Friday, June 27, 2014

ጠባቂዬ ቅዱስ ገብርኤል ከመዓት እንዳወጣኝ አምናለሁ


አቶ ቴዎድሮስ አሸናፊ የሳውዝ ዌስት ሆልዲንግስ ፕሬዚዳንት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ ሳውዝ ዌስት ሆልዲንግስ የኢንቬስትመንት ቡድን ሲሆን በሥሩ (ሳውዝ ዌስት ዴቨሎፕመንት፣ ሳውዝ ዌስት ኢነርጂ) ሳውዝ ዌስት ቴክኖሎጂስ የተሰኙ ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኢንቬስትመንት ዘርፎች ተሰማርተዋል፡፡ በተጨማሪም ሳው ዌስት የተሰኘ ፋውንዴሽን ለመመሥረት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሪፖርተር ከአቶ ቴዎድሮስ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበርሁለቱን ጥያቄ እነሆ

ሪፖርተር፡- 1999 .. የአውሮፕላን አደጋ ገጥምዎት ነበር፡፡ ስላደጋው ይንገሩን? 
አቶ ቴዎድሮስ፡- በወቅቱ ፔትሮናስ በጋምቤላ የሚያካሂደውን የነዳጅ ፍለጋ ሥራ ጐብኝተን ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ ሳለን የአውሮፕላኗ ሞተር ተበላሽቶ ቆመ፡፡ 11,000 ጫማ ከፍታ ወደ መሬት ተከሰከስን፡፡ በአደጋው ጓደኛዬ የፔትሮናስ የኢትዮጵያ ቢሮ ሥራ አስኪያጅ የነበረው መሐመድ አሪስ ሕይወቱ አለፈ፡፡ 

ሪፖርተር፡- በርስዎ ላይ ጉዳት አልደረሰም? 
አቶ ቴዎድሮስ፡- አንድም አጥንቴ ሳይሰበር ከአደጋው ተርፌያለሁ፡፡ በሆስፒታል አላደርኩም፡፡ ከአደጋው ሁለት ቀን በኋላ ወደ ሥራ ገበታዬ ተመልሻለሁ፡፡ ከአደጋው ጠባቂዬ ቅዱስ ገብርኤል ከመዓት እንዳወጣኝ አምናለሁ፡፡

Thursday, June 19, 2014

የጳጳሳቱ ማረፊያ


(አንድ አድርገን ሰኔ 13 2006 ዓ.ም)፡-
116ኛው የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ 6ኛ በፓትርያርክነት ዘመናቸው ይቀመጡበት የነበረው በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል የሚገኝ አንድ ያረጀ ክፍል ነበር፡፡ በዚህ ክፍል ሲኖሩ አንድ የካቶሊክ መነኩሴ ሊጎበኛቸው መጣ፡፡ ፓትርያርኩን ማረፈያ ቤትና ዕቃዎቻቸውን ሲመለከት ለክብራቸው የሚመጥን ባለመሆኑ ደነገጠ፡፡ (ፓትርያርክ የሚሆኑ አባቶች በደህና ማረፊያ ሊኖሩ ይገባል  ይህም  ለእነርሱ ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን ክብር ሲባል ነው፡፡) መነኩሴው አቡነ ቄርሎስን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው  ‹‹እባክዎን በእንዲህ ዓይነት ቤት ውስጥ መኖር ለእርስዎ የሚመጥን አይደለም፡፡ ፈቃድዎ ከሆነ እኔ ቤትዎን ላድስልዎትና ምርጥ ምርጥ ዕቃዎችን ላስገባልዎት?›› ፓትርያርኩ ይህንን ጥያቄ ሲሰሙ ፈገግ ብለው  በፍቅር ዓይን ከተመከቱት በኋላ ‹‹የእኔ ልጅ እጅግ አመሰግናለሁ!  እርግጥ  ነው ይህ  ቤት በጣም  የተጎሳቆለ  ነው፡፡  እንደዚህም ሆኖ ግን ጌታችን ከተወለደበት በረት ይሻላል!!›› አሉት፡፡

