቀነቅኑ ወጣቶች እንደተዘረፈ መረጃው ደርሶናል ፤ እዚህ አካባቢ ያለ የአክራሪነት እንቅስቃሴ ጠንካራ መሰረት እንዳለው ይታወቃል ፤ ለዓመታት በፊት ወደ ጊሸን ማርያም ሲጓዙ የነበሩ ምዕመናን ላይ እነዚህው ወጣት ውሀቢያ እንቅስቃሴ አራማጆች የተኮስ እሩምታ ማውረዳቸው ይታወቃል ፤ ሲጀመር ከዓመት በፊት መንግስት ውሃቢዝምን በተመለከተ በርካታ መረጃዎች እጁ ውስጥ እያሉት በጊዜው እርምጃ መውሰድ ሳይችል ቀርቶ ጉዳዩን እዚህ ደረጃ እንዲደርስ የበኩሉን አስተዋጽዎ አድርጓል ፤ ይህ ማለት ሀገሪቱ ያለችበትን ያለመረጋጋት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከሳምንታት ወይም ከወራት በኋላ በአካባቢው ምን አይነት ነገር ሊፈጠር እንደሚችል አመላካች ምልክት ነው ፤ አክራሪዎቹ አሁን ያለውንም ክፍተት ለመጠቀም ያሰቡ ይመስላሉ ፤ አሁን መሳሪያ ያነገተ የተቃውሞ ኃይል አማካኝነት መብታችንን እናስከብራለን በማለት በቅርባቸው የሚገኝውን የጦር መሳሪያ ግምጃ ቤት ዘርፈዋል ፤ መሳሪያ የታጠቀ የውሀቢዝም ሰራዊት በመላ ሀገሪቱ ለመነሳት እያኮበኮበ የሚገኝበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ፤ በዚህ መሀል መጀመሪያ ተጎጂዎች ከደሙ ንጹህ የሆኑ ዜጎች መሆናቸው አይቀሬ ነው ፤ አንድ መሳሪያ 30 ጥይት የመጉረስ አቅም አለው ፤ በአንድ ሰው አማካኝነት የብዙዎችን ነፍስ ሊነጥቁ መሳሪያዎችን አንድም ሳይቀር ዘርፈው ወስደዋል ፤ ይህ ጉዳይ መንግስት አንደኛ ለራሱ ህልውና ሲል ሁለተኛ ደግሞ ለሰላማዊው ህዝብ ብሎ የተዘረፈውን መሳሪያ ለቅሞ መመለስ ካልቻለ አደጋው ወደፊት እየሰፋና ከቁጥጥሩ ውጪ ሊሆን ይችላል፡፡

 አሁንም ጊዜው አልረፈደም ከዓመታት በፊት ቤተክርስትያኖች ላይ ሲፈጸም የነበረው ጉዳት አሁን በመሳሪያ በታጠቁ ሰዎች አማካኝነት ዳግም እንደማይፈጸም ምንም ማረጋገጫ የለንም ፤ ይህ የተዘረፈው መሳሪያ ወደ ስራ ካስገቡት የበርካቶችን ደም የሚፈስበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል ፤ የሀገሪቷ ሰላም ሊያናጋ ይችላል ፤ ሰዎች በሰላም ወጥተው በሰላም እንዳይገቡ እንቅፋት ሊፈጥር ይችላል ፤ እንደ አልሻባብ አይነት ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ቡድኖች እንዲያድጉ እና ወደ ተሻለ ጥቃት የመፈጸም አቅማቸውን ሊያሳድግላቸው ይችላል ፤ በዚህ መሀል የመጀመሪያ ተጎጂዎች ከመንግስት ተቋማት ቀጥሎ በየአካባቢው የሚገኙ አብያተክርስትያናት እና ክርስትና እምነት ተከታዮች መሆናቸው አይቀሬ ነው ፤ ይህ መሳሪያ መጀመሪያ መንግስትን ለመቃወም እንደ ግብአት ሊጠቀሙበት ይችላሉ ፤ የመጀመሪያ አላማቸው ከተሳካለቸው ሁለተኛ ዓላማቸውን ለመገመት አያዳግትም ፤ ከሁለት ዓመት በፊት በአንድ ለሊት “አላህ ዋክበር” እያሉ በአንድ መሳሪያ 38 ቤተክርስትያኖች የተቃጡበት በርካቶችን ያፈናቀሉበት ድርጊት ትዝ ሊለን ይገባል ፤ የዚህ ሁሉ ማስረጃ በእጁ እያለ ሰዎችን ለማስተማር መንግስት የሄደበት መንገድ አሁን አላስፈላጊ ዋጋ ሊያስከፍለው ይችላል ፤ በጅማ አካባቢ ጉዳት ያደረሱት አክራሪዎች የእያንዳንዳቸው መረጃ  ቀርቦ ሳለ ህጉን ከማስፈጸም ይልቅ ትምህርት በመስጠት ብቻ የተለቀቁ በርካቶች ናቸው ፤ ተምሮ የሚቀየር ሰው እንዳለ ሁላ የወንዝ ድንጋይ የሆነ እድሜ ልኩን ውሃ ቢፈስበት ወደ ውስጡ የማይዘልቅ ጭንቅላት ያላቸው ፍጹም ጨለምተኛ አመለካከት የተጠናወታቸው ሰዎች በውስጣቸው እንዳሉ መንግስት አላስተዋለም ፤ ሁሉም ሙስሊም አክራሪ ነው አንልም ነገር ግን እምነቱን ሽፋን በማድረግ ሌላ አላማ ለማሳካት የሚንቀሳሱ ቡድኖች መኖራቸው ግን የማይታበይ ሀቅ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለሁሉም አደጋ ነው፡፡ መንግስት ያስብበት ፤ ሰላማችን በዋጋ የማንለውጠው ትልቁ ሀብታችን ነው፡፡

