Monday, November 11, 2013

በሳውዲ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግሥት ኃፊነቱን ይወጣ


(አንድ አድርገን ህዳር 3 2006 ዓ.ም)፡- ከወራት በፊት የሳውዲ መንግሥት በህገወጥነት ስራ የተሰማሩ የማንኛውም ሃገር ሰዎች አንድም ህጋዊ እንዲሆኑ ያለበለዚያ ከሀገር እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር ፤ ብዙ የፊሊፒንስ ፤ የኢንዲኒዥያ ፤ የህንድ እና የፓኪስታን ዜጎን መንግሥታቸው ጊዜ ገደቡ ሳይጠናቀቅ በኢምባሲዎቻቸው አማካኝነት አንድም ሕጋዊ የማድረግ ሥራ ሲሰሩ ነበር ያልሆኑትም በርካቶችን ወደ ሃገራቸው ሲመልሱ ነበር ፡፡ የኛ ሃገር መንግሥት ግን ተኝቶ ሲያበቃ የቤት ለቤት አፈሳው ሲጀመር ፤ የሰዎች ደም እንደ ከንቱ ሲፈስ ፤ የኢትዮጵያውያን ሞት ከውሾች እኩል ሲታይ ፤ አፈናው ፤ ዱላው ፤ ግድያው ፤ አስገድዶ መድፈሩ ሲባባስ አቤት እንኳን ማለት አለመቻሉ እጅጉን ያሳዝናል ፡፡ በተለያዩ የዓለም የመገናኛ ብዙሃን በግልጽ የኢዮጵያኖችን መከራ ሲያስተላፉ  የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲ በኤፍ ኤም 97.1 ላይ ቀርበው ‹‹ኢትዮጵያኖች ላይ እየደረሰ ያለው ነገር እንደሚወራው አይደለም ፤ ኢትዮጵያውያ ሳውዲ ውስጥ በቁጥር እዚህ ግቡ የሚባሉ አይደሉም›› ብለው አስተያየታቸው ሲሰጡ መስማት ውስጥን ያደማል፡፡ እስኪ አሁንም ጊዜው አልረፈደም ፤ ከዚህም የባሰ ጉዳት ሳይደርስ መንግሥት አቤት ይበላቸው ፡፡ ወደ ሀገራቸው ለመምጣት ያሰቡትን በእስር ላይ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን ከሰዓታት እድሜ ውስጥ ይድረስላቸው ፡፡ ከዚህ የባሰ ሰብአዊ መብት ረገጣ እንዳይካሄድባቸው ሁሉም በያለበት ድምጹን ያሰማላቸው፡፡  

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በስደት ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሌም ታስታውሳለች ታስባለችም። ይልቁንም በአሁኑ ሰዓት በአረማውያኑ ሃገር የሚሰቃዩትንና ሕይወታቸውም ያለፈውን እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን ከአብርሀም ከይሳቅ ወገን እንዲያሳርፍና ለወገኖቻቸውም መጽናናትን ይህንንም አስከፊ ግፍ ለሚፈጽሙባቸውም ልቦናን ይሰጥ ዘንድ ዘውትር ትጸልያለች። እግዚአብሔር በስደት ያሉትን ወገኖቻችንን ያስብልን፡፡ መድኃኒዓለም ይድረስላቸው፡፡


እስኪ ስለነዚህ ወገኖች ሁላችን እንጸልይ

‹‹የቅዱስ ያሬድ ዜማን ማጣጣም ያልቻልነው ሥጋዊ ጆሮ ስላለን ነው ፤ መንፈሳዊ ጆሮ ቢኖረን መንፈሳዊው ባልሆነው ዜማ ምንኛ ባዘንበት ነበር›› ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

