Tuesday, June 12, 2012

በርካታ ቤቶችን የበላው የሐዲያ ቃጠሎ እስካሁን መንስዔው አልታወቀም


(*** Reporter ***):- በደቡብ ክልል ሐዲያ ዞን በታህሳስ ወር በተለያዩ ቀናት 140 ቤቶችን የበላው የእሳት ቃጠሎ መንስዔ በእስካሁኑ ሒደት አልታወቀም፡፡ በዞኑ ሰሮ፣ ሻሼጌ፣ ጌሌቦ፣ ሚሻና ጊቤ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ቤቶች በታህሳስ ወር ውስጥ በ15 ተከታታይ ቀናት ድንገተኛ እሳት እየተነሳ መውደማቸው ይታወሳል፡፡ የቃጠሎው ሁኔታ አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተ ከመሆኑም በላይ፣ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አካባቢውን እንዲጎበኙ ምክንያት ሆኗል፡፡

የዞኑ ፖሊስ ባልደረባ ኢንስፔክተር ክብነህ አበበ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አቶ ሽፈራውአካባቢውን በጐበኙበት ቀንም ቤቶች ተቃጥለው ነበር፡፡ ፖሊስ አስፈላጊውን ክትትልናምርመራ እንዲያደርግ አቶ ሽፈራው ለዞኑ ፖሊስ መመርያ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መሠረት ፖሊስ ደፈጣ በማድረግ የእሳቱን መንስዔ ለማወቅ ጥረት ቢያደርግም፣ የተገኘ ፍንጭ አለመኖሩን ኢንስፔክተር ክብነህ ገልጸዋል፡፡ ሰው ነው የሚለኩሰው? የሚለውን ለማጣራት ሙከራ አድርገን ነበር፡፡ ሰው ስለመለኮሱ ግን መረጃዎች ልናገኝ አልቻልንም፤ ሲሉኢንስፔክተሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ 

ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ድንገት ሳይታሰብ ከመኖርያ ቤት (ጎጆ) ምሰሶ ሥር እሳት ይነሳና ድንገት ቤቱን ሙሉ በሙሉ ያቃጥላል፡፡ የዞኑ ነዋሪዎች ክስተቱን ቁጣ ነው፤ የፈጣሪ ተግሳጽ ነው፤ በማለት እንደየ እምነታቸው በየማምለኪያ ስፍራዎች በመገኘት ፈጣሪያቸውን ተለማምነዋል፡፡ የእኛ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ይበዛበታል፣ አሁን ደግሞ የተፈጥሮ ቃጠሎ እየተከሰተ ነው፤ ሲሉ በዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት የሚሠሩ አንድ ሠራተኛ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡  አደጋ ለደረሰባቸው ነዋሪዎች ጊዜያዊ መጠለያ፣ ምግብና አልባሳት እየተሰጠ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ ገልጿል፡፡ በአሁኑ ወቅት ቃጠሎው ጋብ ቢልም ነዋሪዎቹ እሳቱ ተመልሶ እንደማይመጣ ማረጋገጫ አላገኙም፡፡ ክስተቱን እንዲያጣራ ኃላፊነት የተሰጠውየዞኑ ፖሊስም በእስካሁኑ ሒደት መንስዔውን ማረጋገጥ ያልቻለ ከመሆኑም በላይ፣ ከሚመለከታቸው ምርምር ተቋማትም የተሰጠ መግለጫ የለም፡፡



እሳቱ ከሰማይ ላይ እንደ ዝናብ ሲዘንብ የነበረበት ጊዜ የታህሳስ ወር ሲሆን በስልጤ ዞን የምትገኝው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን የተቃጠለችበትና  የወራቤ ደብረ ኃይል ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስትያንን በአክራሪ ሙስሊሞች ለማቃጠል የተሞከረበት ፤ ቤንዚልና ክብሪት የያዙ ሰዎች እጅ ከፍንጅ በውድቅት ሌሊት የተያዙበት መሆኑ ይታወቃል ፤ በጊዜው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያንን ያቃጠሉት የቡድን መሪያቸው በሳምንት ጊዜ ውስጥ በኤሌክትሪክ አደጋ ህይወቱ እንዳለፈ እና ሁለተኛው በመሰል አደጋ ህይወቱን እንዳጣ የወራት ትውስታችን ነው 

No comments:

Post a Comment