Sunday, June 3, 2012

የተሐድሶና ምንፍቅና አራማጁ ስራ አስኪያጅ ሆኖ ተሾመ

  • ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የአሜሪካ 3ቱ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆነ
(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 24/2004 ዓ.ም፤ ጁን 1/ 2012/READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በተሐድሶነቱ የሚታወቀውና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወ/ሮ እጅጋየሁን ተክቶ የፓትርያርኩ ቀኝ እጅነትን የተረከበው ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን በአቡነ ጳውሎስ ፈቃድ በአሜሪካ የሚገኙት የሦስቱም አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ መሾሙን ምንጮቻችን እየገለፁ ነው። ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በአሜሪካ ሥራ አስኪያጅነትን ሥልጣን ተረክቦ እንዲሠራ የተሾመው ኃ/ጊዮርጊስ በተሐድሶ እምነት አራማጅነቱ በግልጽ የሚታወቅና ዓላማዎቹን እና እምነቶቹን በተለያዩ የተሐድሶ ብሎጎቸ በይፋ በማስተላለፍ የሚታወቅ፣ ከዚያም አልፎ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ከተሐድሶዎቹ ብሎጎች ጋር በማገናኘት ደብዳቤዎቻቸው በዚያ እንዲስተናገዱ እና ምእመኑ ከንጽሕት እምነቱ ተናውጾ በኑፋቄ ትምህርት እንዲበከል ከፍተኛውን እንቅስቃሴ የሚያድርግ ግለሰብ መሆኑ ይታወቃል።
በአሜሪካን አገር “ዋይት ሐውስ ነው የምሠራው” በሚለው ማታለያው ከሲ.አይ.ኤ ጋር ግንኙነት እንዳለው በማስመሰል የዋሆች በማስፈራራት እና “የኢህአዴግ አባል ነኝ” በሚል ብዙዎችን ለማሳቀቅ እና ከእምነታቸውና ከቤተ ክርስቲን አገልግሎታቸው እንዲንራተቱ ለማድረግ በመጣር ላይ የሚገኘው ይኸው ግለሰብ አያሌ ሊቃውንት ባሉባቸው አህጉረ ስብከት የበላያቸው ሆኖ እንደፈቀደው እንዲፏንን እንደተለቀቀ ለመረዳት ተችሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በታሪክ እጅግ ሊያስመሰግነው በሚችል መልኩ በተሐድሶ ድርጅቶች እና አራማጆች ላይ የውግዘት ቃሉን ባስተላለፈ ማግሥት ቅዱስነታቸው ቀንደኛውን ተሐድሶ በአሜሪካ የሾሙበት ምክንያት የንፁሐን ኦርቶዶክሳውያንን ቅስም ለመስበር እንዲሁም ወደ ውጪ አገር ሰው በመላክ ሰበብ የሚያጋብሱትን ገንዘብ በታማኛቸው አማካኝነት ለማካሔድ በማሰብ መሆኑን ምንጮች አብራርተዋል።
በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስለ አቡነ ፋኑኤል የቀረቡት አቤቱታዎች በአጀንዳነት እንዳይያዙ፣ በመካከሉም በሚነሡበት ወቅት እልባት እንዳያገኙ ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ የከረሙት ፓትርያርኩ ይባስ ብለው ኃ/ጊዮርጊስን መላካቸው በሰሜን አሜሪካ የተጀመረውን ተቃውሞ የበለጠ ያጎላው ካልሆነ በስተቀር የሚፈይደው አንዳች ፋይዳ እንደማይኖር ይታወቃል።

ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁ
በአሜሪካ ሦስት አህጉረ ስብከት ሲኖሩ የዋሺንግተን ዲሲው በዋና ፀሐፊው በቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝ፣ የኒውዮርኩ በመ/ገነት ቆሞስ አባ ዘርዓ ዳዊት በርኼ፣ የካሊፎርኒያና አካባቢው ደግሞ በሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁ ሥራ አስኪያጅነት ሲመራ ቆይቷል።
ር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

12 comments:

  1. Qeeneu Leeinteteabi TsegaJune 4, 2012 at 1:41 AM

    It is really shame for our Patriarch to do such unlawful things on the church he is leading as the highest father of the church. We know Hailegiorgis when we were students in 6 kilo university. he was our friend. How ever I don't know what his mind was thinking at that time except his being spiritual friendship with us all. All of us were taught by ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁ and other true religious fathers. Why Abune Paulos is making this small kid to be on his fathers shoulder and on their religious service,I don't understand. Isn't there any one around abune Paulos to advice him his doings are not expected from any religious leader? No one can come near abune paulos except these tehadiso groups and money minded individuals who are pulling the patriarches mined as they want? is there no any shimagile who can do this for the sake of our church and advice the patriarch to come to his mind on deciding about church matter?