  • በዚህ ዘመንም ከአባታችሁ ከቅዱስ ያሬድ የተቀበላችሁትን ዜማ ትታችሁ ሌላ ያሬዳዊ ያልሆነዜማን እናሰማችሁ ባዩ በዝቷል፡፡
  • ከአባቶች ባልተሰጠ ሥርዓት ዓይንን ጨፍኖ እጅን እያወራጩ እስከመዝለልም ተደርሷል፡፡
  • “ያሬዳዊ ዜማ ለገበያ_አይመችም” በሚል መፈክር ብዙዎች ገንዘብን ፍለጋ የዜማ ርስታቸውንጥለዋል፡፡
  •  ያሬዳዊ ዜማን እንከተል እያሉ የናቡቴን ድምጽ የሚያሰሙ ምዕመናንና ካህናትም በቃልምበየመዝሙሮችም ላይ ‹ሜልኮሎች›፣‹ወግ አጥባቂዎች›፣‹ኋላ ቀሮች›፣‹ትምክህተኞች› እየተባሉ ሲወረፉ እንመለከታለን፡፡

(አንድ አድርገን ህዳር 03 2006 ዓ.ም)፡- አባቶቻችን ብዙ መስዋዕትነትን የከፈሉትና ደማቸውን ያፈሰሱት ሥጋቸውን የቆረሱት አጥንታቸውንም የከሰከሱት ግዑዟን ምድር ለማውረስ ብቻ አልነበረም፡፡ ከብዙ መስዋዕትነት ጋር ወደዚህ ትውልድ ያሻገሩት ሌላ ትልቅ ርስት አለ፡፡ይህም ሃይማኖትና ትውፊት ቋንቀዋና ፊደል ዜማና ሥርዓት ነው፡፡

Sunday, November 10, 2013

የወ/ሮ ዘርፌ ቃለ መጠይቅ


(አንድ አድርገን ህዳር 1 2006 ዓ.ም) ወ/ሮ ዘር ከበደ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጋ ነበር ፡፡ ቃለ መጠይቁን አለፍ አለፍ ብለን እንዲህ ለማየት ወደድን…

ወ/ሮ ዘርፌ፡- ብዙ ዘማሪዎች ግጥምና ዜማ ራሳቸው ናቸው የሚሰሩት... እንደ ዓለማዊ ዘፈን ከሰው ብዙ አይቀበሉም… የስጦታ ጉዳይ ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡ አንድ ሰው ካልተሰጠው ምንም ነገር መስራት አይችልም። ጌታ ቢፈቅድ ብዙ ልሰራቸው ያቀድኳቸው ነገሮች አሉ፡፡ በእኛ አገር በተለያዩ ቋንቋዎች መዝሙሮች መሰራት አለባቸው፡፡ እዚህ አሜሪካ ብዙ የአበሻ ልጆች አማርኛ መስማት አይችሉም፡፡ ቤተክርስቲያን ይመጣሉ፤ ግን ለማምለክ ብዙ ይቸገራሉ፡፡
ቃለ መጠይቁ ቃናው ከመናፍቃኑ አልለይ አለ ፤ አባቶቻችን ሲናገሩ እጅጉን ሲጠነቀቁ ነው የምናውቀው ፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ውዴ›› ፤ ‹‹ፍቅሬ›› እያሉ ሲናገሩ አንሰማም ሰምተንም አናውቅም፡፡ የአምላክን ስም አንጠልጥለው ሲጠሩን አንሰማም ፡፡ እነዚህ ፕሮቴስታንታዊ ዘይቤ ያላቸው አነጋገሮች ‹‹ማምለክ›› ፤‹‹ስጦታ›› ፤ ‹‹ሙላት›› …… ከየት የመጡ ናቸው…? ለነገሩ ‹‹ስለ እመቤታችን መዝሙር መዘመር አልችልም፤ አንድ መዝሙርም ሲበዛባት ነው፡፡ እኔ የኢየሱስን ክብር መግለጥ ነው የምፈልገው›› ብላ ከአንደበቷ የተናገረች ቃሏ እንዴት እኛን ይመስል?