በእኚህ አባት እግር የተተኩት ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ደግሞ በግብፅ መንግሥት በታሰሩ ጊዜ  ምእመናኑ  ከእስር ቤት ወጥተው ማረፊያ ቤት እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ሰልፍ ወጥቶ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ አቡነ ሺኖዳ  ለሕዝቡ ንግግር አድርገው ማረፊያ ይሰጣቸው በሚል የተወጣውን ሰልፍ እንዲበትኑ ተጠየቁ፡፡ እኚህ  አባትም ሕዝቡን  እንዲህ ሲሉ አረጋጉት፡፡ ‹‹ለእኔ ማረፊያ እንዲሰጠኝ ብላችሁ ሰልፍ ወጥታችኋል  ነገር ግን በፍቅር ከተሞሉት ከእናንተ ልቦች የተሻለ ማረፊያ ለእኔ አያስፈልገኝም!››  አሏቸው፡፡
ከሄኖክ ኃይሌ


ይህ የሆነው በ116ኛው የኮፕት ፓትርያርክ በአቡነ ቄርሎስ እና በ117ኛው ፓትርያርክ በአቡነ ሺኖዳ ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት አባቶችን ማየት እድለኝነትን ይጠይቃል፡፡ መንጋውን በአግባቡ እየመሩ ከመቶ በላይ መንፈሳዊ መጻሕፍት ለእመነቱ ተከታዮች እየጻፉ ፤ በየሳምንቱ ቋሚ መርሐ ግብር በመያዝ ወንጌል እየሰበኩ ፤ አክራሪ ሙስሊሞች ቤተ ክርስቲያቱ ላይ የሚያነሱትን ችግር ተቋቁመው ከአስር በመቶ የማይበልጡ የእምነቱን ተከታዮች መንፈሳዊ ልዕልናው ከፍ እንዲል የሚሰሩትን ሥራ መመልከት እጅግ ደስ  ያሰኛል፡፡ ወደ እኛ ቤተክርስቲያን ስንመጣ ደግሞ በርካታ ችግሮች የተጋፈጡባት ቤተ ክርስቲያን ብዙ የመነጋገሪያ አጀንዳ አንስቶ ሸክሟን ማቅለል ሲገባ ‹‹የጳጳሳት ንብረት ውርስ››ን በሚመለከት በሲኖዶስ ደረጃ አጀንዳ ይዞ መነጋገር ያለንበትን የመንፈሳዊ ደረጃ ዝቅጠት ያሳየናል (አንዳንድ አባቶች በአዲስ አበባ ከ500 ካሬ ሜትር በላይ የተንጣለለ ቪላ እና G+1 በስማቸው የተመዘገበ ንብረት ባለቤቶች ስለሆኑ)፡፡


‹‹በፍቅር ከተሞሉት ከእናንተ ልቦች የተሻለ ማረፊያ ለእኔ አያስፈልገኝም!›› በማለት ምንም  ዓለማዊ ሀብት ንብረት ሳያፈሩ የተሰጣቸውን ሓላፊነት በሚወጡ አባቶችን እኛ ለምን አጣን?  እኛን እጅግ የሚገርመን በጥቂት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በግብጽ ኮፕት ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ያለው ዘርፈ ብዙ-------------------------------------------- ልዩነት ነው፡፡ 