    ReplyDelete
    Replies
    1. Sometimes comments like this amazes me. What does shimagile has to do with this? The person is doing whatever possible to destroy our church purposely not by mistake. We have seen this for over 18 years or so now. He is doing his job. So can the shimagile stop him from doing his job? We don't need shimagle. We need determination to remove him from that position. We can use different methods to do that. One way is to stop being a financial source for him. This man is using our own money to destroy us. Let everyone I mean every orthodox believer stop giving money to the church. We can provide supplies like "ITAN, ALBASAT,etc.. but no money. Let us stop paying!!!! Let us create the awareness!!! Let us stop destroying our church through this man. Gol Almighty help us!!!

      Delete
    2. Qeeneu Leeinteteabi TsegaJune 4, 2012 at 6:32 AM

      ለአስተያየቴ መልስ ለሰጠኸኝ ወንድሜ ስለመልስህ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ነገር ግን እኔ በግሌ ሽማገሌ ጠፋ ወይ መካሪ አጥተው ነው ወይ ወዘተ… ያልኩበት የራሴ የሆነ አመለካከት ስላለኝ ነው፡፡ ይህም ብዙውን ጊዜ ቤተክርስቲያንን ከሚያስተዳድሩ አባቶች ፀባይ ተረዳሁት ነገር ቢኖር አብዛኞቹ በተለይም መትክክለኛው የምንኩስና ሕይወት ሳይሆን በአለም እየኖሩ አብያተ-ክርስቲያናትን የሚያስተዳደርሩት (ገዳማውያኑን መናንያን ቀርቤ ስላላየሁ አላውቅም ) መረታትን ፈጽሞ የማይፈልጉ በጣም ኢምንት በሆነች ነገር ልቦናችው የሚጠነክር(በተለይም በስልጣናቸውና በመሪነታቸው በገንዘብ ጉዳይም የመጡባቸው ሲመስላቸው አሁን አሁን ደግሞ በዘር ጉዳይ) ና በዚያው ልክ ደግሞ በቀላል ምክርና ውይይት ምልስ የሚሉ ልቦናቸው ለበጎ መካሪዎች ስስ የሆነውን ያህል በክፉ መካሪዎችም ለመሳሳት የዛኑ ያህል የተከፈተ እንደሆነ በጥቂቱ የተረዳሁ ስለማሰለኝ ነው፡፡ አቡነ ጳውሎስም ከዚህ አይነቱ ባህርይ ውጭ የሚሆኑ ስለማይመስለኝ በዚህ ባለቀ ዕድሜያቸው ወገኔ ነው የኔው ነው ከሚሉት ክፍል ምነው እውነቱን የተረዳና የሚመክራቸው ሽማግሌ ጠፋ ወይ ማለቴ ነው፡፡
      በጎናቸው ያሉትን አባቶች እንደ ስልጣን ተጋፊዎቻቸው የሚቆጥሯቸውና የማይሰሟቸው ከሆን በምንም ነገር የማየቀናቀኗቸው ሰዎች የሉም ወይ እነሱ ቢመክሯቸው ምናልባት እንዳልኩት ሊረዱ ይችላሉ ብዬ ነው፡፡ በትንሹ የሀይለጊዮርጊስን ሹመት ትክክል አለመሆን ከሱ የተሸሉ ሊቃውንት ባሉበት መደረጉ ለማንም ሰው በቀላሉ ማስረዳት ሚከብድ አይደለም፡፡ ምናልባት የሳቸውን አላማ እኔ ባላውቅም ከግምት የማይገባ አላማ ዘው ዋናውን ቤተክርስቲያን ጉዳይ ቸል ብለውታል ብዬ ስለማስብ የተሸለ ስራ መስራት እንደሚችሉ የሚያስረዳ አዋቂ ጠፋ ወይ ማለቴ እንደሆና ተረዳልኝ፡፡
      በመጨረሻ አንተ Let every one I mean every orthodox believer stop giving money to the church. We can provide supplies like "ITAN, ALBASAT,etc.. but no money. ባልከው አልስማማም፡፡ ለምን ብትለኝ ችግሩ ገንዘብ ለቤተክርስቲያናችን ማስገባታችን ሳይሆን የቤተክርስቲያናችን የገንዘብ አስተዳደርና አጠቃቀም ነው ብዬ ስለማምን ነው፡፡ አስተዳደሩን ዘመናዊ ዘመኑን ዋጀ ካላደረግን ገንዘብ ባናስገባና ቁሳቁስ ብቻ ብናቀርብ እያየነው ካለነው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ዛሬ ካዝናዋን እያራገፉ ወደኪሳቸው እከተቱ ያሉት ሰዎች ረሷን እንጻ ቤተክርስቲያኗን ሸጠው ለመሄድዳ ኋላ የሚሉ አይደሉም(የባቦ ጋያንና የጥምቀተ ባህሩን ጉዳይ ልብ ይሏል)፡፡ በየአድባራቱ በከልማት ስም በግብዣ ሸበብ በእድሳት ምክንያት እየተባለ የሚባክነውን ገንዘብ ማስተካከል ካልተቻል ቁሳቁሱም ይሸጣል፡፡ አገልግሎቱም በየምክኝያቱ ይታጎላል፤ ይህ ደግሞ ባሰ ጥፋት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቁሳቁሱንስ ገዝተን እናስገባ አልክ፤ግን የአገልጋይ ካህናቱስ ደሞዝ በቁስ ልናደርገው ይቻለናልን፡፡ እንደምናስበው ቀላል ሆኖ አላገኘሁትም ግን አስተዳደሩ ላይ ከአትቢያ ጀምሮ ማጥራት አድርገን መስራት ከቻልን በእግዚአብሄር ርዳታ ልናስተካክለው እንችላለንና እስቲ በያለንበት በጎ ሆነውን ሁሉ ከቀና ክርሲቲኖች ጋር በመመካከር ለመፈጸም እንትጋ፡፡