‹‹ተዋሕዶ›› ነን ባዮች በሕብረት በመሆን ገዳሞች ላይ እየዞሩ ይገኛሉ


  • ቦሌ ሚካኤል ቤተክርስትያን ውስጥ የቅዳሴ ስነ ሥርዓት እየተካሄደ እያለ ወደ ቤተ መቅደስ በመግባት “ኤልያስ መጥቷል የተዋህዶን ነገር በደንብ መናገር አለብኝ፤ እናንተ በከንቱ ነው የምትደክሙት፤ ኦርቶዶክስ ትክክለኛ ሃይማኖት አይደለም፤ በውስጡ ቅባትና ዘጠኝ መለኮት የሚገለጽበት ነው፡፡ እውነተኛ እና ትክክለኛ ሃይማኖት ተዋህዶ ብቻ ነው፤ ይሄንን እውነታ ለህብረተሰቡ አስተምራለሁ እሰብካለሁ” በማለት ሃይማኖታዊ ስነሥርዓቱ እንዲታወክ አድርገዋል፡፡


 (አንድ አድርገን ህዳር 1 2006 ዓ.ም)፡- አቶ አበበ ነጋሽ የሚባል ሰው በደብረ ብርሃን ኩክ የለሽ ገዳም ‹ትውልድ አልቋል› ፤ ‹8 ሺ ደርሷል› ፤ ‹ሰንበትና ነቢያት ይከበሩ› ፤ ‹ስለ ሰንበተ አይሁድ› ፤ ‹ትውልድ ሊቀጠፍ ነው› ፤ ‹ኤልያስ ወደ ምድር ወርዷል› ብሎ ሲሰብክ ተይዞ ‹የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ሆኖ ሳለ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስያን ገዳም ስብከት በማከናወንና የሃይማኖት ተከታዮች ውስጥ ሁከት በማነሳሳት›› እና ተያያዥ ክሶች ቀርበውበት ፍርድ ቤት መቅረቡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከቦታው በደረሰን መረጃ መሰረት ይህን ጉዳይ ፍርድ ቤቱ  ወደ ማህበራዊ ጉዳይ ፍርድ ቤት አዙሮ እየተመለከተው መሆንን ለማወቅ ችለናል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ጀማነሽና እንከተለዋለን የሚሉት የእምነቱ ተከታዮች ከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ መሆናውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዛሬ ህዳር 1 2006 ዓ.ም የዳዊት ኮከብ ቀስተደመና እና መሰል እኛነታችን ይገልጻል ያሉትን ልብስ በመልበስ በብዛት በመሆን በደብረ ብርሃን ኩክ የለሽ ገዳም አዳራቸውን ለማድረግ ተጉዘዋል ፤ ቦታው ላይም  እንደደረሱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ እነሱ እንደሚሉት ከሆነ ከገዳም ገዳም የሚዞሩት በረከት ለማግኝት በሚል ምክንያት ሲሆን በገዳሞች ውስጥ የሚያካሂዱት ነገር ግን የዚህ ተገላቢጦች መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Friday, November 8, 2013

ሰበር ዜና ፡- ብጹዕ አቡነ ኤፍሬም ለተሀድሶ አቀንቃኙ ለ” አባ” ማርቆስ ብርሃኑ የእግድ ደብዳቤ ጻፉለት



(አንድ አድርገን ጥቅምት 30 2006 ዓ.ም)፡- በደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስያን አስተዳዳሪ “መልአከ ብርሃናት አባ” ማርቆስ ብርሃኑ ከምዕመኑ እና ከማኅበረ ካህናት በተነሳባቸው አስተዳደራዊ እና  ሃይማኖታዊ ህጸጽ ጥያቄ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትአስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በኋላ በ28/02/06  ዓ.ም አባ ማርቆስን ከአስተዳዳሪነት ሥራቸውን ከደመወዝ ጋር አግዷል ፡፡ ጉዳዩም ለመንበረ ፓትያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ወስኗል፡፡ ደብዳቤውን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡



በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት

ቁጥር ፡- 367/02/06
ቀን ፡- ጥቅምት 28 2006 ዓ.ም

ለ፡- መልአከ ብርሃናት አባ ማርቆስ ብርሃኑ
ደ/ብርሃን

ጉዳዩ፡- ከሥራ እና ከደመወዝ የታገዱ መሆኑን ስለመግለጽ

በገለልተኛ አስተዳደር ስር የሚኖሩትን አጥቢያዎች ቁጥር በአንድ እንደሚቀንስ ይጠበቃል

  • ‹‹እግዚአብሔር ቅዱስ ፍቃዱ  ሆኖ ወደ ህብረትና አንድነታችን አንደምንመለስ ትልቅ ተስፋ ነው ያለኝ፡፡›› ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከ12 ዓመት በፊት ካደረጉት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

(አንድ አድርገን ጥቅምት 29 2006 ዓ.ም)፡- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ለሁለት አስርተ ዓመታት ወደኖሩበት አሜሪካ ጥቅምት 27 2006 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በዘመነ ፕትርክናቸው እንደሚሄዱ ሰሞኑን ከተለያዩ ዜና ማሰራጫዎች ለመረዳት ችለናል። በመረጃው መሰረት ብፁዕነታቸው 6ተኛ ፓትርያርክ ተብለው ከተሸሙ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅምት 27 2006 ዓ.ም ወደ አሜሪካ አቅንተዋል ፡፡ ከብፁዕነታቸው ጋር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ እና ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ አብረዋቸው እንደተጓዙ ታውቋል ፡፡አካሄዳቸው በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘውን የመድኅኒዓለም ቤተክርስቲያን የቅዳሴ ቤት ለማክበር እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

Thursday, November 7, 2013

የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በሶስት ዓመት ውስጥ 4.6 ሚሊየን ብር መመዝበራቸው ተገለጠ


  •  የታገድነው በደብሩ የተፈጸመውን ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ በማጋለጣችን ነው (ሰበካ ጉባኤው)
  • ጉዳዩን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዚዮን ተይዟል፡፡ 

(አንድ አድርገን ጥቅምት 28 2006 ዓ.ም)፡- በአዲስ አበባ ደቡብ ክፍለ ከተማ የሚገኝው የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ጳግሜ 3 ቀን 2005 ዓ.ም ሕገ ወጥ ተግባር ፈጽሟል  በሚል በመታገዱ ችግር መፈጠሩ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ የመጋቢ ሐዲስ ቀሲስ ይልማ ቸርነት ፊርማና ማኅተም ያለበት በቁጥር 450/25/06 በቀን 03/01/2006 ዓ.ም የተጻፈ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የደብሩ ሰበካ ጉባኤ የታገደው የሥራ ዘመኑን መጋቢት 12 ቀን 2005 ዓ.ም ቢያጠናቅቅም ሌላ የሰበካ ጉባኤ ሳይመረጥ በመቅረቱ በተለያየ ጊዜ ጭቅጭቅ ንትርክና ሁከት እንዲፈጠር በማድረጉ ማታገዱ ይገልጣል፡፡

Wednesday, November 6, 2013

ዘመቻ ፀረ-ተሃድሶ በደብረ ብርሃን


  • ‹‹ኢየሱስ አማላጅ ነው የሚል ምዕመንም ሆነ ካህን በሀገረ ስብከቴ እንዲኖር አልፈቅድም››ብጹዕ አቡነ ኤፍሬም
  • ‹‹አምስት ዓመት ከጣልያን ጋር የተዋጋነው ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ለሃይማኖታችን ጭምር ነው›› አባት አርበኛ
  • ‹‹የዘርያቆብ ከተማ ኑፋቄ አይዘራባትም›› የቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ካህናት