Monday, June 16, 2014

‹‹የተቀደሰችው ደጅ ከዚህ በላይ መርከስን ማስተናገድ የለባትም›› መምህር ተስፋዬ ሸዋዬ

  • ኢትዮጵያ እና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ተለያይተው አያውቁም፡፡
  • ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያ ከነበራት የቀድሞ ስፋትዋ ቢያንስ አሁን ባለችበት ቅርጽና ይዘት እንድትቆይ በማድረግ ባለውለታ ናት እንጂ ሀገር ያደኸየች አይደለችም፡፡
  • ድርሳንና ገድላትን የሚነቅፏቸው ከርዕይ ያልደረሱ ጣዕመ ጸጋ ያልቀመሱ ዐይኑ ግንባር ሆኖ እንደተፈጠረው የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ ግንባር የሆነ ዐይነ ነፍሳቸው በክርስቶስ ጣት ያልተዳሰሰ በመለኮት ምራቅ ያልራሰ ሰዎች ናቸው፡፡
  • …. ከባለቤቱ የእግር ሰላም አንዲት ጠብታ እንዳይቀርባት በፍቃዷ ከግብጽ ጳጳሳትን ስታስመጣ ኖራለች፡፡ ያስገደዳት አልነበረም የአባቶቻቸውን ቃል ውሉድ በፍቅር ሲጠብቁት ኑረዋል እንጂ ከግብጻውያን ያገኝችው ትምህርት የለም፡፡


(አንድ አድርገን ሰኔ 9 2006 ዓ.ም)፡-
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከሃይማኖቷ ፤ አስተምህሮዋ እና ቀኖና ውጪ የሆኑ ድርጊቶች በመስፋፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህን ድርጊት በሚመለከት መምህር ተስፋዬ ሸዋዬን እንደ አንድ የእምነቱ ተከታይ ግለሰብ ያላቸውን ሃይማኖታዊ አስተያየት ለፎከስ መጽሔት ሰጥተው ነበር፡፡ የዚህንም ቃለ መጠይቅ ምላሽ እንደሚመለከተው አቅርበነዋል፡፡

ፎከስ፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት መቼ እና እንዴት ተጀመረ?
መምህር ተስፋዬ፡- ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር የምትባልበት ምክንያት በሦስቱም ሕግጋት ታውቀው ስለነበረ ነው፡፡ እነዚሁ ሕገ ልቡና ፤ ሕገ ኦሪት እና ሕገ ወንጌል ናቸው፡፡ ሕገ ኦሪት ስትሰራ ኢትዮጵያዊቷ ከሙሴ ጋር ነበረች፡፡ ከእርሷ ወገን የምትቆጠር ንግሥት ሳባም ከሰሎሞን ጋር የነበረውን ጥበበ እግዚአብሔር ለማየት ወደ ኢየሩሳሌም እንደሄደች ከዚያም ልጇ ሕገ እግዚአብሔር በራሱ በእሳት ጣት የተጻፈበትን ጽላት በዘመኗ እንዳመጣ የሚያገለግሉ ካህናትም አብረው እንደመጡ ተደጋግሞ የነገለጸ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በአጸደ ነፍስ ሳለች ባለቤቱ ያላቸውን ባልሰሙ ትውልድ ላይ የመፍረድ ስልጣን የሰጣት ናት፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የወልደ እግዚአብሔር ሰው  መሆን በኢትዮጵያ ሲጠበቅ ቆይቷል፡፡ አዳምንና ልጆቹን ከፍዳና ከመርገም ከዘላለም ኩነኔ ሊታደግ በሁለት ወገን ዘላለማዊት ድንግል ከሆነች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በመዋሕድ እንደኛው ሰው ሥጋም ሆኖ በተወለደ በሁለተኛው ዓመቱ ከአዳም በፊት የገነት በር ለተከፈተለት  በቀኙ ለተሰቀለው ሰው ቃል ኪዳን በመግባት በግብጽ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በመጣ ጊዜ መልኩን ዐይታ በሕጻን አንደበቱ ያስተማራትን ትምህርት የሠራላትን ገቢረ ተዓምራት አስተውላና ተረድታ የባሕርይ አምላክነቱን አምና በክብር አስተናግዳዋለች፡፡ መንፈስ ቅዱስ በጽርሀ ፅዮን በወረደ ጊዜ ለመገኝቷ  አቡነ ዘበሰማያት በቋንቋዋ በግዕዝ ተጽፎ መገኝቱ ምስክር ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ እና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ተለያይተው አያውቁም፡፡

Saturday, June 14, 2014

‹‹አንድ ሚሊዮን ወጣትም ቢሆን የፈለገበት ይድረስ ፤ ምንጣፍ አነጠፈም አላነጠፈም የፈለገበት ይድረስ›› የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ


  •  " ገመድ የምትበላ ብትሄድ ጠፍር የምትበላ ትመጣለችሀገርኛ ብሂል

(ፋክት ቅዳሜ ግንቦት 7 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ወጣቶች ማኅበራት ሕብረት ፍቃድ መሰረዙ ተሰማ፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ግንቦት 8 ቀን 2006 ዓ.ም ለሕብረቱ በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸው ፤ ሕብረቱ ከሕገ-ቤተክርስቲያን እና ከቃለ አዋዲው ሕግጋት ፍቃድ መሰረዙን ገልጿል፡፡

አባ ማትያት ፡- ከሕለተ ሙሴ ወደ ሕለተ ወርቅ


ከታደሰ ወርቁ
ቅዳሜ ሰኔ 7 2006 ዓ.ም ፋክት መጽሄት የተወሰ
  • አቡኑ ጉዱ ካሳን የሆኑ እስኪመስለን ድረስ የለውጥ አባት ተደርገው ተወሰዱ ፤ በቤተ ክርስያኒቱ ምሁራን ልጆች ተሳትፎ እየፈራረስ የነበረውን ጽመታዊ ቡድንን ከያለበት እየፈለጉ በማሰባሰብ ነፍስ ዘሩበት፡፡ቅዱስነታቸው ፤ ራሳቸውን ለአላስፈላጊ ተጽህኖ ያጋለጡበት ፈቃደኝነትና ዝግጁነት ቄሳራዊው ወገን ብቻ ሳይሆን ጽምታዊውም ቡድን ያልጠበቀው ምርኮ ኾነለት፡፡
  • ፓትያርኩ ቤተ ክርስቲያናችን ለመንፈሳዊ ተቋምነቷ የሚመጥኑ ሰዎች ሊመደቡላት እንደሚገባ ቢናገሩም በቅዱስነታቸው የሚታየው አቋም የለሽነትና አቅመ ቢስነት ከፍቶ አደባባይ ወጥቶ አሸማቃቂ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
  • ቅዱስነታቸውን በክብረ-ክህነት ላይ አመንዝረው ፤ ከአባቶቻችን አዋራጆች ፤ ምሁራን ልጆቻቸውን በጠራራ ጸሀይ ለማስገደል ጭምር ከሚያሴሩ ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱን በግላጭ ከሚዘርፉና ከሚመዘብሩ እንዲሁም ለመሰረተ እምነቷ  ፤ ለሥርዓቷ ፤ ለትውፊቷና  ታሪኳ ግድ ከማይላቸው አማሳኞችና ጽልመታዊ ኃይሎች ጋር የተሰለፉት ሕለተ ሙሴን ጠልተው ሕለተ ወርቅን በማፍቀር አባዜ ነው፡፡


(አንድ አድርገን ሰኔ 7 2006 ዓ.ም)፡-በአዲስ ፓትርያርክ ፤ ዋና ጸሐፊ እና ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ሥራውን የጀመረው ቤተ ክህነት ባሳለፍነው ወርሀ ግንቦት አንደኛ አመቱን ይዟል፡፡ ይህው የአንድ ዓመት የሥራ ዘመን ገና ከጅምሩ ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ለውጥ ብዙ የተለፈለፈበት ቢኾንም መሠረታዊ ችግሮቿን መፍታት ይቅርና አንዲት ክንድ አንኳን ፈቅ አላደረገውም፡፡ ዓመቱ ፤ በመልካም አስተዳዳር እጦት መንስኤ የኾኑት ብልሹ አሰራር - ሙስና- ጎጠኝነት ከየትኛውም ጊዜ በላይ ጎልተው የታዩበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ኻያ አንድ አመታት በርዕሰ አበውነት ‹ሲገዙ› የነበሩትን የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ሞትን አስከትሎ ስድስተኛውን ዘመነ ፕትርክና  የምደባ ያህል  የተረከቡት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀናኢ ሊቃውንትና ምእመናን ለዘመናት ሲያንገሸግሽ የቆየውን አድሏዊ አሠራር ፤ ጎጠኝነትና ሙስና በመጠኑም ቢኾን ይፈታሉ የሚል ግምት ተሰጥቷቸው ነበር፡፡