(ሁኔታውን ተከታትለን እናንተው ዘንድ እናቀርባለን)
ቸር ያሰማን    

MOGADISHU (Reuters) - Somali Islamist militants hailed on Tuesday the death of Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi as an "historic day" and said Ethiopia, which has troops inside Somalia, would now crumble.
"We are very glad about Meles' death. Ethiopia is sure to collapse," Sheikh Ali Mohamud Rage, the spokesman for Al Shabaab told Reuters.
Meles twice rolled his troops across the border to help crush Islamist insurgencies.
(Reporting by Feisal Omar; Editing by Richard Lough and Jon Hemming)

Monday, August 20, 2012

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ዛሬ ጠዋት በኢቲቪ ይፋ ሆኗል

  • የቀብር ስነ ስርዓቱ እስኪፈጸም ድረስ ብሔራዊ ሀዘን ቀን የሚንስትሮች ምክር ቤት አውጇል
  • የሀገሪቱ ባንዲራም ዝቅ ብሎ ይውለብለብ ተብሏል
  • የኮሙኒኬሽን ጉዳች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ በረከት ስምኦን ስለ መለስ ዜናዊ ሞት የሰጠው መግለጫ ለማድመጥ ይህን ይጫኑ
  • ነገሮች ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይሄዱ ከፍተኛ ስጋት አለ ፤ 
    ትንሽ ክፍተት የሚፈልገው የንግዱ ማህበረሰብ በዚህ አጋጣሚ የዋጋ ንረቱን አያባብሰውም ወይ ? የሚል ጥያቄ ለአቶ በረከት ቀርቦላቸዋል፡፡
  • ሀገሪቷን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አማካኝነት ለጊዜው ትመራለች፡፡
  • የተለያዩ መንግስታዊ ፤ መንግስታዊ ያልሆኑ መስሪያ ቤቶች ፤ ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ ኢምባሲዎች የሀዘን መግለጫቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡
  • ኢትዮጵያ ሬድዮ ድርጅት ለአንድ ሰዓት ያህል የዘፈን ክላሲካሎችን ሲያሰማ ቆይቷል ::
  • የቀብር ስነስርዓቱን በተመለከተ 7 አባላት ያሉት ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሟል  

    • BRUSSELS (Reuters) - Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi died on Monday night in Brussels, a spokesman for the EU executive said on Tuesday. For more information click here
    •  David Cameron said Ethiopian prime minister Meles Zenawi had set an example for the African regio
    • ''We are very glad about Meles' death. Ethiopia is sure to collapse," Sheikh Ali Mohamud Rage, the spokesman for Al Shabaab told Reuters. 
    • Ethiopian strongman and Western ally, Meles, dies
       
    • የኢቲቪ የመጀመሪያ ዜናን ለማድመጥ ይህን  






በአንድ ሳምንት ውስጥ ......



ፈጣሪ ሆይ ለአገራችን ለኢትዮጵያ መልካም የሆነ የእምነትም ሆነ የመንግስት መሪ ስጣት ፤ ለመለስ ዜናዊ ቤተሰቦች  እግዚአብሔር መጽናናትን ያድልልን ፤  ነፍስ ይማር