(አንድ አድርገን ጥቅምት 27 2006 ዓ.ም)፡- በአሁኑ ሰዓት በደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስያን አስተዳዳሪ በትምህርተ ሃይማኖት ፤ በአስተዳደር እና መሰል ጉዳዮች ላይ የተነሳባቸውን የካህናትና የምዕመኑን ተቃውሞ በማስመልት አጠር ያለች ዘገባ ማቅረባችን ይታወቃል፡፡  ይህን ዘገባ ያነበቡ ብዙዎች(በሁለት ቀን 6ሺ ጊዜ ተጎብኝቷል) የእኝን ሰው መጨረሻ ተከታትላችሁ አቅርቡልን ባሉን መሰረት ጉዳዩ የደረሰበትን ደረጃ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡

Tuesday, November 5, 2013

ኑፋቄ የተገኝበት መጽሐፍ ታገደ


በዳዊት ደስታ
  • መጽሐፉ በዋልድባ ገዳም የሚኖሩ መነኩሴ የጻፉት ነው፡፡

(አንድ አድርገን ጥቅምት 26 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ  ባደረገው ስብሰባ ‹‹ምስጢረ ሥላሴ በአበው ሊቃውንት›› በመል ርዕስ በዋልድባ ገዳም በሚኖሩት በመ/ር አባ ገ/እግዚአብሔር አብርሃ የተዘጋጀውን ቅጽ አንድና ሁለት መጽሀፍ በሊቃውንት ጉባኤ አስመርምሮ የኑፋቄ ትምህርት ያለበት መሆኑን ስለተረጋገጠ እንዳይራጭና እንዳይሸጥ አገደ፡፡

መጽሐፉ በማንኛውም የቤተክርስቲያኒቱ ዐውደ ምህረትም ሆነ የመጻሕፍት ማከፋፈያ ቦታዎች እንዳይሸጥና እንዳይሰራጭ ቋሚ ሲኖዶሱ ያገደው የዋልድባ አብረንታት ገዳም መጽሐፍ ኑፋቄ ያለበት መሆኑን ለጠቅላይ ቤተክህነት በተደጋጋሚ ጥያቄ በማቅረቡ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

Monday, November 4, 2013

ንግሥተ ሳባን በDNA ምርመራ

  
/ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ/

‹‹በግእዝ አቆጣጠር›› በያዝነው 2005 ዓ.ም. ከኅትመት ጽንሱ ተቋርጦ በኢንተርኔት የተወለደውን የደራሲተስፋዬ ገብረአብን ‹የስደተኛው ማስታወሻ› ሳነበው ሰነበትኩ፡፡ ሰቅዞ በሚይዝ ማራኪ አቀራረብ ይህ ጸሐፊ ‹ከማስታወሻነት› ወደ ‹ማስረሻነት› የሚያዘነብሉ በተለይ የእኛ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን ላይ እና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ላይ መራር ጥላቻን የሚያሳዩ ምዕራፎችንም አስፍሮአል፡፡ ጸሐፊነቱ ለድርሰት ዓለም እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ባለመሆኑ በእሱ አጠራር እንደነ ‹አቡነ አርዮስ› ሊቁ ሳተ ብለን አንደነቅበትም ነገር ግን እንደተጀመረው እኛን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ግን በየዘርፉ ምላሽ መሠጠቱ የሚጠቅም ነው፡፡ /http://www.danielkibret.com/2013/10/blog-post_5157.html/ በዚህ መጽሐፉ የንግሥተ ሳባን ታሪክ Fairy tale ከመሆን ውጪ ፋይዳ የለውም በሚል ጠቅሶታል፡ ስለዚህች ንግሥት ከሰሎሞን የሚበልጠው ጌታችን ‹በዚህ ትውልድ ተነሥታ ትፈርድበታለች› ማለቱ ብቻ ለእኛ ከተረት ያለፈ ትኩረት እንድንሠጣት ያደርገናል፡፡