(አንድ አድርገን ታህሳስ 17 2004 ዓ.ም) ፡-የቤተክርስትያናችን ፈተና መልኩን እየቀየረ መጥቷል ፤ ፈተናችንም ከብዷል ፤ የዛሬ አንድ ወር ገደማ አክራሪ ሙስሊሞች የቅድስት አርሴማን ቤተክርስትያን ሲያቃጥሉብን ፤ ሀዘናችን ከልባችን ሳይወጣ ፤ መንግስትም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዞ ሄዶ ፍትህ ሳናገኝ ፤ ሌላ ትንኮሳ ተካሂዶብናል ፤ ፤ የሙስሊም ማህበረሰቦች ያሉበት አንዳንድ ቦታ ላይ ቤተክርስትያን መስራትም ሆነ በተሰሩት ላይ አምልኮተ እግዚአብሔር መፈፀም እየከበደ ነው፡፡
Tuesday, December 27, 2011
Monday, December 26, 2011
የዮሐንስ ወንጌል መቅድም (የመጀመርያ ሳምንት ጥናት)!!
ተከታታይ ሳምንታዊ መርሐ ግብር
(አዘጋጅ፡- ገ/እግዚአብሔር ኪደ)
በአዳራሽ ገብቶ ወደ እልፍኝ ማለፍ፣ እርካብ ተረግጦ ወደ ኮርቻ መውጣት እንደሚመች ሁሉ እኛም ለዛሬ መቅድሙን ተምረን ከቀጣይ ሳምንት በኋላ ወደ ወንጌሉ እንሄዳለን፡፡
1. የጸሐፊው ዜና መዋእል በአጭሩ፡-
የዮሐንስ ወንጌል ጸሐፊ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ነው /ቅዱስ ኤጲፋንዮስ/፡፡ ዮሐንስ ማለት “ጸጋ እግዚአብሔር” ማለት ነው፡፡ አባቱ ዘብዴዎስ የሚባል የሲዶና ሀገር ገሊላዊ ሲሆን ዓሣ አጥማጅ ሳለ ከወንድሙ ከያዕቆብ ጋር ሰዎችን እንደ ዓሣ በወንጌል መረብ ከዚሁ ዓለም ባሕር ለማጥመድ ተጠራ /ማቴ.4፡21/፡፡ እናቱም ማርያም ባውፍልያ ትባላለች /ማቴ.28፡1/፡፡ ወንድሙ ያዕቆብ በ44 ዓ.ም በሄሮድስ ዘአግሪጳ ተገደለ /ሐዋ.12፡1-2/፡፡ ብዙ ቅጽል ስሞችም አሉት፡- የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት በመግለጡና ለጌታችን ባለው ቅንዓት ባሳየውም የኃይል ሥራ “ወልደ ነጐድጓድ” /ማር.3፡17/፣ የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት ስለሚናገር “ታዖሎጐስ- ነባቤ መለኰት”፣ ኃላፍያትንና መጻእያትን ስለሚናገር “አቡቀለምሲስ-ረአየ ኅቡአት- ባለ ራዕይ”፣ እንዲሁም የጌታን ጸዋትወ መከራ አይቶ ፊቱ በኃዘን ተቋጥሮ ይኖር ስለ ነበር “ቁጹረ ገጽ- ፊቱ በኃዘን የተቋጠረ” ይባላል፡፡
የሀዋሳን ህዝብ ያስለቀሱ ሰው ለአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ተሾሙ
- “አባ” ናትናኤል ለአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ተሾሙ፡፡
(አንድ አድርገን ፤ ታህሳስ ኪዳነ ምህረት ፤2004 ዓ.ም)፡- አሁንስ እኛም ጆሯችን ጥሩ ነገር ናፈቀው ፤ ባለፈው ዓመት የሀዋሳን ህዝብ ሲያስለቅሱት የነበሩት ደብረ ገነት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ከቀናት በፊት ለአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ከቤተክህነት ተሾሙው ነበር ፤ ነገር ግን ህዝቡ እኝን አባት አስተዳዳሪ አድርገን አንቀበልም ብሎ እሳቸው በእግራቸው ቢመጡም በኮንትራት ታክሲ ከቤተክርስያን እንዳባረሯቸው ከቀናት በፊት ዘግበን ነበር፡፡ የበፊቱን ዘገባ ለማንበብ ይህን ይጫኑ
Sunday, December 25, 2011
ፌደራል ፖሊስ መረጃ ሰጥተዋል ያላቸውን ሰዎች ከቤተክርስትያኗ ውስጥ እያሰረ ነው