Wednesday, June 4, 2014

መንግሥት በዋልድባ ገዳም በመሥራት ላይ ያለውን የሥኳር ፕሮጀክት 12 በመቶ ማጠናቀቁን ገለጸ


(አንድ አድርገን ግንቦት 28 2006 ዓ.ም)፡- ከወር በፊት መንግሥት በዋልድባ ገዳም በመሰራት ላይ ላለው የሥኳር ፕሮጀክር  ቻይና መንግሥት ሥራውን ማጠናቀቂያ የገንዘብ ብድር ማግኝቱ ይታወቃል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ የኢቲቪ የምሽት ዜና ላይ የሥኳር ፕሮጀክቱ 12 ከመቶኛ መጠናቀቁን ተገልጿል፡፡ ከወር በፊት ቦታው ላይ በአካል ደርሰው ከመጡ ምዕመናኖች እንደተረዳነው ከሆነ በገዳሙ የሚገኙ መናንያን ጋር በመቅረብ መረጃ ማግኝት አስቸጋሪ ቢሆንም መነኮሳቱ የዘወትር የሥራ መርሃ ግብር በተጨማሪ  በጾምና በጸሎት መጠመዳቸውን ገዳሙ ድረስ ደርሰው ከመጡ ሰዎች ለመረዳት ችለናል፡፡ በቦታው ከሄዱ ሰዎች አንዱ አንድን አባት ስለ ሁኔታው ለመጠየቅ ሞክሮ ‹‹ጸልዩ›› ተብለናል ስለዚህ ‹‹ሁሉንም ነገር በሂደት የምናየው ነገር ይሆናል እኛ እየጸለይን ነው፡፡›› በማለት መልስ ሰጥተውታል፡፡

Tuesday, June 3, 2014

‹‹ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት››



 (አንድ አድርገን ግንቦት 26 2004 ዓ.ም)፡-
ፕሮፌሰር ታደሰ ይባላሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ፕሮፌሰር  ሲሆኑ የዩኒቨርሲቲው የመጻሕፍት ዝግጀት ተቋም ዳይሬክተርና ዋና አዘጋጅ በመሆን አገልግለዋል፡፡ በአሜሪካ ሀገር በኮኔል ፤ ኖርዝዌስት ዩኒቨርሲቲ ኢሊኖይ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በጎብኝ ፕሮፌሰርነት ከማስተማር በተጨማሪ በሳባቲክና ፈቃዳቸውን  በፈረንሳይ ሀገር ባሳለፉት ዓመት በታዋቂው ኮሌዥ ዲፍራንስና በፓሪስ ዩኒቨርሲቲ እየተጋበዙ ጥናታዊ ጽሑፎችን ያደረጉ ምሁር ናቸው፡፡ እኚው ፕሮፌሰር በጦቢያ መጽሔት ቅጽ 5 ቁጥር 10 1990 ዓ.ም በአምስተኛው የፕትርክና ዘመን ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የተሰጠውን ‹‹ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት››ን ማዕረግ አሁንም የቀጠለው መጠሪያ በሚመለከት ተጠይቀው የመለሱት መልስ ለማስቃኝት ወደድን ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ‹‹ሊቀ ጳጰስ ዘአክሱም›› የሚለው መጠሪያ ላይም ውዝግብ እንደነበር የምናስታውሰው ነገር ነው፡፡

Monday, June 2, 2014

የሲኖዶስ ጉባኤ በፓትርያርኩና ጳጳሳቱ ፍጥጫ ተቋጨ

Addis Admass
  • ጳጳሳት የፓትርያርኩን የማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ማሻሻያ ቅድመ ኹኔታ አልተቀበሉትም
  • ‹‹ቅድመ ኹኔታው የማኅበሩን አገልግሎት የሚያቀጭጭና በሒደትም የሚያስቆም ነው›› /ታዛቢዎች/
የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅን እንደ አንድ አጀንዳ የያዘው የዘንድሮው የሲኖዶሱ የርክበ ካህናት ጉባኤ ከረቂቁ ጋር በተያያዘ በፓትርያርኩና በሊቃነ ጳጳሳቱ መካከል በተፈጠረ ፍጥጫ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡ 