      Delete
  2. It's really shame. But whatever they did, we have 2 belive that our churh could never destruct: because it's made on the blood of God.

    ReplyDelete
  3. this is amaizing information for me. pls andadirgen keep it up

    ReplyDelete
  4. degmo yesim atfinetun sira jemerachu esti nigerugne yih deakon tehadiso yehonebetin ande netib awtitachu asredu enem betehadisonetu lireda.

    ReplyDelete
  5. 'TO Stop giving money to the church in cash and Provide only supplies like "ITAN, ALBASAT,etc..,' It looks a good way to explain your disagreement and discomfort with the administrative bodies. But at the same time the fathers and other workers who serve the church will be affected (they can't get their salary) and other expenses needed to run the churches (light, phone, ...expenses)will be in short. If this is the only solution, other mechanisms have to be created to get money and pay.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Thank you for partialy supporting the idea of not financing our own distruction. I understand the fathers and others working in the church will be affected. The thing is:
      1. They get paid as long as the church exists. If not they can't.
      So isn't it better to emphesize on the church's existence first? We need to be risk takers. In addition these people are part of us and they should be ready to take the risk.


      On the other hand if we think this is too much for them we can come up with some ideas to solve the financial problem the fathers may face as a result of this action.

      I think orthodox believers all over the world are more than happy to contribute money rather than doing nothing but watching our belif and church totaly destroyed.

      The question is can we manage this kind of project. It is going to be a huge responsibility. Do we have someone ready to take the responsibilty? What about accountablity? etc., etc......

      Delete
  6. በጣም የሚያሳዝን ዘመን ላይ ደረስን ጎበዝ! ስንት ለቃውንት ባላት ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ማንም ይፈንጭባት? አባ ጳውሎስ እባክዎ ስለ እግዚአብሔር ብለው ቤተ ክርስቲያናችን ላይ አይቀልዱ ግድ የልዎትም ለዘለዓለም የሚኖሩ ሰው አይደሉም እባክዎ ንስሐ ይግቡ!! ወይም አርፈው ይቀመጡ እርስዎ የሚፈልጉት ገንዘብ ነው በጉቦም በሌላም መልክ ያገኙታል ግን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ያስቡ ስንት ሊቃውንት በአስተዳደር ... ልምድ ያላቸው እያለሁ በመናፍቅነት የሚታወቅ ወጠጤ ልቡ በክህደት ያበጠ ሰው መላክዎ ለቤተ ክርስቲያኑ ጉዳይ እንደሌልዎ ነው የሚያመለክተው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን አንድ አድርጎ የሚመራት አባት ይሰጠናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን እስከዚያው ግን እኛ ልጆቿ እያለም ማንም አይቀልድባትም ለእርስዎ ወዮ ወዮ ወዮ የተዋህዶ አምላክ ፍርድ ይሰጣል እሱም ወደ መጣበት ይመለሳል

    ReplyDelete
  7. በልዎ ለአግዚአብሔር ግሩም ግብረከ

    ReplyDelete
    Replies
    1. DINGEL MARIYAM TAGALITACHIWALECH KEGNA YEMETEBEKEW METSELEY NEW YEKIRSITEYAN HAYILU TSELOTU NEW

      Delete
  8. I'm no longer certain where you are getting your info, however good topic. I must spend a while studying more or figuring out more. Thanks for magnificent information I used to be looking for this info for my mission.
    My webpage ... GFI Norte

    ReplyDelete