(አንድ አድርገን ታህሳስ 15 2004 ዓ.ም) ፡- በደብረዘይት ከተማ የሚገኝው ታቦት ማደሪያ በአቡነ ጳውሎስ ቀጭን ትዕዛዝ ቤተክርስያናችን ካለት የመሬት ይዞታ ላይ ተቆርሶ ለባለሀብት በመሸጥ ሪዞርት እየተሰራበት መሆኑንና የሚሰራው ሪዞርት ላይ ትንኮሳ እንዳይፈጠርበት በማለት ቀን ከለሊት በፌደራል እና በከተማው ፖሊሶች እየተጠበቀ ይገኛል፤ ዛሬ ለጥምቀት ታቦት የሚያርፍበትን ቦታ መሸጥ ከጀመሩ ነገ ከዚህ የከፋ ነገር እንደማያደርጉ ምን ማረጋገጫ አለን? ፡፡ለመሆኑ የቤተክርስትያኗ መሬት ላይ የማዘዝ ስልጣን ያለው ማነው? ፓትርያርኩ መሬት መሸጥ ይችላሉ እንዴ ? በማለት መዘገባችን ይታወቃል ፤ መንግስት ይህ ነገር አሳስቦት ማነው ይህን ዜና ሚዲያ ላይ እንዲወጣው መረጃ የሰጠው ፤ እንዴት በሚስጥር የተያዘው ነገር ሾልኮ ቀናት ሳይሞላው ድህረ ገፅ ላይ ወጣ? ፤ ማነው ይህን ያደረገው? በማለት ሰዎችን ከደብረዘይት ባቡጋያ አካባቢ ከሚገኝው መድሀኒአለም ቤተክርትያን ውስጥ ፌደራል ፖሊስ እያሰረ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ ይህ ጉዳይ የማንም ጉዳይ አይደለም ፤ የእኛ ጉዳይ ነው ፤ ቤተክርስትያናችን ላይ የሚደረገውን ነገር ማንም አደረገው ማን አይተን የምናልፍበት አይን የለንም ፤ መረጃ እስክናገኝ እስክናረጋግጥ ዝም ያልናቸው ነገሮች ብዙ ናቸው፤ እንደ ማቱሳላ 969 ዓመት እንኖራለን ብለን አናስብም በተሰጠን እድሜ ግን ቤተክርስትያን ላይ የሚደረገውን ነገር ሁሉ ከመፃፍና ለሰዎች ከማሳወቅ ወደ ኋላ አንልም ፤እውነቱ ይሄ ነው ‹‹ ቦታው ተሸጧል ፤ ሪዞርትም እየተሰራበት ነው››
Friday, December 23, 2011
‹‹አይሆንም ፤ አይደረግም›› እንበል
(አንድ አድርገን ታህሳስ 13 ፤ 2004 ዓ .ም)፡- እንደ 1999 ቆጠራ በአዲስ አበባ 3,384,569 ያህል ህዝብ ይኖራል ተብሎ ይገመታል፡፡ 82 በመቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ፤ 12.7 በመቶ የእስልምና ፤ 3.9 በመቶ ፕሮቴስታንት ፤ 0.8 በመቶ ካቶሊክ ፤ 0.6 በመቶ ሌሎች የእምነቶችን ይከተላሉ ይላል የመጨረሻው የህዝብና ቤት ቆጠራ መረጃ ፡፡ እንደሚታወቀው አቶ ዐሊ አብዶ የአዲስ አበባ ከተማ ማስተዳድር ከንቲባ በነበሩበት ጊዜ 98 አዲስ የመስጊድ ቦታዎች መፅደቅ ችለውና መስኪድ ተሰርቶባቸዋል :: ከ 82 በመቶ በላይ የሕዝብ ብዛት ያላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከ131 ያልበለጡ የአምልኮ መፈጸሚያ ይዞታዎች ሲኖሩዋት በአንጻሩ ከ12.7 በመቶ የማይሞለው ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ከ180 በላይ የአምልኮ መፈጸሚያ ይዞታዎች እንዲኖሩት ተደርጎአል ፡፡
Thursday, December 22, 2011
አብዝተን እናጭድ ዘንድ አብዝተን እንዝራ! (በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!! አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከ347 እስከ 407 ዓ.ም. የነበረና ከ398 እስከ 404ዓ.ም. የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ሆኖ ያገለገለ ታላቅ የቤተክርስቲያን አባት ነው፡፡ ይህ አባት ከሚያስተምረው የትምህርቱ ጣዕም የተነሣ “አፈወርቅ፣ ጥዑመ ልሳን” ተብሏል፡፡ በእርግጥም በትምህርቱ ሁሉንም መማረክ የሚችል፤ ለማንም የማያዳላ ይልቁንም ለድሆች ጠበቃ የሚሆንላቸው የፍትሕ አባት ነው፡፡ ትምህርቶቹም ዘመን ተሻጋሪና ክርስቲያናዊ ሕይወቱን መመዘን ለሚፈቅድ ሰው የማያዳሉ ሚዛኖች ናቸው፡፡ እስኪ ዛሬም በዚያ አንደበቱ ይናገረን፤ እኛም እንደ ሊድያ ልቦናችንን ከፍተን እንስማው፤ ከዚያም ራሳችንን እንመርምር፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)