የጎመጀው ፤ የደነዘዘው እና የደነቆረው ሕዝብ……

ኃይለጊዮርጊስ ማሞ
(የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል መምህር)

(አንድ አድርገን ግንቦት 25 2006 ዓ.ም)፡- ሰሞኑን የከተማችን ወሬ ሆኖ የከረመው አንድ አስገራሚ(እንደዚህ ጸሐፊ እምነት አሳፋሪ) ክስተት ነበር፡፡ ክስተቱ አንድ ዜግነቱ የማላዊ የሆነ “ነብይ” ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ ጋር በተያያዘ በሚሊኒየምና እንዲሁም በነጋታው ‹‹መድህን ዲኮር›› በተባለ አዳራሽ የታየ “ሕዝባዊ ውርደት” ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ አይነት ክስተቶችን ልብ ብሎ ለተመለከተ ሃገሪቱ ጠባቂ የሌላትና ማንም እንደፈለገ እየገባና እየወጣ የሚፈነጭባት ‹‹መሰማሪያ›› ትመስለዋች፡፡ በተለይም ደግሞ የሕዝብ ድህነት ፤ መጎምዥት ፤ መንፋሰዊ ክስረትና ውድቀትን ተገን አድርጎ በየስፍራው የሚነሳው “ሃገር በቀል ቦጥቧጭ” አልበቃ ብሎ ‹‹አለም አቀፉን›› ደግሞ እየጋበዙ  በማምጣት እንዲህ ሕዝብን መጫወቻ ማድረግን ስንሰማ ከዚህ በላይ ሕዝብ የራሱን ክብር ከጭቃ የሚጥልበት ትንሽነት ከወዴት ሊመጣ ይችላል? በማለት ለመጠየቅ እንገደዳለን፡፡

በአንድ ወቅት ‹‹ፓስተርና ፖስተር›› ሲባልበት የነበረው ከተማ ዛሬ “ወደ ነቢያት ጉባኤ” ተቀይሮ ሁሉ በየፊናው  የነብይነት ካባን በየአደባባዩ እየተጎናጸፈ የሕዝቡን መጎምዥትና  ጭንቀት ተገን አድርጎ መቆምን አስተማማኝ የትርፍ መስክ ሲያደርገው “ኧረ ሃይ ባይ የለም ወይ?” የሚያስብል ሆኗል፡፡ እርግጥ ነው ትውልድና ዘመን ብዙ ዓይት መልክ ያለው ክስረት  ውስጥ ለመግባቱ በድፍረት ብቻ ሳይሆን በተሰበረ ልብ እንናገራለን፡፡ ዛሬ የመንፈሳዊነት አገልግሎት በኢትዮጵያ ከሰማዩ ይልቅ የምድራዊውን ሕይወት ጥያቄ ምላሽ በመስጠት የተያዘ የትርፍ መስክ ያደረገውም ይኽው ክስረታችን ነው፡፡ ደርግ የሃይማኖት ነጻነትን ነፍጎ ሕዝቡን ኮሚኒስት (ኢ-አማኒ) ለማድረግ ሲታትር በዚያ ዘመመንና ትውልድ በመንፈሳዊነት ጸንተው ዋጋ የከፈሉ በርካቶች ነበሩ፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ መጣና “የሃይማኖት ነጻነት”  በማለት ሲያውጅ “ዋጋ የተከፈለበት” መንፈሳዊነት “ዋጋ የሚያስከፍሉበት” ሆኖ ቀረ፡፡ በመሆኑም ለዚህ አይነቱ በሀገር ላይ ለመጣ መንፈሣዊ ብቻ ሳይሆን  የማንነት ውድቀት ተጠያቂው ማነው? ወዴትስ እየሄድን ይሆን ?